The Federal Supreme Court of Ethiopia @fscethiopiapr Telegram Kanalı

The Federal Supreme Court of Ethiopia

The Federal Supreme Court of Ethiopia
Federal Supreme Court is the highest court in Ethiopia. It is constitutionaly established court. It is also one of the three pillars of the federal state that assures the check and balance in & among.
10,732 Abone
1,807 Fotoğraf
21 Video
Son Güncelleme 01.03.2025 06:39

The Role of the Federal Supreme Court of Ethiopia

The Federal Supreme Court of Ethiopia is a pivotal institution within the Ethiopian legal system that serves as the highest court in the country. Established under the 1995 Constitution of Ethiopia, it plays a critical role in upholding the rule of law and ensuring justice for all citizens. The Court's primary function is to interpret and apply the law, serving as the final arbiter in legal disputes and safeguarding the rights enshrined in the Constitution. With a mandate to oversee the judicial process throughout Ethiopia, the Federal Supreme Court is fundamental in maintaining the system of checks and balances within the federal state. It operates alongside the federal and state courts, ensuring that justice is not only done but seen to be done, thus fostering public confidence in the judiciary. In addition to its judicial functions, the Court is often involved in significant legal reforms and discussions, impacting the broader socio-political landscape of Ethiopia.

What is the structure of the Federal Supreme Court of Ethiopia?

The Federal Supreme Court of Ethiopia is structured to include a president and several judges appointed by the House of People's Representatives. This structure enables the Court to function effectively and deliver justice impartially. The president of the Court is typically a senior judge with extensive legal experience, ensuring that the leadership of the judiciary is both competent and experienced. Furthermore, the Court's judges are tasked with not only adjudicating cases but also with interpreting complex legal issues that may affect the larger Ethiopian society.

The Court is divided into various benches that specialize in different areas of law, including civil, criminal, and administrative cases. This specialization allows the Court to handle a diverse array of cases, improving the efficiency and effectiveness of the judicial process. The decisions made by the Federal Supreme Court are binding on all lower courts, reinforcing its position as the ultimate judicial authority in Ethiopia.

How does the Federal Supreme Court ensure the rule of law?

The Federal Supreme Court ensures the rule of law by providing a platform for judicial review and interpretation of laws. This function is crucial because it ensures that legislation and executive actions comply with the Constitution. By reviewing laws and actions for constitutionality, the Court serves as a guardian of democracy and civil rights in Ethiopia, allowing citizens to seek justice when their rights are infringed upon. It empowers individuals and groups to hold the government accountable under the law.

Moreover, the Court's decisions set precedents that guide lower courts in their judgments, promoting consistency and fairness in legal interpretations. This role of creating legal precedents helps to stabilize the judicial environment and fosters public trust in the legal system, reinforcing the importance of adhering to established laws and principles.

What types of cases does the Federal Supreme Court handle?

The Federal Supreme Court of Ethiopia handles a broad spectrum of cases, including those related to constitutional law, human rights, civil disputes, and criminal law. It primarily deals with appeals from lower courts, making rulings that can significantly impact Ethiopian jurisprudence. The Court also has jurisdiction over cases involving federal entities and disputes between regional states, which underscores its role in maintaining national unity and legal consistency across the federation.

In addition to handling appeals, the Court may also engage in cases that require its interpretation of laws that affect fundamental rights or constitutional issues. This jurisdiction ensures that the Court remains an essential mechanism for the protection of individual freedoms and the enforcement of the rule of law, making it a cornerstone of Ethiopia's democratic framework.

What is the significance of the Federal Supreme Court in Ethiopia's federal system?

The Federal Supreme Court is significant in Ethiopia's federal system as it acts as a mediator between the federal government and the regional states. It ensures that laws enacted at both the federal and state levels do not violate the Constitution, thus preserving the integrity of the federal structure. This function is particularly important in a diverse country like Ethiopia, where multiple ethnic groups and regional governments coexist, each with their distinct legal frameworks. By adjudicating disputes that arise between different levels of government, the Court plays a crucial role in maintaining harmony and cooperation within the federation.

Furthermore, its existence as one of the three pillars of the federal state enhances the balance of power among the branches of government. By holding the other branches accountable, the Federal Supreme Court helps prevent the misuse of power and fosters a transparent governance system. This balance is essential for the stability and development of Ethiopia, enabling a dynamic political landscape where citizens can engage meaningfully in governance.

How does the Federal Supreme Court contribute to legal reforms in Ethiopia?

The Federal Supreme Court contributes to legal reforms in Ethiopia through its rulings and interpretations of the law, which often highlight gaps or inconsistencies in the legal system. By addressing these issues in its judgments, the Court can influence legislative bodies to amend or introduce laws that better serve the population's needs. The Court's opinions often provide guidance on best practices and necessary changes to enhance the justice system.

Additionally, the Court engages with various stakeholders, including legal professionals, civil society organizations, and international bodies, to foster discussions on legal reforms. These collaborations often lead to the development of comprehensive reform agendas aimed at modernizing the judiciary, improving access to justice, and enhancing the overall rule of law in Ethiopia. Through these efforts, the Federal Supreme Court plays a fundamental role in shaping a responsive and accountable legal system.

The Federal Supreme Court of Ethiopia Telegram Kanalı

Are you interested in learning more about the legal system in Ethiopia? Look no further than the Telegram channel 'The Federal Supreme Court of Ethiopia'! This channel, with the username @fscethiopiapr, provides valuable insights into the highest court in the country, the Federal Supreme Court. Established constitutionally, this court plays a crucial role in upholding justice and ensuring the rule of law in Ethiopia. It serves as one of the three pillars of the federal state, providing checks and balances to maintain a fair and just legal system for all citizens. By following this channel, you will have access to updates on key legal decisions, information on the court's functions and responsibilities, as well as educational content on the Ethiopian legal system. Whether you are a law student, legal professional, or simply interested in the judicial system of Ethiopia, this channel is the perfect resource for staying informed. Join the 'The Federal Supreme Court of Ethiopia' Telegram channel today and gain a deeper understanding of the legal landscape in Ethiopia. Stay up-to-date on important court cases, legal reforms, and judicial developments. Don't miss out on this opportunity to expand your knowledge and engage with others who share your interest in the Ethiopian legal system. Subscribe now and become a part of this informative community!

The Federal Supreme Court of Ethiopia Son Gönderileri

Post image

በፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለዎትን ቅሬታ/አስተያየት በቴክኖሎጂ በመታገዘ ያቅርቡ
********
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለተገልጋዮች ቅሬታ እና አስተያየት ማቅረቢያ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በውስጥ አቅም በማልማት ከየካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ይህን መተግበሪያ ለመጠቀም ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ወቅት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በድምፅ አሊያም በፅሁፍ የሚያሰፍሩበት ሲስተም ሲሆን ወደ ተቋሙ ለአገልግሎት በሚመጡበት ወቅት ተቋሙ ውስጥ በሚገኘው የወንጀል ይግባኝ ጉዳዮች የአንድ ማዕከል ሬጅስትራር አገልግሎት መስጫ ማዕከል ውስጥ የዳኝነት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ክፍል በመቅረብ በስራ ክፍሉ በሚገኙ ባለሙያዎች በመታገዝ አሊያም በእጅ ስልኮ በተቋሙ ኢንተርኔት/ዋይፋይ በመጠቀም የተቋሙን QR ኮድ ስካን በማድረግ የዳኝነት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት የሚለውን በመጫን በድምፅ ወይንም በፅሁፍ ቅሬታዎን/አስተያየቶን ያቅርቡ ከሚሉ አማራጮች የሚፈልጉትን በመምረጥ ቅሬታዎን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ቅሬታው/አስተያየቱ የሚቀርበው በድምፅ ከሆነ የድምፅ ምልክቷን በመጫን መልእክቱን ማስተላለፍ የሚቻል ሲሆን በፅሁፍ የሚቀርብ ሲሆን ከተዘረዘሩት አስተያየት መስጫ ነጥቦች (እጅግ ከፍተኛ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ ወይም ዝቅተኛ) አንዱን በመምረጥ አስተያየቶን መስጠት ይችላሉ፡፡

የተገልጋይ ቅሬታም ወደ ሰርቨር ገብቶ ደህንነቱን በጠበቀ ሁኔታ ለኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የሚላክ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡

የአጠቃቀሙን ቅደም ተከተል ከስር ባለው ምስል ይመልከቱ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

28 Feb, 14:28
1,363
Post image

የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የለውጥ ሥራ ተፈጻሚ ለማድረግ የፍርድ ቤቶችን የሰው ኃይል አቅም መገንባት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገለጸ
*********
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተጀመረውን የለውጥ ሥራ ተፈጻሚ ለማድረግ የፍርድ ቤቶችን የሰው ኃይል አቅም መገንባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ገለጹ፡፡

ክብርት ምክትል ፕሬዝደንት ይህን የገለጹት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባዘጋጀውና ከሶስቱም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ 110 ሠራተኞች ከየካቲት 20-22 ቀን 2017 ዓ.ም በተዘጋጀው የሶስት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በጀመሩት የለውጥ ሥራ የተከናወኑ እና በመሠራት ላይ ያሉ ማሻሻያዎች እንደሚገኙ የጠቆሙት ም/ፕሬዚደንት ከእነዚህ መካከል የሕግ ማሻሻያዎች፣ የቴክኖሎጂ ሥራዎች እና የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ሥራዎችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸው እነዚህ ማሻሻያዎች የሚተገበሩት በሰው ኃይል በመሆኑ የሰው ኃይል ግንባታ ትኩረት ከተሰጣቸው የለውጥ ሥራዎች መካከል የሚመደብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ፍርድ ቤቶቹ ተግባራዊ ያደረጉትን ለውጥ መሠረት በማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቅልጥፍና፣ ጥራት እና ውጤታማነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን ከፍርድ ቤቶች የሰው ኃይል ምን እንደሚጠበቅ በቂ ግንዛቤ መያዝ፣ ለአንድ ዓላማ በጋራ መስራት እንዲሁም በቁርጠኝነት መፈጸም ከእያንዳንዱ ሠራተኛ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ለሶስት ቀናት በሚቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ላይ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሰው ሀብት ሥራ አመራር ደንብ እና መመሪያዎች፣ ተቋማዊ ለውጥ፣ የሥራ ባህል እና ሥነምግባር፤ አዲሱ የህዝብ አገልግሎት አቀራረብ ስልት ለተሻለ ተቋማዊ አፈጻጸም እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ጉዞ በፌደራል ፍርድ ቤቶች በሚሉ ርዕሶች ላይ ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው በተከታታይ 7 ዙሮች የሚሰጥ ሲሆን በክልል ከተሞች የሚገኙ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሠራተኞችን ባካተተ ሁኔታ አሁን በሥልጠናው ላልታቀፉ ሌሎች ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎችን ባሳተፈ መልኩ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሙዩኒኬሽንና ስትራቴጅያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

27 Feb, 12:18
796
Post image

"የፍርድ ቤቶችን አሰራር ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ናቸው!"

------ቋሚ ኮሚቴው------

(ዜና ፓርላማ) ጥር 30 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፍርድ ቤቶች አሰራር ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጿል።

ቋሚ ኮሚቴው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት አመት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም፣ የፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ያለበትን አፈፃፀም እና ቀጣይ ስራዎችን ገምግሟል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ ዕቅዱና አፈፃፀሙ ከፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን በጥንካሬ የሚታይ መሆኑንና ችግሮችን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ምን ያህል ትኩረት ተሰጥቶ እና የዕቅድ አካል ተደርጎ እየተሰራ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

አያይዘውም ለለውጥ ፍኖተ ካርታ የህግ ማሻሻያ ምሰሶ መሆኑን ጠቁመው ለአሰራር ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

ችሎቶችን በቴክኖሎጂ ለማገዝ፣ ባለድርሻ አካላትን ለማሳተፍ፣ የባለ ጉዳይ አያያዝ፣ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ፣ በተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችን ወደ ህዝብ ለማድረስ እና ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር የተሰሩ ስራዎች አበረታች እና በጥንካሬ የሚጠቀሱ ስራዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

መስሪያ ቤቱ ለብልሹ አሰራር ተጋለጭ የሆኑ ጉዳዮችን በየጊዜው ትኩረት ሰጥቶ እየፈተሹ፣ እያረሙና እያስተካከሉ መሄድ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን፤ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ችግሩን መፍታት እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ በበኩላቸው የስድስት ወራት አፈፃፀም እያንዳንዱ ስራ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት በፍ/ቤቶች ያልታዩ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት፣ ፍርድ ቤቶችን ለመቀየር የተጀመረው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

ከሰፋፊ የኔትዎርክ ዝርጋታ፣ ከስማርት ኮርት ሩም ሲስተም፣ ድምፅን ወደ ፅሁፍ የመቀየር ቴክኖሎጂዎች በስራ ላይ መዋላቸው ጥሩ ጅምሮ መሆናቸውን እና በሚፈለገው ፍጥነት መሄድ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

አያይዘውም ከፌዴራል ፍርድ ቤት ጀምሮ በአካል በመስክ ምልከታ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማየት መቻሉን እና ቀሪ ስራዎች በመኖራቸው ወደ ተጨባጭ ስራ መገባት እንዳለበትም አመላክተዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው የሩብ አመቱ ዕቅድ የአምስት አመቱ ስትራቴጅክ ዕቅድ አካል መሆኑን ጠቁመው፤ የህዝብ አመኔታ ያተረፈ የዳኝነት አካል ሆኖ ለመገኘትና ለማሳካት ስድስት ግቦችንና የትኩረት መስኮችን ለይተው በዝርዝር አቅርበዋል።

ከቅንጅት አሰራር ጋር ተያይዞ ከፌዴራል የዳኝነት እና የፍትህ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ጥሩ መሆኑን ለአብነትም ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ጋር አንድ የቪዲዮ ኮንፍረንስ እና የኢፋይል አገልግሎት መስጫ ሞዴል ማዕከል መከፈቱንና ወደ ሌሎች የሚስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል።

ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያየዘም ተገልጋዮች የሚያነሷቸውን ቅሬታዎች በመቀበል የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አመላክተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው በግማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ተመስረተው የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን በሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ምንጭ: የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

07 Feb, 15:26
2,334
Post image

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት የወሰናቸው መዝገቦች ዝርዝር
ተ.ቁ መዝገብ ቁ.
1. 5096/12
2. 5215/12
3. 5279/12
4. 5333/13
5. 5355/13
6. 5357/13
7. 5359/13
8. 5457/13
9. 5466/13
10. 5516/13
11. 5517/13
12. 5912/13
13. 5960/13
14. 6015/13
15. 6564/14
16. 6579/14
17. 6582/14
18. 6595/14
19. 6597/14
20. 6603/14
21. 6608/14
22. 6614/14
23. 6660/14
24. 6907/14
25. 6921/14
26. 7854/15
27. 8732/16
28. 8798/16
29. 8866/16
30. 8908/16
31. 9008/16
32. 9032/17
33. 9037/17
34. 9131/17
35. 9282/17
36. 9283/17
37. 9371/17
38. 9372/17

*ማስታወሻ*
1. ቁጥራቸው የቅርብ ጊዜ የሆኑት ጉዳዮች ቀድመው የታዩበት ምክንያት በጉባዔው መመሪያ መሰረት ቅድሚያ አግኝተው ምርመራቸው የተጠናቀቀ (የወንጀል፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአሰሪና ሰራተኛ፣ ከፍ/ቤት ሪፈራል የተላኩ፣ የታገዱ መዝገቦች) መሆናቸውን እየገለፅን ከዚያ ውጭ ያሉት ግን እንደ አመጣጥ ቅደም ተከተላቸው የተስተናገዱ ናቸው፡፡
2. ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች የውሳኔ ግልባጭ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጉባዔው ፅ/ቤት በመቅረብ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

07 Feb, 12:26
2,344