آخرین پست‌های Ethiopian Media Authority (@ethmediaauth) در تلگرام

پست‌های تلگرام Ethiopian Media Authority

Ethiopian Media Authority
This channel is an official channel of Ethiopian Media Authority (EMA).
EMA is an autonomous government organization accountable to the House of Peoples’ Representatives of the FDRE.
2,967 مشترک
2,533 عکس
137 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 06.03.2025 09:13

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Ethiopian Media Authority در تلگرام

Ethiopian Media Authority

25 Feb, 11:03

524

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  ከዚህ በታች በተመለከቱት የስራ መደቦች ላይ ስራ  ፈላጊዎችን አወዳድሮ  መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በተባለው ጊዜና ቦታ ተገኝታችሁ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡
Ethiopian Media Authority

25 Feb, 05:49

472

ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታችንን ስንጠቀም በሌሎች ላይ ጥላቻ ወይም መድልዎ የሚያስፋፋ ንግግር አለመሆኑን እናረጋግጥ!

#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
Ethiopian Media Authority

24 Feb, 12:19

529

https://youtu.be/04FDXHqV0z8?feature=shared
Ethiopian Media Authority

24 Feb, 07:08

508

ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ የሬዲዮ ሞገድን በመጠቀም የሚሰራጭ የሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፍቃድ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ፡-

1. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራጭ ሲሆን ለ10 ዓመት
2. የሥርጭት ሽፋኑ በክልል ደረጃ የተወሰነ ሲሆን ለ8 ዓመት
3. የሥርጭት ሽፋኑ በአካባቢ ደረጃ የተወሰነ ከሆነ ለ6 ዓመት
4. የማኅበረሰብ ብሮድካስት አገልግሎት ፍቃድ ከሆነ ለ10 ዓመት፤ እና
5. የአጭር ጊዜ የማኅበረሰብ ብሮድካስት አገልግሎት ፍቃድ ከሆነ ለ1 ዓመት ዪሆናል፡፡

#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
Ethiopian Media Authority

21 Feb, 06:38

606

ማንኛውም ሰው ከባለሥልጣኑ የብሮድካስት ፍቃድ ሳይሰጠው ወይም በታገደ ወይም በተሰረዘ ፍቃድ የብሮድካስት አገልግሎት ማሠራጫ መንገዶችን ተጠቅሞ በብሮድካስት አገልግሎት ሥራ ላይ መሰማራት አይችልም፡፡

#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
Ethiopian Media Authority

20 Feb, 12:50

583

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀፅ 48 ንዑስ (1 ) እንደሚያስረዳው ማንኛውም መገናኛ ብዙኃን ተግባሩን ለመወጣት፡-

• ዜና ወይም መረጃን የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት
• በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ወይም ትችት የማቅረብ
• ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን፣ መሣሪያዎችን የመጠቀም እና
• የተለያዩ ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም የሕዝብን አስተያየት በመቅረፅ ሂደት መሳተፍ አለበት፡፡
 
*በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡

#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
Ethiopian Media Authority

20 Feb, 06:00

602

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ የቤተሰብን፣የአካባቢን ብሎም የሀገርን ልማት የሚጎዳ እና ለትዉልድ የማይበጅ አሻራ ነዉ ፡፡

በመሆኑም ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠርና ለመግታት ጥረት ማድረግ አለበት።

 በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡

#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
Ethiopian Media Authority

19 Feb, 07:30

634

የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን በብቃት እና በጥራት በማስፋፋት ለሁሉም ዜጎች መረጃን ተደራሽ ለማድረግ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ ተዘጋጅቶ በትግበራ ላይ ይገኛል፡፡ ፖሊሲውም የሚከተሉት ዋና ዋና ግቦች አሉት፡፡

•  ሁሉም መገናኛ ብዙኃን በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸውን መብትና ግዴታ በመወጣት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ
•  አመኔታና እርካታን ማሳደግ
•  ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት
•  የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም
•  ሀገራዊ ባህልና እሴትን ማጠናከር ናቸው፡፡
Ethiopian Media Authority

18 Feb, 11:00

602

የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን በመቃወምና በማጋለጥ ከጥላቻ የጸዳች ሀገር እንገንባ!

የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ለሀገራዊ አንድነትና መረጋጋት፣ ለዜጎች ደህንነት እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፈተና  ሆነዋል። በመሆኑም የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን በማጋለጥና በመቃወም የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡

#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
Ethiopian Media Authority

18 Feb, 05:59

561

ያለክፍያ ስለሚሰጡ ቅጅዎች

ማንኛውም ሀገር አቀፍ ሥርጭት ያለው በየጊዜው የሚወጣ ህትመት አሳታሚ ህትመቱ ታትሞ ከወጣ ከ5 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የእያንዳንዱን  እትም 2 ቅጂዎች ያለ ክፍያ ለብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ መስጠት አለበት፡፡

በአንድ ክልል ውስጥ ብቻ የሚሰራጭ በየጊዜው የሚወጣ ህትመት አሳታሚ ህትመቱ ታትሞ ከወጣ ከ5 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የእያንዳንዱን እትም 2 ቅጂዎች ያለ ክፍያ ለክልሉ ቤተ-መዛግብት ወይም ለሚመለከተው ቢሮ መስጠት አለበት፡፡

#ብቁመገናኛብዙኃንለማህበረሰባዊንቃት