Geez Media Center (@geezmediacenter)の最新投稿

Geez Media Center のテレグラム投稿

Geez Media Center
https://t.me/GeezMediaCenter
4,141 人の購読者
3,447 枚の写真
206 本の動画
最終更新日 06.03.2025 09:47

Geez Media Center によってTelegramで共有された最新のコンテンツ

Geez Media Center

20 Apr, 19:21

1,912

በቃ!
አሁን ሁለገብ ውድቀት ላይ ነን።
ይህን መካድ በእየእለቱ የሚያርደውን አእምሮ የሚያስታጥቅ አመራር አለ፣ በእየለቱ የሚታረደውን ሕዝብ ከላላና ፍትሕ የሚነፍግ ሥርዓት አለ።
የሚያዋጣው ይህን ተጨባጭ ሰው ክብሩን ጥሎ በእንስሳ ደረጃ የሚኖርባት አገርና በአራዊት ደረጃ ለሰው ደምና መከራ የማይጨነቁ መሪዎች፣ እምነታቸውን ለምቾትና ለድሎት መሣሪያ ያደረጉ የእመነትና የባህል መሪዎች መስራፋታቸውን ተቀብሎ ንስሐ መግባት፣ ጥፋታችንን የሚመጥን መልካምነትን ለመላበስ፣ ክፋትና ርኵሰትን ለመጋደልና ራሳችንን ነፃ በማውጣት የደምን ጎርፍና የመከራም ናዳ ማስቆም ነው።

በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሕሊና ቀረለት፣ ሰብእናው ያልወደቀበት፣ ለሕሊናው የሚገዛ እና የፈሪሐ እግዚብሔር ጠብታ በልቡ ያለ ሁሉ ማንንም ነፃ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ሳይጠበቅ የሚከተሉትን ተግባራት በአስቸኳይ መጀመር አለበት፡-
1) ንስሐ መግባት፣ የበደሉትን መካስ፣ የወሰዱትን መመለስ፣ ያሳዘኑትን ይቅርታ መጠየቅ፤
2) በመዋቅር፣ በሥርዓት፣ በክፌ ርእዮትና ትርክት ምክኒያት መከራ ለሚቀበሉት ድምጽ መሆን፤
3) ክፉ ሰዎችን ከቤታችን ጀምረን እንስተካከሉ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ፤
4) የንዑስ-ማንነት ፖለቲካ የሚፈጥረው የዘረኝነት ደዌ ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ በመጠንቀቅ ስለ ሰብአዊነት፣ ፍትሓዊነት፣ እውነትና ፍቅር፣ የአገር ጠቃሚና አሰባሳቢ ታሪክ፣ ስል ዘመነኞችን የክፉዎች ፖለቲካን አሁን እያስከተለ ያለው እልቂትና ስስት በግልጽ ማስተማር፤
5) በመራው የተሰደዱትን፣ ያዘኑትን፣ እናትና አባት፣ ባልና ሚሰት አጥተው የተቸገሩትን በአቅም መርዳት፤
6) ለመከራችን ምክኒያት የሆነው በሐሰትና ስሕተት ራሱን ከሰብእና፣ ከዜግነትና ሃይማኖት በላይ ያደረገውን የንዑስ ማንነት ፖለቲካ በሚቻለው መንገድ ሁሉ መቃወም፣ ማጋላጥ፣ ርኵስ የጥፋት መንገድ መሆኑን በንግግርና ባለመተባበር ተግባር ማሳየት፤
7) ከመልካሞች ጋር በመደራጀት ክፉዎችን መከላከል፣ ማሸነፍ፣ መመለስ፣ ሰው ማድረግ፤
8) በየባህላችን፣ እመነቶቻቸን፣ የማኅበረሰብ መዋቅሮቻችን ውስጥ ከመንገድ የወጡ፣ የፖለቲካ አገልጋይ የሆኑ የምቾትና የድሎት ምርኮኞችን ወደ ንሥሐና ወደ የሚመሩትን ሕዝብ እረኝነት ተመልሰው በተግባር እንዲገልጡ ጫና ማድረግ፣ ድጋፍ መንሳት፤
9) አገር ውስጥ ለሚገኙ የክፋት ብድኖች ሁለገብ ድጋፍ መንሳት፤ በተቃራኒው መልካሞችን፣ አውነተኞችን፣ እውነትና ፍትሕን የሚያሳድዱትን አካላት ለይቶ መቃወም፣ ማጋለጥ፣ አሠራራቸውን ለዜጎችና ለውጭ መንግሥታት ሁሉ ማሳጣት፤
10) ቴክኖሎጂን ለተራ ወሬና ጊዜ ማጥፊያ ሳይሆን የሰውን ልጆች ለማዳን መጠቀም።

ይህ ሁሉ የሚቻለው ግን በእግዚአብሔር ላይ ፍጹም እምነት በማኖር፣ ሁሉን ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ማድረግ እና ለግል ሥልጣን፣ ለግል ዝና፣ ለግል ጥቅምና ድሎትና ምቾትን ፍለጋ አለመሆኑን ከልቡ ተማክሮ ራሱን ላሳመነ ሰው ነው እንዲሁ ለመሆን ቁርጥ ሕሊና ማድረግ።
Geez Media Center

20 Apr, 07:24

2,687

መምህር ፋንታሁን ዋቄ - አማናዊው ሰው
የዚች ሀገር እና ቤተክርስቲያን አንዱና የመጨረሻው ልጇ ይናገራል አድምጡት።
@GeezMediaCenter
Geez Media Center

17 Apr, 20:29

2,066

"የእምነት አባቶች ፣የአውደምህረት ሰባኪያን ዛሬ ላይ እስጢፋኖስን የስብከት ርዕስ ለማድረግ አትጨነቁ። እንደ እስጢፋኖስ ድንጋይ የተከመረባቸው የእራሳችሁ ወገኖች አይኗችሁ ላይ ተስለው ተቀምጠዋልና "

እግዚአብሔር ይቅር ይበለን !!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch