Everest Youth Academy (Kara Kore Branch) @everestyouthacademykara Channel on Telegram

Everest Youth Academy (Kara Kore Branch)

@everestyouthacademykara


Everest Youth Academy (Kara Kore Branch) (English)

Welcome to Everest Youth Academy (Kara Kore Branch), a Telegram channel dedicated to empowering and inspiring young individuals to reach their full potential. Our channel aims to provide a supportive community where youth can engage in meaningful discussions, participate in educational activities, and connect with like-minded individuals. Who is it? Everest Youth Academy (Kara Kore Branch) is a branch of Everest Youth Academy, a renowned institution that focuses on holistic development and academic excellence for young students. The Kara Kore Branch specifically caters to youth in the Kara Kore region, offering a range of educational programs and resources to help them succeed in their personal and academic lives. What is it? Our Telegram channel serves as a platform for young people to access valuable resources, participate in interactive workshops, and engage in discussions on various topics such as leadership, career development, and personal growth. With a team of experienced mentors and educators, Everest Youth Academy (Kara Kore Branch) is dedicated to nurturing the next generation of leaders and change-makers. Join us on Everest Youth Academy (Kara Kore Branch) and be a part of a supportive community that encourages growth, learning, and collaboration. Together, we can empower young individuals to climb the metaphorical Everest of success and make a positive impact on the world. We look forward to welcoming you to our channel and supporting you on your journey to greatness.

Everest Youth Academy (Kara Kore Branch)

21 Nov, 16:02


አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ አገደች
On Nov 21, 2024 48

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ የሚያግደውን ህግ በፓርላማ አፅድቃለች፡፡

በውሳኔው መሰረትም በሀገሪቱ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የቲክቶክ፣ ስናፕ ቻት፣ ፌስቡክ፣ ሬዲት፣ ትዊተር (ኤክስ) እና ኢንስታግራም አካውንት መክፈት አይችሉም፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ታዳጊዎች አካውንት እንዲከፍቱ የሚፈቅዱ ከሆኑ 50 ሚሊየን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት እንደሚጠብቃቸው መንግስት አስጠንቅቋል።

የአውስትራሊያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሚሸል ሮውላንድ÷ በሀገሪቱ ሰፊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ድጋፍ ያገኘው ይህ ውሳኔ የታዳጊዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአውስትራሊያ እድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች ጎጂ ይዘት ያላቸውን ጉዳዮች በማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲመለከቱ እንደነበር አስታውሰው÷ ክልከላው ታዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚደርስባቸውን ጫና ይቀንሳል ብለዋል፡፡

ከአውስትራሊያ አስቀድማ ስፔን ባለፈው ሰኔ ወር ከ14 እስከ 16 ዓመት ያሉ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ መከልከሏ ይታወቃል።

በአሜሪካም በተወሰኑ ግዛቶች ላይ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

Everest Youth Academy (Kara Kore Branch)

20 Nov, 05:03


የክፍለ ከተማው አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ምክንያት በማድረግ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር አካሂዷል።

ህዳር 10/2017 ዓ.ም

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ከክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት በመተባበር "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በአማረኛ እና በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደዋል።

ውድድሩ ያስጀመሩት የተከበሩ አቶ ሚልኪያስ ገበየሁ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ምክትል ዋና አፈ ጉባኤ እንደተናገሩት የዛሬ ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች በመሆናችሁ የፌደራል ስርዓት፣ ህገመንግስትና ህገመንግስታዊነት ዙሪያ የተዘጋጀው ጥያቄና መልስ በአግባቡ ተረድታችሁ በትምህርት ቤታችሁ ለመተግበር ያስችላችኋል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች የትንሿ ኢትዮጵያ መገለጫ በመሆናቸው የበአሉ መከበር እህትማማችነትና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ይረዳል ያሉ ሲሆን በእለቱ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የምስክር ወረቀት በማበርከት በቀጣይም መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው አበረታቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አስመልክቶ የተዘጋጀው የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በትምህርትቤቶችና በወረዳ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን አሸናፊዎቹ በቀጣይ በከተማ ለሚዘጋጀው ውድድር ክፍለ ከተማው ወክሎው እንደሚወዳደሩ ማወቅ ተችለዋል።

🙏🏾ኮልፌ ኮሙኒኬሽን

Everest Youth Academy (Kara Kore Branch)

19 Nov, 10:24


19ኛ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አስመለክቶ በክፍለ ከተማ ደረጃ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በ21 ትምህርት ቤቶች መካከል በተደረገው ውድድር ወረዳ 03 ትምህርት ጽ/ቤት ወክሎ የተወዳደረው ቃልዓብ ደረጀ ከኤቨረስት አካዳሚ 3 ኛ በመውጣት ወረዳውንም ትምህርት ቤቱን በማስጠራት ተሸላሚ ሁኗል
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

Everest Youth Academy (Kara Kore Branch)

15 Nov, 15:19


በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ አቤም ጌቱ የመለያ ጥያቄን ጨምሮ ከቀረቡለት ሰባት ጥያቄዎች ሰባቱንም በመመለስ ከ7D ክፍል አንደኛ ወቶ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል