🙏🙏🙏
የፍቅር ሽኝት የተደረገለት ፖሊስ
Inbox ሰላም ሰላም ጉርሻዎች በዱባ ሞት ይህን ቅን የፖሊስ አባል አመስግነን ሸኝተናል ጉርሻዎች የኛም ድምፅ በሆነው ገፃችንና ገፃችሁ እናንተም አመስግኑልን።
በትላንትና ዕለት የዌራ ዲጆ ወረዳ ወጣቶች ባለፉት አምስት አመታት በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በፖሊስነትና በፖሊስ አዛዥነት የመራውንና ሰሞኑን በስራ አስፈላጊነት ወደ ዞን ለሄደው ረዳት ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ ስጦታና ሽኝት ተደርጎለታል።
ይህ ፖሊስ ወረዳውን በፖሊስ አባልነትና በዋና አዛዥነት ባገለገለባቸው ጊዜያት
* ለአባቶች
* ለእናቶች
* ለሴት እህቶች
* ለወንድሞች
በቃ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍፁም አስተዋይና ለሁሉም የሚተናነስ ስናገር በአዳብ ሆኖ ህግን በግድ ሳይሆን በፍቅር በማስተማር ህዝብ ልብ ውስጥ መግባት የቻለ ሰው ነው።
ባለፉት አምስት አመታት ፍፁም በሆነ ቅንነትና ታማኝነት፣ በመተናነስ፣ ውብ ስነ ምግባርን በመላበስ በወረዳው በፖሊስ አዛዥነትና በፖሊስ አባልነት ለመራው ለረዳት ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ የምስጋና፣ የመልካም የስራ ጊዜና ሽኝት ፕሮግራም ተካሂዷል።
በዛሬው ዕለት ለሱ ይገባል ይመጥነዋል ባንልም ካለን ላይ ቀንሰን ትንሽዬ ስጦታ በማዘጋጀት ከወረዳው ቅን ወጣቶች ጋር በመሆን የክብር እንግዶች በተገኙበት ሸኝተነዋል።
ረዳት ኢንስፔክተር ሁሲ አንተ ቅን ሰው
መልካም የስራ ጊዜ ይሁንልህ!!!
የአካባቢው ወጣቶች
🙏🙏🙏