Últimas Postagens de ኤል_ማሮስ (@el_maros) no Telegram

Postagens do Canal ኤል_ማሮስ

ኤል_ማሮስ
2,377 Inscritos
58 Fotos
2 Vídeos
Última Atualização 09.03.2025 02:45

Canais Semelhantes

Dev2op
8,530 Inscritos
.
7,894 Inscritos
@MENFESS: CHANNEL
1,901 Inscritos

O conteúdo mais recente compartilhado por ኤል_ማሮስ no Telegram

ኤል_ማሮስ

05 Mar, 06:19

191

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን

በተደጋጋሚ አብይ ፆም በደረሰ ጊዜ ሁሌ የሚነሳ ጥያቄ

ዓሳ በጾም ይበላልን

ግዜው ደርሶ እንግዲህ ጾም ገባ አሳ ካልበላን ብለው አይናቸው እንባ የሚያቀር ሰዎች ስለሚኖሩ ቤተክርስትያናችን ለምን አሳ በጾም እንደማይበላ ዛሬም ሳትሰለች ለዚህ መንቻካ ጥያቄ መልስ ትሰጣለች።

1⃣ አንዳንድ ሰዎች በጾም ሰአት ዓሳ ይበላል ይላሉ፤ ለመብላት እንደ ምክንያት የሚያነሱት አንዱ በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት) ላይ ያለውን

"ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ አሳ" የሚለውን ነው።

በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት) ላይ "ኢትብልዑ ...ስጋ ዘእንበለ አሳ " የሚል ቃል አለ ።

እዚህ ቃል ውስጥ <ዘእንበለ> የሚለው የግእዝ ቃል ሁለት ትርጉም ስላለው ሰዎችን ሲያምታታ ቆይቷል ትርጉሙም
📌 #ዘእንበለ = በቀር
📌 #ዘእንበለ = ሳይቀር የሚል ነው።

አንዳንድ ሰዎች "ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ ዓሳ "የሚለውን "ስጋን አትብሉ ከዓሳ በቀር" ብለው ተርጉመው ዓሳ ይበላሉ፤ ነገር ግን ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት ትክክለኛው ትርጉሙ "ስጋን አትብሉ ዓሳም ሳይቀር" የሚለው መሆኑን ተናግሩል።

🔘ምሳሌ እናቅርብ

“እግዚአብሔር ፈጠረ ኩሉ አለም ዘእንበለ ትል” ሲል እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ፈጠረ ትልን ጭምር ይባላል እንጂ ከትል በቀር አይባልም።

ስለዚህም አሳን ጭምር አትብሉ ማለት ይሆናል ማለት ነው፤ ዓሳ ከበግና ከበሬ ስጋ የተሻለ ጥቅም አንዳለውም ይታወቃል።

ስለዚህ ከበግና ከበሬ ተከልክሎ አሳን መብላት እራስን ማታለል ነውና ቤተ ክርስቲያን በጾም ሰአት ዓሳን መብላት ትከለክላለች፤ (ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም 📖ዳን 10፥3

2⃣ አንዳዶች በጸሎተ ሐሙስ ጌታ ለሐዋርያቱ አሳ መግባቸዋል ስለዚህ ዓሳ በጾም ወቅት ቢበላ ችግር የለውም ለሚሉ መጸሐፍን ጠንቅቆ ካለማወቅ የመጣ ነው።

ሐዋርያት ጾማቸው በአዲስ ኪዳን የተጀመረው ጌታችን ካረገ ከሀምሳ ቀን ቡሃላ ነው፤ ጌታም ሐዋርያትን ዓሳ በሚያበላበት ወቅት እነሱ አይጾሙም ነበር፤ ነገር ግን እኛ አሁን በምንጾምበት ሰአት ምሴተ ሐሙስ በአቢይ ጾም የመጨረሻው ሳምንት በሆነው በህማማት ወቅት አብረን ስለምናስበው ጌታ ለዋርያትን ዓሳ ያበላችው በጾም ወቅት ይምስለናል ይህ ግን ስህተት ነው፤ ምክኒያቱም በዚያ ወቅት ሐዋርያቱ ጾም እንደማይጾሙ ተናግሩአል ላይ የዪሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ ጌታ መጥተው ለምንድን ነው እኛና ፈሪሳውያን እንጾማለን ያንተ ደቀመዛሙርት የማይጾሙት ብለው ጠየቁት ጌታም ሲመልስ እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከነሱ ጋር እያለ ሊያዝኑ ይችላሉን፤ ነገር ግን ሙሽራው ከነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል በዚያን ጊዜ ይጾማሉ አላቸው።
📖ማቴ 9፥14-18

ይህንን ቃል እንደተመለከትነው ሙሽራው የተባለው ጌታ ከነሱ ጋር እያለ ሐዋርያት አለመጾማቸውን ነው፤ ነገር ግን ሙሽራው የተባለው ጌታ ከእነርሱ ከተለየ ቡሀላ ሐዋርያት ጾመዋል።

ለዚህም የመጸሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ስንመለከት "በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም...... " ላይ "በየቤተክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው....." ስለዚህ በጾም ወቅት ዓሳ አይበላም ማለት ነው።
📖ሐዋ 14፥23
📖ሐዋ 13፥2

3⃣ አመክንዮአዊ መልስ (Logic)
ይህማ ያሰባናል ያወዛናል ነፍሳችንን ያስረሳናል በጾም እንዴት አርገን እንበላዋለን ብለን ጾም ከመግባቱ በፊት ከተራኮትንበት ከሥጋ በላይ እጅግ የበለጠ "Nutritious content" ወይም አልሚ ንጥረ ነገር ያለውን አሳ ከበሉ በኋላ እየጾምኩ ነው ማለት ይቻላል ወይ አሳ ከመብላት በላይ ለሰውነት እንክብካቤ ከየት ይምጣ፤ ማንን ልናታልል ነው፤ አሳ በልቶ ሰውነቱ ደክማ ዝላለት ለነፍሱ ያደረ ሰው ሰምተህ ታቃለህ፤ ዓሳን መብላት ትከለክላለች።

አስቡት እስቲ አደለም አሳ የጣመ የላመ የጾም ምግብ እንኳን ቀንሱ የምትል ቤተክርስትያን አሳ ብላልኝ ትልሃለች፤ ከዛ ሲቀጥል አቀብተ ሃይማኖት የሆኑት አባቶቻችን ስርአትን በደነገጉበት ግዜ "በመብል ክርክር ቢነሳ ለጾም አድሉ ብለዋል" አከተመ።

ይህ ሁሉ ጥያቄ የጾም መሰረታዊ አላማ ከሥጋ ምቾት ማማ መውረድ እንደሆነ ስላልተረዳን ነው እና እናስብበት፤ እራስን ማታለል ይቻላል ፈጣሪን ግን ማታላል አይቻልም።

"ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም፤ አለ ነብዩ ዳንኤል።
📖ዳን 10፥3"

#አሳ_ስጋ_አይደለም_ብላቹ_ምትከራከሩ_ሰዎች_እና_ታድያ_አሳ_አትክልት_ቅጠላ_ቅጠል_ነው_እንዴ እራሳችንን አናታልል።

መደምደሚያ

አበው አባቶቻችን በጾም ክርክር ቢነሳ ለጾም አድሉ ከመብላት አለመብላት እጅግ ይሻላልና ብለው አልፈዋል

" ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን ሁሉም ነገር አይጠቅምም"
📖1ኛ ቆሮ 10፥23


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱
ኤል_ማሮስ

26 Feb, 20:25

145

ስለጣዖታት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ኤል_ማሮስ

26 Feb, 19:43

153

ከሚከተሉት ውስጥ የማይደገመው የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር የቱ ነው??
ኤል_ማሮስ

11 Feb, 18:44

55

መንፈስቅዱስ ለአብ ምኑ ነው?
ኤል_ማሮስ

08 Feb, 11:07

199

የሐዲስ ኪዳን ጥምቀት መስራቹ ማነው?
ኤል_ማሮስ

29 Jan, 19:05

145

ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ለማነው?
ኤል_ማሮስ

29 Jan, 18:14

159

አምስቱ አዕማደ ሚስጥራት ማን ማን ናቸው?

ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?

የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ሰባቱ አፅዋማት እነማን ናቸው?

አስሩ ቃላቶች እነማን ናቸው?

6ቱ ቃላተ ወንጌልስ ምን ምን ይለናል?


በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉን 👇👇
ኤል_ማሮስ

29 Jan, 04:46

1,481

እንኳን አደረሳችሁ🥰

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱
ኤል_ማሮስ

26 Jan, 04:35

1,197

+ የብርሃን ዓይን ናት +

"ቅዱስ ኤፍሬም" ድንግል ማርያም የብርሃንን ምንጭ የተቀበለች መሬት ናት ፣ በርሷ በኩል ዓለምና በዓለም ያለው ኹሉ በብርሃን ተመላ ፣ በሔዋን ምክንያት ጨልሞ ነበር ፣ የክፍ ሁሉ ምንጭ ኾናለችና እመቤታችን ማርያም ሔዋን በምሳሌያቸው አንድ ዐይኑን እንዳጣ በአንድ ዓይኑ ሰውነቱ ሁሉ ብርሃን የኾነለት ሰውን ይመስላሉ ፣ የሚታየው ዓለም ኹለት ዐይኖች አሉት ሔዋን የታወረ የግራ ዐይን ናት የሚያየው የቀኝ ዓይን ግን ድንግል ናት ። በጨለማው ዓይን በኩል ዓለሙ ሁሉ በጨለማ ተውጧል ፣ ሰዎችም በጨለማ ዳሰሳ ጀመሩ ፣ ግን የሚያደናቅፍቸው ድንጋይ ጣዖት ሐሰትን የሚናገር በድን ነው ። ነገር ግን በቀኝ ዓይኑ ዓለም በብርሃን ሲመላ ከሰማይ የወረደው ብርሃን በመካከል ሲገኝ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ታረቀ በማለት የብርሃን ዐይን መሆኗን የገልጣል ። በእርግጥም ድንግል ማርያም ለሰው ልጆች በሙሉ የብርሃን ዓይን ናት ! ( "መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት" ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው ገጽ -158 )


ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱
ኤል_ማሮስ

25 Jan, 07:05

575

💐ንብ ዲኮር 💐
ለሰርግ
ለብራይዳል
ለመልስ
ለቤቢ ሻወር
ለልደት
ለምርቃት እንዲሁም ለተለያዩ ፕሮግራም ዲኮር እንሰራለን
ያናግሩን @pilupadier
በስልክ መስመር 0927334801
0717273301
ለመቀላቀል👇👇

https://t.me/nib_decor