Últimas publicaciones de FASHY (@fashyairdrop) en Telegram

Publicaciones de Telegram de FASHY

FASHY
የcryptocurruncy እና Airdoprs ዜናዎች ምንጭ✅
1,060 Suscriptores
139 Fotos
2 Videos
Última Actualización 10.03.2025 15:21

El contenido más reciente compartido por FASHY en Telegram

FASHY

18 Aug, 05:02

374

ጥቂት ስለ ፆታዊ ጥቃት...
* * *

ከብዙ ወንዶች ጋር ትወጣለች። "ሴሰኛ" ልትባል የምትችል ናት። ወንድ እየቀያየራች ጭኗን ትከፍትላቸዋለች። ገና በአበባነት ዘመኗ ከብዙዎች ጋር አንሶላ ተጋፋለች። ለፀፀት የሚዳርግ አይነት የወሲብ ህይወት አላት።

ይህች ወጣት እንዲህ ሂያጅ ከመሆኗ በፊት ክብሯት የገረሰሰው የገዛ ወንድሟ ነው። የአባትና የእናቷ ልጅ አስገድዶ አነወራት። ታላቅ ወንድሟ "ያደረግነውን ብትናገሪ እገድልሻለሁ" ብሎ እየዛተ ደጋግሞ ተገናኝቷታል። ብዙ ጊዜ ደፍሯታል።
ልጅት ከዚህ በኋላ ባከነች። ካገኘችው የምትተኛ ሆነች።

ሌላ ታሪክ

ባለትዳር ናት። ከባሏ ጋር ወሲብ ልትፈፅም ስትሞክር መቀመጫዋ አከባቢ ያማታል። ከወገብ በታች ህመም ይሰማታል። ህመሙ ሲባባስባት ወደ ሀኪም ሄደች። ከምርመራ በኋላ "ህመም የለብሽም" ይሏታል። ሀኪሞች በሽታ የለብሽም ቢሏትም ሁሌም ወሲብ ልትፈፅም ስትል ያማታል።

በመጨረሻም አንድ ሃኪም የስነልቦና ባለሞያ ጋር እንድትሄድ መከራት። ያኔ የህመሟ መንስኤ ታወቀ።

ልጅ እያለች በአያቷ ፆታዊ ጥቃት ተፈፅሞባታል። አያቷ በመቀመጫዋ በኩል ፆታዊ ጥቃት አድርሶባታል። ያ ክስተት የአእምሮ ጠባሳ ፈጠረባት። ወሲብ ስትፈፅም የሚያማት ጥቃቱ ባደረሰበት የስነልቦና ህመም የተነሳ ነበር።

ሁለቱ እውነተኛ ታሪኮች "ምን ሆኛለሁ?" በሚለው መፅሐፍ ላይ የሰፈሩ ናቸው።
ሁለቱ ታሪኮች ብዙ ይነግሩናል።
ተጠቂዎቹ ጥቃት የደረሰባቸው በቤተሰባቸው አባል ነው። መከታ እና ከለላ ሊሆኗቸው ከሚገባ ሰው ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን ጉዳቱ ዘመን ዘለል አእምሯዊ ጠባሳ እና ስነልቦናዊ ጉዳት አደርሶባቸዋል።

ሴቶች ሲደፈሩ የሚደርስባቸው ስነልቦናዊ መቃወስ ሳይታከም መቅረቱ ጉዳቱ ለማህበረሰቡ ጭምር ነው። ስነልቦናቸው የተጎዳ ሴቶች እናት ሲሆን ልጆቻቸውን እንዴት ያሳድጉታል?
ሴትን ከጥቃት መጠበቅ ማህበረሰብን መጠበቅ ነው።

አርቲስት እግቱ የጥቃት ሙከራ ከተደረገባት በኋላ በርካታ ሰዎች ተሳልቀውባታል። አንዳንዶች "ይቺን መልከ ጥፉ ማን ይነካታል" የሚል ከነውረኛ አእምሮ የሚፈልቅ መከራከሪያ አቅርበዋል።

ይህ የሚነግረን ነገር አለ።

ሴት ተገዳ እንድትደፈር ቆንጆ መሆን አይጠበቅባትም። ሴት በመሆኗ ብቻ ለጥቃት ተጋላጭ ናት።
ቆንጆ ሚስታቸውን አስቀምጠው የቤት ሰራተኛ የሚደፍሩ አሉ። የጎዳና ተዳዳሪዎች ይደፈራሉ። በልመና የተሰማሩ ይደፈራሉ። የአእምሮ ህሙማን ይደፈራሉ።

ሻሸመኔ የማውቃት የአእምሮ ህመምተኛ ነበረች። አንድ ወቅት አርግዛ አየኋት። ማነው ያስረገዛት? መልሱ ግልፅ ነው።

በዙሪያችሁ ያሉ ሴቶችን ስለፆታዊ ጥቃት ብትጠይቁ ልባችሁ ይሰበራል። ብዙ ሴቶች በተለያየ አጋጣሚ ለጥቃት ተጋልጠዋል።
ህፃናት በአዋቂዎች ይደፈራሉ። ሰራተኞች ከአሰሪዎች ትንኮሳ ይደርስባቸዋል። ደግሞም በቤተሰብ አባል የሚሰነዘር ጥቃትም አለ።

ሐገር የሚወድ ሴትን ከጥቃት ይጠብቅ።
ማህበረሰብን የሚወድ ሴትን ከጥቃት ይጠብቅ።
ራሱን የሚያከብር ወንድ ሴትን ከጥቃት ይጠብቅ።

https://t.me/+9k2KYUWaftM2OGRk
FASHY

16 Aug, 08:48

418

እንዴት ናችሁ አንድ እህታችን የ7 አመት ፍቅርኛ አለኝ አንድ ሀገር አንድ ስፍር ነው የምንኖርው ግን አብርን አንኖርም ይሄን ያክል አመት ስንቆይ አንድ ቀን አብርን አድርን አናቅም እሱም በሀይማኖቱ ጠንካራ ነው እኔም እንደዛው እና ከጋብቻ በፍት በጭራሽ አናስበውም በሳምንት አራት ቀን እንገናኛለን ተገባብዘን እንለያያለን ስልክ አናወራም አይወድም እና እስካሁን ያልተጋባነው የገቢ ምንጩ ትንሽ ናት እና ከቤት ኪራይ አታልፍም እና በዚህ ስራየ አንችን ባገባሽ ደስተኛ አላደርግሽም ትንሽ ጠብቂኝ እያለ ይሄው በ26አመቴ ተዋወኩት ይሄው እድሜየም ሄደ አልተወው ጥሩ ልጅ ነው ፅባይ አለው እድሜየ ሄደኮ ስለው ዞሮ ዞሮ የኔነሽ ቢሄድም አልተውሽም ነው የሚለኝ እሽ ብየው ነበር ግን አሁን አሁን እየፍራሁ መጣሁ ጓደኞቼ የሚጠብቃት ፍቅርኛ ልትኖርው ትችላለች ወንድ አይታመንም ቢወድሽ ቢያንስ አብርን እንሁንና ስርተን እንቀየራለን ይልሽ ነበር አይሆንሽም እያሉ ያስፍራሩኛል እኔም እድሜየ ሄደ ትለናለች በትህትና አማክሯት

https://t.me/+9k2KYUWaftM2OGRk
FASHY

14 Aug, 15:30

423

እንዴት ናችሁ ቤተሰቦቼ 🙌
ባለትዳር ነኝ አራስ ነኝ ! ባለቤቴ ሊረዳኝ ስላልቻለ እንደዚህ ፃፍኩለት። እሱም ምንም አልመለሰልኝም። ስናወራ የሱም ግዴለሽ መሆን ሲያበሳጨኝ በቃ ቁጣ ቁጣ ይለኛል። የሚስትነት ጥበቤ ሙልጭ ብሎ ጠፍቷል ከውስጤ። እሱ ስራ ነው የሚውለው። እኔ ደሞ የወሊድ እረፍት ላይ ነኝ። ብቻዬን ነው የምውለው። አጋዥም ጓደኛም ዘመድም ማንም አብሮኝ የለም። በኦፕሬሽን ነው የወለድኩት በቃ የማያመኝ ቦታ የለም እራሴን ወገቤን እጄን ሁሉ ነገሬን ያመኛል።። በዚ ላይ የሱ እንደዚህ መሆን ግራ ገባኝ።

እባካችሁ ይህንን ጊዜ የማልፍበትን ጥበብ ንገሩኝ ልጄን ያለእናት እንዳላስቀር እየፈራሁ ነው። ብዙ ስሜት ይሰማኝ እና ዞር ብዬ ልጄን ሳይ ያሳዝነኛል። እራሴ ላይ መጥፎ ውሳኔ ሳልወስን ድረሱልኝ። እናንተ ባለፋችሁበት ጥበብ እንዳልፍ አበርቱኝ በእግዚአብሄር🤲😭😭😭

ምን አይነት ስሜት ውስጥ ሆኜ እንደፃፍኩላችሁ እኔና ፈጣሪ ነን የምናውቀው። እህት ወንድሞቼ እርዱኝ በምክር🤲

https://t.me/+9k2KYUWaftM2OGRk
FASHY

14 Aug, 13:51

391

እናማክራት

https://t.me/+9k2KYUWaftM2OGRk
FASHY

10 Aug, 08:32

497

እንኳን ደስ አለን!

በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ታምራት ቶላ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በወንዶች የማራቶን ውድድር አግኝታለች፡፡

https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0
FASHY

09 Aug, 04:56

499

ይሄን ጥያቄ ሞክሩ

መልሱን በኮሜንት መስጫዉ ላይ ያኑሩ።

https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0