Latest Posts from Injibara University (@injiuniversity) on Telegram

Injibara University Telegram Posts

Injibara University
15,162 Subscribers
4,022 Photos
18 Videos
Last Updated 15.03.2025 09:10

The latest content shared by Injibara University on Telegram

Injibara University

12 Mar, 12:33

4,197

ለአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ሴት አመራሮች በስራ ፈጠራ(Entrepreneurship) ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ
ስልጠና ተሰጠ፡፡
---------
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከብሄረሰብ አስተዳደሩ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር ሴት አመራሮች ከአመራርነት ባለፈ በኢኮኖሚ የበቁ ሆነው ጎን ለጎን ስራ ፈጥረው መስራት እንዲችሉ የሚያግዝ የአቅም ማልበቻ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መልካም አባተ
እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ ምርምር ባሻገር ማህበረሰብ አግልግሎት በርካታ የአቅም ግንባታ
ስልጠናዎች መስጠቱን ገልጸው ይህ ስልጠና በዩኒቨርሲቲው አንዱ የትኩረት መስክ በሆነው ቱሪዝም፣ ስራ ፈጠራ እና ልማት ዙሪያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር መልካም አያይዘውም ስልጠናው ሴት አመራሮች ለሚመሯቸው መስሪያ ቤቶች በስራ ፈጠራ የተሻለ ግንዘቤ ኖሯቸው ከአመራርነት ባለፈ በስራ ፈጠራም ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ነው ነው ብለዋል፡፡

የስልጠናው አስተባበሪ እና ኮር አመራር የሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት ነጋ እንደተናገሩት ስልጠናው ለአዊ ብሄረሰብ
አስተደዳር ሴት አመራሮች የመሪነት እና ስራ ፈጠራ አቅማቸውን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረው
ዩኒቨርሲቲው ሴቶች በሁሉም መስክ እንዲበቁ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ ወ/ሮ ወይንሸት አያይዘውም ብሄረሰብ አስተዳደሩ በቀጣይ በርካታ ስራዎችን በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02kn1HV3KCbFZgXiphevhWF5YgYSwSX3CkfcWwSfBzkiWGRJ8VeYPXHRpK7DA6TNX2l/
Injibara University

11 Mar, 17:21

5,198

ማስታወቂያ

ጉዳዩ፡- የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና እና ምዝገባ ቀናት የተራዘሙ መሆኑን ስለማሳወቅ

በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጋቢት 01/2017 መጠናቀቁ እና ፈተናው መጋቢት 05/2017 ከ3፡00 ጀምሮ እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል። ይሁን እንጂ በአንዳንድ ተፈታኞች ጥያቄ መሰረት ምዝገባው እስከ መጋቢት 04/2017 ዓ.ም እስከ ምሽቱ 12:00 የተራዘመ ሲሆን ፈተናው ደግሞ መጋቢት 12/2017 ከ3:00 ጀምሮ ይሰጣል።

በዚሁ መሰረት በተለያየ ምክንያት ምዝገባ ያመለጣችሁ አመልካቾች ምዝገባችሁን ቀደም ሲል በተገለጸው ሊንክ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ፈተናውን ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት በምትመደቡበት የፈተና ማዕከላት ተገኝታችሁ እንድትፈተኑ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
1. ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በምትሄዱበት ወቅት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
2. ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
3. የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
4. የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር
Injibara University

11 Mar, 17:19

4,528

"ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪቃል ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ።

ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (march 8)በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ114ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ49ኛ፣በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለ8ኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር)
ከዘንድሮው ዓለማቀፍ የሴቶች ቀን አመታዊ ክብረ በዓል መሪ ቃል የምንረዳው ዋና ቁም ነገር ሴቶች ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁለንተናዊ ለውጥ መምጣት ይቻል ዘንድ የሚጫወቱት አወንታዊ ሚና ላቅ ያለ
በመሆኑ በማንኛውም ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ በቤተሰብ፣በማህበረሰብና በሀገር ደረጃ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻል የሁላችን ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

ሴቶች እንደ አንድ የማህበረሰብ ክፍል ለቤተሰብ ለማህበረሰብ አና ለሃገር ሁለንተናዊ ለውጥና እድገት መምጣት ማበርከት ያለባቸውን አስተዋፅአ ማበርከት ይችሉ ዘንድ የሴቶችን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባናል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid033mBxL591aAmxDgVA3juw6M3ciDnpasBWNZ8JzwDdohMp3SidyGWvcxmv5Ltnx45ml/?app=fbl
Injibara University

06 Mar, 06:51

2,398

ማስታወቂያ
----
የሶስተኛው ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ እና የፈተና ጊዜን ስለማሳወቅ

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያሊንክ በኩል ይከናወናል፡፡
ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ [email protected] ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።

የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል፡፡

ማሳሰቢያ
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ ሆኖ በፈተና ወቅት የተሰጣችሁን User Name and Password፣ እና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቃባችኋል።

የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር
Injibara University

03 Mar, 11:35

5,316

ማስታወቂያ
Injibara University

03 Mar, 08:24

5,841

ማስታወቂያ
-----
ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ
Injibara University

28 Feb, 19:58

7,158

"ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል ” በሚል መሪ ቃል የዓድዋ ድል በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡
----
የካቲት 21/2017ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

በበዓሉ የዓድዋ ድል ተግዳሮቶች ፣ትሩፋቶች እና አስተምሮቶች፣The Dramatic Irony Of Ethiopia’s victory at Adwa እና የዓድዋ ድል እሳቤ እና ትውልድ፣በክብርት ዶ/ር እጅጋሁ ሽባባው ሙዚቃ የሚሉ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በበዓሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል ስናከበር የዓድዋ ድል የነጭን የተሳሳተ የዘረኝነት እና የበላይነት አስተሳሰብ በመሰረታዊነት የቀየረ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የድል በዓል በመሆኑ ብለዋል፡፡ ዶ/ር ክንዴ አያይዘውም እኛ ኢትጵያዊያን የዓድዋ ድልን በየዓመቱ ከመዘከር ባሻገር አንድነታችንን እንደ ትናንት የአድዋ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ማጠናከር እና የዓድዋ ድልን የይቻላል መንፈስን በመላበስ ተከባበብረንና እጅ ለእጅ ተያይዘን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02xPH9Wj2AZHABEh543oHArX89jNxnhSMToNwsSmsHb7NCJAoKPWj21V8eki2dCacal/?app=fbl
Injibara University

27 Feb, 18:21

7,468

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
-----
የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ከእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈራረሙን አስታውሰው የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን በንድፈ ሃሳብ ከሚማሩት በተጨማሪ በተግባር የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት ከአቅራቢያ ሆስፒታሎች ጋር ለመስራት በሚያግዝ መልኩ የስምምነት ሰነዱ ፊርማን አስፈላጊነት ተናግረዋል።

የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አዳነ ገበየሁ በበኩላቸው የሰምምነት ሰነዱ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤና ከማሻሻሉ በተጨማሪ የሆስፒታሉን ደረጃ የሚያሳድግልን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የስምምነት ሰነዱ አጠቃላይ ሃሳብ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በሆኑት ዳንኤል አዳነ (ረ/ፕሮፌሰር) የቀረበ ሲሆን ዓላማውም በሁለቱ ተቋማት መካከል የመማር ማስተማርን፣ጥናትና ምርምርን፣የማህበረሰብ አገልግሎትን፣የመድሃኒትና የቁሳቁስ ድጋፎችን እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።

በስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርስቲው ከፋተኛ አመራሮች እና የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ኃላፊዎች እንዲሁም የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
የካቲት 20/2017 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
Injibara University

27 Feb, 14:59

6,345

"የማዕድን ሀብት ልማት ለሀገራችን የኢኮኖሚ ግንባታ!" በሚል መሪ ቃል ከአጋር አካላት ጋር የውይይት
መድረክ ተካሄደ፡፡

የካቲት 20/2017 ዓ፣ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምህድስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ከማዕድን ልማት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ማዕድን
ልማት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል
ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ተወካይ ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) ዪኒቨርሲቲው የማዕድን ሀብት ዙሪያ
ለመስራት የማዕድን ዘርፍን ለማሳደግ እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የማዕድንን ትምህርት ክፍል በመክፈት የተማረ የሰው ሀይል በማፍራት፣ ጥናት እና ምርምር በማድረግ፣ ስልጠና በመስጠት እና ማህበረሰቡ
ከዚህ ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ክንዴ አያይዘውም የዚህ መድረክ ዓላማ የኒቨርሲቲው ያለውን የተማረ የሰው ሀይል ተጠቅሞ በሀገራችን፣ በክልላችን እና በብሄረሰብ አስተዳደሩ የሚገኙ ጠቃሚ የማዕድን ሀብት ማውጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መነጋገር፣ መወያየት እና አቅምን መገንባት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ውይይቱ
ያሉንን ሀብት ለመለየት፣ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄዎችን ለመፈለግ እና በቀጣይ በማዕድን ልማት ዙሪያ በጋራ መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታም ለመምከር የሚያስችል መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0cLjmbK8Kf2CRsFPqf7Fj9oSdMKJwEubgiB8sc1cC7NQmGUV1DsBrk3Hnu2HuqNrFl/?app=fbl
Injibara University

20 Feb, 10:07

4,727

የሀዘን መግለጫ

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መጀመሪያ ዓመት የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የነበረው ተማሪ ሞላልኝ ልንገረው ባደረበት ህመም ምክንያት ወደቤተሰቦቹ ሄዶ በህክምና ሲረዳ የነበረ ቢሆንም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ ሞላልኝ ህልፈት ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል!