آخرین پست‌های Hani Tube (@hanitube) در تلگرام

پست‌های تلگرام Hani Tube

Hani Tube
አካውንቲንግ ትምህርት እና የኢትዮጵያ ታክስ አሰራር እና አዋጆችን ለመማር :-
📣You tube:
https://youtube.com/@ethiopiatax
📣ዌብሳይት:Www.hanitube.com
📣ፌስቡክ:https://www.facebook.com/haniaccounting
1,510 مشترک
106 عکس
14 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 10.03.2025 12:58

کانال‌های مشابه

Addis Eyita
12,510 مشترک
Last Seen Monitoring
2,924 مشترک

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Hani Tube در تلگرام

Hani Tube

13 Jan, 20:48

1,892

አንድ ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ በላይ ለሆኑ ቀጣሪዎች የማይሰራ ወይም ግብርን ቀንሶ ገቢ የማድረግ ግዴታ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ግብሩን የማስታወቅ ግዴታ የለበትም፡፡

አንድ ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ በላይ ቀጣሪዎች ያሉት ወይም ከራስ ገቢ ላይ ግብር ቀንሶ የመያዝ ግዴታ ያለበት እንደሆነ፣ ተቀጣሪው ከየሦስት ወሩ መጨረሻ በኋላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የግብር ማስታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡


አንድ ተቀጣሪ ግብር የማሳወቅ ግዴታ የሌለበት ሲሆን ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚሰጠው ግብር ተቀንሶ ቀሪ መሆኑን የሚያሳየው ደረሰኝ ለዚህ አዋጅና ለታክስ አስተዳደር አዋጅ ዓላማ ሲባል ቀጣሪው በየወሩ መክፈል በሚኖርበት ግብር ላይ እንደተሰጠ የግብር ውሳኔ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
Hani Tube

10 Jan, 19:17

2,147

የንግድ ፈቃድ እድሳት እስከ ጥር 15/2017 ዓ/ም  የተራዘመ መሆኑን
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የገለጸ በመሆኑ አለቅጣት  የንግድ ፈቃድዎትን በኦንላይን (https://etrade.gov.et) ያድሱ።
ዌብሳይት-www.Hanitube.com
You Tube http://youtube.com/@hanitubeaccounting?si=6prlZI8Q5qz1DCEp
#ንግድ #ንግድፈቃድ #ግብር #ክሊራንስ
Hani Tube

05 Jan, 22:18

2,359

የወር ኪራይ 10,000 (ለመኖሪያ ከተከራየ)ቢሆን  እንዴት እንሰራለን የሚለው ለማየት

10,000*12=120,000
120,000*50%= 60,000

የተጣራ ትርፍ    60,000
(ስንጠረዥ ለ)  በማየት

60,000*20%-3,630=8,370
ቴምብር ቀረጥ
10,000*12*0.5%=600
ጠቅላላ 8,370+600=8,970 
Hani Tube

20 Dec, 14:27

1,888

https://youtu.be/V0a-Te8x3jA
Hani Tube

17 Dec, 20:52

1,588

https://youtube.com/shorts/-68dRnW8NXo?feature=share
Hani Tube

17 Dec, 07:02

1,830

ስለ ተቀናሽ ወጪዎች የወጣ መመሪያ ቁጥር 5/2011
ወጪዎች ስለሚቀነሱበት ሁኔታ
ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች

1. ማንኛውም ወጪ በግብር ከፋዩ ገቢ ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማስገኘት፣ ለስራው ዋስትና ለመስጠት እና ስራውን ለማስቀጠል በግብር ዓመቱ ውስጥ የተደረገ አስፈላጊ የሆነ ወጪ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ እንደወጪ ይያዛል፡፡

2. አስፈላጊ ወጪዎች የሚከተሉትን ይጨምራል፣
ሀ. በነፃ በሚጠቀምበት ወይም በተከራየው ህንፃ ስራውን ሲያከናውን ቤቱን በሰጠው ወይም በአከራዩ ስም በሚታወቀው የመብራት፣ የውሃ ወይም የስልክ ቆጣሪ የተጠቀመ እደሆነ እነዚህን ክፍያዎች በግብር ከፋዩ እንደሚከፈሉ በግልፅ በውል ውስጥ የተካተተ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ እና ወጪው የተከፈለበትን ደረሰኝ ኦሪጂናል ካቀረበ፣

ለ. ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የተከፈለ ክፍያ፣

ሐ. የተመዘገበ ተርን ኦቨር ታክስ እና ኤክሳይዝ ታክስ እንዲሁም ተመላሽ ያልተደረገ ወይም በጊዜው ባለመቅረቡ ተመላሽ የማይደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣

መ. የተበላሸ ዕቃ ዋጋ፣ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው እና የተወገዱ እቃዎች ዋጋ እና ለማስወገድ የወጣ ወጪ፣

3. ግብር ከፋይ ለንግድ ድርጅት እና መኖሪያ  ቤት በአንድ የመብራት፣ የስልክ ወይም የውሃ ቆጣሪ የሚጠቀም በሚሆንት ጊዜ የመብራት፣ ስልክ እና የውሃ ወጪ በወጪ ተቀናሽ የሚያዘው ከወጪው 75 በመቶ ብቻ ይሆናል፡፡

4. ከላይ የቀረቡት ወጪዎች ከሚያስገኙት ገቢ፣ ለስራው ከሚሰጡት ዋስትና እና ቀጣይነት ጋር ሲነጻጸር ያልተጋነኑና ተመጣጣኝ መሆን አለባቸው፡፡ ወጪዎቹ የተጋነኑ በሚሆኑበት ጊዜ ባለስልጣኑ በተገቢው መረጃ ላይ ተመስርቶ ማስተካከያ ሊያደርግ ይችላል፡፡

5. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተጋነኑ ወጪዎችን ለመወሰን የሚረዳውን የራሱ የአሰራር ሥርዓት አዘጋጅቶ ተፈፃሚ ሊያደርግ ይችላል፡፡

6. አንድ ግብር ከፋይ የንግድ ስራ እንቅስቃሴው በተቋረጠበት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ወይም ስራ ባላገኘበት ጊዜ ያወጣው ወጪ የማይቀር ወጪ ሆኖ ከተገኘ ገቢ ያላስገኘ ወጪ ቢሆንም በወጪ ተቀናሽ ሊፈቀድለት ይችላል፡፡

7. ግለሰብ የንግድ ስራ ባለሀብት ከመደበኛ የሥራ ቦታው ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ በመሄድ የንግድ ስራውን ለማከናወን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ለሚያወጣቸው ወጪዎች ለምግብ እና ለመኝታ ለአንድ ቀን እስከ 1000ብር፣ ለትራንስፖርት  ያወጣው ወጪ በስራ ላይ ባለው የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ መሰረት በማስረጃ ተረጋግጦ የወጪ ተቀናሽ የሚፈቀድለት ሆኖ ከዚህ መጠን በላይ የሚያወጣው ወጪ በተቀናሽ ወጪ አይያዝም፡፡

8. ለግብር ከፋዩ ሠራተኛ የሚከፈል ያኃላፊነት አበል ወይም የውክልና አበል ተቀናሽ ሊሆን የሚችለው የንግድ ስራውን የማስተዋወቅ እና የማሳደግ ሥራ ላይ በሃላፊነት ለሚሰራ ሰራተኛ ወይም የስራ መሪ የተከፈለ ሲሆን ነው፡፡

9. በኢትዮጲያ ነዋሪ ያልሆነ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው በቋሚነት ለሚሰራ ድርጅቱ ጥቅም ያደረገውን ትክክለኛ ወጪ ለመተካት በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራው ድርጅት የሚፈጽመው ክፍያ ተቀናሽ የሚደረገው ወጪው የንግድ ስራ ገቢ ለማግኘት፣ ለንግዱ ስራ ዋስትና ለመስጠት ወይም የንግድ ሥራውን ለማስቀጠል የተደረገ እና በቋሚነት በሚሰራው ድርጅት ሊሰራ የማይችል ከሆነ ብቻ ነው፡፡
10. የጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት በሥራ ላይ ላሠማራው አባሉ የሚከፍለው ደሞዝ እንደ ወጪ ተቀናሽ ይፈቀድለታል፡፡
11. በዲዛይን ለውጥ ምክንያት ህንጻ ፈርሶ ሲገነባ የፈረሰው ህንፃ የመዝገብ ዋጋ በወጪ ተቀናሽ ይያዛል፡፡

12. የተሽከርካሪ ጎማ የሚሰጠው አገልግሎት ከአንድ አመት ያነሰ እንደሆነ እንደ አላቂ ዕቃ ተቆጥሮ ወጪ የሚያዝ ይሆናል፡፡

የወለድ ወጪ

1. የወለድ ወጪ ሊፈቀድ የሚችለው በብድሩ የተገኘው ገንዘብ ለንግድ ሥራ እንቅስቃሴ መዋሉ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ሆኖም የፋይናንስ ተቋማትን ሳይጨምር አንድ ግብር ከፋይ ለተወሰነ የሥራ እንቅስቀሴ የወሰደውን ብድር ለሌላ ዓላማ የሚያውል ወይም ይህንኑ ብድር ለሌላ ተግባር በብድር የሰጠ ከሆነ፣ የሚፈቀድለት ተቀናሽ የወለድ ወጪ ለሌላ ያበደረው ወይም ለሌላ ዓላማ ያዋለው ተቀንሶ ለንግድ ስራው እንቅስቃሴ በዋለው ብድር መጠን ብቻ ይሆናል፡፡

2. አንድ ግብር ከፋይ በዱቤ ለሚገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋውን እስኪከፍል ድረስ ወለድ እንደሚከፈልበት ውል የገባ እንደሆነ ለከፈለው የወለድ መጠን በአዋጁ እና በደንቡ መሰረት የወጪ ተቀናሽ ይፈቀድለታል፡፡

3. ግብር ከፋይ ህንጻ ለመገንባት ብድር የወሰደ እንደሆነ፣ ህንጻው እሰኪጠናቀቅ ድረስ የተከፈለው ወለድ በእርጅና ተቀናሽ የሚካተት ሆኖ ህንጻው ተገንብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ የተከፈለው ወለድ በወጪ ተቀናሽ የሚፈቀድ ይሆናል፡፡

በምርት ዘግጅትና አቅርቦት ሂደት የሚያጋጥምን ብክነት እንደ ወጪ ስልመያዝ

1. በምርት ዝግጅትና አቅርቦት ሂደት(በብጣሪ፣ በትነት፣ በማቅለጥ፣ በሽርፍራፊ፣ በቆይታ ጊዜ ወዘተ) የሚባክን ምርት የዕቃ መጠን በሚመለከተው የመንግስት አካል በቀረበ ጥናት መሰረት እንደ ወጪ ሊያዝ ይችላል፡፡

2. የተሟላ ጥናት ማግኘት ካልተቻለ ባለስልጣኑ ከግል ተቋማት፣ ከግብር ከፋዮች፣ አግባብነት ያለው አካል ወይም ባለስልጣኑ በሚያደርገው ጥናት መሰረት ውጪ የሚያዝበትን መጠን ሊወሰን ይቻላል፡፡

3. ለእያንዳንዱ ምርት መረጃ ሊሰጥ የሚገባውን አግባብነት ያለውን አካል ባለስልጣኑ ይወስናል፡፡

ተቀናሽ የሚደረግ የመዝናኛ ወጪ

1. የማዕድን ማውጣት እና ፍለጋ፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርናና የሆርቲ ካልቸር ስራ ላይ የተሠማራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብ እና መጠጥ ዋጋ በዚህ መመሪያ መሰረት በወጪ የሚያዘው በአንድ ወር የሚያወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ካወጣው አጠቃላይ የደሞዝ ወጪ ከ30% ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

2. በሆቴሎች፣ በሬስቶራንቶች ወይም በሌሎች የምግብ አገልግሎት በሚያቀርቡ ተቋማት ውስጥ ለተሰማሩ ሰራተኞች ቀጣሪዎች የሚያቀርቡት የምግብ እና መጠጥ ወጪ ተቀናሽ የሚያደርገው በአንድ ወር የወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ከወጣው አጠቃላይ የደሞዝ ወጪ 20% ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

3. የሚፈቀደው የመጠጥ ተቀናሽ ወጪ ምንም የአልኮል ይዘት የሌለው መጠጥ ነው፡፡

4. ከላይ የተገለፁት ተቋማት የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡት በራሳቸው አዘጋጅተው  ከሆነ ከምግብ ዝግጅት ጋር በተያያዘ የተደረጉት የግብዓት ወጪዎች በወጪ ተቀባይነት አግኝተው ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ ተቀናሽ ሊደረግ የሚችለው ከድርጅቱ በሚቀርብ ህጋዊ ደረሰኝ/የግዢ ማስረጃ መሰረት ይሆናል፡፡

5. ከላይ የተገለጹት ተቋማት የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡት በ3ኛ ወገን አማካኝት ከሆነ ወጪው ተቀባይነት የሚኖረው ስለአቅርቦቱ ከአቅራቢው ጋር የተደረገ ውል፣ አገልግሎቱ ስለመገኘቱ ከድርጅቱ በሚቀርብ ማረጋገጫ እና ለአቅራቢው ገንዘቡ ስለመከፈሉ በሚቀርብ ህጋዊ ደረሰኝ መሰረት ይሆናል፡፡

6. በማዕድን ማውጣት፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በግብርና እና በሆርቲካልቸር ስራ የተሠማራ ቀጣሪ ከከተማ ርቆ በሚገኝ ቦታ ለተመደበው ተቀጣሪው በነፃ ለሚያቀርበው የማረፊያ ቤት አገልግሎት ያወጣው ወጪ ተቀናሽ ይፈቀድለታል፡፡

7. "ከከተማ ርቆ የሚገኝ ቦታ" ማለት ቢያስ ሃያ ሺህ ነዋሪ ካለው የከተማ ወሰን ሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሥፍራ ነው፡፡ www.hanitube.com
YouTube..🌟..https://youtube.com/@hanitubeaccounting?si=6prlZI8Q5qz1DCEp
Hani Tube

14 Dec, 18:52

1,541

https://youtube.com/live/VsE8tMJuEFY?feature=share
Hani Tube

10 Dec, 21:59

1,785

ፈቃድ ሳይኖረው በህገ-ወጥ መንገድ ከመርካቶ ዕቃ በማሸሽ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሲያከማች የነበረ ግለሰብ ላይ ርምጃ ተወሰደ

AMN - ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ የኑሮ ማረጋጋት እና የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይል ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻና ኦፕሬሽን ፈቃድ ሳይኖረው በህገ-ወጥ መንገድ ከመርካቶ ዕቃ በማሸሽ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ እንደ መጋዘንና ስቶር አድርጎ ሲያከማች የነበረ ህገወጥ ነጋዴ ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃ ተወስዷል፡፡

የክፍለከተማው የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ፣ በህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችም ሆነ ተባባሪ አካላት ላይ የሚወሰደው ህጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ ....

https://youtube.com/live/uARAG7WL5_8?feature=share
Hani Tube

08 Dec, 01:12

1,825

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ይገኙበታል ።
ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።

ተመሳሳይነታቸዉ
• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ።

ልዩነታቸዉ
አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን (share company ) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል።
• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም
• አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም
• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል።

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም  ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ
• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transferable አይደለም።

ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
• አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም።


🔥እኔን ለማግኘት ከፈለጋችሁ
t.me/youhanii

🔥ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል
👇
t.me/hanitube

🔥ዌብሳይት
👇
www.hanitube.com

🔥YouTube👇
https://youtube.com/@hanitubeaccounting?si=6prlZI8Q5qz1DCEp

ማንኛውም አካውንቲንግ ትምህርቶች እና ስለኢትዮጵያ ታክስ ህጎችን በተመለከተ መማር ከፈለጋችሁ



🔥እኔን ለማግኘት ከፈለጋችሁ
t.me/youhanii

🔥ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል
👇
t.me/hanitube

🔥ዌብሳይት
👇
www.hanitube.com

🔥YouTube👇
https://youtube.com/@hanitubeaccounting?si=6prlZI8Q5qz1DCEp

#የተጨማሪ_እሴት_ታክስ_አዋጅ #hanitube #አዲስአበባገቢዎች #tax
Hani Tube

22 Nov, 13:42

2,092

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የአድራሻ ለውጥ ለማድረግ መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ


1-አዲስ የንግድ አድራሻ የተቀየረ የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፣

2-ለታክስ ባለ ስልጣኑ የአድራሻ ለውጥን ማሳወቅ ፣

3-የአድራሻ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል ከግብር ከፋዪ የታክስ ማዕከል የተጻፈ

      የአድራሻ ለውጥ ደብዳቤ ለአቅራቢው መውሰድ፣

4-የተጨማሪ እሴት ታክስ ካላቸው ማቅረብ አለባቸው፡፡

@Ethiopiatax
#hanitube #የተጨማሪ_እሴት_ታክስ_አዋጅ #ገቢዎች
#ታክስ

#tax #hanitube #አዲስአበባገቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ
#ቫት_Vat

ለበለጠ መረጃ
ዌብሳይት www.hanitube.com
YouTube..🌟..https://youtube.com/@hanitubeaccounting?si=6prlZI8Q5qz1DCEp
ቴሌግራም ቻናል🌟http://t.me/hanitube