የተጻፈ ቢነበብ የተነበበው ቢተረጎም በተተረጎመው ምግባር ቢሠራ የዚህ ሁሉ የሃይማኖት ፍፃሜው ትንሣኤው ነው ። ትንሣኤ ከሌለ ሃይማኖት ሁሉ ከንቱ ነው ። የሃይማኖት የመጨረሻው ዋጋው በትንሣኤ ማክበሩ ነው እንጂ በምድር ማቀማጠሉ አይደለም ። "ወእመሰ ኢትነሥኡ ምውታን ክርስቶስኒ ኢትነሥአ እሙታን ወእመሰ ክርስቶስ ኢትንሥአ እምውታን ከንቱ ሃይማኖትክሙ - ሙታን የማይነሱ ከሆነ ክርስቶስ አልተሣማ ክርስቶስ ካልተሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት" እንዳለ ሐዋርያው (፩ኛ ቆሮ .፲፭-፲፯) ።
ሰው የተፈጠረው ለትንሣኤ ነው ፤ የሚኖረውም ለትንሣኤ ነው ፤ የሚፅናናውም በትንሣኤ ነው ። ጌታም ሥጋውን የበላውን ደሙን የጠጣውን ሰው ስለሚሰጠው ዋጋ ሲናገር እሾመዋለሁ እሸልመዋለሁ ጤና እሰጠዋለሁ ሀብት አድለዋለሁ አላለም ። ይልቁንም "ወበደኃሪት ዕለት አነሥኦ-ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ። እኔም በመጨረሻው ቀን አነሣዋለሁ " (ዮሐ ፮፥፶፬) ። ሌሎች የማያስፈልጉን ሆነው ሳይሆን እነዚያ የፍጡርነት ዋጋ እንጂ የሃይማኖት ዋጋ ስላልሆኑ ነው ። የሃይማኖት ዋጋ በክብር መነሣት ነው (ዮሐ ፭-፳፱) ። (ጸያሔ ፍኖት ርዕሰ ሊቃውንተ አባ ገብረ ኪዳን ገጽ 158-159)
ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS