وبيجوت Tube @hubi_resulilah Channel on Telegram

وبيجوت Tube

@hubi_resulilah


ይህ ቻናል የኡስታዞች የክርክር ወይም የውይይት መድረክ ነው #YouTube ላይ የሚተላለፉት የኡስታዞች ውይይት በቀጥታ ወደዚኛው ቻናላችን እንፖስትላችኃለን እንዲሁም ኢስላሚክ ታሪኮች፣ ትረካዎችን፣ ወቅታዊ ጉዳዩችን እና የመሳሰሉትን በዚ ቻናል ይለቀቃሉ ።

#YouTube https://www.youtube.com/channel/UCe1iUwdqZzyQHQcDyYuPOQQ

ለአስተያየት @Latekzebun_bot

وبيجوت Tube (Amharic)

ወደ 'وبيجوت Tube' የቴሌግራም ቻናል በተመለከተ እንደሚረዳ የሚለውን የፈቃድ ይዘት ይጠቀሙ። ይህ ቻናል የኡስታዞች የክርክር ወይም የውይይት መድረክ ነው በተጨባለ አገልግሎት፣ የኡስታዞች ውይይት በቀጥታ የሚተላለፉትን እና ኢትዮጵያውያንን የመከላከያ ውይል ለመሳሰሉ 'وبيجوت Tube' ቻናል ያደርጋል። እንደተጨባለ አገልግሎት በዚ ቻናል አርክቶ እንዲሁም ኢስላሚክ ታሪኮች፣ ትረካዎችን፣ ወቅታዊ ጉዳዩችን እና የመሳሰሉትን በዚ ቻናል ይለቀቃሉ። የቴሌግራም እና ኢትዮጵያውያን የሆነው አገልግሎት ይህን ይጠቀሙ። ስለእኛም አብሮን @hubi_resulilah ላይ በመጠቀም። #YouTube https://www.youtube.com/channel/UCe1iUwdqZzyQHQcDyYuPOQQ

وبيجوت Tube

05 Aug, 08:27


📘ርዕስ፦ የእዝነቱ ነቢይ

ፀሐፊ፦ ዑስማን ኑሪ

📄ትርጉም፦ ሐሰን ታጁ

📜የገፅ ብዛት፦ 140

🗓 ዓ.ም፦ 2004

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

05 Aug, 08:25


📘ርዕስ፦ ኢስላም ብቸኛው መለኮታዊ እምነት

ፀሐፊ፦ ኡስማን ኑሪ

📄ትርጉም፦ ሐሰን ታጁ

📜የገፅ ብዛት፦ 114

🗓ዓ.ም፦2004

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

04 Aug, 06:04


📘ርዕስ፦ የመጨረሻው እስትንፋስ

ፀሐፊ፦ ዑስማን ኑሪ

📄ትርጉም፦ ሐሰን ታጁ

📜የገፅ ብዛት፦ 40

🗓 ዓ.ም፦ 2003

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

03 Aug, 06:29


📘ርዕስ፦ ቀናት ከህይወቴ

ፀሐፊ፦ ዘይነብ አል-ገዛሊይ

📜የገፅ ብዛት፦ 138

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

31 Jul, 08:19


▫️የተባረከው የፍልስጤም ምድር

▪️ክፍል~4

የአይሁድ ሠፋሪ ታጣቂዎች ዴር-ያሲን የምትባል ከኢየሩሣሌም አቅራቢያ የምትገኝ ፀጥተኛ መንደር ላይ ከበባ ያደርጋሉ፡፡ ከዚያም ዕድሜና ፆታ ሳይለዩ ፊለፊት ያገኙትን ሁሉ በጥይት ቆሉት፡፡ በስለትና በመጥረቢያ ጨፈጨፉት፡፡ ለማምለጥ የሚሞክረውን መግቢያ መውጫውን ዘግተው በመጠበቅ ደፉት፡፡ በመጨረሻም 256 ነዋሪዎችን ጭፍጭፍ አድርገው አንድም እንዳልተረፋቸው እርግጠኛ ሲሆኑ ቤት ንብረቱ ላይ (የፍየልና የግመል ማደሪያ፣ የጥራጥሬ ማከማቻ ሳይቀር) እሣት ለቀቁበት፡፡ ይህ ይኾነው በሜይ 15 ቀን 1948 ላይ ነው፡፡ ፍልስጥኤማውያን ይህን ቀን ´አን-ነክባ’ ይሉታል፡፡ በታላቅ ምሬትም ያስታውሱታል፡፡ የሐዘንና የዕልቂት ቀን ማለት ነው፡፡
አይሁድ ግን በዚህ አልበቃቸውም፡፡ ´ታንቱራ’ በተባለች መንደር ላይም ተመሳሳይ ጥቃት ሠንዝረው 200 ነዋሪዎችን ፈጅተዋል፡፡
ፍልስጥኤማዊያን በዴር-ያሲን ወገኖቻቸው ላይ በተፈጸመው ጅምላ ፍጅት ክፉኛ ተናወጡ፡፡ ተረበሹ፡፡ በገዛ ቤት ቀያቸው ላይ ውለው ለማደር ደህንነት አልሰማቸው አለ፡፡ ባፋጣኝ ቀያቸውን እየለቀቁ በቀንና በለሊት ተሰደዱ፡፡ ምንም አልያዙ፡፡ ምንም አልቋጠሩ፡፡ አልሰነቁ- ብቻ ነፍሳቸውን ይዘው እግር ወደመራቸው ጎረፉ፡፡ አንፃራዊ ሰላም እናገኛለን ወዳሉበት ርቀው ሄዱ፡፡
ድርጊቱ ዓለም አቀፍ ውግዘት አስከትሎ ተኩስ አቁም ሲደረግ 800,000 ፍልስጥኤማዊያን ቤተሰቦች የትውልድ ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡ ገሚሱ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ኡርዱን ገቡ፡፡ ገሚሱ በረሃ አቋርጠው ሉብናን ደረሱ፡፡ ገሚሱ እስከዚህ ጊዜ ድረስ የዐረቦች ጠንካራ ይዞታ ወደነበረው የምዕራብ ዳርቻ (ዲፋ-ገርቢያ) እና የጋዛ ሠርጥ ሄደው ሜዳ ላይ ፈሰሱ፡፡ የተቀሩት ወደ ማዕከላዊ ፍልስጥኤም ተራራማ ቀበሌዎች በመሄድ ተገን ያዙ፡፡ በጊዜው 160,000 የሚሆኑ በገሊላ ነዋሪ ዐረቦች ብቻ እዚያው የመጣ ይምጣ ብለው ሲቀሩ ሌላው ተበትኗል፡፡
ተኩስ አቁም ተደርጓል ተብሎ አገር አማን የሆነ ሲመስል ተሰዳጆቹ ፍልስጥኤማዊያን ሌላ ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው፡፡ ወደየነበሩበት ቀየ አትመለሱም ተባሉ፡፡ ተከለከሉ፡፡ የኢስራኤል ጦር መንገዱን ሁሉ በከባድ መሣሪያና ፀረ-ሰው ፈንጂ አጥሮ አላስገባ አላቸው፣ አሳደዳቸው፣ ተኮሱባቸው፡፡ ይህን ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ኮሚሽን ተቋቁሞ ፍልስጥኤማውያኑ እዚያው ተሰደው ባሉበት ወደ 50 የሚሆኑ ጊዜያዊ መጠለያ (እነሱ ሙኸየማት ይሏቸዋል) በማቋቋም ተፈናቃዩን ህዝብ ማስተናገድ ጀመሩ፡፡
በአይሁዶች ላይ ጫና አሳድሮ ተፈናቃዩን ህዝብ ወደ ቀየው የማስመለሱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከዐረብ መንግሥታት በኩል ለረጅም ጊዜ ቢቀጥልም ውጤት አላመጣም፡፡ የፍልስጥኤማዊያኑ ከዛሬ ነገ ወደ ቀያችን እንመለሳለን ተስፋም የሩቅ ምኞት ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢስራኤል ቁጥጥር ሥር ባሉት ከተሞች የሚገኙ ፍልስጥኤም ዐረቦች ሌላ አመፅ በማስነሣት የ1953ቱን የግዲያ ርምጃ ወሰዱ፡፡ ከአይሁዶችም በኩል ተመሳሳይ ጥቃት በዐረቦቹ ላይ ሲፈጸም ነገሩ ተቀጣጠለ፡፡ በግጭቱ የተገደሉት ሥርዓተ-ቀብራቸው ሲፈጸም በዐረቦችና በአይሁዶች መካከል ሌላ ዙር ረብሻ ተቀሰቀሰ፡፡ አመፁ እየተባባሰ ቀጥሎ ማዕበሉ ሌሎች ከተሞችንም አዳረሰ፡፡ የብሪትሽ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በጃፋና በቴልአቢብ ከተሞች የሠዐት እላፊ ገደብ እስከመጣል ደረሱ፡፡ በናብሉስ ከተማም አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ አጠቃላይ የህዝብ አድማ ተጠራ፡፡
ሁኔታውን ተከትሎ የብሪትሽ ጦር ወደ 20,000 የወታደር ኃይል ከፍ ከተደረገ በኋላ በፍልስጥኤም የፊዳዒይን ንቅናቄ አባላትና በብሪትሽ አይሁድ ጣምራ ኃይላት መካከል ኖቬምበር 1953 ላይ ደም አፋሳሽ ውጊያ ተካሄደ፡፡ የነዚህ ተከታታይ አመፆችና ግጭቶች ድምር ውጤት ብዙ እንግሊዞችና ሠፋሪ አይሁዶች የተገደሉበትና የአካል ጉዳት ያገኙበት ሲሆን ከዐረቦቹም በኩል 145 ሰዎች የተሰዉበትና በመቶዎች የሚቆጠሩ የተጎዱበት ሁኖ ተመዝግቧል፡፡
የፍልስጥኤሞች መነሳሳት እንደገናም በመቀጠል የእንግሊዝ መንግሥት እስከዛ ጊዜ ድረስ ይዞት የነበረውን አይሁድ ዘመም አቋም እንደገና እንዲያጤነው የተገደደበትን ርምጃ ወሰዱ፡፡ የጀሊል ከተማን እንግሊዛዊ አስተዳዳሪ ገደሉት፡፡ በዚህም የተነሳ እንግሊዞች ካንዳንድ አቋሞቻቸው በማፈግፈግ አገሪቱን በአይሁዶችና በፍልስጥኤሞች መካከል የመክፈል ሃሳብም ለማቀንቀን ተገደዋል፡፡
ባንድ በኩል ምንም ውጤት ያለመገኘቱ ነገር እንዳለ ሁኖ ውስጥ ውስጡን ደሞ የኢስራኤል ሠፋሪ መንግሥት ድንበር እየገፋ ሠፈራውን የማስፋፋቱ ድርጊት የተጎራባች ዐረብ መንግሥታትን ቁጣ እያስነሣ ቁርቋሶና ወታደራዊ ግጭቶች ተካሂደዋል፡፡ በ1956 ሲናይ ምድር ላይ ከግብጽ ጋር የተደረገው ውጊያ ተጠቃሽ ነው፡፡ አይሁዶች በሲናይ ድንበር በኩል ከግብጽ የሚደርስባቸውን ወታደራዊ ጫና ለማርገብና እስከ ወዲያኛው ከግብጽ ተከታታይ ጥቃት ለመጠበቅ ሲሉ ከፈረንሳይና ከእንግሊዝ ጎን በመሆን ግብጽን ወግተዋል፡፡ የሲናይን ምድር ለመቆጣጠር የነበራቸው ሃሳብ ግን አልሠመረም፡፡ በ1967 የስድስቱ ቀን ጦርነት ግን ተሳክቶላቸው ከግብጽ የሲናይን ምድር፣ ከሶሪያ የጎላንን ኮረቦታዎች፣ የደቡብ ሊባኖስን ከፍታማ ቀበሌዎች መያዝ ችለዋል፡፡ በዐረቦች ይዞታ ሥር በሚገኙት የምዕራብ ዳርቻና የጋዛ ሠርጥ ላይ ቁጥጥር ማጥበቅ የሚያስችላቸውን ገዢ መሬትም ተቆናጠጡ፡፡ ይህንንም አዲስ ጥቃትና ወረራ ተከትሎ ተጨማሪ ፍልስጥኤሞች ለስደት ተዳረጉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኛ ኮሚሽንም ተጨማሪ 10 መጠለያዎችን በማቋቋም የመጠለያውን ቁጥር ወደ 60 ከፍ አደረገው፡፡
ፍልስጥኤማዊያን ከቀያቸው ላይ በግፍ ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ እስካሁንም ድረስ በምዕራብ ዳርቻ፣ በጋዛ ሠርጥና በጎረቤት ዐረብ አገራት በስደተኛ ካምፖች እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ በጎረቤት አገራት የምጣኔ ሀብትና የማኅበራዊ ህይወት መዋቅር ውስጥ መቅለጥና ሟምተው መጥፋት አልፈለጉም፡፡ የማንነት ጉዳይ ነው፡፡ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ፡፡ በመሠረቱ ይህ የፍልስጥኤማዊያን ወደ አገር ቤት የመመለስ ቁርጠኛ አቋም ነው እስካሁንም አይሁዶችን ዕንቅልፍ እየነሣ ያለው፡፡

[ምንጭ፦ تاريخ فلسطين]

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

30 Jul, 06:59


▫️የተባረከው የፍልስጤም ምድር

▪️ክፍል~3

ፍልስጥኤሞች ከ20ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ህልውናቸውን ሊያስክድ የመጣባቸውን ባዕድ ኃይል በከፍተኛ አልበገር ባይነት የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ በመከላከል ላይ ናቸው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመምለካና በቃሂራ የሚገኙ አንቱ የተሰኙ ሙፍቲ ዑለሞች ሳይቀሩ ለምን ምድሩን እንዳለ ጥላችሁላቸው አትሰደዱም የሚል ወኔ ሰላቢ ምክር እየለገሷቸውም እንኳ እጅ አልሰጡም፡፡ የመከላከሉ ጦርነት አጀማመርና ሂደት እንደ አንድ ተጨቋኝ ህዝብ ትግል የተለያዩ መርሐላዎችን (ስቴጆችን) ማለፍም ነበረበትና የሚከተለውን ይመስላል፡-
በ1918 አንድ የአርበኞች ኮሚቴ የፍልስጥኤም ሹርጣ አባላትን በማካተት በሕቡዕ ተቋቋመ፡፡ ይህ ኮሚቴ ለዐረብ አብዮት መሠረት በመጣልና በምሥራቅ ኦርዶን በሚኖሩት በረኸኛ ዐረቦች (አዕራብ) ዘንድ የጽዮናዊያንን ሤራ በማጋለጥና ንቃተ-ኅሊና በመፍጠር የላቀ ሚና ተጫውቷል፡፡ ኮሚቴው በመሪዎቹና በአስተባባሪዎቹ ላይ በደረሰው እስራትና ማሳደድ የተነሣ ሊዳከም ቢችልም ብሶት እያባባሰው የመጣው የፍልስጥኤሞች መነሳሳት ግን እየቀጠለ በመሄድ በ1920 ከኤፕሪል 4 እስከ 10 የዘለቀ አመፅ ተካሂዷል፡፡ ቀጥሎም በ1921 የጃፋ አብዮት ተቀጣጥሏል፡፡ እንደገናም የቡራቅ አብዮት በ1929 ቀጥሏል፡፡ እነዚህ አመጾች ምንም እንኳ ባደረጃጀት ያልተሟሉና ግብታዊ የነበሩ ቢሆንም ትግሉን በማቀጣጠልና የጽዮናዊያን መሠሪ እቅድ ባንዴ ፍጻሜ እንዳያገኝ በማጓተት የጎላ ድርሻ ነበራቸው፡፡
የፍልስጥኤም ታጋዮች ተጨማሪ ኃይል ማደራጀት ቀጠሉ፡፡ ከነዚህ መሀል በኢዘዲን አልቀሳም የተደራጀው በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ ኢዘዲን አልቀሳም ማነው? እሱ ከሶሪያ ወደ ፍልስጥኤም በመምጣት የዲን ኡስታዝ ሆኖ የራሱን የትግል እንቅስቃሴ የጀመረ ሰው ነው፡፡ በ1926 አንድ የንቅናቄ ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት ይመዘገባል፡፡ በ1928 የንቅናቄውን የሐይፋ ቅርንጫፍ ይመሰርታል፡፡ ቀጥሎም የዚሁ ቅርንጫፍ መሪ ይሆናል፡፡ በ1930 የንቅናቄው የአስተዳደር ኮሚቴ አባል በመሆን የመሪነቱን ቦታ ይጨብጣል፡፡
ከዚህ በኋላ አልቀሳም የመንግሥት ሠራተኛ በመምሰል በብዙ የፍልስጥኤም ክልሎች እየተዘዋወረ በአምስት አምስት አባላት የተደራጁ ህዋሳትን በስፋት አዋቀረ፡፡ ኢስላማዊ ህግጋት የትግሉ መመሪያ መሆን እንዳለባቸው አስተማረ፡፡ ብቸኛው የነፃነት መንገድም ጂሃድ ፊ ሠቢሊላህ መሆኑን አሠመረበት፡፡ አፅንዖት አደረገበት፡፡
ይህ በኢዘዲን አልቀሳም የተደረጃ የህቡዕ ንቅናቄ በዐይነቱ ለየት ያለና በዐረብ ፍልስጥኤሞች የትግል ታሪክ ውስጥ ትልቁ የፊዳዒይን (የመስዋዕትነት) ንቅናቄ እንደሆነም ይታመናል፡፡ ማዘዣ ቢሮዎቹ ደሃው ህዝብ በሚበዛበት የኢያሪኮ ከተማ ነበር፡፡ በአካባቢው ላይ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ ሲመጣ አደረጃጀቱን አሰፋው፡፡ የደዕዋና የአህዝቦት፣ የወታደራዊ ሥልጠና፣ የአቅርቦት፣ የኤሌክትሮኒክስና የውጭ ግንኙነት አካላትን በመፍጠር አቋሙን ይበልጥ አጠናከረ፡፡
በ1935 ኢዘዲን አልቀሳም የአብዮቱን መጀመር ይፋ አደረገ፡፡ ይህም የሆነው ሠላማዊ መፍትሄ የማፈላለጉ ጥረት ለተደጋጋሚ ጊዜ ተሞክሮ ያለውጤት መቅረቱ እውን ከሆነ በኋላ ነው፡፡ የአብዮቱን መጀመር ተከትሎ በቀሳም ታጣቂዎችና በእንግሊዝ ጦር መካከል ተከታታይ ግጭቶች ተካሄዱ፡፡ ብዙ ፍልሚያዎች ተደረጉ፡፡ ኋላ አልቀሳም ማፈግፈግ ግድ ሆነበት፡፡ ከተወሰኑ የጦር ጓዶቹ ጋር አንድ ቦታ ላይ ከበባ ተደረገበት፡፡ እጁን በሰላም እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ አልፈቀደም፡፡ በተከተለው የተኩስ ልውውጥ ዐቅጣጫዋ በውል ያልተለየ ጥይት አገኘችው፡፡ ተገደለ፡፡ በተቀሩት ጓዶቹና በእንግሊዝ ጦር መካከል የከረረ ውጊያ ተካሂዶ የሞቱት ሞተው የተቀሩት ጠላት እጅ ወደቁ፡፡
አልቀሳም የመሰዋቱ ዜና ሲሰማ መላው ፍልስጥኤም ተላወሰ፡፡ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ለፍልስጥኤም ሌላ የትግል ቃል ኪዳን ማሰሪያ ቀን ሁኖ ዋለ፡፡ የቀሳም ንቅናቄ በዓላማውና በተነሳሽነቱ ረገድ በዐይነቱ የመጀመሪያው ነው፡፡ በአይሁዶችና በእንግሊዞች ላይ በቀጥታ ያነጣጠረ ወታደራዊ ንቅናቄ ነበር፡፡
ኢዘዲን አልቀሳም ለፍልስጥኤም ነፃነት መዋጋትን ሊልላሂ ብሎ ኒይያው አድርጎ ከሶሪያ ወደ ፍልስጥኤም በመምጣት ኑሮውን እዚያው ያደረገ አላህን ፈሪ ሰው መሆኑ ይታወቃል፡፡ እሱ ባቀጣጠለው ሰውራና በከፈለው መስዋዕትነት በፍልስጥኤሞች ዘንድ የላቀ ተነሳሽነት ተፈጠረ፡፡ ህዝቡ ተቀሰቀሰ፡፡ በርግጥም እሱ ያመላከተው የትግል መንገድ፣ የውጊያ ስልትና የተጋፋጭነት አቋም ትምህርት ሰጪ ነበር፡፡ የአይሁድ/ እንግሊዝን ጣምራ ኃይል ጂሃድን መርሁ ባደረገ ስልት መዋጋት እንደሚያስፈልግ በሁሉም ፍልስጥኤማዊ ዘንድ እየታመነበት መጣ፡፡
በቀሳም መሞት የፍልስጥኤም አብዮት አብሮ አልሞተም፡፡ ነገሮች ቤንዚን እንደተርከፈከፈበት እሣት ይበልጥ ተቀጣጠሉ፡፡ የ1936ቱ የተራዘመ አብዮት ፈነዳ፡፡ የሥራ ማቆም አድማ፣ ተገዳዳሪ ሠልፍ፣ ለቅኝ አገዛዝ ህጎች አልታዘዝ ባይነት፣ የዚህ አብዮት ዐይነተኛ መለያዎች ነበሩ፡፡ ህዝባዊ አመጹ ብረታዊ ድጋፍም እየታከለበት በ1930ዎችና በ1940ዎች ቀጥሏል፡፡
ሁኔታው በፍልስጥኤሞች ወገን ባጭሩ ከላይ የተወሳውን ዐይነት ገጽታ ሲኖረው በአይሁዶች በኩል ደሞ የተጀመረው አፍራሽ ድርጊት በእንግሊዝ ጦር ሽፋን ሰጪነት እንደቀጠለ ነበር፡፡ በ1930ዎቹና በ1940ዎቹ ይበልጥ እየተጠናከረና ዐይን እያወጣ የመጣው የጽዮናዊያን እንቅስቃሴ ጭፍን ደረጃ በመድረስ የ1948ቱን የአይሁድ መንግሥት (Jewish state) ምሥረታ እውን አደረገ፡፡
ፍልስጥኤሞች ይህን ፈጣጣ ድርጊት በይሁንታ አላለፉትም፡፡ በቁጥርና በትጥቅ ከፍ ብሎ ተጠናክሮ ከተጋረደባቸው የእንግሊዝ ጦርና የአይሁድ ሠፋሪ ታጣቂ ኃይል ጋር እጃቸው ላይ ባለ ነገር ሁሉ ተፋልመዋል፡፡ የተቀሰቀሰው የህዝብ ፍልስጥኤም ቁጣ በዋዛ እንደማይበገር የተረዱት እንግሊዞችና አይሁድ ሠፋሪዎች የተነሱበትን ግዛት የማስፋት እቅድ ዳር ለማድረስ ሲሉ እስከዛሬ ድረስ ጠባሳው ያልሻረውንና በሙስሊሙ ዓለም በተለይም ዐረብ ፍልስጥኤም ዘንድ መሪር ትውስታ ያስከተለውን የሜይ 15/1948 አስከፊ ድርጊት በፍልስጥኤም ሠላማዊ ህዝብ ላይ ፈፀሙ፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

27 Jul, 06:43


▫️የተባረከው የፍልስጤም ምድር

▪️ክፍል~2

እ.አ.አ. በ1907 በወቅቱ በእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ባሔንሪ ካምፕቤል የተቋቋመ ኮሚቴ ወደ ሥራ መግቢያ ጥናቱን አቀረበ፡፡ በጥናቱ መሠረት ከዐረቦች በኩል በማንኛውም ጊዜ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ለመከላከል በመሀከላቸው የኖረውን ታሪካዊ፣ መንፈሳዊና ዝምድናዊ ትስስር እንደመነሻ እያደረገ የሚፈጠረውን አንድነት መስበርና ህብረታቸውን ጨርሶ ማድከም አስፈላጊ መሆኑ ይሰመርበታል፡፡ ይህ ደሞ በተሳካ መልኩ ሊከናወን የሚችለው የክልሉን አፍሪካዊና እስያዊ ክፍል ሁለት በመክፈልና መሀል ላይ ለምዕራቡ ወዳጅ ታማኝ ለዐረቡ ጠላት ባላንጣ የሆነ ሰብዐዊ ጋሬጣ ማቆም ሲቻል መሆኑንም አያይዞ ግልጽ ያደርጋል፡፡ የአፍሪካና የእስያ አገናኝ መሬት ፍልስጥኤም ናት፡፡ የአፍሪካና የእስያ ሙስሊሞች ታላላቅ ጦርነቶችን እንደተናሰ ግንብ ትከሻ ገጥመው የተዋጉበት ምድር ቢኖር ፍልስጥኤም ቅድሚያ ተጠቃሽ ናት፡፡ ይህ ደሞ ከሁለት አህጉራት አገናኝነቷም በተጨማሪ በኢስላም ካላት የላቀ ደረጃና የተከበረች የተባረከች ሥፍራ ከመሆኗም አንፃር ነው፡፡ ከሙስሊሙ ዓለም የምዕራብ በር ላይ መገኘቷንም ልብ ይሏል፡፡
እናም ይህን ሥፍራ መያዙና ከአካባቢው ህዝብ ጋር የጎሪጥ የሚተያይ ባዕድ ኃይል መሀል ላይ ሰንቁሮ ማስጠበቁ ከሙስሊሙ ዓለም በኩል ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በመከላከል ረገድ ሁነኛ ብልኃት መሆኑን ነው የሄንሪ ካምፕቤል ኮሚቴ ጥናት የሚያትተው፡፡ በ1917 ኖቬምበር 2 ይፋ የሆነው የባልፎር ሠነድ መሠረታዊ ይዘትም ይኸው ነበር- በፍልስጥኤም ምድር ላይ አይሁዳዊ ሀገር ቤት መመሥረት፡፡
በተለያዩ ዘገቦች፣ ጥናቶችና የአቋም መግለጫዎች እየተጠናከረ የመጣው የአይሁድ አገር ቤት ምሥረታ ከተሠነደና ይፋ ከተደረገ በኋላ በ1917 ዲሴምበር 11 ቀን የብሪትሽ ጦር ሠራዊት በጀነራል አለንቢ እየተመራ ኢየሩሣሌም ገባ፡፡ በወቅቱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥም በአርተር ባልፎር የተሰየመውና Balfour Decleration የተሰኘውን ፍርደ-ገምድል ሠነድ መሬት ላይ የማዋሉ ሥራም አንድ ተባለ፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በነዋሪው ዐረብ ማኅበረሰብና በመጤ የአይሁድ ሠፋሪዎች መካከል አስፈሪ ውጥረት ነገሠ፡፡
ጽዮናዊያን ዕለቱን እንደ አንድ የድል ቀን ሊያከብሩት ሲሞክሩ ከዐረቦቹ በኩል ደሞ የአይሁዶችን ሤራ የሚቃወሙ ኮሚቴዎችን በማዋቀርና የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት በፍጥነት የተገዳዳሪ ሠልፍ ጥሪ ተላለፈ፡፡ ገና ከወጥኑ አንስቶ የሤራው አባሪ ተባባሪ የነበሩት እንግሊዞች ከዐረብ ፍልስጥኤሞች በኩል እየተጠነሰሰ የመጣውን አመፅ ባጭሩ ለማስቀረት ሲሉ በተቃውሞ ሠልፉ የሚገኝ እያንዳንዱ ዐረብ ተይዞ ዘብጥያ እንደሚወርድ በማስጠንቀቅ በብሪትሽ ከፍተኛ ኮሚሽነር ሐርበርት ስሜል በኩል እንዲተላለፍ አደረጉ፡፡
በሜይ 1920 የእንግሊዝ መንግሥት በፍልስጥኤም ላይ ሙሉ ማንዴት ተሰጠው፡፡ ባለ ሙሉ ሥልጣን ሆነ፡፡ ከማንዴቱ መታወጅ ሶስት ቀናት በኋላ የእንግሊዞች ልዩ ተልዕኮ (Special mission) የአይሁድ አገር ቤት ምሥረታ መሆኑንም እራሳቸው እንግሊዞች ይፋ አደረጉት፡፡ በእንግሊዝ ዘቦችና ዐረቦች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የለየለት ግጭት ተካሄደ፡፡ በኢያሪኮ ከተማ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የፍልስጥኤሞች ሁለተኛ ጉባኤም በዚሁ ሰበብ ታገደ፡፡
እንግዲህ! የእንግሊዝና የአይሁድ ጽዮናዊያን ሤራ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ሲውጠነጠን እንደነበረ ግልጽ ነው፡፡ በመሠረቱ የፍልስጥኤም መከራና ሥቃይ የተጠነሰሰው መላውን ሙስሊም ዓለም በሥሩ ሲያስተዳድር የነበረው የቱርክ ዑስማንያ ኢስላማዊ መንግሥት በምዕራባዊያን እጅ ሲሸነፍና ጨርሶም በ1924 እንዲያበቃለት ሲደረግ ነው፡፡ የውድቀቱ ቀጥተኛ ውጤት ሆነናም ባንድ መንግሥት ጥላ ሥር ተማክሎ ይኖር የነበረው ሙስሊሙ ዓለም ዛሬ በሚታየው መልኩ በምዕራባዊያን እቅድና ፍላጎት የተከፋፈለ ጭፍራ ሆነ፡፡ እያንዳንዱ ራሱን ’ነፃ መንግሥት´ እያለ ዐወጀ፡፡
ምዕራባዊያን ይሄን ነገር እንደምን አሳኩት? ኢስላማዊውን መንግሥት ለመከፋፈል የተጠቀሙበት ዘዴ የቱርክና የዐረብ ብሔረኛ ስሜት በመጫር ነበር፡፡ በኢስላም መለኮታዊ ዓርማ “ላ ኢላሀ ኢልለላህ ሙሐመዱን ረሡሉልላህ” በሚለው ሥር ወንድማማች ሁኖ ባንድ ዱንያዊና ዲናዊ ዓላማና ግብ ተሳስሮ የኖረውን ህዝብ ገዢና ተገዢ አድርገው በመሳል አቃቃሩት፡፡ ቱርኮችን እንደገዢ፡፡ ዐረቦቹን እንደ ተገዢ፡፡ በዚህም ዐረቦች ከቱርክ ነፃ መውጣት አለባችሁ ተባሉ፡፡ እነሱም በየፊናቸው የተነገራቸውን ተቀብለው ዐረብ ብሔረተኝነትን በማራገብ ተጠመዱ፡፡ ስለሆነም ያቺ የታሪካቸውና የሃይማኖታቸው ሞገስ የሆነችው ፍልስጥኤም ሐቢባ ክብሯን ስትገፈፍና በባዕዳን ስትመዘበር እነሱ የእንግሊዝ መንግሥት በሰጣቸው የቤት ሥራ ተጠምደው አይሰሙም አይለሙም፡፡ የነቢያቱ አገር ቤት፣ የእስራእ ወል ሚዕራጅ አገር፣ የአቅሷና የኸሊል ምድር፣ የስንቶች ሙጃሂዲን ደም የፈሰሰባት ቅድስት ሀገር ከሐዲያን ሲያረክሷት ዐረቦች እዚያው ግድም ሆነው አንድ ነገር ማድረግ አልቻሉም፡፡ ክብርና ሞገሳቸው ከነበረው ኢስላማዊ አንድነት ይልቅ እስከዛሬ ተዋራጅ ሆነው ያሉበት ብሔራዊ ልዩነት ይሻለናል በሚል የዘቀጠ እምነት ጎራ ለይተዋል፡፡ ወደ ፍልስጥኤም ዞረው ለማየትና ተቃውሞ ለማደራጀት ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ለዘላለም ከክብር ሰገነት የወረዱበት ጎሠኛ ስሜት ዛሬ ወደሚገኙበት የውርደት አዘቅት እያንደረደራቸው ሌላ ምንም ቢባሉ የሚያዳምጡ አልነበሩም፡፡ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ግብጽ፣ ሱዑድ ዐረቢያ … ተብለው እንደተለያየ አገር መታወጅን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገው መሽቀዳደም ይዘዋል፡፡ ምዕራባዊያን ውጥናቸው በዐረቦች እጅ ሲፈፀም እያዩ ባደባባይ ይስቃሉ፡፡ ዛሂድ ዑለሞች ተደብቀው ያለቅሳሉ፡፡
ፍልስጥኤሞች የዐረብ ወገኖቻቸውን እገዛ በመሻትም ጭምር አገራቸው ፍልስጥኤም የታላቁ ሶሪያ (ቢላዱ ሻም) አንድ አካል መሆኗን አበክረው ለማስረዳት ቢሞክሩም ለነሱ የተደገሠላቸው ሌላ ነገር ስለነበረ ሰሚ አላገኙም፡፡ እንደሌሎቹ ሁሉ ለነሱም አገራዊ ነፃነት እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም አልተደመጡም፡፡ እነሱ እስከመኖራቸውም እውቅና ሊሰጣቸው አልተፈለገም፡፡ በነሱ ላይ የአይሁድ አገር ቤት ተመሥርቶ ያ እንደ መንግሥት እንዲታወቅ ነው የተፈለገው፡፡ “የምን ፍልስጥኤም ብሎ ሀገር”፡፡ ሌሎቹ ዐረብ አገራት በመሬታቸው ላይ የአይሁድ ሠፋሪ ሳይኖርባቸው ብሔራዊ ተብዬውን ነፃነት ሲሰጡ ፍልስጥኤም ግን ባዕድ ሠፋሪም ሠፍሮባት ብሔራዊ ተብዬውን የይስሙላ ነፃነትም ተነፍጋ ህልውናዋን ለማስቀጠል ትታገል ይዛለች - እስካሁንም አለች፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

26 Jul, 14:46


▫️የተባረከው የፍልስጤም ምድር

▪️ክፍል~1

የተባረከው የፍልስጥኤም ምድር መቼም ቢሆን የአይሁድ ይዞታ ሆኖ አያውቅም፡፡ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ለአይሁድ የተለየ አገር (separate homeland) የመፍጠሩ ሀሳብ ሲንሸራሸር በነበረበት ወቅት ከፍልስጥኤም ውጭ ሌላም ቦታ ታስቦ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ዓለምን ለማደናገር እንደሚሞከረው የፍልስጥኤም ምድር ከድሮም የአይሁድ ይዞታ የነበረ ቢሆን ኖሮ፣ ለነሱ አገር ቤት በመፍጠሩ ሀሣብ ውስጥ አርጀንቲናና ዑጋንዳ ታሳቢ ባልተደረጉ ነበር፡፡
ለአይሁድ የብቻ አገር ቤት የመፍጠሩ ሀሣብ የአውሮጳን ቡራኬ አግኝቶ በዋናነት ፍልስጥኤም ተመረጠች፡፡ ዓላማውን እውን የማድረጉ እንቅስቃሴም ተጀመረ፡፡ ጊዜው በ8ኛው መቶ ሂጅሪያ ማብቂያ ላይ ነበር፡፡ ይህ ወቅት ደሞ የምዕራብ የኩፍር ኃይላት የዑስማንያ ቱርክን ኢስላማዊ መንግሥት ለመጣል የተጠናከረ ርብርብ እያደረጉ የነበረበት ወቅት ነው፡፡ አይሁዶችም ይህንኑ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና ገፀ-በረከት በማስያዝ አንድ ከማኅበረ-አይሁድ የተውጣጣ የልዑካን ቡድን በአውሮጳ ድጋፍ ሰጪነት ወደ ወቅቱ የዑስማኒያ ካሊፌት ሡልጣን ዐብዱልሐሚድ ላኩ፡፡ ልዑኩም በሡልጣኑ ቤተ-መንግሥት ተገኝቶ አይሁዳዊያን በፍልስጥኤም መሬት ላይ መሥፈር እንዲችሉና የመግቢያ ፈቃድም እንዲሰጣቸው ተማጽኖ አቀረበ፡፡
ሡልጣን ዐብዱልሐሚድ ግን በጊዜው መንግሥታቸው ላይ እየተደረገ በነበረው አሉታዊ ጫና ሳይበገሩ፣ በቀረበላቸው ገፀ-በረከትም ሳይደለሉ የአይሁዶችን ጥያቄ ውድቅ አደረጉት፡፡ አይሁዶች አንዴ እንደምንም ብለው ፍልስጥኤም መሬት ላይ እግር መትከል ከቻሉ አገሪቱን ከተቀረው ኢስላማዊ ግዛት በቀላሉ በመነጠል የግላቸው ሊያደርጓት ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራቸው፡፡ ቀድሞ ከታያቸው ከዚህ ሥጋት በመነሳትም ይመስላል ሡልጣኑ በ1900 እና በ1901 መካከል በነበረው አጭር ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ ደንቦችን በማስረቀቅ ማንኛውም የአይሁድ መንገደኛ ከሶስት ወር ባለፈ ፍልስጥኤም መሬት ላይ ውሎ ማደር እንደሌለበት ይደነግጋሉ፡፡ ከዚህም ሌላ ምንም ዐይነት የመሬት ሽያጭ ከአይሁድ ጋር እንዳይፈፀም ጥብቅ ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡
የአይሁዶች ጥረት ግን በቀላሉ የሚቆም አልነበረም፡፡ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን የወርቅ ዲናሮችን በከረጢት ቋጥረው እንደገና በ1920 ወደ ሡልጣኑ ቤተ-መንግሥት አመሩ፡፡ በጊዜው የዑስማኒያ ኢስላማዊ መንግሥት ካዝና በብዙ ወጪዎች ተራቁቶ ባዶ እንደነበረም ያውቃሉ፡፡ እንደዛም ሁኖ ግን የኢስላማዊውን መንግሥት ይሁንታ በወርቅ ሳንቲሞች ለመግዛት ያደረጉትም ጥረት በሡልጣኑ ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ ሡልጣኑ የጉዳዩ ዋና አስተባባሪ ለነበረው ለቴዎዶር ሄርዞል በላኩት ማስታወሻ ግልጽ እንዳደረጉት “… ከፍልስጥኤም መሬት ላይ ስንዝር ቆርሼ መስጠት አልችልም፣ ምክንያቱም የግል ንብረቴ አይደለምና ነው፡፡ ባለመብቱ ህዝቡ ነው፡፡ ህዝቦቼ ለዚህ መሬት ሲሉ የህይወት መሥዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ደማቸውን አፍሰውበታል፡፡ ስለዚህ አይሁዶች የወርቅ ዲናሮቻቸውን ለራሳቸው ያድርጉት፡፡ ምናልባት መንግሥቴ ቢፈርስ ያን ጊዜ ፍልስጥኤምን በቀላሉ ነጥሎ መያዝ ይቻላቸው ይሆናል፡፡ እኔ በአፀደ ሥጋ እያለሁ ግን ከሰውነቴ ላይ በስለት ተቆርጦ ቢወሰድ ይቀለኛል - ፍልስጥኤም ከኢስላማዊው መንግሥት ተነጥላ ስትሄድ ከማይ፡፡ ይህ ደሞ ከቶም ሊሆን የማይችል ነው” በማለት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ግልጽ አደረጉላቸው፡፡
እንደሚታወቀው ቴዎዶር ሄርዞል ዋነኛ የአይሁድ አገር ቤት ምሥረታ አቀንቃኝ የነበረ ሰው ነው፡፡ ሠፈራን መሠረት ያደረገ ቅኝ ግዛት እንዴት ሊቋቋም እንደሚችል ቀድም ሲል ጀምሮ ከሮዲዚያ የዛሬዋ ዚምባውቤና መሠል ሀገራት ልምድ በመውሰድ የአይሁድ አገር ቤት ምሥረታም በተመሳሳይ መንገድ ሊከናወን እንደሚችል የፀና እምነት ነበረው፡፡
ከዚህ በኋላ አይሁዶች በቀጥታ ወደ ፍልስጥኤም ለመግባት ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካ እየገባቸው ሲመጣ አሳቻ መንገዶችን መጠቀም ይጀምራሉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜም ተሳክቶላቸው ´Union & progress society’ በተሰኘና አባላቱ ቱርካዊ ሥያሜ በመያዝ ሙስሊም ነን በሚሉ አንድ የአይሁድ ጎሣ ድርጅት በኩል ቀስ በቀስ ወደ ፍልስጥኤም መግባት ቻሉ፡፡ ይህን ያህል መግቢያና እግር መትከያ ክፍተት ካገኙም በኋላ ወደ ፍልስጥኤም የሚያደርጉትን ንቅናቄ በድርጅቱ አባላት በኩል የበለጠ በማጠናከር እስከ 1924 የካሊፌቱ ይፋ ውድቀት ድረስ ቀጥለዋል፡፡
ከ1917 ጀምሮ ኢየሩሣሌም የገባውና ቁጥጥሩን የዘረጋው የእንግሊዝ ጦር በሚሰጣቸው ከለላ አንዳንድ እያሉ በፍልስጥኤም መሥፈር የጀመሩት አይሁዶችም፣ ዋል አደር እያሉ ድንበር እየገፉ አጥር ማጠራቸውን ተያያዙት፡፡ ድርጊቱ ነዋሪዎቹን ዐረቦች እያስቆጣ ሲመጣ የእንግሊዝ ጦር ከሠፋሪ አይሁዶች በስተጀርባ በመሆን ይተኮስባቸው ጀመር፡፡ በዚህ ዐይነት ሤራ የአይሁድ በፍልስጥኤም ምድር ላይ መሥፈርና ብሎም መስፋፋት ከእንግሊዞች በኩል ያልተቆጠበ ድጋፍ እየተቸረው የብረት ሽፋንም እየተደረገለት ሲቀጥል እናያለን፡፡
በምዕራባዊያን በኩል ፍልስጥኤምን ቅኝ የማድረጉ ፍላጎትና የአይሁድ የአገር ቤት ምሥረታ ጥያቄ አንድ ላይ መገጣጠሙ በራሱም የራሱ ድርሻ ነበረው፡፡ ምዕራባዊያን የዑስማንያን ኢስላማዊ መንገሥት ካሸነፉ በኋላ ለዘመናት በሥሩ የቆየውን ሰፊ ኢስላማዊ ግዛት ለመቀራመት ሲከጅሉ ዐይናቸውን ከጣሉባቸው መሬቶች አንዷ ፍልስጥኤም ነበረች፡፡ ፍልስጥኤም የምዕራባዊያኑን ክጃሎት የሳበችው በታሪካዊነቷ ብቻ ግን አልነበረም፡፡ በመልክዐ-ምድራዊ አቀማመጧ በአፍሪካዊት ዐረባዊት ግብጽና በኢስያ ዐረቦች መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ ናት፡፡ ስለሆነም በዚህ ጊዜና ከዚህም በኋላ ሊኖር በሚችለው የሙስሊሞች ድንበር ዘለል ትብብር ላይ ሣንካ ለመፍጠር ከመሀል ፍልስጥኤምን ነጥሎ መያዙ በምዕራባዊያን ዘንድ እንደ አዋጭ መንገድ የታሰበበት ጉዳይ ነበር፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ በጊዜው የግብፅ አገረ-ገዢ የነበረው ሙሐመድ ባሻ ወደ ሻም ጉዞ ያደርጋል፡፡ የሱ ጉዞ ግብፅና ሶሪያን ሊያስተባብር ይችላል የሚል ግምት በማሳደሩ እንግሊዞች ሀሣብ ገባቸው፡፡
ቀደም ሲል ጀምሮ ሲቀነቀን በነበረው መሠረት ግብጽና ሻም በሚገናኙበት ማዕከላዊ ግዛት ላይ የአይሁድን የሠፈራ ፕሮግራም መቀበልና ማጠናከር እንዳለባቸው ተማመኑ፡፡ እንቅስቃሴም ጀመሩ፡፡ ይህ ደሞ ለምዕራባዊያን ሌላ ድብቅ በረከት ነበረው፡፡ ራስ ምታት ከሆኑባቸው አይሁዶች መገላገል፡፡ እናም ፍልስጥኤም በእንግሊዞች እጅ ለአይሁዶች ተበረከተች፡፡ መርዛሙን እሾህ ፍልስጥኤም ምድር ላይ በመትከልና ተንከባክቦ በማሳደግም አውሮጳ በተለይም ኢንግልተራ (እንግሊዝ) እኩል ተጠያቂ ናቸው የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

25 Jul, 08:12


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ የوبيجوت Tube ቤተሰቦች
ይህን እስላማዊ ቻናል ቀጣይነት እንድኖሮው እና የበለጠ የተሻለ ለማድረግ የእርሶን ድጋፍ እንሻለን!
የዚህ ቻናል ወዳጆች ቢያንስ እያንዳንዳችሁ 5 ሰው ብቻ ወደዚህ ቻናል በመቀላቀል ድጋፋችሁን አሳዩን!👍

አስተያየታችሁን ፃፍ ፃፍ አድርጉልን!👇
@AL_RISALAt 👈

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

25 Jul, 06:41


📘ርዕስ፦ በሠይፎች ጥላ ሥር

ፀሐፊ፦ አማን አሰፋ

📜የገፅ ብዛት፦ 115

🗓 1441 ሂጅሪያ

📖መፅሐፉ የሚዳስሰው:- ስለ ሰሐቦች፣ ስለ ደውላ ዑስማኒያ መስራቾችና የጀግኖችን ታሪክ ነው።

|አንብቡት በሚገባ ትጠቀሙበታላችሁ|

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

21 Jul, 06:41


📕ዘፈንና ሙዝቃ በኢስላም

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

18 Jul, 05:12


📕ብቻህን ትኖራለህ ብቻህን ትሞታለህ

ባል በበረሓ መሀል የሞት ጣር ያጣድፈዋል፤ ሚስት ትይዝ ትጨብጠው ጠፍቷት ግራ ቀኟን እያማተረች ታለቅሳለች።
‹‹ለምን ታለቅሻለሽ?›› ሲል ከሞት አፋፍ ላይ የሆነው ባሏ ጠየቃት።
‹‹መከፈኛ ልብስ እና ቀብር ቆፋሪም ሆነ ቀባሪ በሌለበት በዚህ በረሀ ማን ነው ሰግዶብህ ሚቀብርህ?›› ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች።
‹‹አብሽሪ! ይህ እኮ ድሮ ረሱል ያበሰሩኝ ብስራት ማረጋገጫ ነው። እየውልሽ አንድ ግዜ ምን ሆንን መሰለሽ! ረሱልለአንድ ዘመቻ ሰሀቦቻቸውን አስከትለው ከከተማ ቀድመውኝ ወጡ፤ እኔም ተከታትያቸው የበረሀውን ጉዞ ለብቻዬ ጀመርኩት።
ነገር ግን በቅሎዬ እግሩ መጓዝ ሲሳነው እሱን ትቼ በእግሬ የበረሀውን አሸዋ ማቋረጥ ጀመርኩ። አንዴ ስሮጥ አንዴ ስራመድ ብዙ ከተጓዝኩ በኋላ ከረሱል እና ከሰሀቦቻቸው ጋር ተገጣጠምን።
ረሱል እኔን ሲመለከቱ ፊታቸው መፍካት ጀመረ። በሁኔታዬ ተደስተው የምርጠትን ዘውድ ከራሴ ላይ ደፉልኝ። እንዲህም አሉ አባ ዘር ሆይ! አላህ ይዘንልህ። ብቻህን ትጓዛለህ። ብቻህን ትሞታለህ። ብቻህንም ትቀሰቀሳለህ።
ብቻህን በሞትክ ግዜም የሙስሊሞች ቆንጮ የሆኑ ቡድኖችም በበድንህ ላይ ይሰግዱብሀል›› ሲል ከህይወት ማህደሩ ወደ ኋላ በትዝታ ተመልሶ ተረከላት።
ንግግሩንም ቀጠለ፦ ‹‹ነፍሴ ስትወጣ ጎዳናው አፋፍ ላይ አስጠግተሽ አስቀምጪኝ። ከዝያ ጎዳና በኩል እነዝያ የሙስሊሙ ቁንጮዎች ይመጡ ይሆናል›› ብሎ ተናዘዘላት።
ነፍስ ወጣች። ሚስትም የባሏን በድን ተሸክማ ከጎዳናው አፋፍ አጋድማ ያለአፅናኝ ታለቅስ ጀመር። ብዙም ሳይቆይ አብዱላህ ኢብኑ መስዑድን ያቀፈ የሰሀባዎች ጀመዓ ከዝያ ጎዳና ብቅ አለ።
‹‹ለምን ታለቅሻለሽ?›› ብለው ጠየቋት።
‹‹ይህ ባሌ አባ ዘር በበረሀ ሞተብኝ ምከፍንበትም ልብስ አጣሁ ቀባሪም የለም›› አለቻቸው።
ሰሀባዎቹም ልብሶቻቸውን እያወላለቁ በመሽቀዳደም ከፈኑት። ዱዓም እያደረጉ የሰሐቢዩን ገላ ከማረፍያ ላህዱ ውስጥም አስገቡት።
ያኔ በደጉ ዘመን በእግሩ በረሀውን አቋርጦ ወደ ነቢዩ የመጣ ጊዜ የረሱልን ደስታ እያወሱ ቀብረውት ጉዟአቸውን ቀጠሉ።

ሰላም በአቡ ዘር ላይ ይሁን!
የአላህ ውዴታም በሱ ላይ ይሁን!

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

16 Jul, 13:16


አውሮፓዊው የታሪክ መምህር የመስቀል ጦረኞችን ልብስ ለብሶ የአባት አያቶቹን ግፍ እንደ ጀግንነት ገድል ለተማሪዎች ሲያብራራ ይታያል።
አውሮፓውያን የመስቀል ጦረኞቻቸውን በአደባባይ ያወድሳሉ። የሰሩትን፣ የፈፀሙትን ጭፍጨፋ እንደ ጀግንነት ይዘክራሉ። የግፍ ብትራቸውን እንደ ጀብዱ ይተርካሉ። እነአንደሉስ እነቁድስ ምስክሮች ናቸው። በሆዳቸው ውስጥ ልጆችን ያቀፉ እናቶች ሳይቀሩ ሆዳቸው በቢላ እየተቀደደ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል። መሬት ላይ አስተኝተው በእግሮቻቸው ሽሎች የተረገጡበት ታሪክ የቅርብ ጊዜ ትውስታዎች ናቸው። ይህንን ነው የጀግንነት ታሪካችን ብለው የሚዘክሩት።

የእኛን ግን ስለ ኢስላም የተፋለሙ፣ ስለላኢላሀ ኢለላህ የተዋደቁ፣ ስለሙስሊሞች መብት ጦር የሰበቁ ጀግኖቻችንን ወራሪ ብለው ይሰይሟቸዋል። በየትምህርት ቤቱም ይህንኑ ያስተምሩናል። በእነሱ የተፃፈን ታሪክ ብቻ እንድናጠና የተዛባውን ታሪክ ፀሐፊዎቻቸው በብዕራቸው ደራሲዎቻቸው በፊልሙ ከሽነውና አሳምረው ወደእኛ ያደርሱታል።

የትኛው ሙጃሂድ ነው ኢ ሰብአዉ ጭፍጨፋን በጠላቶቹ ላይ ያደረሰ? እነሱ ስለፈፀሙት ግፍና በደል ይቅርታ አድርገው ነበር በነፃ የለቀቋቸው።

ኢስላም ይህቺን ምድር ሲያስተዳድር በደልን ሳይሆን ፍትህን በቀልን ሳይሆን ይቅርታን ስለማሳየቱ ታሪክ ምስክር ነው።

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

16 Jul, 03:14


▫️ሙስሊሞች የተሸከሙትን ያህል
መከራ ማን ተሸክሞ ያውቃል❗️

እስልምና በስፔን ለ800 ዓመታት ያህል ኖሯል። ሙስሊም ስፔናውያን ለሌሎች አውሮፓውያን የእውቀትና የስልጣኔ ምንጭ ሆነው አገልግለዋል። ለአውሮፓ የህክምና፣ የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪና ሌሎች የሳይንስ ጥበባትን አሰተምረዋል። ለዘመናዊ ሳይንስ እድገት አብይ ሚና የተጫወቱት ፋራንሲስ ቤከንና ሮጀር ቤከን የሳይንስ እውቀት የቀሰሙት ስፔን ውሰጥ በሙስሊም ሊቃውንት ከተቋቋሙ የትምህርት ማዕከላት ውስጥ ነው። መሰቀላውያን ይህን ሁሉ ውለታ በመርሳት 8 ሚሊዮን የስፔን ሙስሊሞችን ክርስትናን ለመጠመቅ ሰላልፈቀዱ ብቻ በሰይፍ እንዳረዶቸው ታሪክ ይነግረናል።
በዚህ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ስፔን አንድም ሙስሊም ቤተሰብ እንዳይኖርባት ተደረገች። ናዚዎች በአይሁዶች ላይ የፈፀሙትን ዓለም አጋኖ ሲያቀርብ የስፔን ሙስሊሞችን እልቂት ግን ለማውሳት እንኳ አይፈቅድም። አልፎ አልፎ ቢያወሳውም በሹክሹክታ ነው።
በ1095 ዓ/ል የካቶሊክ ሊቀ-ጳጳስ ኤርባኖሰ በፈረንሳይ ከተማ በክሊርምንት "ቁድስን ከሙስሊሞች ነፃ እናውጣ" የሚል ቀሰቃሽ ንግግር አደረገ። በጦርነቱ ለሚሳተፉ ሁሉ ሀጢያታቸው እንደሚማር ዋሰትና ሰጠ። ለነርሱም ሆነ ለቤተሰቦቻቸው ቤተ-ክርስቲያን እንክብካቤ እንደምታደርግ አሳወቀ። ንግግሩ ለዘመናት የንፁሃንን ደም ሲያፈሱ ለኖሩ ተከታዮቹ ስሜታቸውን የሚያቀጣጥል ነበር።
"ጀግንነታችሁንና እምነታችሁን የምታስመሰክሩበት ጊዜ አሁን ነው። ሂዱና ሙስሊሞችን ተበቀሉ። እጆቻችንም በነርሱ ደም እጠቡ"
አንደበተ ርቱዕና መሳጭ በመሆኑ ታዳሚዎች አለቀሱ። የደም ጥማታቸው ጨመረ። የመስቀል ጦርነት ችቦም ተለኮሰ ለዘመናት የሚሊዮኖችን ደም ያፈሰሰችው ቤተ ክርስቲያን ተጨማሪ ደም ለማፍሰስ ህዝበ-ክርሰቲያን ባህር ተሻግሮ በሙስሊሞች ላይ እንዲዘምት አደረገች። ጭፍጨፋው ክርስቲያን የታሪክ ፀሀፍትን ሳይቀር ያሳቀቀ ነበር።
"መሰቀላዊያን መእራት ኑዕማን የተባለችውን የሶሪያ ታላቅ ከተማ በተቆጣጠሩ ጊዜ በውሰጧ የሚገኙ ሙስሊም ነዋሪዎቿን በሙሉ ጨፈጨፉ። ከመቶ ሺህ በላይ እንደሆኑ ይገመታል። ቁድስን የተቆጣጠሩት የሀይማኖት ሊቃውንትን ጨምሮ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ካረዱ በኃላ ነው። ቁድስን ሲቆጣጠሩ በታሪክ ውስጥ አምሳያ የማይገኝለት ጭካኔ ፈፀመዋል። ሙስሊሞች ከኮረብታዎች ወይም ከቤቶች ጣሪያ ላይ ወጥተው ወደ ታች እራሳቸውን እንዲወረውሩ ያሰገድዶቸው ነበር። እሳት አቀጣጥለው ይማግዷቸዋል። እጆቻቸውን አስረው ከጎዳና ላይ ይጎትቶቸው ነበር። ሙስሊሞችን የማረዱ ተግባር ለሳምንታት ቀጠለ። የሟቾቹ ቁጥር 70 ሺህ እንደሚደርስ የምስራቅም የምዕራብም የታሪክ ፀሀፊዎች ይሰማማሉ። ሸሽተው በየቤቱ የተደበቁትን ከነህይወታቸው በእሳት ያቃጥሏቸው ነበር። መሰቀላዊያን ወደየትኛውም ከተማ ሲገቡ ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ፣ ቤቶችን በማቃጠል፣ ንብረት በማውደም፣ መፅሐፍትና ቅርሶችን ሳይቀር በማውደም ይወሳሉ። የሊቢያን ትሪፖሊ ከተማ ሲቆጣጠሩ ባቃጠሉት "ዳረል መክነማህ" በተሰኘ ቤተ-መፅሐፉት ውስጥ 100 ሺ ጥራዝ መፅሃፍት እንደነበሩ ተዘግቧል።
የታሪክ ፀሀፊ ጆሰተን ሊቦን መሰቀላዊያን በቁድስ የፈፀሙት ጭፍጨፋ እጅግ አሰቃቂ እንደነበር ይገለፃል። መነኩሴና የአይን ምስክር ሮበርት በዚያን ጊዜ የነበረውን ሲገልጽ "ወገኖቻችን የመግደል ጥማታቸውን ለማርካት በየመንገዱ ይዘዋወራሉ። ህፃናትን፣ ወጣቶችና አዛውንትን በግፍ ያርዱ ነበር። በማድረድ ብቻ ሳይወሰኑ ሬሳዎችን ይቆራርጣሉ። የግድያ ያሰራቸውን ለማቀላጠፍ በአንዲት ገመድ ብዙ ሰዎችን ያንቁ ነበር።
ሰላሀዲን አል-አዩቢ ቁድስን ከነዚህ ሰዎች ባሰለቀቀ ጊዜ የፈፀመው ነገር ግን እጅግ ይደንቃል። ቁድስ ውስጥ ከህፃናትና ከሴቶች ውጭ ከ100 ሺህ ያላነሱ መስቀላውያን ተማረኩ። 60 ሺህ ያህሉ የሙስሊሞችን ደም እንደ ጎርፍ ያፈሰሱ ወታደሮች ነበሩ። እንዲገደሉ አላዘዘም እንክብካቤ እንዲደረግላቸው እንጂ። በነፃም ለቀቃቸው። ወደየመጡበት ሀገር በስላም እንዲሄዱ ፈቀደላቸው። ሌላው ቀርቶ የቁድስ ፓትሪያርክ እንኳ ንብረቱን ይዞ እንዲወጣ ፈቀደለት። የታሪክ ፀሀፊ ጆስትሊበን ይሄን የሰለሀዲንን አንፀባራቂ በጎነት አድንቋል።
ሰላሀዲን ሌላም አስገራሚ ተግባር ፈፅሟል። የመሰቀላውያን የጦር አዝማች የሰላህዲን ተቀናቃኝ ሪቻርድ በታመመ ጊዜ መድሀኒት እና ፍራፍሬዎች እንዲሁም የሚጠጡ ነገሮችን ላከለት። ሪቻርድ ግን ጤናው ሲመለስለት ሰለሀዲንን ለመዋጋት ፈጥኖ ተሰማራ።
የመስቀል ጦርነት በሙስሊሞች ላይ ለሶስት ተከታታይ ምዕተ አመታት ማለትም ከ11-13ኛው ክ/ዘመናት ቀጥሏል። ተመሳሳይ ግፎች በክርስቲያኑ በኩል ተፈፅመዋል። ሙስሊሞች ግን ከላይ የተጠቀሰውን አይነት አንፀባራቂ ስነ-ምግባር አሳይተዋል።
በመስቀል ጦርነት ህፃናት፣ አዛውንትና ሴቶች አልተረፉም። ከሆድ ውስጥ ያሉ ሺሎች እንኳ ቅጣትን ተቋድሰዋል። የእርጉዝ ሴቶች ሆድ በሳንጃ እየተወጋና በቢላዋ እየተዘረገፈ ከነፅንሶቻቸው ተገድለዋል። የመስቀል ጦርነትን ዝርዝር ታሪክ የፃፉ ምሁራን በሙሉ ይህን መሰል በርካታ ክስተቶች ዘግበዋል። እውቆቹ የታሪክ ሊቃውንት ኢብኑ ከሲርና ኢብኑል አሲር በየመፅሐፎቻቸው አስፍረውታል። ምዕራባዊ የታሪክ ፀሀፍትም እንደዚሁ።

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

14 Jul, 03:44


▫️ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

🎙Title|| የአላህ ውዴታ

🎬Size|| 18.1 MB

#SHARE//🌐
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

10 Jul, 07:47


በሳዑዲ ዓረቢያ ትናንት ማታ ጨረቃ ባለመታየቷ የተከበሩት አስሩ የዙል ሒጃህ ቀናት ነገ እሁድ ይጀምራሉ።

አላህ በአግባቡ ከሚጠቀሙባቸው ባሮቹ ያድርገን።

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

10 Jul, 07:43


▫️ተወዳቹ የዙል ሒጃህ አስር ቀናት

(ያለፈውን የረመዷን ወር ሳትጠቀምበት አልፎብሃል? በወንጀል ጨቅይተሃል?)

ስለ ተከበሩት ውድ የወርሃ ዙል ሒጃህ የመጀመሪያ አስርት ቀናት ትንሽ እንተዋወስ።
"وليال عشر" ماذا بعد هذا القسم يا صديقي؟
እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች «በአስሩ ሌሊቶች» በማለት ታላቁ ጌታችን አላህ ምሎባቸዋል። ወንድሜ ሆይ! ከዚህ መሃላ በላይ ስለነዚህ ቀናት ታላቅነት ምን ማሳያ ይምጣ⁉️
إنها فرصة تصحيح المسار مع الرب الكريم مقبلة
فلا تكن لها من المدبرين.
እነዚህ ቀናቶች ለወንጀል መታበሻ ጥሩ አጋጣሚዎች ናቸውና ሳታባክን በአግባቡ ተጠቀምባቸው።

العشر فرصة لعلاج الأمراض القلبية فرصة للتقرب
والتحبب لله الواحد الأحد.
እነዚህ ቀናቶች ለቀልብ በሽታ ሕክምና፣ ወደ አንዱ አምላካችን አላህ ለመቃረብ እንዲሁም እርሱ ዘንድ ለመወደድ መልካም አጋጣሚዎች ናቸው።

في العشر من ذي الحجة ابكِ على خطيئتك
ووجه قلبك لخالقك وتمنى على الله العفو والعافية.
በነዚህ አስርት የዙል ሒጃህ ቀናት በወንጀልህ አልቅስ፣ ፊትህን ወደ ፈጣሪህ አቅጣጭ፣ አላህ ይቅር እንዲልህና ነፃ እንዲያወጣህ ተማጸን።

تجتمع في هذه الأيَام أهمّ العبادات؛
حيث تجتمع فيها الصَلاة، والصِيام، والصَدقة، والحج.
በነዚህ አስርት ቀናቶች ውስጥ አሳሳቢ የሆኑት ቁልፍ የዒባዳህ አይነቶች ይሰባሰባሉ። ሶላት፣ ጾም፣ ሰደቃና ሐጅ!

في العشر طهر قلبك من كل دخيلة
ونقيصة طهر قلبك من أسباب الذنوب
هي فرصتك أنت فلا توليها الأدبار
በነዚህ ቀናቶች ወደ ቀልብህ የገባውን ወንጀል አስወጣ፣ ታዘህ ላላሟላኸው ይቅርታ ጠይቅ፣ ወደ ወንጀል ከሚያዳርሱ መንገዶች ራቅ፣ ይህን አጋጣሚ ተጠቀምበት እንጅ ፊትህን እንዳታዞር።
أرهقتك الذنوب ،ضيعت رمضان ،
ها هي ( عشر ذي الحجة )
منحة ربانية ..
ወንጀልህ በዝቶ ተብትቦሃል፣ ረመዷንን በአግባቡ አልተጠቀምክበትም፣…
لتبدأ صفحة جديده مع الله

فرغ نفسك في هذه الأيام،
وخفّف من الاشتغال بالدنيا،
واجتهد؛
فإنها والله أيام معدودة،
ما أسرع أن تنقضي، وتُطوى صحائفها.

يبدأ صيام العشر الأوائل من ذي الحجة يوم الأحد ١١ يوليو ٢٠٢١ ..
وذكر وفقك الله

የእስካሁኑን ህይዎትህን ተወውና ላለፈው ወንጀልህ አላህን መሃርታ ጠይቀህ ለወደፊቱ ከአላህ ጋር ያለህን አዲስ የህይዎት ምዕራፍ ጀምር።
እነዚህ የተገደቡ አስርት ቀናቶች ብቻ ስለሆኑ ከዱንያ ጉዳዮች ቀነስ አድርግና በቁርኣን፣ በሶደቃ፣ በሶላት፣ በዚክር፣ በጾምና በመሳሰሉት መልካም ሥራዎች ላይ ተጠመድ።

አላህ እኔንም እናንተንም ለሚወደው ተግባር ይግጠመን።

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

09 Jul, 08:44


📕27ቱ ለትዳር የማይፈቀዱ ሴቶች

▪️በኡስታዝ አቡ ሐይደር

ሼር በማድረግ አዳርሱት

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

08 Jul, 11:20


▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~8

ዑስማኒዮች በነቢያቸው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ንግግር የቂን ብለዋል፡፡ ተፈፃሚ እንደሚኾን አምነው ጥረት አድርገዋል፡፡ በጥረታቸው ላይ ሶብረዋል፡፡ በመጨረሻም ድሉን አረጋግጠዋል፡፡ ቁስጠንጢኒያን ከፍተዋል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እውነት ተናገሩ “….ምን ያምር አሚር ነው አሚሯ፣ ምን ያምር ጦር ነው ያም ጦሯ” ከዚህ ከዑስማኒዮች የጂሃዳዊ ተጋድሎ ታሪክ የሚወሰደው ትምህርት በዱሩሥ ወ ኢበር የቂን ማለት፣ ጥረት ማድረግ፣ በጥረቱ ላይ መሶበር ይኾናል ስኬት ነው፡፡

ሡልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲሕ የቁስጠንጢኒያን መከፈት አረጋግጦ፣ ድሉን አጠናከረ፡፡ ቀሪ መሰናክሎችን አስወገደ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ቀጣይ ፉቱሐቱ አመራ፡፡ ን
ሰርቢያ የዑስማኒያ መንግሥት አካል መሆን

እንደሚታወሰው ቀደምቱ የዑስማኒያ ሡልጣኖች በዓመታዊ የጂዝያ ክፍያ ለሰርብ ነፃነቷን ሲያውቁላት ቆይተዋል፡፡ ሰርቦች ግን በሁሉም አጋጣሚ የዑስማኒዮችን በሌላ ግንባሮች መጠመድ ባዩ ቁጥር የገቡትን ቃል በማጠፍ (ነቅዱል ዓህድ) በመፈፀም ጂዚያ አልከፍል ይላሉ፡፡ ስለዚህ ሡልጣን ሙሐመድ አልፋቲህ ሰርቢያን ከእንግዲህ ወዲያ ሙሉ ለሙሉ የዑስማኒያ መንግሥት አካልና ኣንድ ክፍለ-ሀገር ለማድረግ ቆርጦ ተነሳ፡፡ ወደዚያው በመዝመት በ858 ሂጅሪያ ሰርቢያ ገባ፡፡ ዙሪያ መሬቷን ቢቆጣጠርም ታዲያ ርዕሰከተማዋን ቤልግሬድን የሀንጋሪ ንጉሥ ባደረገው መከላከል ሳቢያ ሊከፍታት አልቻለም፡፡ ይሁንና በዚህ ድል ሰርቢያ ነፃነቷን አጥታ የዑስማኒያ መንግሥት አንድ ክፍለ-ሀገር (ዊላያ) ሆናለች፡፡

በመጨረሻም ከቤልግሬድ ውጪ አንዲትም ጋት መሬት ከዑስማኒያ ቁጥጥር ውጪ ሳትሆን ከተማዋን እንዳለች ትተው ወደ ሌላ ግንባር በ885 ሂጅሪያ በጣሊያን የባህር ጠረፍ ላይ የ‹ኦውትራኑት ከተማን ቢከፍትም የሱ መሞት የሠራዊቱን ግስጋሴ ሊገታው ችሏል፡፡ እነሆ ሡልጣን ሙሐመድ ዳግማዊ በአላህ መንገድ ስላደረገው ታላቅ ጂሃድና ብዙ ሀገራትንም ስለ መክፈቱ አል-ፋቲሕ መባልን የተቀፀለው ጀግና ሰው - በረቢዑል አወል 4ኛ ቀን 886 ሂጅሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ኢጣሊያን ለመክፈት ታላቅ ጦር አስከትቶ በንቅናቄ ላይ ነበረ ፈጀዛሁላህ ኸይረን ዓኒል ሙስሊሚን ጀሚዓን

📕ማጠቃለያ

ዑስማኒያ ቱርኮች የኢስላም ጠላቶችን በመዋጋትና በነሱ ላይ ጂሃድ በማድረግ ከስድስት ክፍለ-ዘመናት በላይ ኢስላማዊውን ደዕዋ ተሸክመዋል፡፡ ከነሱ በፊት ማናቸውም ያላሳኩትን የቆስጠንጢኒያን መከፈት በጂሃዳዊ ተጋድሎ አሳክተዋል፡፡ ከነሱ በፊት ሌሎች ሙስሊሞች ችለው ያልከፈቷቸውን ሀገራትም እነሱ ከፍተዋል፡፡ የፉቱሐት ንቅናቄያቸውን አድማስ በማስፋት እስከ አውሮጳ እምብርት ድረስ ዘልቀው- ግሪክን ሰርብና ጀበል አስወድን፣ ሩማኒያን፣ ሀንጋሪያን፣ ስሎቫኪያን፣ ኢጣሊያን፣ ከትንሹ አስያ የተቀረውን ግዛት ሙሉ ቱርክን ፣ አርሜኒያን፣ ጆርጂያን፣ በተለይም ደሞ ቀውቃዝን፣...እያሉ ቀጥለው ግሥጋሴያቸው የተገታው ኦስትሪያ ርዕሰ ከተማ ቪየና በር ላይ ነው፡፡ እስከ ዛሬም አሻራቸው ለተመልካች እዚያ ይገኛል፡፡

ደውላ ዑስማኒያ ወይም የዑስማኒያ መንግሥት በታሪክ ብቅ ያለችበት ጊዜ 699 ሂጅሪያ ሲኾን መንበረ-ኸሊፋውን ግን እስከ 923 ሂጅሪያ አልጨበጠችም፡፡ የዑስማኒያ መንግሥት በዘመኑ እጅግ ገናና መንግሥት ነበረ፡፡ በዓለም ላይ በባህል በሥልጣኔና በወታደራዊ ክህሎት ወደር አልነበረውም፡፡ በአንድ ጊዜ በአራት ግዙፍ የውጊያ ግንባሮች የኢስላምን ጠላቶች ገጥሞ በኢስላማዊ መንገድ እየተዋጋ የተፅዕኖ አድማሱን በፉቱሐት እያሰፋ ኖሯል፡፡

📕አራቱ ግንባሮች የሚከተሉት ናቸው

1. በምዕራብ ግንባር - በዘመኑ ሰፊ ሀገረ-ግዛት የነበረውን የነምሳን ኢምፓየር - በዛው ግንባር - በመግሪበል ዐረቢያ ስፓኝን

2. በደቡብ ግንባር - ወደ ዐረብ ጀዚራ መስፋፋት የሚሹትን ፖርቱጋሎችን

3. በሰሜን ግንባር - ሩሲያን

4. በምሥራቅ ግንባር ከመስቀላዊያን ጋር በቃል ኪዳን ተሳስረው ባጠቃላይ አህሉ ሱንና ወልጀማዓን በተለይም ደሞ የዑስማኒያ መንግሥት የሚዋጉትን ራፊዳ ሺዓዎችን ይዋጋሉ፡፡

ነሣራ አውሮጳ የዑስማኒያን ኺላፈት በሙስሊም ሀገራት ላይ ዐረብ በሆኑትና ባልሆኑት ላይ ሁሉ - በኃይል እንደተጫነባቸው ቅኝ ገዢ ኃይል አስመስለው በመሳል በኡምማው መሀል ክፍፍል ለመፍጠር ሲዶልቱ ኖረው ወደ መጨረሻ ተሳክቶላቸዋል፡፡ እውነታው ግን እነሱ የዑስማኒያን ኺላፈት ከሳሉበት በተቃራኒ ነው፡፡ በዚህ የአውሮጳ ወጥመድ ውስጥ የወደቁና ኢስላማዊውን የዑስማኒያ ኺላፈት በኃይል እንደተጫነባቸው ቅኝ ገዢ ኃይል የተመለከቱ ዐረቦች በመሰረቱ የረሱልን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሐዲስ የዘነጉ ናቸው “ዐረቡ በአዕጀሚዩ ላይ ብልጫ አይኖረውም-በተቅዋ ቢኾን እንጂ ... ይሁንና ለዑስማኒያ ቱርኮች የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምስክርነት ከምንም በላይ በቂያቸው ነው፡፡

“ወኒዕመል አሚር አሚሩሃ ፣ ወኒዕመል ጀይሽ ዛሊከል ጀይሽ”

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------

وبيجوت Tube

07 Jul, 11:11


▫️ጭራቁ የቻይና ግድብ

ℹ️ለመረጃ ይሆናቹህ ዘንድ...

ሰሞኑን ብዙዎች ፌስቡክ ላይ የሚቀባበሉት ግድብ የህዳሴ ግድብ ምስል አይደለም ። ይህ ግድብ ስያሜ "Three Gorges" የሚባል ሲሆን በአለማችን ቁጥር አንድ ግዙፉ ግድብ ነው። የሚገኘው በቻይና ሀገር በይቻንግ ግዛት ነው። 22,500 MW ሀይል በአመት ማመንጨት አቅም አለው። በአማካኝ ሀይል የማመንጨት አቅሙ የህዳሴ ግድብ 3 እጥፍ በላይ እንደማለት ነው። ግድቡ ከግዝፈቱ የተነሳ የምድርን ዙረት ፍጥነት በ0.06 microseconds ቀንሷል ይላሉ የናሳ ሳይንቲስቶች። 39 ትሪሊየን ኪሎግራም ውሀ የተሸከመው ይህ ግድብ ሲገነባ 1.4 ሚሊየን በላይ ህዝብ ተፈናቅሏል። ታዲያ መሬት መንቀጥቀጥ የሚያስጋት ቻይና በግድቡ ላይ crack (ስንጥቅ) ሊከሰት ይችላል ስንጥቁን ተከትሎ ግድቡ ቢደረመስ አለም አይታው የማታውቀው ጥፋት ይደርሳል ተብሎ ስለሚታመን ግድቡን ጭራቁ የሚል ቅፅል ስም አሰጥቶታል።

አባይ ግድብ ሞልቶ
ህወሀት ከነችግሩ ለዘላለም ሞቶ
ብሄሮች አገር በሚለዉ ተተክቶ
መራራ ጉዲና አግብቶ☺️
ለማየት ያብቃን!


👌ለማንኛዉም የህዳሴዉ ግድብ ሁለተኛዉ ዙር መሞላት መጀመሩ ደስታችን ወደር የለዉም።

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------