Latest Posts from Hani Tube (@hanitube) on Telegram

Hani Tube Telegram Posts

Hani Tube
አካውንቲንግ ትምህርት እና የኢትዮጵያ ታክስ አሰራር እና አዋጆችን ለመማር :-
📣You tube:
https://youtube.com/@ethiopiatax
📣ዌብሳይት:Www.hanitube.com
📣ፌስቡክ:https://www.facebook.com/haniaccounting
1,510 Subscribers
106 Photos
14 Videos
Last Updated 10.03.2025 12:58

Similar Channels

Last Seen Monitoring
2,924 Subscribers
EFFSAA Official
2,229 Subscribers
Accounting Tips (G G)
2,020 Subscribers

The latest content shared by Hani Tube on Telegram

Hani Tube

19 Nov, 20:20

1,659

የካፒታል ጌን ጥቅም #capitalgaintax በሚከናወንበት ወቅት inflation index መመልለት የግድ ነው።ይህን በተመለከተ ከዚህ ቀደም የሰራሁት ቪዲዮ ታች ባለቀ ሊንክ ይመልከቱ
የ capital gain tax አሰራር👉https://youtu.be/PqV5xI1q8oQ?si=dQrUGzzn0UT-YKt3


#capital #ካፒታል #EthiopiaTaxlaw #አዲስአበባገቢዎች #tax #ለታክስ #taxlaw
Hani Tube

19 Nov, 20:10

1,704

በከተማችን ከደረሰኝ ውጪ ግብይቶች እንዳይፈፀም የተጀመሩ ቁጥጥሮች ተጠናክፈው እንደሚቀጥሉ ከአስመጪዎች፣ ከአምራችና አከፋፋዮች ጋር በተካሄደ የውይይት መድረክ ተገለፀ።

ህዳር 10 / 2017 ዓ. ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በደረሰኝ ግብይት ዙሪያ በመርካቶ ከሚገኙ አምራቾች፣ አከፋፋይዮችና አስመጪዎች ውይይት አካሄደዋል ።
አዲስ ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አስተው ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል
ሙሉ መረጃውን ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የፌስቡክ ገጽ ቀጥሎ ባለው ሊንክ ላይ ያገኙታል...https://www.facebook.com/100069067094802/posts/pfbid02k4mauMq4fPexovyzDdAp42c5CPBnKTZMb6QgmsRq6TPtq3W8pF9oCJwk3iGsA9aXl/?app=fbl

#የግብርዜና #የተጨማሪ_እሴት_ታክስ_አዋጅ #AddisAbaba #EthiopiaTaxlaw #አዲስአበባገቢዎች #ገቢዎች #በመርካቶ #ጉምሩክ #Hanitube #Ethiopiatax
Hani Tube

16 Nov, 09:06

1,955

የእርጅና ተቀናሽ

በግብር ዓመቱ በሙሉ ጥቅም ላይ ያልዋለ ዋጋው የሚቀንስ ሀብት

አንድ ወጋው የሚቀንስ ሀብት በግብር ዓመቱ ከፊል ለሆነው የዓመቱ ጊዜ ብቻ በጥቅም ላይ የዋለ እንደሆነ የሚፈቀደው የእርጅና ተቀናሽ ወጪ ከጠቅላላ የዓመቱ የእርጅና ቅናሽ ሂሳብ ላይ ጥቅም ላይ ያልዋለበት የዓመቱ ከፊል ጊዜ ተመጣጣኝ በሆነ መቶኛ ከተቀነሰ በኋላ ያለው ተቀናሽ ወጪ ብቻ ነው፡፡

ለንግድ ስራ በጥቅም ላይ የዋለው የህንፃ ክፍል

1. በግብር ከፋይ የተገነባ ህንፃ የእርጅና ቅናሽ መታሰብ የሚጀምረው ሀብቱ የንግድ ስራ ገቢውን ለማስገኘት ለአገልግሎቱ ዝግጁ ከሆነበትና አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ቀን አንስቶ ሲሆን ተቆጣጣሪው ባለስልጣን ለግብር ከፋዩ የህንፃ ግንባታው ስለመጠናቀቁ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከሰጠበት ጊዜ በፊት ሊሆን አይችልም፡፡

2. ለእርጅና ተቀናሽ አያያዝ ከጠቅላላው የህንጻ ስፋትና ዋጋ ለንግድ ስራው ጥቅም ላይ የዋለው የህንጻው መጠን ዋጋ ተለይቶ ካልቀረበ በወለሉ ስፋት መቶኛ በማስላት ዋጋው ተለይቶ መቅረብ አለበት፡፡

3. ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ግብር ከፋዩ ለይቶ ካላቀረበ ከጠቅላላ የህንጻው ዋጋ ለንግድ ስራው የዋለውን የህንጻው ስፋት መጠን በማስላት ባለስልጣኑ በራሱ ወስኖ ተቀናሽ ያደርጋል፡፡

4. ጥቅም ላይ የዋለ የህንጻ ክፍል ማለት የህንጻው ክፍል ለሌላ ዓላማ እስካልዋለ ድረስ ግብር ከፋዩ ህንጻውን ለኪራይ አገልግሎት ዝግጁ ያደረገ ከሆነ ህንጻው ባይከራይም ለኪራይ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንደዋለ ተቆጥሮ ከቤት ኪራይ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር በሚሰላበት ጊዜ እንደወጪ ተቀናሽ ሊያዝለት ይገባል፡፡

5. በዚህ አንቀጽ 2 እና 3 የተደነገገው ድንጋጌ ለኪራይ ገቢ ግብርም በተመሳሳይ ተፈጻሚ ይሆና፡፡

6. የዚህ አንቀጽ 4 ድንጋጌ ለሌሎች ዋጋቸው የሚቀንስ እና ግዙፋዊ ሀለዎት ለሌላቸው ሀብቶች እንደ አግባብነቱ ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡

ለእርጅና ቅናሽ መሠረት የሆነ ዋጋ ካልቀረበ በገበያ ዋጋ ስለመወሰን

1. የአንድ ዋጋው የሚቀንስ ሀብት የእርጅና ቅናሽ ለማስላት መሠረት የሆነው የተሰራበት ወይም የተገዛበት ዋጋ የሚገልጽ ሰነድ ታክስ ከፋዩ ማቅረብ ያልቻለ እንደሆነ ባለስልጣኑ በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት በሚወሰነው የተሰራበት ወይም የተገዛበት የገበያ ዋጋ 70 በመቶ የእርጅና ተቀናሽ የፈቀድለታል፡፡
2. ሀብቱ የተገዛበት ወይም የተሰራበት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብአት ታክስ የተካካሰለት ከሆነ የተካካሰው መጠን በሚፈቅድለት የእርጅና ተቀናሽ ዋጋ ውስጥ አይካተትም፡፡
የእርጅና ቅናሽ የሚፈቀድበት ሁኔታ
1. ስለ እርጅና የሚደረገውን ቅናሽ ለመወሰን የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ ይገባል፣

ሀ. የእርጅና ቅናሽ ጊዜያቸውን ያልጨረሱ ንብረቶች ሽያጭ የተከናወነው ግንኙነት ባላቸው ሰዎች መካከል ከሆነና የተላለፈበት ዋጋ ከተጣራ የመዝገብ ዋጋው የሚበልጥ ከሆነ የእርጅና ቅናሽ ለማስላት መሰረት የሚሆነው የተጣራ የመዝገብ ዋጋው ነው፡፡

ለ. በታክስ ከፋዩ ስም ላልተመዘገቡ ሀብቶች የእርጅና ተቅናሽ ወጪ አይፈቀድም፡፡

ሐ. በባል ወይም በሚስት ስም የተመዘገበ ህንጻ ለግለሰብ ንግድ ስራ የዋለ እንደሆነ የእርጅና ተቀናሽ ሊፈቀድ የሚችለው ህንጻው ለንግድ ስራው አገልግሎት እንዲውል፣ የእርጅና ተቀናሽ እንዲጠየቅበትና ህንጻው ሲሸጥ ተገቢውን ግብር እና ታክስ እንዲከፈልበት የባልና የሚስት የስምምነት ሰነድ ሲቀርብ ነው፡፡

2. ለቀጥተኛ የእርጅና ተቀናሽ የግብር ከፋዩ ዋጋው የሚቀንስ ሀብት ወይም ግዙፋዊ ሀለዎት የሌለው የንግድ ስራ ሀብት ቀሪ ዋጋ ከብር 2000 የሚበልጥ ከሆነ የእርጅና ተቀናሽ ይፈቀድለታል፡፡

3. ማንኛውም የንግድ ስራ ሀብት የተናጠል ዋጋ ከብር 2000 በታች ከሆነ በአንድ ጊዜ በወጪነት መያዝ አለበት፡፡

4. በዓይነት የሚደረግ የካፒታል ሀብት መዋጮ እና በውርስ ለሚተላለፍ ሀብት የእርጅና ቅናሽ መሰረት በሚተላለፍበት ጊዜ የነበረው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ነው፡፡

ዋጋው እየቀነሰ የሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ አቀናነስ

1. ዋጋው እየቀነሰ የሚሄድ የእርጅና መጠን የሚሰላው በግብር ዓመቱ መጀመሪያ በነበረው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ላይ የእርጅና ተቀናሽ መጣኔውን በማስላት ይሆናል፡፡

2. “በግብር ዓመቱ መጀመሪያ የነበረው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ” ማለት ከመጀመሪያው የመዝገብ ዋጋ በየጊዜው የተቀነሱ የእርጅና ተቀናሾች ከተቀነሱ በኋላ የሚገኝ ዋጋ ነው፡፡

ሀብትን ማስተላለፍ እና በባለቤትነት መያዝ

ለእርጅና ቅናሽ እና የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ ለሚከፈል ግብር ዓላማ ምዝገባ የሚፈፀምበት ሀብት በሽያጭ፣ በልውውጥ ወይም በስጦታ ሲተላለፍ አስተላላፊው ሀብቱን እንዳስተላላፈ የሚቆጠረው እና የተላለፈለት ሰው ሀብቱን በባለቤትነት እንደያዘ የሚቆጠረው የሽያጭ፣ የልውውጥ ወይም የስጦታ ውሉ፣ ውል ለመዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ዘንድ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ሆኖ የእርጅና ተቀናሽ ሊጠየቅ የሚችለው ሀብቱ የተመዘገበ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
ይህን ያውቁ ኖሯል?👆🏾

#tax #hanitube #አዲስአበባገቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ
#ቫት_Vat

ለበለጠ መረጃ
ዌብሳይት www.hanitube.com
YouTube..🌟..https://youtube.com/@hanitubeaccounting?si=6prlZI8Q5qz1DCEp
ቴሌግራም ቻናል🌟http://t.me/hanitube
Hani Tube

15 Nov, 20:14

1,000

ቅድመ ታክስ /With Holding Tax/

የፈደራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008፤የፈደራል ታክስ አስተዳደር ቁጥር 983/2008፤ በመመሪያ ቁጥር 2/2011 መሰረት :-

ቅድመ ታክስ ማለት አንድ አገልግሎት ወይም የዕቃ ግዢ በሚከናወንበት ግዜ ገዢዉ ለአገልግሎት ወይም ለዕቃ ከሚከፍለዉ ክፍያ ላይ ግብር ቀንሶ ለመንግስት የሚያሳዉቀዉ የግብር አይነት ነዉ ፡፡

አላማ፡-መንግስት ቅድመ ግብርን በበጀት አመቱ መጨረሻ ከሚሰበስብ ይልቅ  ገቢ በተገኘበት ወቅት ሰብስቦ ልማትን ለማፋጠን አመቺ ነዉ ከሚል አንጻር  የመጣ ነዉ፡፡

ምጣኔው...

አንደኛ:-ለንግድ ለሚዉሉ ዕቃዎችን ወደ አገር ስያስገቡ የእቃዎቹ የጉምሩክ ዋጋ ፤ የመጓጓዣ ዋጋ (CIF) መሰረት በማድረግ 3%የንግድ ስራ ገቢ ግብር በቅድሚያ ለባለስልጣኑ ይከፍላል ፡፡

ሁለተኛ:-በሀገር ዉሰጥ ከሚፈፀሙ ክፍያዎች ላይ ግብር ቀንሶ የማስቀረት ግደታ የተጣለባቸዉ ድርጅቶች (ሰዎች)፤

በአንድ የዕቃ ግዥ ከ10,000 በላይ ለሆነ የዕቃ አቅርቦት ለሚፈፀም ክፍያ እና
በአንድ በአገልግሎት ዉል ከ3,000 በላይ ለሚፈፀም ከፍያ 2% ግብር ቀንሰዉ የማስቀረት ግዴታ አለባቸዉ ፡፡

በመጨረሻ

✍️ግብር ተቀናሽ የሚደረግበት ዕቃ ወይም አገልግሎት አቅራቢ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እና የፀና የንግድ የስራ ፈቃዱን ግብር ቀንሰዉ ለሚያስቀረዉ ገዢ ልያቀርብ ካልቻለ ገዢዉ ለአቅራቢዉ ከሚፈጽመዉ ጠቅላላ ክፍያ ላይ 30% ግብር ተቀናሸ ማድረግ አለበት ፡፡

ለበለጠ ስለ ግብር ለመማር ከ 78,600 በላይ ተከታይ ያለውን የ You Tube ቻናል ማለትም  Hani Tube ይቀላቀሉ

አካውንቲንግ ትምህርት እና የኢትዮጵያ ታክስ አሰራር እና አዋጆችን ለመማር :-
📣You tube:- https://www.youtube.com/@Ethiopiatax
📣ዌብሳይት:Www.hanitube.com
📣https://t.me/hanitube   ቴሌግራም ቻናል

#Withholdingtax #ታክስ #ንግድ #ገቢዎች #አዲስአበባገቢዎች #በመርካቶ #ethiotax #EthiopiaTaxlaw #የተጨማሪ_እሴት_ታክስ_አዋጅ #የቴምብር_ቀረጥ_አዋጅ #AddisAbaba
Hani Tube

13 Nov, 22:14

1,146

የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ ማሻሻያ ቁጥር 188/2017

በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት ግዴታ መሆኑን እንዲሁም ከዚህ ቀደም ታትሞ በእጃቹ የነበረ ደረሰኞች ይህ መመሪያ ከተሻሻለበት እስከ 3 ወር ብቻ እነደሚያገለግል ይገልጻል ።

#ደረሰኝ_Receipt_Invoice #book_keeping

@hanitube
#ገቢዎች #ታክስ #ንግድ #መመሪያ
Hani Tube

13 Nov, 18:53

998

#በመርካቶ ሸራ ተራ አካባቢ በገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ ስም ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ ።

ህዳር 4/ 2017 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር ባካሄደው ቅንጅታዊ ክትትል የቢሮ ሰራተኛ በመምሰል ነጋዴዎችን ሲያጭበረብር የነበረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ ።

ቢሮው ከህዳር 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፌደራል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ያለደረሰኝ ሽያጭ ላይ ቁጥጥር መጀመሩ ይታወቃል ።

ይህን መነሻ በማድረግ በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ግለሰብ በመርካቶ ገበያ በአንድ ግለሰብ ሱቅ ውስጥ በመግባት የዕቃዎች ደረሰኝ ሲጠይቅና ሲያጭበረብር በደረሰ ጥቆማ መሠረት ለማምለጥ ቢሞክርም በፓሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ።

ቢሮው የንግዱ ማህበረሰብ ማንኛውም በግል ወይም በቡድን የሚንቀሳቀሱ አጭበርባሪዎች ወደ ንግድ ስፍራቸው ሲመጡ የቢሮ ሰራተኛ መሆናቸውን መታወቂያና መለያ ባጅ በመጠየቅ ሊያረጋግጥ እንደሚገባ ተጠቁሟል ።

ከዚህም በተጨማሪ አጠራጣሪ ድርጊቶች ሲያጋጥሙት በነፃ የስልክ መስመር 7075 በመጠቀም እንዲጠቁም ጥሪ ተላልፏል ።
ምንጭ -ከአዲስ አበባ ገቢዎች ፌስቡክ ገጽ
#አዲስአበባገቢዎች #ንግድ #ገቢዎች #ታክስ
Hani Tube

13 Nov, 17:45

926

https://youtu.be/i1RDWGtZQJk?si=02qlrEOz_pmSjGQq
Hani Tube

11 Nov, 22:51

760

#AddisAbaba

" ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል።

ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ዘመቻ ሲባል ፦
- ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣
- ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድረግ፣
- ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ማስቻልን ያካትታል።

የቁጥጥር ስራው በተለይም በገበያ ሞሎች ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ታውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም አንዳንድ ነጋዴዎች እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ " ንብረት ለመውረስ እና ሱቆችንም ለመዝጋት ነው " በሚል ሱቃቸውን ዘግተዋል ንብረትም ወደ ሌላ ቦታ አዙረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ በመርካቶ አካባቢ የሚሰሩ ነጋዴዎሽ  " ከምንም በፊት ያሉትን ችግሮች ማወቅ ይገባል። ቸርቻሪውን ማነጋገር ያስፈልጋል። ችግሮቹን ለመቅረፍ መሰራት አለበት። " ብለዋል።

" ነጋዴው ከአስመጪ እቃ ሲገዛ አስመጪው ከዋጋው በታች ደርሰኝ ይሰጣል አልያም ጭራሽ ላይሰጥም ይችላል ፤ ምንም  አይነት የግዢ ደረሰኝ ባላገኘበት ' ነጋዴው ሱቅ ውስጥ ያለዉን ንብረት እንወርሳለን ' ማለት ትክክል አይደለም " ሲሉ አክለዋል።

" መንግሥት ታች ያለው ነጋዴ ላይ ጣቱን ከመቀሰር አስመጪዎቹን ደረሰኝ እንዲሰጡ ማድረግ እና ቸርቻሪውን ማወያየት ያስፈልጋል " ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አንዳንድ የራሳቸው የገቢዎች ሰዎች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ቸርቻሪዶችን ማስጨነቅ እንደሚቀናቸው ቃላቸውን የሰጡ አንዳንድ ነጋዴዎች ጠቁመዋል።

ያለ ደረሰኝ ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት የገንዘብ ድርድር ሁሉ እንደሚያደርጉና ያሉ ችግሮች ስር የሰደዱ እንደሆኑ ገልጸዋል።

" ከምንም በላይ ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይኖር ከላይ ጀምሮ መስራት እንደሚገባ ነጋዴው በደረሰኝ ከገዛ በደረሠኝ እንደሚሸጥ ከላይ ግን እጃቸው የረዘመ ሰዎች ስላሉ መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ " አመልክተዋል።

ሁኔታዎችን በመጠቀም በህግ ሰበብ ከነጋዴው ገንዘብ የሚቀበሉና ሙስና የሚሰሩ ህገወጥ ተግባራትንም የሚያባብሱ በገቢዎች አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዲታረሙ መሰራት እንዳለበት አክለዋል።

ሌላ አንድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ የሃሳብ መለዋወጫ መድረክ ሃሳባቸውን ያካፈሉ ዜጋ ፥ አስመጪዎች እና አምራቾች ለጅምላ ነጋዴ እና ቸርቻሪ ያለደረሰኝ ስለሚሸጡ ያለደረሰኝ የተገዙ እቃዎች እንደሚኖሩ ገልጸዋል።

" ነጋዴዎች እቃዎቻቸው ሳይወዱ ደረሰኝ ስለሌላቸው እንዳንወረስ ብለው ወደ ሌላ ቦታ ያሸሻሉ ሱቅም ለመዝጋት ይገደዳሉ  " ብለዋል።

" ዋናው ስራ መጀመር ያለበት ከአስመጪዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች መሆን አለበት ፤ እነሱን በሚገባ ከተቆጣጠሩ እና እርምጃ ከወሰዱ በኋላ በተዋረድ ጅምላ ነጋዴዎች እና ቸርቻሪዎችን መቆጣጠር ይገባል " ብለዋል።

" የችግሩ ምንጭ ከሆኑት አስመጭዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች ጠበቅ ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት " ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

" በዛሬው ዕለት በመርካቶ አካባቢ ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው " የሚል ውዥንብሮች በመፈጠራቸው አንዳንድ ነጋዴዎችን ግርታ ውስጥ መክተቱ ተናግሯል።

ስለ ጉዳዩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽን አነጋግሯል።

ዳይሬክተሩ ምን መለሱ ?

➡️ " ጠዋት ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል " ተብሎ ተወርቶ በአካል ዞሬ አይቻለሁ የተወሰኑ ሱቆች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተዘጉ የሚመስሉ አሉ ነገር ግን መደበኛ ሥራ ቀጥሏል።

➡️ " በዚህ ደረጃ ተዘግቷል ለማለት እይቻልም ተዘጋ የሚባለው ምን ያህል ሱቅ ሲዘጋ ነው ? አንድ ቤት ሁለት ቤት ተዘግቶ ይሆናል ነገር ግን አብዛኛው እየሰራ ነው።

➡️ ህገ ወጥነትን ማስቀጠል የሚፈልግ አካል  አለ። ሆን ብሎ ' የሆነ ነገር ተሰርቷል፣ ሊሰራ ነው ' የሚል ውዥንብር መፍጠር የሚፈልግ አካል እንዳለ ነው የተረዳሁት።

➡️ ቁጥጥር ሊደረግ ነው በተለይ አስመጪ እና አከፋፋይ ላይ ሲባል ቸርቻሪ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ አሉ፣ በትላንትናው ዕለትም የሚሸሹ ነጋዴዎች ገጥመውናል ያለፍቃድ ይነግዱ የነበሩ ናቸው ብንጠየቅ መልስ የለንም በሚል ስጋት ነው። ሱቃቸውን ቢዘጉም እነሱ ናቸው የሚሆኑት።

➡️ ተዘግቷል የሚለውንም እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል በእርግጥ የተዘጋ ነው ወይስ ነጋዴው በsocial ችግር ሱቃቸውን ዘግተው ስለሌሉ ነው የሚል ጥርጣሬ የሚያጭር ስለሆነ የተዘጉ አይደሉም ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስነው።

➡️ ይርጋ ሃይሌ የገበያ ሞል ላይ ከ15 ቀን በፊት ኮንትሮባንድ ስለነበረ ጎምሩኮች በርብረዋል ደረሰኝ የሌለውን ወርሰዋል ደረሰኝ ያለውን ጥለው ወጥተዋል።

➡️ የገበያ ሞሉ ላይ እቃዎችን መለየት አስቸጋሪ ስለነበር እና ሰዎቹም ተባባሪ ስላልነበሩ ለጊዜው ታሽጎ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ሀሉም ተከፍተዋል። የቀረ ካለ በንግድ ቢሮ በኩል ፈቃድ ያልነበረው በመሆኑ በተወሰደ እርምጃ ነው።

➡️ ታሽገው የነበሩ አብዛኛው ሱቆች ተከፍተዋል። እስካሁን ያልተከፈተ ካለ ፈቃድ ስላላወጣ ነው የሚሆነው በተረፈ እቃ የሚወረሰው ኮንትሮባንድ ሲሆን ብቻ ነው።

➡️ ሁሉም ሰው ደረሰኝ ስለማይሰጥ የሚመለከተው ብቻ ነው ደረሰኝ እንዲሰጡ የሚጠበቀው መስጠት የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች ደረሰኝ እየሰጡ ግብይታቸውን ይቀጥሉ።

➡️ " እቃችሁ እየተወረሰ ነው፣ ሊወረስብን ነው" የሚሉ አካላት እቃቸው ምን ስለሆነ ነው የሚወረሰው ? እንደዚህ የሚሉ አካላት ኮንትሮባንድ ስለሆነ ይመስላል።

➡️ ያለደረሰኝ አትግዙ ፣የሚሸጥላችሁን ጠቀሙ እኛ ደግሞ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽምን አካል እንቆጣጠራለን ብለናል የምንከታተላቸውም ለዛ ነው።

➡️ እቃ ለመውረስ የህግ መሰረት ያስፈልጋክ። እቃ የሚወረሰው የታክስ እዳ ማካካሻነት ከተያዘ ብቻ ነው።

➡️ ግብይት ላይ ያለ እቃን የታክስ ማካካሻ ብለን የምንወርስበት ምክንያት የለንም። ክፍተት ያለበትን ነጋዴ ለማወናበድ የሚሮጥ ሌላ ጥላ የሚፈልግ አካል የሚያወራው ወሬ ነው።

➡️ " ያለደረሰኝ አትሽጡ " አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም። ይህም ለነጋዴዎች በደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

ምንጭ tikvahethiopia

#AddisAbaba #ለታክስ #tax #ታክስ #ግብር #ethiotax #ጉምሩክ #አዲስአበባገቢዎች
Hani Tube

10 Nov, 13:35

769

ውድ ግብር ከፋዮቻችን
በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀጽ 83 ሰነድን የማቅረቢያ ጊዜ ቅዳሜ፤ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ካረፈ በቀጣዩ ቀን ግብሩን ማሳወቅ እንደሚቻል ይደነግጋል። ስለሆነም ሰኞ ማለትም ህዳር 02 ቀን 2017ዓ.ም የመጨረሻ ቀን መሆኑን  በመገንዘብ ለተጨማሪ ወለድ እና ቅጣት እንዳይዳረጉ ግብርዎትን በወቅቱ እንዲያሳውቁ በማክበር እንገልጻለን።

የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
#taxlaw #tax #ገቢዎች #ታክስ #ግብር #hanitube #EthiopiaTaxlaw
Hani Tube

09 Nov, 20:00

1,048

ሰኞ ህዳር 2 ያለ ቅጣት አሳውቁ፡ ክፈሉ

ለዉድ ግብር ከፋዮች በሙሉ

አመታዊ እና ወርሀዊ የገቢ ማስታወቂያና መክፈያ  ቀን  ጥቅምት 30 /2017  ዓ.ም ቅዳሜ ቀን ስለዋለ ሰኞ ህዳር  2/2017 ዓ.ም ያለቅጣት መስተናገድ ትችላላቹ።