የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሚመሩት መንግስት ጦር ማምሻውን በምክትላቸው ሪክ ማቻር መኖሪያ ቤት ከበባ በማድረግ የቁም እስረኛ እንዳደረጋቸው ከስፍራው የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
እስካሁን ለማቻር ቅርበት አላቸው የተባሉ ሶስት ሚንስትሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። መንግስት እርምጃውን የወሰደው ለማቻር ታማኝ ነው የተባለ ታጣቂ ቡድን በላይኛው ናይል ግዛት በሚገኝ የመንግስት የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሶ ከተቆጣጠረ በኋላ ነው። በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንትና በምክትላቸው መካከል ከአስራ ሁለት አመት በላይ የዘለቀ ተደጋጋሚ ውጊያ ያደረጉና ለሚሊዮኖች ሞትና መፈናቀል ሰበብ ናቸው።
Image: Pope Francis literally begs for peace at retreat for South Sudan leaders, April 11, 2019, CNS photo/Vatican Media via Reuters