来自 JUECSF Main & Beco (@juecs_fellowship) 的最新 Telegram 贴文

JUECSF Main & Beco Telegram 帖子

JUECSF Main & Beco
ይህ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስትያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማህበር (EvaSUE) የጅማ ዩኒቨርስቲ (Main and Beco Campus) ወንጌላውያን ክርስትያን ተማሪዎች ህብረት የመገናኛ የtelegram channel ነው


ለማንኛውም ጥያቄ :
@juecsfmainbeco
0936281818

ንግድ ባንክ አካውንት
1000306692147
(Naol Ararsa and/or Tigist Dereje)
1,512 订阅者
1,345 张照片
19 个视频
最后更新于 09.03.2025 12:13

JUECSF Main & Beco 在 Telegram 上分享的最新内容

JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:23

354

በስምህ ውስጥ ሃይል አለ
በስምህ ውስጥ ሞገስ
በስምህ ውስጥ ድል አለ
በስምህ ውስጥ ፈውስ

የጸና ግምብ ነው ስምህ የጻድቅ መሸሻ
ከዚህ ዓለም ግብግብ መሸሸጊያ ዋሻ
ከድካም ህመሜ የምፈወስበት
ኢየሱስ ያንተ ስም መድሃኒት አለበት

ኢየሱስ ኢየሱስ  እግዚአብሔር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ

ስምህ ማንነትህ ማንነትህ ስምህ
እንደተጠራህበት እንደዚያው መሆንህ
አዳኝ ሲሉህ አዳኝ ነህ ህይወት ሲሉህ ህይወት
ኢየሱስ ያንተ ስም እውነተኛ እውነት

ኢየሱስ ኢየሱስ  እግዚአብሔር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ

በሰልፉ ሜዳ ላይ በውጊያው መንደር
ስምህ የጦር እቃችን የማይበገር
የልጆችህ አንገት ቀና የሚልበት
ኢየሱስ ያንተ ስም ታላቅ ሃይል አለበት
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:22

349

ታላቅ የሆነውን ስምህን ጠራዋለሁ በህይወቴ ዘመን እታመነዋለሁ

(አመልጥበታለሁ እድንበታለሁ ስምህን እጠራዋለሁ) 2x

እግዚአብሄር ስምህ እግዚአብሔር ነው ለዘመናት ሁሉ የተከበረ ከሃይልና ደግሞም ከብርታቱ ያልተገታ ያልተከለከለ

ዛሬም ይሰራል ያድናል ጨለማውን ብርሃን ያደርጋል ስምህ በሃይል ይሰራል ዛሬም ይሰራል ያድናል ተራራውን ሜዳ ያዳርጋል ስምህ ሃይል አለው ይሰራል

ታላቅ የሆነውን.....

በላይ በታች ካለው ፍጥረት ከሚመጣውም አለም ከሚጠሩት ስሞች መካከል እንዳንተ ያለ የለም ባህር አይታ የሸሸችህ ተራሮችም የዘለሉ አንተን አይተው እንደሆነ መፅሃፍትም መሰከሩ

በሰማያት ላይ ታላቅ ነህ በምድርም ላይ አንተ ታላቅ ነህ በፍጥረት ሁሉ ታልቅ ነህ ኢየሱስ አንተ ትልቅ ነህ ጌታዬ አንተ ታላቅ ነው ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነውx2 አንተ እኮ እጅግ ታላቅ ነህ ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው x2

ወደ አምላኬ ፊት የምቀርብበት የምስጋና ድምፅ የማሰማበት ሞገሴ ነው ስምህ ነው ድፍረቴ መቀበያ መልሽ የለፀሎቴ

(የሰማያትን ደጅ ይከፍታል አባት ለልጁ መልስ ይሰጣል ስምህ ሃይል አለው ይሰራል)×2

ታላቅ የሆነውን
JUECSF Main & Beco

31 Jan, 08:22

446

1.አንደፈሰሰ ሽቶ መዓዛው የሚያውድ
ጣፋጭ ሽታ ያለው ውድ ነፍስን የሚማርክ
የስምህ መዓዛው ህልዉና ይህን ቤት ይሙላው
በዚህ ትውልድ መሃል ስምክን አክብደውና


አዝ:ስምህ ከስሞች ሁሉ በላይ 4x
አብ ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ጉልበት ሁሉ ሊሰግድለት የተገባው
ምላስ ሁሉ የሚመሰክርለት
ስምህ ከስሞች ሁሉ  በላይ 2x


2.ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትና ዛሬም ያው ነው
ቀናት አልወጡህ የዘመን ብዛት አላስርጀህ
የስልጣንህን ግርማ የስምህን ጉልበት ተመልክተን
ይሄው ፊትህ አለን ልናመልክህ ፈቅደን

በስምህ ስልጣን መናፍስት ሁሉ ይንቀጠቀጣል
ደዌ ይፈወሳል የበሽታ ሃይል ሁሉ ይቀልጣል
ደካሞች በረቱ ወድቀው የነበሩ ተነሱ
በስምህ ሃይል አግኝተው ከፍታ ላይ ቆሙ

አዝ:ስምህ ከስሞች ሁሉ በላይ 4x
አብ ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ጉልበት ሁሉ ሊሰግድለት የተገባው
ምላስ ሁሉ የሚመሰክርለት
ስምህ ከስሞች ሁሉ  በላይ 2x
JUECSF Main & Beco

30 Jan, 12:13

577

☕️ Coffee Challenge: Day #4 ☕️

ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።   ዕብ 13:16

💰 ዛሬ ቡና እና ሻይ ባለመጠጣት 10 ብር ይለግሱ!

🎯 አላማው በPurelove team የሚሰሩ ስራዎችን ለመደገፍ ገቢ ለማሰባሰብ ነው።

ስለተሳተፋቹ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ  !
💙 Pure Love Team 💙
JUECSF Main & Beco

29 Jan, 10:38

594

☕️ Coffee Challenge: Day #3 ☕️

ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።   ዕብ 13:16

💰 ዛሬ ቡና እና ሻይ ባለመጠጣት 10 ብር ይለግሱ!

🎯 አላማው በPurelove team የሚሰሩ ስራዎችን ለመደገፍ ገቢ ለማሰባሰብ ነው።

ስለተሳተፋቹ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ  !
💙 Pure Love Team 💙
JUECSF Main & Beco

28 Jan, 09:27

614

☕️ Coffee Challenge: Day #2 ☕️

ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
  — ያዕቆብ 1፥27

💰 ዛሬ ቡና እና ሻይ ባለመጠጣት 10 ብር ይለግሱ!

🎯 አላማው በPurelove team የሚሰሩ ስራዎችን ለመደገፍ ገቢ ለማሰባሰብ ነው።

ስለተሳተፋቹ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ  !
💙 Pure Love Team 💙
JUECSF Main & Beco

27 Jan, 13:39

672

☕️ Coffee Challenge: Day #1 ☕️

ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።   ዕብ 13:16

💰 ዛሬ ቡና እና ሻይ ባለመጠጣት 10 ብር ይለግሱ!

🎯 አላማው በPurelove team የሚሰሩ ስራዎችን ለመደገፍ ገቢ ለማሰባሰብ ነው።

ስለተሳተፋቹ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ  !
💙 Pure Love Team 💙
JUECSF Main & Beco

21 Jan, 11:00

861

ዛሬ ማታ ከ 12:00-2:00
🧎‍♂የአጠቃላይ ህብረቱ የፀሎት ጊዜ

“እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት።”
  ኢሳይያስ 55፥6

@JUECS_Fellowship
JUECSF Main & Beco

18 Jan, 19:18

713

ሰላም የህብረታችን ተማሪዎች!!!

በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ በ17 እና በ 18
''ወደ ዳነ ልብ የተሸጋገረ ህዝብ-የቤተክርስቲያን ሚና ለፈውስ፣ለይቅርታ እና ለእርቅ'' በሚል ርዕስ የስልጠና ግዜ በ counseling team አዘጋጅነት ስለተሰናዳ ስልጠናውን መውሰድ የምትፈልጉ ከታች ባሉት መንገዶች ቀድማችሁ ተመዝገቡ::

@BreGF
@ayimofA
@naold2

የስልጠናው ግዜ: ከጠዋት 2:30-11:00
ስልጠናው ምሳ እና እራት
በነፃ ያካትታል::
ቦታ: ጅረን ቃለህይወት ቤተክርስቲያን

#hesed multimedia
@juecsfcounseling
JUECSF Main & Beco

18 Jan, 05:03

468

የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ!

ነገ(ቅዳሜ ) እንደተለመደው 11:30 ላይ የአጠቃላይ ህብረታችን የአምልኮ ጊዜ ይቀጥላል። በዚህም "የመንፈስ ፍሬ እና የስጋ ስራ" በሚል ርዕስ የትምህርት ጊዜ ይኖረናል። ስለሆነም ሁላችንም ማስታወሻ እና መፅሀፍ ቅዱሳችንን እየያዝን  በአንድነት ሆነን ጌታን ለማምለክ በጊዜ እንድንገኝ ስንል በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።

“የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል።”
— ገላትያ 5፥24 (አዲሱ መ.ት)

ነገ (ቅዳሜ)- 11:30-2:00
💒መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ

ተባረኩ!

@JUECS_Fellowship