ፕሮጀክቱ ከተማዋን በሁለገብ ዲጂታል ሶሉሽኖች ለማዘመን ያለመ ሲሆን፣ የክላውድ መሰረተ ልማትን፣ የጥሪ ማዕከልን፣ ጠንካራ የመረጃ ማዕከልን፣ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት ያለው ኢንተርኔትን፣ የላቀ የሲሲቲቪ ደህንነት ካሜራ ሲስተምን፣ የኦፕቲካል ፋይበር እንዲሁም ሌሎች የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ያካትታል።
ስምምነቱ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን ጨምሮ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በትራንስፖርት፣ ግብር የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማዘመን ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ከመሆኑም ባሻገር እጅግ ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን ዕውን በማድረግ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ህይወት ቀላል ያደርጋል።
ጅማ ለቱሪዝም ቀዳሚ መዳረሻነት፣ ለኮንፈረንስ፣ ለኢንዱስትሪ እና ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ተመራጭ እንድትሆን የሚያስችላትን አቅም በማጎልበት ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድግ ሲሆን፣ ይህም የንግድ እንቅስቃሴን በማነቃቃት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያሳድጋል።
የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ (ሲቲኔት)፣ አዳማ፣ ሸገር ሲቲ፣ ሐረር፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ባህር ዳር የመጀመሪያውን ምዕራፍ በስኬት የተገበርን ሲሆን በጅግጅጋ ከተማ በትግበራ ሂደት እንዲሁም ከሌሎች ከተሞች አስተዳደሮች ጋር በውይይት ላይ እንገኛለን።
#Jimma #SmartCity #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia