Últimas publicaciones de Ethio telecom (@ethio_telecom) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Ethio telecom  

Ethio telecom
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
335,074 Suscriptores
6,383 Fotos
115 Videos
Última Actualización 01.03.2025 04:18

Canales Similares

telebirr
275,035 Suscriptores
Soccer Ethiopia
87,453 Suscriptores
DW Amharic
56,760 Suscriptores

El contenido más reciente compartido por Ethio telecom en Telegram


ኩባንያችን የድርጅቶችን አሰራር እና የአገልግሎት አሰጣጥ የሚያሻሽሉ ሶሉሽኖችን አቅርቧል!

"የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት" የተሰኘው ሶሉሽን የድርጅት ደንበኞች ስራዎችን በሲስተም በማቀናጀት እና የግንኙነት መድረክን በማመቻቸት የቡድን ትብብር እና ቅልጥፍናን ማሳደግ የሚያስችል ነው።

እንዲሁም "ቴሌ የደንበኞች ማዕከል" ሶሉሽን የድምጽ ጥሪ፣ የጽሑፍ መልዕክትና የማህበራዊ ሚዲያ መልእክቶችን በአንድ መድረክ በራስ ሰር በማቅረብ ከደንበኞች ጋር የተቀላጠፈ ግንኙነት ያስችላል።

ኩባንያችን ያቀረበው "የኢ.አር.ፒ ሶሉሽን" ደግሞ የድርጅት ደንበኞች የፋይናንስ፣ የሰው ኃይል እና የአቅርቦት ሰንሰለት አሰራራቸውን በዲጂታል በማቀናጀት የአሰራር ቅልጥፍና እና ዘላቂ ዕድገት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል አማራጭ ነው።

ሶሉሽኖቹ ድርጅቶችና ተቋማት በኩባንያችን ግዙፍ የክላውድ መሰረተ ልማት በመጠቀም ጊዜና ሃብታቸውን በመቆጠብ በዋና ሥራቸው ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ ውጤታማነታቸውን ለመጨመር ያለሙ ናቸው።

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG ያንብቡ!

🎉🏆 የአድዋ ድል በዓል ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር!!

የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን የሚያሸልም ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር አዘጋጅተናል!

🌐 የማኅበራዊ ገጾቻችንን ይከተሉ ለሌሎች ያጋሩ https://bit.ly/4aLCQVO

🗓 ነገ ቅዳሜ ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ ይጠብቁን!


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

🎁 የአካል ጉዳተኞች የሞባይል ጥቅል!!

ከመደበኛ ጥቅል እስከ 35% በሚደርስ ታላቅ ቅናሽ የቀረቡትን ልዩ ጥቅሎች በ *999# ወይም 999 በመደወል ያገኟቸዋል፡፡

👉 ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ሲገዙ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር!

🚨 ጥቅሎቹን መግዛት የሚችሉት ከአካል ጉዳተኞች ማኅበር በተላከልንን ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ብቻ ሲሆኑ መግዛት ያልቻሉ ደንበኞች አቅራቢያቸው በሚገኝ የማኅበሩ ቅርንጫፍ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማንኛውም ሰው ጥቅሎቹን ለተመዘገበ የማኅበሩ አባል መግዛትና በስጦታ መላክ ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/4b0vFub


#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia

የካቲትን ለወደቁትን አንሱ!!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለወደቁትን አንሱ የነዳያን በጎ አድራጎት ማኅበር እንለግሳለን!

🤝 እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን | ዩትዩብ | ቲክቶክ

በተጨማሪም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ለበጎ አድራጎት በሚለው አማራጭ የፈቀዱትን የገንዘብ መጠን በመለገስ ለወገንዎ ተስፋ ይሁኑ!

🙏 ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!


#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

የትምህርት ተቋማት አሰራርን የሚያዘምን ዲጂታል የትምህርት አስተዳደር ሶሉሽን ይፋ አድርገናል!

ይህ በክላውድ የተደገፈ ሶሉሽን ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የትምህርት ተቋማት አስተዳደርን፣ መምህራንን፣ ተማሪዎችን እና ወላጆችን በዲጂታል ፕላትፎርም በማስተሳሰር ጠንካራ የትምህርት ተቋም ማህበረሰብ ለመገንባት ያስችላል፡፡

ሶሉሽኑ የተማሪዎችን ውጤት ክትትል፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የተማሪ-ወላጅ-መምህር ተሳትፎን በማጎልበት እንዲሁም የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት በማቅረብ የትምህርትን ጥራት በእጅጉ ለማሳደግ ያግዛል።

በተጨማሪም፣ ሶሉሽኑ የክፍያ ሂደቶችን በቴሌብር በማቀናጀት የወላጆችን ጊዜና ጉልበት ይቆጥባል፤ የትምህርት ተቋማትን አስተዳደራዊ ቅልጥፍና ያሳድጋል።

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia

https://youtu.be/Utwzkf32XKI

የቀድሞ ኦፕሬተራችን በሞርስ ኮድ እና ቴሌፕሪንተር አማካኝነት የቴሌግራፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ!

1960ዎቹ መጀመሪያ
ጎንደር


#ትውስታ
#throwbackthursday
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

ለፋይናንስ ተቋማት አዲስ በክላውድ ላይ የተመሰረተ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ይፋ አድርገናል!

ኩባንያችን የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን እና የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራትን በዘመናዊ የዲጂታል ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ለማስታጠቅ የሚያስችል የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ሶሉሽኑ የፋይናንስ ተቋማት አሰራራቸውን በማቀላጠፍ፣ የደንበኛ ተሞክሮን በማሻሻል እና አገልግሎታቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ክላውድ አማካኝነት ለብዙኃን ተደራሽ በማድረግ፣ የመሠረተ ልማት ወጪዎችን እንዲቀንሱ ያስችላቸዋል።

ኩባንያችን አስተማማኝ የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን በማቅረብ የፋይናንስ ተቋማት ደንበኞቻቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያገለግሉ እና በሀገራችን የፋይናንስ አካታችነት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia #DigitalAfrica

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ጂ ኔትወርክ ማስፋፊያ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በደሴና በኮምቦልቻ ከተሞች አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡

ይህ ኩባንያችን የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያደርገው ሀገራዊ ጥረት አካል ሲሆን፣ የላቀ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት በማዳረስ ለአዳዲስ ፈጠራዎችና ኢኮኖሚያዊ የዕድገት ዕድሎች በር ለመክፈት ያስችላል።

በደሴ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ፣ ሉሲ ሆቴልና ደሴ ሙዚየም አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡

በኮምቦልቻ ደግሞ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡

አገልግሎቱ አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኦንላይን ትምህርት፣ ለጀማሪ የንግድ ተቋማት ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ የስማርት ስልክ አቅርቦት ለማሳደግና ዲጂታል ክህሎትን ለመጨመር ያስችላል።

5ጂ የግል እና የመንግስት ተቋማትን አሰራር ያዘምናል፤ እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ማኑፋክቸሪንግን፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝምን የመሳሰሉ ቁልፍ ዘርፎችን በማዘመን ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

በአዲስ አበባ በ2022 እ.ኤ.አ ያስጀመርነው 5ጂ ደሴ እና ኮምቦልቻን ጨምሮ በ14 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ፣ ቢሾፍቱና ጅማ አገልግሎት ላይ ውሏል።

ክቡራን ደንበኞቻችን፣ የ5ጂ አገልግሎት ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም በአገልግሎት ማእከላችን በማግኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዛለን፡፡

ለተጨማሪ፡- https://bit.ly/3F2QyJe

🌟 በቴሌብር ሲቀበሉ ተጨማሪ 5% የገንዘብ ስጦታ ያገኛ!!

🌐 ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ ከዕለታዊ የምንዛሬ ተመን በተጨማሪ 5% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

🗓 እስከ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia