Dirilis Ertugrul Ethiopia @ertugrulbeyseries Channel on Telegram

Dirilis Ertugrul Ethiopia

@ertugrulbeyseries


Ιѕℓαм ιѕ σиє ☝️

Dirilis Ertugrul Ethiopia (English)

Welcome to the 'Dirilis Ertugrul Ethiopia' Telegram channel, also known as '@ertugrulbeyseries.' This channel is dedicated to fans of the hit Turkish historical fiction series, 'Dirilis: Ertugrul,' which has gained popularity worldwide, including in Ethiopia. The series follows the journey of Ertugrul, the father of Osman I, the founder of the Ottoman Empire, as he fights against enemies and builds his tribe in the 13th century. If you are a fan of epic battles, courageous heroes, and intricate political intrigue, this channel is the perfect place for you. Stay up to date with the latest episodes, behind-the-scenes insights, cast interviews, and fan theories. Engage with like-minded individuals who share your passion for the show and immerse yourself in the rich history and culture of the Turkish Seljuk Empire. Whether you are a long-time fan of 'Dirilis: Ertugrul' or a newcomer looking to discover this captivating series, 'Dirilis Ertugrul Ethiopia' is the ultimate destination for all things related to the show. Join us today and become part of a vibrant community that celebrates the legacy of Ertugrul and his enduring impact on Turkish and Ethiopian audiences alike. Embrace the spirit of brotherhood, loyalty, and heroism that defines the world of 'Dirilis: Ertugrul.' Islam is one - ☝️.

Dirilis Ertugrul Ethiopia

30 Nov, 17:21


ኦርጅናል ሚኖክሲዲል የምትፈልጉ በፍሬና በብዛት እኛ ጋር ያገኛሉ @royalboyyyyyy ወይም 0967654268

Dirilis Ertugrul Ethiopia

28 Oct, 18:10


Original minoxidil metfelgu @royalboyyyyyy

Dirilis Ertugrul Ethiopia

23 Oct, 13:25


https://youtu.be/Ov5vr_vzY4c?si=PctKbeS4USU9V9EV

Dirilis Ertugrul Ethiopia

09 Oct, 12:17


10 ሺህ ዶላር ሽልማት የተዘጋጀለት Cherry game ሊጠናቀቅ 9 ቀን ብቻ ቀርቷል።

አሁንም invite እና share በማረግ ከ10 ዶላር ጀምሮ ማሸነፍ ትችላላችሁ ።

አሁንም ያልጀመራችሁ ጀምሩ........... Invite ያረጋቹት እንዲቆጠር 3
4 ወይም 5 Task መስራት እንዳትረሱ

https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_930700953 Join the cherry game using this referral link and win prizes!

Dirilis Ertugrul Ethiopia

06 Oct, 11:04


🛒 I'm buying old telegram groups

🔥 ዋጋ ጨምረናል ይፍጠኑ💱

⭐️ 2017 , 2018
🌟 2019 , 2020
⭐️ 2021 , 2022

በነዚ አመት የተከፈተ member 0 ቢሆንም እንገዛለን........ምን አስጨነቃቹ ድሮ ቴሌግራም group ከፍታቹሃል ማለት አሁን ሀብታም ናችሁ ማለት ነው🤩

🔰2023 መግዛት ጀምረናል🔥

ለመሸጥ INBOX ME

       👉 @royalboyyyyyy
       👉 @royalboyyyyyy

Dirilis Ertugrul Ethiopia

03 Oct, 13:17


ታሪኩ እንዲቀጥል ምትፈልጉ share ማድረጋቹን አትርሱ😊😊✌🏾

Dirilis Ertugrul Ethiopia

02 Oct, 12:34


#በርኬ_ኻን_የኢስላማዊው_ስልጣኔ_አዳኝ_የባግዳድ_ደመላሽ !
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
        ( የሞንጎሎች ታሪክ ክፍል -4)
        Seid sicial -ሰኢድ ሶሻል
ዛሬ ፍፁም ወደማትጠብቁት የሞንጎሎች ታሪክ እንሸጋገራለን ። ጄንጊስ ኻን ሞቷል ። ግዛቱን ለአራቱ ልጆቹ ለጆቺ ፣ ቱሉይ ፣ ኦገዳይና ቻጋዳይ አከፋፍሎ ይህችን አለም በንፁሀን ደም አጨቅይቶ ተሰናብቷል ።
ግና የናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ የጂንጊስ ልጆችም ዥንጉርጉር ነበሩ።

በተለይ ጆቺ ከሌሎች ወንድሞቹ ወንድሞቹ የተለየ ነበር ። ልጆቹማ ፍፁም የተለዩ ። ጆቺ የጂንጊስ ኻንን ወረራ መቃወሙን አይተናል። በዚህም ጂንጊስ ኻን በመርዝ እንዳስገደለውም ጭምር ። ጆቺ የሞተው ጂንጊስ ኻን ከመሞቱ ከወራቶች በፊት ነበር።

የኢስላም ብርሃን በጆቺ ልጆች በኩል ወደ ሞንጎሎች ፈነጠቀ ። ከህያዊያን ውስጥ ሙታንን ከሙታንም ውስጥ ህያውያንን የሚያወጣው አላህ ከልበ ድንጋዮቹ ሞንጎሎች ልቡ በእዝነት የተሞላውን በርኬ ኻንን አወጣ ። በርኬ ኻንን በአንድ ቃል እንገለፀው ከተባለ እርሱ የኢስላሙ አለም ደም መላሽ ነው ።
በርኬ የቱርክኛ ቃል ሲሆን ጠንካራ ሀያለኛ እንደማለት ነው ። በርኬ ኻን የጆቺ ልጅ የጂንጊስ ኻንም የልጅ ልጅ ነው!!

በርኬ እስልምናን የተቀበለው በ 1452 ቡኻራ ከተማ እያለ ነበር ። ቡኻራ ከተማ በነበረበት ወቅት የሙስሊም ነጋዴዎችን ስለ እምነታቸው እስልምና ይጠይቃቸዋል ። እነርሱም ኢስላምን አብራሩለት ። የጂንጊስ ኻን የልጅ ልጅ በሰማው ነገር እጅግ ልቡ ተነካ በእስልምና ፍቅርም ተማርኮ ወደቀ ። እናም ሸሃዳን ተቀብሎ ኢስላምን የህይወቱ መስመር አደረገ ።

በርኬ ኻን ኢስላምን ተቀብሎ ብቻ ዝም አላለም ይልቁንስ ከአባቱ ከጆቺ እና ከወንድሙ ባቱ ኻን የተቀበለው የ ኡሉግ ኡሉስ ( Golden Horde ) ኢምፓየር ኦፊሴላዊ ሀይማኖት እንዲሆን አደረገው እንጅ ።Ulug ulus ማለት በቱርክኛ " ታላቁ  ሀገር " እንደማለት ነው ። ባለፈው እንደነገርኳችሁ ጂንጊስ ኻን ከሩሲያና እስከ ምስራቅ አውሮፓ ያለውን ግዛት ለበርኬ አባት ለጆቺ ሰጥቶት ነበር ። እና Golden Horde ኢስላማዊ ኢምፓየር ሆነ ።

በርኬ ኻን ኢስላምን በተቀበለ በ 6 ኛ አመቱ የአጎቱ ልጅ የሆነው ሁላጉ ኻን ባግዳድን አወደማት ። የአባሲዱን ኸሊፋ አልሙስተእሲም ቢላህን በግድያ ቀጣው ። በዚህ የሁላጉ ኻን ድርጊት በርኬ ኻን እጅግ ተናደደ ! ሁላጉ የኢስላማዊው አለም ብቻ ሳይሆን የመላው አለም ብረሃን የነበረችውን ባግዳድን ወደ መቃብርነት የጤግሮስ ወንዝንም ወደ ቀይ የደም ጅረት እንደቀረው በሰማ ጊዜ በርኬ በብስጭት ጬሰ ። እናም እንደዚህ አለ " በአላህ ፈቃድ በሙስሊሞች ላይ ለፈፀመው ግፍ ሁሉ እተሳሰበዋለሁ ይህንንም ፊት ለፊት ተጋፍጬ ዋጋውን አስከፍለዋለሁ " በማለት ዛተ ። በርኬ ኻን ቀደም ብሎ ሁላጎ ባግዳድን ሳይወር በፊት ለአቃውና ለወንድሙ ለሞንግኬ ደብዳቤ ፅፎ ወረራውን እንዲያስቆም ጠይቆት ነበር  ። ግና የበርኬ ደብዳቤ ሲደርስ ሞንኬ ሞቶ ነበር።

ሁላጉ ኻን የቱሉይ ልጅ ነው ቱሉይ ደግሞ የጂንጊስ ። በርኬ የጆቺ ልጅ ነው ጆቺ ደግሞ የጂነሰጊስ ። ስለዚህ ጂንጊስ ኻን ለበርኬም ሆነ ለሁላጉ አያታቸው ነው ማለት ነው ።
ሁላጉ ኻን ባግዳድን ካወደመ በሗላ ቀጣይ ኢላማው መላው ሙስሊም አለምን ማንበርከክ የኢስላም ቅዱስ ከተሞችን ሁሉ ማውደም ነበረ ። ከባግዳድ በሗላ የሁላጉ ኢላማዎች መካ ፣ መድና ፣ ቁድስ ( ኢየሩሳሌም ) ፣ ካይሮ እንድሁም ደማስቆ የመሳሰሉ ከተሞች ነበሩ ። በዚህም ወደ ደማስቆ አምርቶ ሶሪያን በቅፅበት በእፍኙ ውስጥ አስገባት ። ከዚያም ግብፅ ቀጣይዋ ኢላማ ሆነች ። ወደ ግብፅ እገሰገሰ እያለ የኻኑ የሞንግኬ ሞት ተነገረውና ወደ ሞንጎሎች ዋና ከተማ ካራኮረም ተመለሰ ። የጦር መሪውን 20,000 ጦሩን እየመራ ግብፅን እንዲቆጣጠር ትእዛዝ ሰጥቶ ሁላጎ ወደ ሞንጎል እምርት አቀና ። ይሁን እንጅ ግብፅና ሶሪያን የሚያስተዳድረው የቱርኮቹ ማምሉክ ሱልጧኔት በአይን ጃሉት ጦርነት የሞንጎልን ጦር ደመሰሰው ። ሁላጉ ኻን ሞንጎሊያ እያለ የሽንፈት መርዶው ደረሰው ። በዚህም በመቶሺህ የሚቆጠር የሞንጎል ሰራዊቱን እየመራ ኢስላሙን አለም ሰልቅጦ ሊውጥ ጉዞውን ጀመረ።

በዚህ ጊዜ ነበር የአጎቱ ልጅ በርኬ ኻን ሁላጉን ለኔ ተውልኝ በማለት " ና ወንድ ከሆንክ እኔን ግጠመኝ እጠብቅሃለሁ " በማለት ለሁላጉ መልእክት የላከበት ። በርኬ ኻን ከሙስሊም መሪዎች ጋር በተለይም ከማምሉክ ጋር ወዳጅነት መስርቶ የሞንጎል ወረራን ለመመከት ተስማማ።

በአርቱግሩል ፊልም ላይ እንዳያችሁት የካይ ጉሳዎችን ጨምሮ የተለያዩ የቱርክ ጎሳዎች ጋር ውህደት ፈጥሮ የሞንጎል ሰራዊትን ተፋለመ።

የበርኬ ኻንን የግጠመኝ መልእክት የሰማውና በዚህም ክፉኛ የተደናገጠው ሁላጉ ኻን የኢስላም ከተሞችን ማፈራረሱን ትቶ ወደ በርኬ ጦሩን አዞረ። ከዚያ በሗላማ ሞንጎል ለሞንጎል እርስበርሱ በሰይፍ ተሞሸላለቀ ።

በሁለቱ ጦርነት የሁላጉ ኻን ጦር ተሰበረ ። ሁላጉም ከበርኬ የደረሰበትን ምት መቋቋም ተስኖት ወደ አዘርባጃን ሸሼ። ከዚያም ወደ ሗላ እያፈገፈገ እያለ በሽሽት ላይ ህይወቱ አለፈ ።
በርኬ ኻን የባግዳድን ደም ተበቀለ !
በርኬ ኻን የኢስላም ከተሞችን ከውድመት ታደጋቸው!
በርኬ ኻን ኢስላማዊውን ስልጣኔ ከጨርሶ መጥፋት ታደገው !
የሞንጎሎችን ውድመት የታደገው ሌላ ሳይሆን ሞንጎሏዊው ጀግና በርኬ ኻን ነው!

በርኬ ኻን ከሞንጎሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ኢስላምን የተቀበለ የምንጎል መሪ ነው ። በርኬ ኻን የሰልጁቅ ሱልጧኔትን ከውድቀት ለመታደግ የተቻለውን ሁሉ አድርጓል ። ሱልጧን ኢዘዲን ካይካውስን ከአርቱግሩል ጋር በማበር ከሞንጎሎችና ከባይዛንታይኖች ምርኮኝነት አድኗል ። የአርቱግሩልን ፊልም አስታወሱ! 

በርኬ ኻን ከተንግሪዝም ወጥቶ ኢስላምን ሲያገለል ስለ ኢስላምም ሲጋደል ኖሮ በሁላጉ ኻን መሞት ከወራቶች በሗላ እርሱም ጌታውን ተገናኘ። በርኬ ኢስላምን ተቀብሎ ኢስላምን በሞንጎሎች ተክሎ አለፈ ። ከበርኬ በሗላ የእርሱ መንግስት ሞንጎሎች በሙሉ ኢስላምን ተቀብሎ ። መንግስቱም ከሞንጎሏዊነት ይልቅ ቱርካዊ ነኝ አለ ። የበርኬ ግዛት ከሳይቤሪያ እስከ ፖላንድ  ይለጠጣል። በርኬ ፖላንድን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ አንበርክኮ ገዝቷታል ።

በርኬ እንደዚህ አይነት ጀግና ነበረ ። ከጂንጊስ ኻን ልጆች ህልፈት በሗላ አብዛኛው ሞንጎሎች ቱርካዊ ሆነዋል ። ከሀይማኖት እሰከ ቋንቋ ከዚያም እስከ ባህል ወደ ቱርካዊነት ተቀይረዋል።

ከዚህ በሗላ ስለ ሞንግሎች የምፅፈው ስለ ቲሚር ኻን ( ታመርሌን ) እና ስለ ባቡር ኻን ወይንም እርሱ ስለመሰረተው ስለ ሙጋል ኢምፓየር ይሆናል ።
የሞንጎሎች መጨረሻ ምን ሆነ ? አሁንስ የት ናቸው ? ምን ያክልስ ናቸው ? በምንስ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ? ወዘተ በመጨረሻ ፅሁፌ ይጠብቁኝ!

#Share

#ታሪክ_በኢስላም
ቴሌግራም
             @ertugrulbeyseries

Dirilis Ertugrul Ethiopia

20 Sep, 04:26


#የጄንጊስ_ኻን_የመጨረሻ_ዘመናት
አሰገራሚው የሞንጎሎች ታሪክ
------------------------------------------------------
      (  Seid Social - ሰኢድ ሶሻል )
               ክፍል - 3

በክፍል አንድ እና ሁለት ፅሁፎቼ ሞንጎሎች ከጂንጊስ ኻን በፊትና በጂንጊስ ኻን የዘመን መባቻ ምን አይነት ታሪክ እንዳላቸው አስቃኝቻችሗለሁ ። ዛሬ ደግሞ የጂንጊስ ኻን የመጨረሻ ዘመናትና የልጆቹን የነ ኦገዳይ ኻን መባቻን እንመለከታለን ።

ጄንጊስ ኻን ቻይናን አንበርክኮ በአቅራቢያ የሚገኙትን የቃራ ኻኒድ ኡይጉር የመሳሰሉ የቱርክ ስርወ መንግስታትን አጠቃሎ እጅግ ትልቅ በታሪክ ተወዳዳሪ አልባውን የሞንጎል ኢምፓየር እንደመሰረተ አይተናል ። ጄንጊስ ኻን የኸዋሪዝም ሙስሊም ሱልጧኔትን ወርሮ እነ ቡኻራ ሰመርቀንድና ኡርጌንችን አውድሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃንን ጨፍጭፎ የአሁኖቹን ኢራንን አፍጋኒስታንን ኡዝቤኪስታንን አዘርባጃንን ካዛኽስታንን ተቆጣጥሮ የግዛት ማስፋፋቱን ወደ ምእራቡ አለም እንዳዞረ አይተናል።

ጂንጊስ ኻን የሙስሊም ከተሞችን ከተቆጣጠረ በሗላ የተወው ነገር አልነበረም ሁሉንም አወደመ ሁሉንም አጠፋ ። እኔ ወደ በሃጢያታችሁ ምክንያት የተላኩ የፈጣሪ ቅጣት ነኝ እያለ የምድር አዛብን አቀመሳቸው። በርግጥም ቺንጊስ ኻን የፈጣሪ ቅጣት ነበረ!!

ጄንጊስ ኻን የሙስሊም ግዛቶችን ከተቆጣጠረ በሗላ ፊቱን ወደ አውሮፓዊያን አዞረ ። የምስራቅ ኦርቶዶክስ ሀያላን ኢምፓየሮችን ተራ በተራ እየገጠመ ሁሉንም ደመሰሳቸው ።

በ 1220 አርሜኒያን በቁጥጥሩ ስር አስገባትና የሞንጎል ግዛት አደረጋት ። ከዚያም ጉዞውን ወደ ሩሲያ አደረገ ። ሩሲያን ያንበረክኩ ዘንዳ   ሱቡታይን እና ጄቤን ላካቸው ። እነርሱም አላሳፈሩትም ። ሩሲያን በሙሉ ተቆጣጥረው ሞስኮ ላይ ነገሱ ። ሞስኮ የሞንጎሎች ከተማ ሆነች ።

በጃንጊስ ኻን የሚመራው ጦር ወደ አፍጋኒስታን አቅጣጫ ዞሮ መላው የመካከለኛው ኤሲያን እስከ አሁኖቹ ፓኪስታንና ህንድ በቁጥጥሩ ስር አስገባ። የጆርጂያ ኪንግደም የሞንጎሎችን ወረራ መቋቋም ተስኖት ፈራረሰ ። ክራይሚያ በሞንጎሎች እጅ ወደቀች ። ዩክሬይን ወደመች ዋና ከተማዋ ኬቭን ሞንጎሎች ፈነጩባት ። ቡልጋሪያ ከሞንጎሎች ቅጣት አላመለጠችም ። "የእግዚአብሔር ቅጣት " በላያቸው ላይ ወረደ ። የጂንጊስ ኻን ወረራ ሃንጋሪን አሰጨንቆ ያዛት።

ምስራቅ አውሮፓ በጂንጊስ ኻን ቁጥጥር ስር ገባች ። አብዛኛውን የተቆጣጠራቸውን የሙስሊሞችም ሆነ የኦርቶዶክስ ከተሞች ከ 50% በላይ የሚሆነውን ህዝባቸውን አውድሟል ። ጂንጊስ ኻን የገባባት ከተማ በዜጎች የደም ጎርፍ ትታጠባለች ፤ በወደሙት በተቃጠሉት ግንባታዎቿ ትጨልማለች ! ጄንጊስ ኻን በርግጥ ተወዳዳሪ አልባው ጭራቅ ነበረ!

አሁን የሞንጎል ኢምፓየር ተወዳዳሪ አልባ ሆኗል ። ከ ኮሪያ ተነስቶ እስከ ምስራቅ አውሮፓ ያለው በጣም ግዙፉ የአለማችን ክፌል የሞንጎሎች ግዛት ሆኗል ግማሹ የአውሮፓ ክፍል የሞንጎሎች ግዛት ነበረ ። እነ ሞስኮ ፣ ቤይጂንግ ፣ ተብሪዝ ፣ ቡኻራ ፣ ኬቭ ፣ ሰመርቀንድ ፣ ኧረ ስንቱ የሞንጎሎች ከተማ ሆነዋል ። ከቻይና ባህር እስከ ካስፒያን ባህር ፤ ከሜድትራኒያን ጫፍ እስከ ጥቁር ባህር የሞንጎሎች የጂንጊስ ኻን ግዛት ነበረ ።
በአለማችን ላይ የሞንጎል ኢምፓየርን ያክል እጅግ ግዙፍ ኢምፓየር ተመስርቶ አያውቅም ። የጂንጊስ ኻን ግዛት ከታላቁ አሌክሳንደር ( Alexander the Great ) ግዛት አራት እጥፍ ከታላቁ የሮማን ኢምፓየር ሁለት እጥፍ ይልቅ ነበረ። ቺንጊስ ኻን እንድህ አይነት ሀያል መሪ ነበረ።

ጂንጊስ ኻን በዋናነት እንደህጋዊ ልጆቹ የሚያቸው አራት ልጆች ነበሩት ። እነዚያ ልጆቹ ጆቺ ፣ ቻጋታ(ዳ)ይ ፣ ኦገዳይና ቶሉይ ይባላሉ ። እናም እርጅና ሲጫጬነውና የመጨረሻ ዘመኑ ሲቃረብ ስልጣኑን ማውረስ እንዳለበት አሰበ ። ይሁን እንጅ ለአንዱ ልጅ ብቻ ስልጣኑን ቢያወርስ ከፍተኛ የስልጣን ውዝግብ ተነስቶ ሁሉን ነገር ሰውቶ የገነባው ሀያል ኢምፓየሩ እንዳይፈርስበት ፈራ ። ስለዚህ ግዛቱን ለአራት ልጆቹ ለማከፋፈል ወሰነ ። አራቱም ኻን እንዲሆኑ መረጠ ። ኻን ቃሉ ቱርክኛ ሲሆን በፐርሺያ ሻህ በሮሞች ደግሞ ቄሳር እንደማለት ነው ።

በተለይም ደግሞ ሁለተኛው ልጁ ቻጋዳይ ታላቅ ወንድሙ ጆቺ የጂንጊስ አልጋወራሽ የሚሆን ከሆነ ወደ ጦርነት ይገባል እንጅ እንደማይቀበለው አሳወቀ ። በዚህ ጊዜ ጂንጊስ አራቱንም አከፋፍሎ የእርሱ ተተኪ ግን #ኦገዳይ_ኻን መሆኑን አወጀ።
በዚህም መሰረት
1 ጆቺ ኻን :- ከሳይቤሪያ አንስቶ መላው ሩሲያን እስከ ምስራቅ አውሮፓ እንዲያስተዳድር ተሰጠው
2 ቻጋዳይ ኻን ፦ ምእራብ ቱርኪስታንን እንዲያስተዳድር ተሰጠው
3 ኡገዳይ ኻን ፦ ማእከላዊ ሞንጎሊያን እንዲያስተዳድር ተሰጠው
4 ቶሉይ ፦ ምስራቅ ሞንጎሊያን እንዲያስተዳድር ተሰጠው።

ነገር ግን በጣም ለምና የበለፀጉ የሆኑት ቻይና እና ኢራን በዋናው ኻን ውስጥ እንዲካተቱ ስለተደረጉ ኦገዳይ ኻን እንዲያስተዳድራቸው ሆነ ። የሁሉም የበላይ ኻንም ኡገዳይ ኻን ነው።

ጆቺ ብዙ ሳይቆይ ተመርዞ ሞተ ። በመርዝ ያስገደለውም አባቱ ጄንጊስ ኻን ነው ይባላል ። በተለይ ጆቺ አባቱ በሙስሊም ከተሞች ላይ የፈፀመውን ሰቅጣጭ ውድመት በጣም አብዝቶ ያወግዝ ነበር ። እንደውም አንድ ጊዜ "ጂንጊስ ኻን እብድ ሰው ነው! ምነው አባቴን አደን ላይ እንዳለ ገድየው በነበረ ኖሮ ከዚያም ከሙስሊሞች ጋር አንድ ላይ ተዋህጄ ከሱልጧን ሙሀመድ ጋር አብሬ በነበርኩ ! ምነው ይህችን ምድር ህይወት ዘርቸባት በነበር ምነው ሙስሊሞችን መርዳት ችየ በነበር " በማለት ጆቺ መናገሩ ተሰማ ። ይህንን የሰማው ጄንጊስ ኻንም ልጁን በድብቅ አስገደለ።

ከዚህ በሗላ ነው የሞንጎሎች ታሪክ ፍፁም እየተለወጠ የመጣው ። ከዚህ በሗላ ስለሞንጎሎች የምነግራችሁ ታሪክ ጣፋጭም መራራም ነው ! እነርሱው ጣፋጭ እነርሱው መራራም ናቸው !! በተለይ ከጆቺ የሚመዘዘውን የሞንጎሎች ትውልድ ስነግራችሁ ልባችሁ በሀሴት ይሞላል !በቀጣይ ፅሁፍ ጠብቁኝ !
ለማጠቃለያ የጂንጊስ ኻንን በጣን አሰገራሚ ነገሮች ነግሪያችሁ ላብቃ!

1 ጂንጊስ ኻን ከሁሉም ነገር ውሻን አብዝቶ ይፈራል

2 ጄንጊስ ኻን 40 ሚሊዮን የአለማችን ህዝብን በመግደል በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ሰው ነው ። ያ ማለት በጊዜው ከነበረው የአለማችን ህዝብ ውስጥ 11% የሚሆነው በቺንጊስ ኻን ተገድሏል።

3 ጂንጊስ ኻን ወንድሙንም ልጁንም የገደለ መሪ ነው ። ወንድሙን ቤግተርን በቀስት ሲገድል ልጁን ጆቺን ደግሞ በመርዝ አስገድሏል ።

4 ጂንጊስ ኻን በጣም ሲበዛ ሴሰኛ ነበር ። እርሱ ወሮ ያልወሰዳት የንግስት ልጅ የለችም። ያሉት ልጆች ተቆጥረው አይዘለቁም። ያሉትም እቁባቶች እንደዚያው ።

5 በአሁኑ ሰአት ከ 200 ሰዎች አንዱ የጂንጊስ ኻን DNA አለበት ። ያ ማለት በናንተ ውስጥ የጂንጋስ ኻን ዝርያ ሊኖር ይችላል
6 ከጂንጊስ ኻን በፊት ሞንጎሎች ማንበብም በፃፍም አይችሉም ። ጂንጊስ ኻን ነው የኢይጉር ፊደሎችን በመውሰድ ሞንጎሎች መፃፍ እንዲችሉ ያደረገው ። ኢይጉሮች የዛሬን አያድርገውና በምስራቁ ተወዳዳሪ የሌላቸው የስልጣኔ ቁንጮዎች ነበሩ ።

ግን ግን ስለሞንጎሎች የምፅፈው ቀጣዩ ታሪካቸው እንዳያመልጣችሁ ። ለዛሬው በዚሁ ይብቃን ። ወሏሁ አእለም!

#Sዘare

🛡 @Ertugrulbeyseries

Dirilis Ertugrul Ethiopia

17 Sep, 19:14


ተቀየረች ። የአለም ስልጡኗ ሀብታሟ ሀያሏ ሀገር ቻይና ለጂንጊስ እጇን ሰጠች ። ቻይና ፈራረሰች ። ይህንን አይቶ መኖር ከመሞት የከፋ መሆኑን ያመነው የቻይናው ንጉስ ራሱን በሰይፉ ገደለ። ጄንጊስን ገብር ያለች ቻይና ግብሯ መቃብር ሆነ ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቻይናዊያን በጄንጊስ የሞት መላእከተኞች ተቀጠፉ ተቃጠሉ ። ጄንጊስ ይህንን ያደረገው በ 1214 ነበር ። ቻይና የሞንጎል ግዛት ሆነች።

ይህ ጦርነት ካለቀ ከ 5 አመት በሗላ ጄንጊስ ኻን ለሌላ እጅግ ከባድ ጦርነት ተዘጋጀ ያ ጦርነቱ ከሙስሊሙ የኸዋሪዝም ሱልጧኔት ጋር የተደረገው እጅግ አስከፊው ጦርነት ነበረ ።

የኸዋሪዝም ሱልጧኔት ከጄንጊስ ኻን ጋር የንግድ ስምምነት አድርገው ነበር። ይሁን እንጅ ለንግድ ወደ ሞንጎሊያ የሄዱት ሙስሊም የኸዋርዚም ነጋዴዎች ንብረታቸው ተዘርፎ ተገደሉ ። ይህንን ጉዳይ በውይይት ለመፍታት ጄንጊስ ኻን ሶስት አምባሳደሮችን ለኸዋርዚሙ ሱልጧን  ሻህ አላኡዲን ሙሀመድ ላከ። በሁኔታው የተበሳጨው ሲልጧኑ በጣም የጄንጊስ ኻን አምባሳደሮች እንዲገደሉ አደረገ ። ሙስሊሙን አምባሳደር አንገቱን ቆርጦ ለጄንጊስ ኻን ላከለት ። ሁለቱ ሀያላን ወደ ጦርነት ገቡ ። በአምባሳደሮቹ መገደል ወስጡ የነደደው አስፈሪው የጭካኔ አምባሳደር እጅግ ጨካኝ ወታደሮቹን ማንም በማያስብበት በረሃ ለበረሃ እያጓጓዘ ጦሩን ለሶስት ጎራ ከፍሎ የኸዋርዚም ሲልጧኔትን ወረረ። ኸዋርዚም በጊዜ ከካስፓያን ባህር እስከ ፐርሺያ ባህረ ሰላጤ የሚያስተዳድር ሀያል የሙስሊም መንግስት ነበር ። እና ቱርክሜኒስታን ኡዝቤኪስታን አፍጋኒስታን ኢራንን የመሳሰሉ የአሁኖቹ ሀገራት በኸዋሪዝም ሱልጧኔት ስር ነበሩ።
ጄንጊስ ኻን ወደ ኸዋርዚም ያዘመተው ሰራዊት 100,000 ነበረ ። በሶስት ጎራ ከፍሎ ሱልጧኔቱን ሲወር የሱልጧኑ ጦር ለበርካታ ግንባሮች ተከፍሎ በተለያየ አቅጣጫ የሞንጎሎችን ወረራ ለመከላከል ተበታተነ ። በዚህ ጊዜ ሞንጎሎች በጣም ተመቻቸው ። የተበታቱነውን የኸዋርዚም ጦር ተራበተራ እየለቀሙ ደመሰሱት ።

ሰመርቀንድ ፣ ቡኻራ ፣ ኡርጌንች ኹራሳን እንዳልነበሩ ሆኑ ።
እነዚያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የሚኖሩባቸው የአለማችን ስልጡን ኢስላማዊ ከተሞች እንዳለ ወደሙ ። ጄንጊስ ኻን ከነዚህ ከተሞች አንድም ሰው እንዳይተርፍ ትእዛዝ አስተላለፈ ። የሚተርፉ ሰዎችም የሚፈለጉ ለምሽግነት ብቻ ነበር ( Human Shield )! 

ጁቫይኒ የሚባለው የፐርሺያ ምሁር በኡርጌንች የተፈፀመውን የሞንጎሎች ጭፍጨፋ እንድህ ሲል ፅፏል " በኡርጌንች ከተማ የገባው 50,000 የሞንጎል ሰራዊት በነፍስወከፍ 24 የኡርጌንች ነዋሪዎችን የመግደል ግደታ ተጥሎበታል " ይላል ። በዚህ መሰረት በኡርጌንች ከተማ ብቻ ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ንፁሃን ተጨፍጭፈዋል።
ከሰመርቀንድ ነዋሪዎች የተረፉት በከፍታ ቦታ ላይ እንዲሰባሰቡ ታዘዙ ። እናም በፆታ እና በእድሜ እየተከፋፈሉ ተሰለፉ ከዚያ ሁሉም ተጨፈጨፉ ይላል አታ ማሊክ የተሰኘው የሞንጎል ሹም ። የሞንጎሎች በነዚያ የሙስሊም ከተሞች በነ ቡኻራ ኡርጌንችና ሰመርቀንድ የፈፀሙት ጭፍጨፋ በታሪክ ተወዳዳሪ አልባው ነው !!
የኸዋሪዝማን ሱልጧኔት ተደመሰሰ ። ሱልጧን ሻህ አላኡዲን ሙሀመድ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአንድት ደሴት ሙቶ ተገኘ።

ክብሯን አንባቢዎቼ ይህ ፀሰሁፍ በጣም በዝቶ እንዳያሰለቻችሁ ለዛሬ እዚህ ላይ ላቁም ። በጣም ከዚህም የሚበልጡ አስገራሚና ዘግናኝ ታሪክ የያዘውን የሞንጎሎችን ታሪክ ለማንበብ ዝግጁ ከሆናችሁ በክፍል-3 እንገናኝ ! ወቢላሂ አተውፊቅ !
#Share

@Ertugrulbeyseries

Dirilis Ertugrul Ethiopia

16 Sep, 16:26


እንዴት ነው ሰዎች የሞንጎሎች ታሪክ ተመቻቹ ይቀጥል የምትሉ እስኪ😇🙌

Dirilis Ertugrul Ethiopia

16 Sep, 04:30


#ሞንንጎሎች_በጂንጊስ_ኻን_ዘመን
የአለማችን ሀያሎቹ ወራሪዎች
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
          ( Seid social - ሰኢድ ሶሻል )
            ክፍል -2
ክብሯን አንባቢዎቼ በክፍል አንድ የሞንጎሎች ታሪክ የሞንጎሎችን አነሳስ ከነብዩ ኑህ ልጅ ከያፌት እስከ ጂንጊስ ኻን ያለውን ታሪክ አይተናል ። ቱርኮች ሞንጎሎች ቻይናዎችና ሩሲያዎች ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸው የያፌት ትውልዶች መሆናቸውንም ተመልክተናል ። በተለይም ደግሞ በቱርኮችና በሞንጎሎች መካከል ያለው የቤተሰብነት ትስስር ከፍተኛ መሆኑንና ሞንጎሎች ለዘመናት በቱርኮች አገዛዝ ስር እንዳሳለፉ ተመልክተናል። ዛሬ ከታሙጂን ( ጀንጊስ ኻን ) ጀምሮ ያለውን ታሪካቸውን እንመለከታለን።

የታሙጂን አባት የሱገይ ይባላል ። አባቱ የጎሳው መሪና ተበታትኖው የሚኖሩት የምንጎል ጎሳዎች ኮንፌዴሬሽን ጦር መሪም ነበር ። እናም አባቱ የሱገይ ወደ ታታሮች ሄዶ በነበረበት ጊዜ መርዝ አብልተው ገደሉት ። ታታሮች የቱርክ ጉሳዎች ነበሩ። ያኔ ታሙጂን እድሜው 9 ብቻ ነበር ። በዘጠኝ አመቱ አባቱን የተነጠቀባት ቅፅበት የታሙጂንን ህይወት የቀየረች ቅፅበት ነበረች። " ከዚህ በሗላ ታሙጂን ልጅ አይደለም ጠላቶቹንም ሳይበቀል መቼም አይምሬቸውም" በማለት ለራሱ ቃል ገባ።

የታሙጂን እናት ሆሉን ትባላለች ። አባቱ እናቱን ያገባው አስገድዶ በመጥለፍ ነበር ። አባቱን በግድያ ያጣው ታሙጂን ጎሳውን ጭምር የሚያስጠጋው ጠፋ ። የእናቱ ቤተሰቦችም አናውቃችሁም አሏቸው ። እናም ስደትን ህይወት አደረጉት ። እያደኑ ውለው እያደኑ ማደር ! ከአደን የሚገኝን ነገሮች ብቻ እየተጠቀሙ እንደ አውሬ መኖር የታሙጂን ጎሳዎች እጣፈንታ ሆነ ።

በዚህ መካከል ነው በታሙጂንና በወንድሙ መካከል የጎሳው መሪነት ይገባኛል ፀብ የተነሳው ። የታሙጂን ታላቅ ወንድሙ ከእናቱ የሚወለድ አልነበረም ። እናም የታሙጂን ወንድም ቤግተር የአባቴ ስልጣን ይገባኛል አለ ። የአባቴ ሚስትም ከዚህ በሗላ ሚስቴ ናት በማለት አወጀ ። በዚህ ጊዜ ነው ታሙጂን ወንድሙን ቤግተርን የገደለው ። ታሙጂን እያልኳችሁ ያለሁት ጂንጊስ ኻንን እንደሆነ ልብ በሉ።

ታሙጂን ወንድሙን ከገደለ በሗላ የጎሳውን መሪነት ተረከበ ። እናም አባቱ በዘጠኝ አመቱ ያጨለትን ሚስቱን አገባ ። የታሙጂን ጎሳዎች የራሳቸውን ድንኳን ቀልሰው መኖር ጀመሩ ። ግና በዚህ መሃል ሌላኛዎቹ የሞንጎል ጎሳዎች የታሙጂንን ጎሳ ወረሩ። ሁሉንም የጎሳው አባላት አባላት ገደሉ ። ሚስቱን ግን ማርከው ይዘዋት ሄዱ ። ታሙጂንም ጥቂት ወታደሮቹን ብቻ ይዞ አመለጠ ። በዚህ ወረራ ታሙጂን ውስጡ ተቃጠለ ። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሚስቱ ምርኮኛ ሆና የጠላት መጫዎቻ መሆኗ አንገበገበው ። እናም አጋር ፈልጎ ከደም ወንድሙ ጋር ሄደ ። የደም ወንድሙ ጃሙካ ታሙጂንን ተቀበለው አብረው ጥምረት ፈጥረውም ጎሳውን ያወደሙበትን ጎሳዎች ተበቀሏቸው ። ሚስቱንም አስመልጦ አመጣ ። የታሙጂንና የጃሙካ ጥምረት ግን ረጂም ጊዜ ሊዘልቅ አልቻለም ።

ታሙጂን የጃሙካንን የደም ወንድምነት ለማረጋገጥ አሰበ ። እናም ለጃሙካን እንደዚህ አለው " ይህ የእኛም መሬት ነው ስለዚህ እዚሁ አብረን እንኖራለን " አለው ። በዚህ ጊዜ ጃሙካን ተቆጣ ። እኛና እናንተ ጠላት ጎሳዎች ነበርን ካስፈለገ አሁንም እንዋጋለን አለውና ተለያዩ ። ጃሙካን ጦሩን አደራጅቶ በደም ወንድሙ በታሙጂን ጎሳዎች ላይ ጥቃት ፈፅሞ እጅቅ ሰቅጣጭ ውድመት አደረሰ ። አብዛኛዎቹን ሰዎች በሰይፉና ከቤት ውስጥ በማቃጠል ፈጃቸው ። የተረፉትን በተፍለከለከ ዘይት ውስጥ ከተታቸው ። ይህ ታሙጂንን አስቆጣ ። እናም ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ጥምረት በመፍጠር በጃሙካን ላይ አፀፋ ወሰደ።

ታሙጂን በቁጥር በጣም የሚበልጠውን የጃሙካንን ጦር በአስደናቂ የታክቲክ ልህቀት አፈራርሶ ደመሰሰው ። ጃሙካን አመለጠ ግና የገዛ ታማኝ ሁለት ወታደሮቹ ከድተው ለታሙጂን አመጡለት ። እነርሱ የታሙጂንን ጠላት አምጥተው ምህረትን ከታሙጂን ለማግኘት አስበው ነበረ። ግና አልተሳካላቸውም ። ታሙጂን በተፈጥሮ ከሃዲና ፈሪ ፈፅሞ አይወድም እነዚያ ጃሙካንን ያመጡ ወታደሮችን ግደሏቸው ብሎ ተገደሉ ። ጃሙካንን ግን ይቅር ብየሃለሁ አለው ። የደም ወንድሜ የድሮ ጓደኛየ እኔ ለአን የይቅርታ ልብ አለኝ አለው ። ግና ጃሙካን እምቢ አለ ። " በዚህ ሰማይ ላይ ያለው አንድ ፀሀይ ብቻ ነው ። ሁለት ፀሀይ ሊኖር አይችልም ስለዚህ እኔን እንድትገድለኝ እጠይቅሃለሁ ግና ስትገድለኝ የክብር አገዳደል ይሁንልኝ ደሜ እንዳይፈስ አድርገህ ግደለኝ " በማለት ታሙጂንን ተማፀነው ። ታሙጂንም የጃሙካን ጥያቄ በመቀበል ወገቡ ተቀጭቶ እንዲገደል አደረገው ።

በቱርኮችና በሞንጎሎች ህግ የመሪ ቤተሰቦች ደማቸው አይፈስም ። ሲገደሉ ደማቸው እንዳይፈስ ተደርጎ ነው የሚገደሉት ። በማነቅ ወይንም ወገብ በመቅጨት ሊሆን ይችላል።

ታሙጂን ጃሙካንን ከደመሰሰ በሗላ መላው የሞንጎል ጎሳዎች በዙሪያው ተሰባሰቡም ። ታሙጂን መሪያችን ነው በማለት በእርሱ ትእዛዝ ስር ገቡ ። ከዚያም እርሱን ለማንገስ ሁሉም የሞንጎል ጎሳ መሪዎች ተሰባሰቡ ። በዚያ የንግስትና ስነስርአት ላይ ታሙጂን የአለማቱ ንጉስ ተሰኘ - #ቺንጊስ_ኻን ! ቺንጊስ ማለት  ተንጊስ ከሚለው የቱርክኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ውቅያኖስ ማለት ነው ። የጂንጊስ ኻን ሌላኛው ስሙ ሞንግኬ ተንግሪን ይሰኛል ። ሁለቱም የፍጥረተ አለሙ ንጉስ ( Universal king ) ማለት ነው ።ፈረንጆቹ ጄንጊስ ኻን ይሉታል ።  ጂንጊስ ኻን የአለሙ ንጉስ ! ስለዚህ ከአሁን በሗላ ታሙጂን ማለታችንን ትተን ጄንጊስ ኻን እንላለን ማለት ነው ።

ጄንጊስ ኻን ሞንጎሎች በታሪካቸው አይተውት የማያውቁትን አንድነት አይተውት የማያውቁትን ሀያልነት ያጎናፅፋቸው ጀመር ። ከአሁኑ ሳይቤሪያ ሩሲያ እና ከአሁኗ ሞንጎሊያ አጎራባች መንግስቱን አቋቋመ ። ሞንጎሎች በታሪክ አንድ መንግስት ሆኑ ።
ጄንጊስ ኻን ሞንጎሎችን ካዋሀደ በሗላ የግዛት ማስፋፋት እቅዱ ከሞንጎሊያ ምድርም ሰፋ ። ድሮስ የአለሙ ንጉስ ለምን ተባለና! እናም የመጀመሪያ ወረራውን በቻይናው ዢን ዢያን ስርወመንግስት ላይ ፈፀመ ። ዢን ዢያን ጠንካራ የሚባል መንግስት አልነበረምና ንጉሱ እጅ ሰጥቶ በጄንጊስ ኻን ስር ተጠቃለለ።

ቻይና በድንበር አካባቢ የሚነሱ መንግስታትን አትታገስም። ዢዮንኙ እና ኡይጉር የመሳሰሉ የቱርክ መንግስታት ለበርካታ ክፍለዘመናት ቻይናን አንበርክከው ከፍተኛ ግብር ሲያስከፍሏት ቆነጃጅት ሴቶቾን እየወሰዱ እቁባቶች ሲያደርጉባት ኖረዋል ። እና ጄንጊስ ኻን ተነሳ ሲባል ቻይና ጊዜ ማጥፋት አልፈለገችም ። ወዲያው ለእርምጃ ተዘጋጀች።

የቻይናው #ጂን ስርወመንግስት አንድ ትልቅ ስህተትን ፈፀመ ። ጄንጊስ ኻን ግብር ለቻይና እንዲከፍልና በቻይና ስር እንዲተዳደር የሚጠይቅ ትእዛዝ ላከለት ። በዚህ " የአለሙ ንጉስ " ጂንጊስ ኻን ተቆጣ ። እኮ እንደት ብደፈር ነው ? አለ ። እናም ከ 50,000 በላይ ከሞንጎልና ቱርኮች የተውጣጣ ሰራዊቱን ይዞ ወደ ቻይና ተመመ ። ግና ቻይናዎች በመሳሪያ ቴክኖሎጅም በሎጀስቲክም ሆነ በተዋጊ ብዛት ይበልጡት ነበረ ። ጂንጊስ ኻን ወረራውን ጀመረ ቻይናዎችም በስኬት መከቱ ። በዚህ ጊዜ ጄንጊስ ኻን አፈገፈገ - የማታለል ማፈግፈግ ! አሳቻ ቦታና ጊዜ ጠብቆ የቻይናው ንጉስ ወደ ሌላ የከተማዋ ክፍል በተጓዘበት ቅፅበት ቤጅንግን አመድ አደረጋት ። ቤጂንግ ያን ጊዜ #ዦንግዱ ነበር ስሟ። ከአለም እጅግ የተራቀቀችው ከተማ ወደ አመድነት

Dirilis Ertugrul Ethiopia

15 Sep, 14:15


ግና በዚህ መካከል ነው እንግድህ እስልምና ወደ አካባቢው መዝለቅ የጀመረው ። በኡመዉዮች ዘመን ታላቁ የጦር መሪ መስሊም ኢብኑ ቁተይባህ ቻይናን ሲያንበረክካት ኸደ አካባቢው ኢስላም በቀላሉ ሊገባ ቻለ ። እናም አብዛኛዎቹ ቱርኮች እስልምናን ተቀበሉ። ከሞንጎሎች ጋር የባህል የእምነት የስርአት ልዩነት በሰፊው ይስተዋል ጀመረ።

በ 12ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ የቱርኩ ኢስላማዊው የኡይጉር ስርወመንግስት በፐርሺያዊያኑ በታጂኮች ወረራ ሲፈራርስ ሞንጎሎች ራሳቸውን ችለው ማንሰራራት ያዙ። በጎሳ በጎሳ እየሆኑ እየተደራጁ የመጡት መሃይምቹ ( መፃፍም ማንበብም የማይችሉ ለማለት ነው ) ሞንጎሎች ጠንካራ የጎሳ ግንባሮችን መፍጠር ያዙ ። ግን አብዛኛው ጦርነታቸው እርስበርሳቸው ነበርና አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ አልቻሉም። እርስበርስ መተላለቅ ብቻ!

በ 1162 በሩቋ መሀል ኤዥያ አንድ እንግዳ ሰው ይህችን ምድር ተቀላቀለ። ያ ሰው ሲወለድ የደም መርጋት በሽታ ጋር ነበረ ። ይህ ታላቅ ጦረኛ እንደሚሆን ምልክት ነው አሉ ወላጆቹ ። ያ አስፈሪ ሰው እንደተወለደ የሞንጎሎች የገሃነም ኑሮ ተቀበለው ። ገና ህፃን እያለ የሞንጎል ሌላዎቹ ጎሳዎች አባቱን በመርዝ ገደሉበት ። ያ ክስተት የነበልባሉን የ9 አመት ህፃን እጣ ፈንታ እስከመጨረሻው የቀየረ ነበረ። አባቱ የጎሳው መሪ ነበረ ። ያ አስፈሪ ልጅ ቁጣው ከእድሜው በላይ እያነደደው አላስቀምጠው አላስተኛው አለ። የጉዞየ እንቅፋት ነው ያለውን ወንድሙን ታላቅ ወንድሙን በቀስት ገደለው ።  ያ ሰው የአለምን ታሪክ የቀየረው #ታሙጂን ነው! ታሙጂን የሞንጎል ጎሳዎችን አሰባሰበና አንድ ሃያል ስርወመንግስትን ጠነሰሰ ። ራሱንም የሞንጎሎች መሪ በማድረግ #ጄንጊስ_ኻን ተሰኘ ።
ጂንጊስ ካን - ሞንግኬ ተንግሪን እነሆ የአለምን ታሪክ መፃፍ በማይችሉት እጆቹ መፃፍ ጀመረ !!

ሞንጎሎች ከጂንጊስ ኻን በሗላ .......ይቀጥላል!

#Share

@Ertugrulbeyseries

Dirilis Ertugrul Ethiopia

14 Sep, 18:08


#የሞንጎሎች_ታሪክ
ከነብዩ ኑህ ( ዐ.ሰ ) እስከ ጄንጊስ ኻን
-------------------------------------------------
( Seid social - ሰኢድ ሶሻል )

ዛሬ የምነግራቸው የአስገራሚዎቹን ህዝቦች የሞንጎሎች ( ሞጉል ) ታሪክ ነው ። እነዚህ አለምን በአንድ እግር ያቆሙት ማንም በታሪክ ያልፈፀመውን ከምስራቁ ጫፍ እስከ ምእራቡ ጫፍ አለምን አንቀጥቅጠው አርበድብደው የገዙት አስፈሪዎቹ ሞንጎሎች ለመሆኑ መነሻቸው ዝርያቸው ከየት ይመዘዛል ? ወደ ሃያልነት ማማውስ እንደት ተቆናጡጡ ? ቱርኮችና ሞንጎሎች ምንና ምን ናቸው ? እነዚህንና መሰል አጃኢብ ታሪኮችን ከ"ቅዱሳን" መፃህፍት እስከ ታሪክ መፅሀፍቶች አገላብጬ ይዤላችሁ ቀርቢያለሁ ። መልካም ንባብ!

በመፅሀፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 6 ቁጥር 10 እንደዚህ ይላል " ኖህም ሶስት ልጆችን ካምን ሴምን ያፌትንም ወለደ ። በዚያው ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 9 ቁጥር 18 ጀምሮ እንደዚህ ይላል " ከመርከቡ የወጡት የኖህ ልጆች እነዚህ ናቸው ሴም ፥ ካም ፥ ያፌት ካምም የከነአን አባት ነው ።የኖህ ልጆች እነዚህ ሶስቱ ናቸው ከነርሱም ምድር ኹሉ ተሞላች " በማለት ይገልፃል።

በመፅሀፍ ቅዱስ ገለፃ መሰረት ኖህ ከማእበሉ መጠናቀቅ በሗላ ገበሬ ሆነ ። እና በዚያ ወቅት ኖህ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰክሮ ራቁቱን ከቤቱ ወድቆ ነበረ ። ከዚያ ካም ወደ ቤት ሲገባ ኖህ እርቃነ ስጋውን ሆኖ በስካር ራሱን ስቶ ያየዋል ። በዚህ ጊዜ ካም ወንድሞቹን ያፌትንና ሴምን ይጠራና " ኑ የአባታችንን ጉድ ተመልከቱ ሰክሮ ራቁቱን ሆኗል ይላቸዋል ። ሴምና ያፌት ገብተው የአባታቸውን ሀፍረተ ገላ ባዩ ጊዜ ልብስ አልብሰው ይሸፍኑታል ። ከዚያም ኖህ ከስካር መንፈሱ ሲነቃ የተከሰተውን ያያል ። በዚህ ጊዜ ካምን ረገመው ይላል ኦሪት ዘፍጥረት ። " አንተ አገልጋይ የነ ሴም ባሪያ ሁን " ብሎ ረገመው ። በተቃራኒው ሴምንና ያፌትን መረቃቸው ገዥ የበላይ ሁኑ አላቸው ይላል መፅሀፍ ቅዱስ ።

በቁርአን አስተምህሮ ግን ነብያቶች ከታላላቅ ወንጀሎች የተጠበቁ በመሆናቸው የመፅሀፍ ቅዱሱ ገለፃ ውድቅ ነው ። ከዚያ በተጨማሪ አላህ የኑህ ( ዐ.ሠ ) ልጆች ሶስት ብቻ እንዳልሆኑ በቁርአን ውስጥ በግልፅ አስቀምጧል። ከማእበሉ ከተረፉት ሶስት ልጆቹ በተጨማሪ አላህ ላይ አምፀው ከተጠፉት ሰዎች ውስጥ የኑህ ልጅ እንደሚገኝበት ቁርአን በግልፅ ያስቀምጣል። " እርሱ ቤተሰቤ ነው " በማለት ኑህ አላህን በተማፀኑት ጊዜ አላህም " እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም " ብሎ መለሰላቸው ።

እናም ከኑህ ልጆች ሶስቱ ተረፉ ። ካም ሴምና ያፌት!
👉 ካም( ሃም) - የሄደው ወደ አፍሪካ ነው ።የኩሽ የከነአን አባት ነው ። በዚህም የአፍሪካዎች የጥንታዊ ግብፆችና የህንዶች አባት እንድሁም የአይሁዶች አባት ካም ነው ማለት ነው።
👉 ሴም ፦ የሄደው ወደ ኢራን ነው ። የፐርሺያዎች ( የኢራኖች ) የአረቦች እንድሁም የሮሞች ( የአውሮፓዊያን ) አባት ነው ። በነገራችን ላይ የአውሮፓውያን መነሻ ዝርያቸው ፐርሺያ ነው!

ክብሯን አንባቢዎቼ የዛሬ ዋነኛ ፅሁፌ የሚያጠነጥነው #የያፌት ልጆች ላይ ነው!!!

ያፌት የሄደው ወደ ሩቅ ምስራቅ ነው ። ወደ አሁኖቹ ሩሲያና ካዛኽስታን አጎራባች አካባቢ። ያፌት ስምንት ልጆችን ወለደ ። እነዚህ ስምንት ልጆች የሚከተሉት ናቸው
1 ቱርክ 3 ሩስ 5 ቺን 7 ሰቅለብ
2 ኻዛር 4 ሚንግ 6 ቀመሪ 8 ታሪኽ

ቱርክ የቱርኮችና የሞንጎሎች አባት ነው ። ሩስ ደግሞ የሩሲያዎች አባት ነው ። ቺን እና ሚንግ ደግሞ የቻይናዎች አባቶች ናቸው ። ሌሎቹም እንደዚያ በአካባቢው የሰፈሩት የሌሎች ህዝቦች አባቶች ናቸው ። ልብ በሉ ! የእጁጅና መእጁጅ የያፌት ዝርያዎች ናቸው ።

ያፌት ቱርክን ተተኪው አድርጎ አለፈ ። ከዚያ ቱርክ ደግሞ ቱቴክን ተክቶ አለፈ ። ቱቴክ ከቱርክ አራት ልጆች ትልቁ ነበር።
ከቱርክ አራተኛ ትውልድ ላይ #ታታር እና #ሞጉል የሚባሉ ልጆች መጡና የቱርክን አገዛዝ ለሁለት ከፈሉት ። #ሞጉል_ኻን ቃራ ኻንን ወለደ ። ቃራ ኻን ደግሞ #ኦጉዝ_ኻንን ወለደ ማለት ነው ። አሁን የተገለጠላችሁ ይመስለኛል። ኦጉዝን አስታወሳችሁት አይደል ። የቱርኮች ሁሉ አባት የሆነው ኦጉዝ ኻን ማለት ነው ።

እናንተየ ኦጉዝኮ በጣም አስገራሚ ታሪክ ያለው ሰው ነው ። ለመሆኑ ብዙዎች ዙልቀርነይን ኦጉዝ ነው እንደሚሉ ታውቃላችሁ? አሁን ወደ ሌላ የታሪክ ውቅያኖስ አልግባ ። ስለ ኦጉዝ ኻን የቱርኮችን ታሪክ በምፅፍበት ጊዜ አስነብባችሗለሁ።

እዚህ ጋር ግን አንድ ነገር ግልፅ ሆኖላችሗል እርሱም ሞንጎሎችና ቱርኮች አንድ ህዝብ እንደነበሩ ! የሞንጎሎችም የቱርኮችም ቅድመ አባት የያፌት ልጅ ቱርክ መሆኑን ። ኢንሻአላህ ስለ ቱርኮች በምፅፍበት ጊዜ ምስሉ የበለጠ ግልፅ ይልላችሗል ። ሞጉል ሞንጎል ሙጋል ተመሳሳይ ተርሞች ናቸው

ቱርኮችና ሞንጎሎች በአንድ የቱርክ ስርወመንግስት ስር መተዳደር ጀመሩ ያ ስርወ መንግስት Xiougnu ( ዢዮኙ ) ይሰኛል ። ከቻይና እስከ ሩሲያ አንበርክኮ ያስገበረው ሀያሉ የቱርክ ሞንጎሎች ኢምፓየር ። የዚህ ስርወመንግስት መስራቹ ሞዱን ( Modun ) ይባላል ።

ሞዱን ጉደኛ ሰው ነው በጣም ጉደኛ !! ሞዱን አባቱ ከአልጋ ወራሽነት ሊያስወግደው መሆኑን መረጃ በደረሰው ጊዜ ታማኝ ወታደሮቹን ለመፈተንም ሲል አባቱን ግደሉት አላቸው እነርሱም ገደሉት ። በዚህ አላበቃም የወታደሮቹን ታማኝነት ለማረጋገጥ የሚወዷቸውን ፈረሶቻቸውን እንዲገድሉ አዘዛቸው አሁንም ያንን ፈፀሙ። አረመኔው ሞዲን በዚህም አላበቃም ለአርሱ ያላቸውን ታማኝነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ሚስቶቻቸውን እንዲገድሉ አዘዛቸው እነርሱም ሚስቶቻቸውን ገድለው አመጡለት ። ከዚያ በሗላ ሞዱንን የሚያስቆመው ሀይል ከቶ አልተገኘም ። ስለ ዢዮንኙ ስርወመንግስት ስለ መሪውም ሞዱን በቱርክ ታሪክ ውስጥ በስፋት እነግራችሖለሁ።

እንደማንም ሞንጎሎች በቱርክ ስርወመንግስታት እየተገዙ በርካታ መቶ አመታትን አሳለፉ ። እነ ኻዛርስ ፣ ቃራኻኒድ ኡይጉር ወዘተ በሚባሉ የቱርክ ስርወመንግስታት ስር ሞንጎሎች ጉዟቸውን ቀጠሉ ። እምነታቸው ተመሳሳይ ነበር ። ተንግሪዝም ፣ ሚስቻኢዝም በሗላም ቢድሂዝም የቱርኮችም የሞንጎሎችም የጋራ ሀይማኖቶች ነበሩ ።

Dirilis Ertugrul Ethiopia

14 Sep, 12:03


ብዙዎቹን ያስቸገሩት የሀያላኖቹ ሞንጎሎች ታሪክ ይለቀቅ የምትሉ እስኪ በላይክ አሳዩኝ😊
https://t.me/Ertugrulbeyseries

Dirilis Ertugrul Ethiopia

08 Sep, 06:19


4 piece sheto yemifelg sw be arif waga ene ga ale inbox @royalboyyyyyy

Dirilis Ertugrul Ethiopia

08 Sep, 04:11


•|| ኤርቱግሩል😢

"በህይወትህ ቦታ ምትሰጣቸው ውድ ነገሮችን ብታጣ ህይወት አትቆምም፤
           በህይወትህ ደስታና ሰላም ብታጣ ህይወት አትቆምም፣
           በህይወትህ ተስፋ ያጣህ ቀን ግን ህይወትህ ያበቃላታል!
         ያጣሀቸውን ውድ ነገሮች በሌላ ልትተካ ትችላለህ! ሰላም እና ደስታህን መልሰ ልታገኝ ትችላለህ! ተስፋ የቆረጥክ ቀን ግን ዛሬን እንኳ መሻገር አትችልም፡፡
       የህይወትህ ህልውና በተስፋህ መሰረት ላይ የተገነባ ነውና በህይወትህ መቼም ተስፋ አትቁረጥ!"
👇👇👇
https://t.me/Ertugrulbeyseries

@OsmanEthiopia

Dirilis Ertugrul Ethiopia

19 Aug, 03:22


﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ﴾

@osmanethiopia
@osmanethiopia

Dirilis Ertugrul Ethiopia

30 Jul, 04:36


🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋

የካዕባ ልብስ ኪስዋ በአዲሱ አመት መግቢያ ላይ ተቀየረ

ስለካዕባ ልብስ ኪስዋ ትንሽ መረጃዎችን ላካፍላችሁ


🕌የካዕባ ልብስ ኪስዋ በየአመቱ የሚቀየር ሲሆን ከዚህ ቀደም በዙልሂጃ 9 ጠዋት ሀጃጆች ወደ አረፋ በተጓዙበት ወቅት ነበር የሚቀየረው:: አሁን ላይ ግን በአዲሱ አመት መግቢያ የመጀመሪያው ምሽት ሙሐረም 1 ላይ እንዲቀየር ተወስኗል::

🕋የካእባ ልብስ ኪስዋ የአለማችን ውዱ ልብስ ነው::

🕋የልብሱ ክብደት 850ኪ. ግ የሚመዝን ሲሆን አጠቃላይ የካዕባን ልብሱን ለማዘጋጀት የዘንድሮ ወጪው $6.5ሚሊዮን ዶላር ነው::

🕋ይህ የካዕባ ልብስ በንጉስ አብዱልአዚዝ ኮምፕሌክስ የሚዘጋጅ ሲሆን ኪስዋውን ለማዘጋጀትም 200ባለሞያዎች ይሳተፉበታል::

🕋በአለም ረጅሙ እና ኮምፒውተራይዝ የሆነው የስፌት ማሽን ይህን የካዕባን ልብስ ለማዘጋጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን የስፌት ማሽኑም
16 ሜትር የሚረዝም ነው::

🕋የከዕባ ልብሱ ኪስዋ 670 ኪሎ የሚሆነው ጥቁር ሀር ሲሆን በሀሩ ላይ ለሚፃፈው የቁርኣን አንቀፆችም 120 ኪሎ 21ካራት ወርቅ እና 100ኪሎ ብር አገልግሎት ላይ ይውላል::

🕋በልብሱ ላይ የሚፃፈው የቁርዓን አንቀፆችም በሰዎች እጅ በጥንቃቄ የሚጠለፍ ነው:

🕋የዘንድሮ አመት 1444 የካእባ ልብስ ኪስዋ የመቀየር ስነ ስርዓትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቀጥታ የቴሌቭዢን ስርጭት ተከታትለውታል


@osmanethiopia
@osmanethiopia