ኤል_ማሮስ @el_maros Channel on Telegram

ኤል_ማሮስ

@el_maros


ኤል_ማሮስ (Amharic)

ኤል_ማሮስ ቅንብሮች እና ቁምነገሮች አደረጉልን! ይህ ቢኖር ፖስተር በኢንስተጉልክ እንዲሁም በአዲስ አበባ ይህን ነገር እንኖራለን እና ስለመረጡና መከታተል እንችላለን። የግምት ተናግረን በትክክለኛ ውይይት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በላይ ይህን ስለምንሰማ ወደ @el_maros ይግቡ። እናመሰግናለን ወደ መልካም ትክክለኛ ቅንብሮች እና መረጃዎች እንችላለን ማለት ለወዳጁ የሚሰማን ሃላፊዎችን ይጠቀሙ።

ኤል_ማሮስ

13 Jan, 19:31


https://vm.tiktok.com/ZMk5Msuor/

ኤል_ማሮስ

08 Jan, 20:09


በቴሌግራም የቱን ማግኘት ይፈልጋሉ

🎧ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች🎧

📖የቅዱሳን ታሪክ📖

🎤ኦርቶዶክሳዊ ስብከት🎤

📖የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ 📖

መናፍቃን ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው🎯

👳‍♂የአባቶች ምክር እና ተግፃፅ 👳‍♂

ሁሉንም ለማግኘት

ኤል_ማሮስ

06 Jan, 18:56


እንኳን አደረሳችሁ 😍

https://t.me/EL_MAROS

ኤል_ማሮስ

06 Jan, 18:43


መሪዎች ቆም ብለው ማሰብ ቢችሉ እኮ ሁሉም እንደሚያልፍ መረዳት ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ቀና መንፈስ እና የተሰበረ ልብ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ስለሆነ እነርሱም ያወቁ መስሏቸው አምላክን ትተው በራሳቸው ዕውቀትና ኃይል በመተማመናቸው ማጣፊያው አጠረባቸው፡፡ የሰው ልጅ ሁሉንም አውቃለሁ ብሎ ካሰበ መጨረሻው ጥፋት ነው፡፡ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ ብቻ እንደሆነና ነግሮች ሁሉ የሚከናወኑት በአምላክ ጥበብና ፈቃድ መሆኑን መረዳት አለበት፡፡ ባይረዳም ግን ነገሮች እንዲህ ከመሆን አይቀሩም፡፡ ሰው ቢችል ኖሮ በሽታንም፣ ድህነትንም፣ ጦርነትንም፣ የማያስፈልጉ ነገሮችን ሁሉ ማጥፋት ይችል ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ከሰው ልጅ አቅም በላይ በመሆኑ (መድኃኒት የሌለው በሽታ ማቆሚያ የሌለው ጦርነት፣ የሥራ አጥ ብዛትና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት) የመሳሰሉ አደጋዎች ውስጥ ገብቷል፡፡ 
የእግዚአብሔር ቃል ሁሉም ነገር በአምላክ ፈቃድ እንደሚደረግ ያለ እርሱ ፈቃድ አንዳችም እንዳልሆነና እንደማይሆን ይናገራል፡፡ ዓለም ደግሞ ለችግሮች ሁሉ መልስ ይሰጣል በሚለው ጥበቡ ስለተማመነ ይህን ቃል ለማዳመጥ ጆሮ የለውም፡፡ ዕውቀቱ ግን ችግሮችን ሲያባብስ እንጂ መፍትሔ ሲሰጥ አይታይም፡፡እግዚአብሔር የሌለበት ዕውቀት… መጨረሻው ጥፋት ነው፡፡ በጌታችን ልደት ዕለት መላእክትና እረኞቹ ሲያመሰግኑ በሄሮድስ ቤተ መንግሥት ግን የጥፋት ሸንጎ ተይዞ ጌታን ስለመግደል ይዶለት ነበር፡፡
እንደዚያ ጊዜው ሁሉ ዛሬም ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው የልደትን በዓል በዝማሬና በምስጋና ሲያከብሩ፣ ሌሎቹ ደግሞ በመንፈሳዊው በዓለ ልደት ስም ፓርቲ አዘጋጅተው በመጨፈርና በመዳራት ያሳልፋሉ፡፡ ለክብር የተፈጠረውን ሰውነታቸውንና አክብረው ሊከብሩበት የተዘጋጀላቸውን ቅዱስ በዓል ጨፍረውም ሆነ አብደው ለማይረኩበትና የውስጣቸውን ጉድለት እንዲያስረሳቸው እንደማደንዘዣነት ለሚጠቀሙበት ጊዜያዊ ፍላጎታቸው ያውሉታል፡፡ ያም ቢሆን ስላመኑበት ብቻ ያደርጉታል እንጂ ሲረኩበት አይታዩም፡፡
ጌታችን በተወለደበት በረት ውስጥ የነበሩት እንስሳት በትንፋሻቸው አሟሙቀውታል ወቅቱ (ታኅሣሥ ወር) በፍልስጥኤም ምድር የብርድ ወቅት ነበርና፡፡ ጌታችን በዚህ አስቸጋሪ ወቅትና በማይመች ሁኔታ መወለዱ እኛን ለማዳን ባደረገው ጉዞው ሁሉ ፍጹም ፍቅሩን ሊገልጽልንና በእኛ ተገብቶ ባደረገው ሥራውም በአዳም በደል ምክንያት ተጥለን ለነበርን ለእኛ የሰው ልጆች ሁሉ በመካስና ከውድቀታችን በማንሳት ፍቅሩን ሊገልጽልን ስለወደደ ነው፡፡
መላእክትንና እረኞችን ለምስጋና የመረጠ ሰብአ ሰገልን ስጦታ ለማቅረብ ያበቃ አምላክ የእኛንም የምስጋና መዝሙርና አገልግሎት የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ይቀበልልን፡፡ አሜን!! !ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ኤል_ማሮስ

06 Jan, 18:43


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!
ለአዳም የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽም በነቢያት አድሮ ያናገረው ትንቢት ሲደርስ ሰው የሆነ አምላክ የተወለደበት ዕለት (የልደት በዓል) እነሆ ደረሰና እኛም በዓሉን አክብረን ከበረከተ ልደቱ እንድንሳተፍ አበቃን፡፡
አምላካችን ለእኛ ላደረገልንና ለሚያደርግልን የቸርነት ሥራው ሁሉ ከምስጋና በቀር ሌላ አቅም ኖሮን መክፈል የምንችለው ነገር የለንም፡፡ ምክንያቱም እንክፈል ብንልም እንኳን ከእርሱ ያላገኘነው ምንም ነገር የለንምና፡፡ ከሕይወታችን ጀምሮ ሁሉንም ነገር ያገኘነው ከእርሱ ነውና፡፡ የሰዎች ልደት የሚከበረው በሕይወት ዘመናቸው ሲሆን ከሞቱ በኋላ የሚከበረው ግን ሙት ዓመታቸው ነው፡፡ አምላካችን ግን ልደቱም፣ ሞቱም ከተወለደበት እስከ ዐረገበት ጊዜ ድረስ ተአምራት ያደረገባቸው ቀናት ሁሉ ሁሌም እንደ አዲስ ይከበራሉ እኛ የምንኖረው ለራሳችን ሲሆን እርሱ ግን ሁሉንም ያደረገው ለሰው ልጆች ደኅንነት በመሆኑ ልደቱን በምናከብርበት ጊዜ ደኅንነታችንን እያሰብን ሲሆን በረከትን እናገኛለን፡፡
ጌታችን ሲወለድ እውነተኛው ሰላም እንደሚገኝና ፍጹም ደኅንነት እንደሚደረግ ነቢያት አስቀድመው በተናገሩት መሠረት በተወለደበት ዕለት መላእክትና እረኞች በአንድነት ሆነው “በሰማያት ምስጋና ይሁን በምድርም እርቅ ተወጠነ ‹‹ሰላም ሆነ›› ብለው አመሰገኑ፡፡ ይህ ብሥራት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ እንደተወጠነ ‹‹ሰላም እንደሰፈነ›› ያስረዳል፡፡ የመላእክትና የእረኞች ምስጋና አምላክ ሲወለድ የተገኘውን ሰላም ታላቅነት ያስረዳናል ምክንያቱም ሰላም ከሌለ ምንም አይኖርምና፡፡
አንድ አዳም በፈጸመው ስሕተት ምክንያት ፶፻ወ፭፻ (አምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመት) ዘመናት ያህል የሰው ልጆች ሁሉ ሰላማችን ጠፍቶ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር እንድንኖር ተገደን ነበር፡፡ አምላካችን የተወሰደብንን ሰላማችንን ሊመልስልን ፈቃዱ ሆኖ የእኛን ሥጋ በመዋሐድ ሰው ሆኖ በተወለደባት ዕለት ይህን የምሥራች የሚያበሥር የምስጋና ዝማሬ መላእክትና እረኞች በአንድነት ዘመሩ፡፡
ጌታችን በወንጌል “ሰላሜን እሰጣችኋለሁ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም፡፡” (ዮሐ. ፲፬፥፳፯) በማለት እውነተኛው ሰላም የሚገኘው ከእርሱ ብቻ መሆኑን ነግሮናል፡፡ አምላካችን ሰላምን የተወልን ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ነው፡፡ ዛሬ ዓለም ሰላምን ለማምጣት የሚከተለው መንገድ ከዚህ በተለየና በተቃራኒው ነው፡፡ ሌላውን አጥፍቶ እየኖረ ሰላም አገኘሁ ይላል፡፡
ሰላም በሥጋዊ ኃይል የሚመጣ በወረቀት ላይ ብቻ የሚሰፍር በአንደበት የሚለፈፍ አይደለም፡፡ ሰላም ከሰዎች የሚሰጥ ገጸ በረከት ሳይሆን ከውስጣችን የሚገኝ ሕይወት ነው፡፡ ሰላም በመተሳሰብ፣ በመግባባትና በፍቅር የሚመጣ የጤናማ ውይይት ውጤት ነው፡፡ ሰላም የውስጥ እፎይታ የመንፈስ እርካታ የኅሊና እረፍት ነው፡፡ ሰላም በዋጋ የማይተመን ከነገሮች ሁሉ የበለጠ ታላቅ ቁም ነገር ነው፡፡
አምላካችን የሰጠን ሰላም በሰዎች ሥጋዊ አስተሳሰብ ያልሆነና የእግዚአብሔር የሆኑት ብቻ የሚኖሩበት ሕይወት ነው፡፡ ሰዎች የጠፋ ሰላማቸውን ለማግኘት በራሳቸው መንገድ ብዙ ሲደክሙና መውጣት ለማይችሉባቸው ብዙ አጓጉል ሱሶችም ራሳቸውን አሳልፈው ሲሰጡ ይስተዋላሉ፡፡ ሰላም በራስ ኅሊና ውስጥ በትዳር መካከል በቤተሰብ መካከል በሥራ ቦታ በሀገር ውስጥ ሊታጣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔርን የያዘ ግን የትም ቢሔድ ሰላም አለው፡፡ ሰላም የራስ የሆነ ማንም የማይቀማው ከእግዚአብሔር የሚገኝ ሀብት ነውና፡፡
ዛሬ ዓለም ያልተረዳውና ሊኖርበት ያልቻለው ይህን ዕውቀት ነው፡፡ በዚህ ሰላማዊ ሕይወት ኖረው ያለፉ የቀደሙ ሰዎችን የሃይማኖት ጉዞ እንደ ሞኝነት ዘመን እየቆጠረ ራሱን ሲያሞኝ ይታያል፡፡ዓለማችን ለሰላም የቆመ ይመስል ቆሜያለሁ እርስ በእርሱ የሚጠፋፋበትን ከባድ መሳሪያ በማምረት ሥራ ላይ ተጠምዷል፡፡ ሰላሙን ማረጋገጥ የሚፈልገውም ባለው የኃይል ሚዛን ሆኗል፡፡ ሰላም በንግግርና በምኞት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን በተግባር የሚገለጥ እውነት መሆኑን ረስቶ ተቃራኒውንና የመጠፋፊያውን አቋራጭ መንገድ ተያይዞታል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ሰው በራሱ ዕውቀት ብቻ በመመራቱ እና የእግዚአብሔርን ቦታ ለመተካት በመፈለጉ ነው፡፡
የሰው ሕይወት ያለ እግዚአብሔር ሙሉ አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር የሌለው ሰው በውስጡ ባዶነት ይሰማዋል፡፡ ስለሆነም ይበላል ይጠጣል ግን አይረካም፣ ይለብሳል ግን አይደምቅም፣ ይናገራል ግን እርስ በእርሱ አይግባባም፣ ይሮጣል ግን ማንንም አይቀድምም፡፡ (ሐጌ. ፩፥፭) የተመኘውን ሁሉ ለማድረግ ይጣደፋል፡፡ በዚህ ሁሉ ሰላም የለውም፡፡ ይህ የሚሆነው በውስጡ እውነተኛው ሰላም ክርስቶስ ስለሌለው ነው፡፡የጌታችንን ልደት ስናከብር ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠትን፣ ይቅር መባባልን በማሰብ ሊሆን ይገባል፡፡ ዓለማችን ያለችበት ሁኔታ አደገኛና እጅግ ፈታኝ የሆነ ወቅት ነው፡፡ ሁሉም የራሱን ጩኸት እንጂ የሌላውን ሐሳብ የሚያዳምጥበት ጆሮ የለውም፡፡ ጌታችን በተወለደበት ዕለት ሰብአ ሰገል (የምሥራቅ ነገሥታት) ከርቀት ቦታ በኮከብ እየተመሩ መጥተው ለጌታችን ከሰገዱለት በኋላ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ (እጅ መንሻ) አቅርበውለታል፡፡ (መዝ. ፸፩፥፱-፲፩)
በሌላ በኩል ደግሞ ሄሮድስ የተባለው ንጉሥ ጌታን ሊገድለው ይፈልገው ነበር፡፡ ‹‹ታሪክ ራሱን ይደግማል›› ሆነና ዛሬ ዓለማችን አንዱ ለመልካም ሌላው ደግሞ ለጥፋት ተልዕኮ የሚጣደፉባት መድረክ ሆናለች፡፡በዓሉን በምናከብርበት ወቅት በዓለም ላሉ መሪዎች ሁሉ እግዚአብሔር እንደ ሄሮድስ ያለውን የድንጋይ ልብ አውጥቶ እርሱን መፍራትና ማስተዋልን እንዲሰጣቸው ልንጸልይላቸው ይገባል፡፡
የዛሬዋ ዓለማችን ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸው በጡንቻቸው የሚመኩ ከወገንና ከሀገር ይልቅ ለራሳቸው ሥልጣንና ዝና ቅድሚያ የሚሰጡ መሪዎች ስለበዙባት የግፍና የሰቆቃ ዓለም ሆናለች፡፡ የሰው ልጅ ኑሮም የተረበሸና መረጋጋት የጠፋበት ሆኗል፡፡ሰላም በድሃውም በሀብታሙም ቤት ባደጉትም በድሆችም ሀገሮች በትንሹም በትልቁም ሕዝብ መካከል ጠፍቷል፡፡ በዓለም ዙሪያ ያለውና በየቀኑ የሚሰማው ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ መጥቷል፡፡ ዓለም ለመጠፋፋት የሚያውለውን ጊዜ መልካም ወደማድረግ መለወጥ አለበት፡፡
ሰላም ከሌለ ሕፃናት ወጥተው መግባት፣ ሠራተኛው ሠርቶ መኖር፣ ነጋዴው ነግዶ ማትረፍ፣ ገበሬው አምርቶ መኖር አይችልም፡፡ ሰዎች ሁሉ አምላካችን ወደዚህ ዓለም የመጣው ሰላምን ለሰው ልጆች ለመስጠት መሆኑን ተረድተው ለሰላም በጎ ምላሽ ሊሰጡ ይገባል ለሁሉም መሠረቱ ሰላም ነውና፡፡ሄሮድስም ጌታን ያገኘው መስሎት እስከ ሁለት ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ዐሥራ አራት ሺህ ሕፃናት ልብስና ቀለብ እሰጣለሁ ብሎ ሰብስቦ በጭካኔ በሰይፍ አስገደላቸው፡፡ የእርሱ ሐሳብ ጌታን ገድሎ እንደ ልቡ በሥልጣን ላይ ለመኖር ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታንም አላገኘውም፣ በሥልጣኑ ላይም አልቆየበትም፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ካልፈራ ለጭካኔው ገደብ የለውም፡፡ ሥጋዊ ጥቅም እስካገኘለት ድረስ በእርሱ አስተሳሰብ ሰውን መግደልም ትክክል ነው፡፡

ኤል_ማሮስ

05 Jan, 17:07


ቅዱስ ገብርኤል ሌሎችን ሲያበሥር "ዳንኤል ሆይ ቃልህ ተሰምቶልሀል ወደ አንተ መጥቻለሁ " ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ እንዳለው ድንግሊቱን "ማርያም ሆይ ጸሎትሽ ተሰምቶልሻል አላላትም ። ምክንያቱም ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን አንድም ቀን ጸልያም አስባም አታውቅም ። ብዙ የእስራኤል ደናግል "መሲሑን እኔ እወልደው ይሆናል " ብለው ድንግልናቸውን ጠብቀው ኖረዋል ። እርስዋ ግን የተመረጠችው ራስዋን አጭታለት ለማታውቀው ጉዳይ ነበር ። እግዚአብሔር በልብዋ እንጂ በማሕፀንዋ ፀንሶ መኖር በእርሷ ዘንድ አሳብ ሆኖ አያውቅም ።

ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ፦

ብዙ ሴቶች " ድንግል ትፀንሳለች" የሚለውን ትንቢት ሰሙ የነገሥታት ሴት ልጆችና የባለጠጋ ልጆች [መሲሑን] ሊወልዱ በተስፍ ተጠባበቁ ። እርሱ ግን ከድሆች ልጅ ተወለደ ። ጌታ ሆይ በአንተ ምክንያት የነገሦታት ልጆች በድሆች ልጅ ቀኑ ። ወደ ደሃዋ ቤትም ነገሥታት እጅ መንሻ ይዘው ሔዱ ። ( የብርሃን እናት ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ገጽ 160-161)


ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

02 Jan, 19:13


✝️የወር አበባና ጠበል መጠጣት ✝️

በወር አበባ ፦ በዚህ ወቅት ያለች ሴት ሰውነቷ ድክምክም ይላል። አንዳንድ ሴቶች ደግሞ ከበድ ያለ ሕማም ሊሰማቸው ይችላል። ከጠበል አገልግሎት ውስጥ አንዱ ደግሞ የሥጋንን ሕማም ማጥፍት ጭምር ነው ። ይህች በወር አበባዋ ጊዜ ከበድ ያለ ሕማም የሚሰማት ሴት ሕማሟ እንዲቀንስላት ጠበል ብትጠጣ መልካም አይደለም ተብሎ ሊታሰብ የሚችለው እንዴት ነው?

በእውነተኛይቱ ሃይማኖት ውስጥ የሌሉ ኢ አማንያን እንኳን መጥተው ከሥጋቸው ደዌ ለመፈወስ የሚጠጡትን እና የሚጠመቁበትን ጠበል እንዴት በእውነተኛይቱ እምነት ውስጥ ያለችው ሴት ተፈጥሮአዊ በኾነ መንገድ ከሰውነቷ ስለሚወጣው ደም ሲባል ከእነዚያ አንሳ አትጠጪ ልትባል ትችላለች ?

ትጠመቅ ተብሎ ቢኾን ይህንን እድፍ በቅዱሱ ጠበል አማካኝነት ለማንጻት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም ? ተብሎ ሊጠየቅ ስለሚችል ፤ ጥያቄው ተገቢ ስለ ኾነ መጠመቅ አይችልም ። መጠጣት ግን ሕማማቸውንም የሚቀንስላቸው ስለ ኾነ አይከለከልም ። ጠበልን መጠጣት የወር አበባ ላይ ከመኾን ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም ሊኖርም አይችልም ። ስለዚህ ጠበል መጠጣት አትችልም የሚለው እሳቤ ስሕተት መኾኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል ። ። ( መጽሔተ ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው ገጽ 243-244)

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

01 Jan, 19:23


🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇

ኤል_ማሮስ

01 Jan, 11:32


+ አሳቧ እንደ አምላክ አሳብ ነው +

የማርያም አሳብ አንደ አምላክ አሳብ ነው ማለት ምን ማለት ነው ?

አንደኛ ይህ ማለት የእመቤታችን አሳብ ፈጽሞ ለእግዚአብሔር አሳብ የተገዛ መኾኑን የሚያመለክት ነው ። ሕይወቷ በሙሉ ለእግዚአብሔር  የተሰጠና የተለየ ነው ፤ እግዚአብሔር ከሚፈቅደው ውጭ አስባም  ሠርታም አታውቅም ማለት ነው ። ለዚህም ነው የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ሲያበስራት እንኳን ምን ብላ ታስብ እንደ ነበር ቅዱስ ሉቃስ ሲገልጥ ሉቃ 1፥29 "እርሷዋም በአየችው ጊዜ ከንግግሩ የተነሳ ደነገጠችና "ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው " ብላ ዐሰበች ።" ተብሎ የተገለጸው ።

ቅዱስ ገብርኤል ያቀረበላት ምስጋና የሚገባት ኾኖ ሳላ ይገባኛል ብላ አልተቀበለችም ፤ ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው ብላ ዐሰበች እንጂ ። ይህ የሚያመለክተው ፈጽሞ ከከንቱ ውዳሴ የራቀች መኾኗን ነው ። ቅዱስ ሉቃስም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አሳቧን የጻፈልን በዐሳቧ ያለትን ፍፁም ንጽሕና እንድንረዳውና እንድናደንቅም ለማድረግ ነው ። በእርግጥ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ የሚያቀርብላትን ልዩ ምስጋና አይገባኝም ብሎ ራስን ዝቅ የማድረግ ንግግር ሳይኾን ዐሳብ እንዴት አስገራሚ ነው !! ይህም ፍጹም ራሷን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ብቻ ማስገዛቷን ሌላ ምንም ዓይነት ነገር አለመፈለጓን የሚያስረዳ ነው ። (ትምህርተ ጽድቅ ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው ገጽ-60)


ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

26 Dec, 13:54


ምሥጢረ #ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለመሆኑ

+ በብሉይ ኪዳን +

+ ኦሪት ዘፍ 1፥26 ( "በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር" )

+ ዘፍ 3፥22 ("ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" )

+ ዘፍ 11፡6-7( “ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው ) ።

+ ኢሳ 6-3( “አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
+ ዘፍ 18፥1 ፦
#እግዚአብሔር ለአብርሃም በአንድነት በሦስትነት እንደተገለጠ (ቁ1.እግዚአብሔር ተገለጠለት ቀ2.እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ )

+ በሐዲስ ኪዳን +

+ ማቴ 3፥16 ( ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
¹⁷ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።)

+ ማቴ 17፥5 (“እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።)

+ ማቴ 28-19 (“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”)
+ ሉቃ 1፥35



( ላዕከ ወንጌል መምሕር ወሰን የለው በሐሩ እየሰጡት ካለው ስልጠና የተወሰደ )

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

25 Dec, 20:14


✝️ቤዛ ✝️

ቤዛ በቁሙ ዋጋ ፤ ካሳ ፤ ለውጥ ፤ ምትክ ፤ ዐላፈ ፤ ዋቢ ፤ ዋስ ፤ መድን ፤ ተያዥ ፤ ጥላ ጋሻ ፤ ማለት ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህች ምድር የመጣበት እና መከራ መስቀሉን የተቀበለበት ዋና ምክንያት ደግሞ አዳምና ልጆች ስለ በደልነው በደል ልንቀበለው የሚገባንን መከራና ስቃይ እኛን ተክቶ በመቀበል በመከራው መከራችንን አጥፍቶ በሞቱ ሕይወትን ሊሰጠን ነው ። ቤዛነትም እያልን ያለነው ይህንን ነው ።

ጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በመሞቱ በሦስት መንገድ ቤዛ ሆኖልናል ። አንደኛ በኦሪት የፈሰሰው ብዙ የእንስሳት ደም ሊያድነው ባለመቻሉ እውነተኛ መስዋዕት በመሆን በመከራው መከራችንን በሞቱም ሞታችንን አጥፍቶ በትንሣኤው ትንሣኤያችንን አውጆልናልና ። ሁለተኛው ሥጋውና ደሙን እውነተኛ የሕይወት ምግብ አድርጎ ሰጥቶናል ።ሦስተኛ ደግሞ የወንበዴዎች መቀጫ የነበረውን መስቀል የዲያብሎስ ድል መንሻ አድርጎ ሰጥቶናል። ነቢዩ ኢሳይያስ ጌታ የተሰቀለው ለእኛ ቤዛ ሊሆነን እንጂ በደል ኖሮበት እንዳይደለ ሲያብራራ "በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞልናል እኛ ግን እንደተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሰፈ አንደ ተቸገረም ቆጠርነው ። እርሱ ግን ስለመተላለፍችን ቆሰለ ስለበደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሳጽ በእርሱ ላይ ነበር በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዘበዝን ጠፍን ከእኛ እያንዳንዱን ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ " ብሏል ኢሳ 53፥4-6 ( "እውነተኛ ክርስትና" ተሶፍዬ ምትኩ ገጽ-256)

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

25 Dec, 20:01


ከሚከተሉት ውስጥ የማይደገመው የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር የቱ ነው??

ኤል_ማሮስ

25 Dec, 19:20


የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ 👇

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

👤 ሊቀ መዘምራን . ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

👤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

👤 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

👤 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

👤 ዘማሪ| በሱፍቃድ አንድአርጋቸው

👤 ዘማሪት ሲስተር ሊዲያ ታደሰ

👤 ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ

👤 ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

👤 ዘማሪ ዲያቆን ብርሃኑ በቀለ

👤ዘማሪት አዜብ ከበደ

👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ

👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ

👤 ዘማሪት ሰላማዊት በርታ

የሁሉንም ዘማሪዎች ለማግኘት🎚

ኤል_ማሮስ

25 Dec, 16:32


+ ወደ አምላኬ የማለቱ ሚሥጢር +

ዮሐ 20፥17

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብን "አምላኬ" ያለበት ምሥጢር ፦ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው ቅድመ ተዋሕዶ ፍጡር የነበረውን በመቃብር ጥሎ አለመኾኑን ለማስገንዘብ ነው ። አካላዊ ቃል የሰውን ልጅ ሥጋና ነፍስ ነሥቶ ሰው የኾነው ፥ በፍጹም ተዋሕዶ ነውና ፥ ስለእኛ ሞቶ ሞትን ድል አድርግ ሲነሳ ቀድሞ የተዋሐደውን ሥጋ አለመቅረቱን ለማስረዳት ነው ። አምላክ የሰውን ልጅ ሥጋና ነፍስ ተዋሕዶ ሰው የኾነው ድኅነትን ከፈጸመ በኋላ የተዋሐደውን ሥጋ ትቶ ለመሄድ አይደለምና። የአካላዊ ቃልና የሥጋ ተዋሕዶ ከኾነ ጊዜ በኋላ የሚቀር ሳይኾን ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር ነው ። በዚህ ምክንያት "አባቴ" ያለው እርሱ ራሱ መልሶ "አምላኬ" በማለት የቃልና የሥጋ ተዋሕዶ ከትንሣኤ በኋላ የጸና እንደ ኾነ አሰረዳን ። ስለዚህ "አባቴ" አምላኬ ማለቱ ጽንዓ ተዋሕዶ የሚያስረዳ መኾኑን ልብ ይሏል። ( ትምህርተ ጽድቅ ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው ገጽ 283 )

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

25 Dec, 05:36


+ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ +

ምን ማለት ነው ?

"የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሚኾን ወደ ኢየሱስ ፥ ከአቤል ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደ ሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።"ዕብ 12፥24 ፤ "አንድ እግዚአብሔር አለና ፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ። " 1ኛ ጢሞ 2፥5

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛም እውነተኛም የሰውና የእግዚአብሔር መካከለኛ ነው ። ለምን ?

የነሣው ሥጋ የሰው ነውና ፦

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነሣው ሥጋና ነፍስ የሰው ነው ።ይኸውም ትምክሕታችን ከምትኾን ከቅድስት ድንግል ማርያም ነው ። ሉቃ 1፥26-45 ፣ ማቴ 1፥1 ። ሥጋውን ከሰው ባይነሣ ኖሮ "ሰው" ሊባል አይችልም ነበር ። የሰውና የእግዚአብሔር መካከለኛ ሊባል አይገባውም ነበር ። አምላክ የኾነ ሰው ሰው የኾነ አምላክ ከእርሱ በቀር የለምና ከእርሱ በቀር የለምና "መካከለኛ" የተባለ ወልደ እግዚአብሔር የነሣው ሥጋ ስለኾነ ነው ።


ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

24 Dec, 19:26


+‹‹ ፈጥኖ ይመጣል ››+

በመጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት ስሙ የተጠቀሰው እረጅም ዓመት የኖረው ማቱሳላ የስሙ ትርጉም፦ "ይሞታል" "ሟቹ" ደግሞም "ፈጥኖ ይመጣል" "ይደርሳል" የሚል ነው ። ታድያ እረጅም ዓመት ሰው ስለኖረ ሳይሞት የሚቀር እንዳይደለ ማስተማርያ ነው ። ከበዛ አርባ ሰማንያ ምንኖር እኛ ቀብርም እየሄድን ወሬው ሞትን ስለ ማሰብ ሳይሆን ሰለመርሳት ነው እርሱ ግን ፈጥኖ ይመጣል ። ከልጁ ያነሰ እድሜ የኖረው ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም ወስዶታል ተባለለት" ከክፍት ጋር ያለንን አካሄድ ጉዞ ከገታን ትንሽ እድሜም ብዙ ከክርቶስ ጋር መኖርን አታግድም ። አሁን ትልቆች ወደኋላ ሚያድጉበት አባቶች ያልናቸው ፖለቲከኛ ሚሆኑበት ፖለቲከኞች አባቶች ልሁን ያገባኛል ያሉበት ጊዜ ላይ ነን ። አካሄድን ከእግዚአብሔር ጋር ከማድረግ ይልቅ ሹመቱም ፈጥኖ እንዲደርስለት ሚሮጥበት እረጅም እድሜ ሚኖር ይመስል ሚባከንበት ነው ። ሐዋርያው" ቅምጥሊቱ ግን በሕይወት ሳለች የሞተች ናት "1ኛ ጢሞ 5፡6 የጽድቅ ስራ ተረስቶ ስለምድር ነገር ምታስብ ነብስ በምድር እያለችም ከእርሱ ከክርስቶስ ከተለየች የሞተች ናት ። ቅዱሳን ግን ዘወትር ሞታቸውን እየናፈቁ " ልሄድ ከክርስቶስ ጋር እናፍቃለሁ፣ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና ። ይላሉ (ፈል 1፡23) የሞትን ፈጥኖ መምጣት ማሰብ ግን ወደ ክርስቶስ ታደርሳለች ።

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሐምሌ 21 2015 ዓ.ም

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

24 Dec, 19:23


ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በሰላም ዘርፍ እጩ በመሆን ተመረጡ !

ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ አዲስ አበባ)

አንቴክስ የተሰኘ የቻይና ልብስ አምራች ድርጅት ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን በሰላም ዘርፍ እጩ አድርጓቸዋል።

ብፁዕነታቸው በጦርነት ውስጥ ሆነው ሁሌም ስለ ሰላም የሚሰብኩና ለተገፉ ሁሉ የሃይማኖትና የዘር ልዩነት ሳያደርጉ ከልብ በመነጨ ሰብአዊነት ከወደቁበት ለማንሳት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለዓለም ኹሉ የሚያስተጋቡ መሆናቸው ተገልጿል።

የብፁዕነታቸው የመወዳደሪያ ኮድ 08 ሲሆን BIW በማስቀደም ማለትም BIW08 በማስገባት 9355 ላይ በSMS ድምፅ መስጠት የሚቻል ሲሆን ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታኅሣሥ 17 ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የሚቆይ ሲሆን የዘርፉ አሸናፊ የ 10 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እንደሚሆንም ተገልጿል።

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

15 Dec, 07:46


#አርሴማ🙏🥰

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

15 Dec, 06:31


ያልተሰጠህን አትሻ

የተሰጠህን ጸጋ እንዳታጣ ያልተሰጠህን አትሻ፡፡ ወደ ጸጋ ወደ ክብር ለመድረስ እግዚአብሔር ቢያበቃህ ያሳየህን እይ ያላሰየህን አያለሁ አትበል። አንድም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፣ በተሰጠህ ጸጋ ለእግዚአብሔር ተገዛ፡፡ ማር አብዝቶ መመገብ እንዳይመች እንደዚህም ሁሉ ያልተሰጠውን መሻት አይገባም አያስመስግንም፡፡

ነፍስ ያልተሰጣትን ጸጋ በመሻት እንዳትደክም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፡፡ የምታየው ማየት ቢኖር እውነተኛውን ምትሐት ሆኖ ታየዋለህ ፤ ሕሊና ያልሰጡትን ጸጋ በመሻት በማውጣት፣ በማውረድ የተሰጠውን ያጣል፡፡

ሰሎሞን መልካም ነገር ተናገረ "በሰጡት ጸጋ የማይኖር ሰው ቅጽር የሌላትን አገር ይመስላል" ብሎ ያን ማንም እየገባ እንዲዘረፈው እሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል ፤ አንተ ብሩህ አእምሮ ሰውነትህን ያልተሰጣትን ጸጋ እንዳትሻ ከልክላት፡፡

ከቁመተ ሥጋ የወጣ አብዝቶ መገበርን ከአንተ አርቅ ያልተሰጠህን መሻት ከአንተ አርቅ፡፡ ባልተሰጠህና በተሰጠህ ጸጋ መካከል ትሕትናህን፣ ንጽሕናህን መጋረጃ አርጋቸው:: አንድም በተሰጠህ ጸጋ ላይ ያልተሰጠህን ጋርደው፡፡ በንጽሕና፣ በትሕትና፣ በልቡናህ የምታስበውን መንፈሳዊ ክብር ታገኛለህ::

ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱

ኤል_ማሮስ

11 Dec, 18:17


ታላቅ የንግስ ጕዞ ወደ ይርጋለም አርሴማ

👉መነሻ ቀን :- ታህሳስ 5

👉መመለሻ :- ታህሳስ 6

የጉዞ ሁኔታ :- አዳር

💰 የጉዞ ዋጋ 1500 ብር

🍽 ሙሉ መስተንግዶን ጨምሮ

🛑 በመንገዳችን ሀዋሳ ገብርኤልን እንሳለማለን ✝️

መነሻ ፒያሳ ጊዮርጊስ, መገናኛ, ጎሮ አደባባይ

👉 መመዝገብ የምትፈልን ከስር ባሉት ስልኮች ደደውሉልን👇

0929 24 38 37

09 29 48 15 96

ኤል_ማሮስ

11 Dec, 18:15


"በቅድስና ወበንጽሕና ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ"

በቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ኦ ፡ ድንግል ፡ አኮ ፡ በተላህዮ ፡ ዘልሕቂ ፡ ከመ ፡
ዐዋልደ ፡ ዕብራውያን ፡ እለ ፡ ያገዝፋ ፡ ክሣዶን ፡
ድንግል ፡ አንገታቸውን ፡ እንደሚያገዝፉ ፡ እንደ ፡ ዕብራውያን ፡ ልጆች ፡ በቧልት ፡ በጨዋታ፡ ያደግሽ ፡ አይደለሽም ። ሐተታ ። እለ ፡ ያገዝፋ ፡ማለቱ ፡ አታሞ ፡ ሲመቱ ፡ አንገታቸው ፡ ይነፋል፡
እስክስታ ፡ ሲወርዱ ፡ ይቀጥናልና ።

አላ ' በቅድስና ፡ ወበንጽሕ ፡ ውስተ ፡ ቤተ ፡
መቅደስ ፡ ነበርኪ

በቅድስና፡ወበንጽሕ፡ ያለውን ፡ ይሻል • በቤተ ፡ መቅደስ ፡ በቅድስና ፡ በንጽሕና ፡ ኖርሽ ፡ እንጂ ። አንድም ፡ ግዙፉነ ፡ ልብ ፡ እንደሚሆኑ ፡ እንደ ፡ዕብራውያን ፡ ልጆች ፡ በቧልት ፡ በጨዋታ ፡ ያደግሽ ፡ አይደለሽም ። በቤተ ፡ መቅደስ ፡ ያለውን ፡ይሻል ፡ በቅድስና ፡ በንጽሕና ፡ በቤተ ፡ መቅደስ፡ኖርሽ ፡ እንጂ ።

☞ ኦ ፡ ድንግል አኮ ፡ ኅብስተ፡ምድራዌ፡ዘተሴሰይኪ።
ኦ፡ ድንግል ፡ ምድራዊ ፡ ኅብስትን ፡ የተመገብሽ ፡ አይደለሽም፡አንድም፡የተመገብሽው፡ ምድራዊ ፡ኅብስት ፡ አይደለም ።

አላ ፡ ኅብስተ ፡ ሰማያዌ ፡ እምሰማየ ፡ ሰማያት ፡
ዘበሰለ ።ከሰማይ የተገኘ ፡ ኅብስትን ፡ ተመገብሽ፡እንጂ፡

ሐተታ ። በሰማይ ፡ ስንዴ ፤ አበዛ ፤ ምጎጎ ፤ ኑሮ ፡ አይደለም ፤ በሰማያዊ ፡ በመልአኩ ፡ እጅ ፡ ስለ፡መጣ ፡ ከወደ ፡ ላይ ፡ መምጣቱን ፡ ሲያይ ፡ በግብር፡ አምላካዊ ፡ ከወደ ፡ ላይ ፡ መገኘቱን ፡ ሲያይ ፡እንዲህ ፡ አለ ።

ኦ ፡ ድንግል ፡ አኮ ፡ ስቴ ፡ ምድራዊ ፡ ዘሰተይኪ፡
ድንግል ፡ ምድራዊ ፡ መጠጥን ፡ የጠጣሽ ፡ አይደለሽም ፤ አንድም ፡ የጠጣሽው ፡ ምድራዊ መጠጥ ፡ አይደለም "

አላ ፡ ስቴ ፡ ሰማያዌ ፡ እምሰማየ ፡ ሰማያት ፡ዘተቀድሐ ።ከሰማይ ፡ የተገኘ ፡ ሰማያዊ ፡ መጠጥን ፡ ጠጣሽ ፡እንጂ ።

ሐተታ ። እምሰማየ ፡ ሰማያት ፡ ዘተቀድሐ
ማለቱ ፡ በሰማይ ፡ ወይን ፤ ማድጋ ፡ አሳላፊ ፡ ኑሮ ፡አይደለም ። በሰማያዊ ፡ በመልአኩ ፡ እጅ ፡ ስለ ፡ተገኘ ፡ ከወደ ፡ ላይ ፡ መምጣቱን ፡ ሲያይ ፡ በግብር አምላካዊ ፡ ስለ ፡ ተገኘ ፡ እንዲህ ፡ አለ ፤ አንድም ኅብስት ፡ ምድራዊና ፡ ስቴ ፡ ምድራዊ ፡ ዘተሴሰይኪና ፡ ዘሰተይኪ ፡ አንድ ፡ ወገን ። የወለድሺው በዘር ፡ በሩካቤ ፡ የተፈጠረ ፡ ዕሩቅ ፡ ብእሲ ፡ አይደለም ። ዘበሰለና ፡ ዘተቀድሐ ፡ አንድ ፡ ወገን ፡ቅድመ ፡ ዓለም ፡አካል፡ዘእምአካል ፡ ባሕርይ፡
ዘእምባሕርይ ፡ የተወለደ ፡ አካላዊ ፡ ነው ፡ እንጂ።

ታሪክ ፤ እመቤታችን ፡ የብፅዓት ፡ ልጅ ፡በተወለደች ፡ በሦስት ፡ ዓመት ፡ ሐና ፡ ኢያቄምን፡ ልጅ ፡ ናት ፡ ይህች ፡ ብላቴና ፡ ሆዷ ፡ ዘመድ ፡ ሳይወድ ፡ ኦፏ እህል ፡ ሳይለምድ ፡ ወስደን ፡ አንሰጥምን ፤ የሰጠ ቢነሣ ፡ የለበት ፡ ወቀሳ ፡ እንዲሉ ፤ አንዳች ፡ ብትሆንብን ፡ ከልጃችንም፡ ከእግዚአብሔርም ፡ ሳንሆን፡ እንዳንቀር ፡ አለችው ። ፍቅርሽ ፡ ያልቅልሽ ፡ ብዬ ፡ነው ፡ እንጂ ፡ እኔማ ፡ ፈቃዴ ፡አይደለምን ፡ አላት።

ከፍቅሯ ፡ ጽናት ፡ የተነሣ ፡ ከጭኑዋ ፡ አውርዳት ፡አታውቅም ። አንድ ፡ ቀን ፡ ብቻዋን ፡ አድርጋ ፡ከደጅ ፡ ወጥታ ፡ ብትመለስ ፡ መልአክ ፡ ሰውሮባት ፡ ጥራ ፡ አግኝታታለች ፡ ከዚያ ፡ በኋላ ፡ ያው ፡
እየመሰላት ፡ ተለይታት ፡ አታውቅም ። ወስደው ፡ለቤተ ፡ መቅደስ ፡ሰጧት ፤ ሊቀ ፡ ካህናቱ ፡ ዘካርያስ ፡ የምግቧ ፡ ነገር ፡ ይያዝልኝ ፡ ብሎ ፡ መጥቅዕ ፡ መትቶ ፡ ሕዝቡን ፡ ሰብስቦ ፡ ሳለ ፤ መልአኩ፡
ፋኑኤል ፡ ኅብስት ፡ ሰማያዊ ፡ ጽዋዕ ፡ ሰማያዊ ፡ይዞ ፡ ረቦ ፡ ታየ ፡ ዘካርያስ ፡ ለኔ ፡ የመጣ ፡ ሀብት፡ ነው ፡ ብሎ፡ ለመቀበል፡ ቢነሣ፤ ወደ፡ ላይ፡ ራቀበት።

የሊቀ ፡ ካህናቱ ፡ ተወራጅ ፡ ስምዖን ፡ ይባላል ። እሱም ፡ ለመቀበል ፡ ቢነሣ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ራቀበት ፤ከዚህ ፡ በኋላ ፡ ጥበበ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይመረመርምና ፡ ምናልባት ፡ ለዚህች ፡ ብላቴና ፡ የመጣ ፡ሀብት ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ እስቲ ፡ እንየው ፡ ብለው ፡ለብቻዋ ፡ አድርገዋት ፡ ፈቀቅ ፡ ቢሉ ፤ ድንኩል፡ድንኩል ፡ እያለች ፡ እናቷን ፡ ስትከተል ፤ መልአኩ ፡ ፈጥኖ ፡ ወርዶ ፡ አንድ ፡ ክንፉን ፡ አንጽፎ
አንድ ፡ ክንፉን ፡ ጋርዶ ፡ በቆመ ፡ ብእሲ ፡ ያህል ምድር ፡ አስለቅቆ ፡ መግቧት ፡ ዐረገ ። የምግቧ፡ነገር ፡ ከተያዘልን ፡ ከሰው ፡ ጋራ ፡ ምን ፡ ያጋፋታል ፡ ብለው ፡ ከቤተ ፡ መቅደስ ፡ አግብተዋት ፡ዐሥራ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ ኑራለች ። ከመዝ ፡ ነበርኪ ፡ ውስተ ፡ ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ወመላእክት ፡ ያመጽኡ፡ ወትረ ፡ ሲሳየኪ ፤ ከመዝ ፡ነበርኪ፡ዐሠርተ፡
ወክልኤተ ፡ ዓመተ ፤ እንዘ ፡ ትትናዘዚ ፡ እምኀበ ፡መላእክት ፡ እንዲል ።

የእናትነት ፍቅሯ የአማላጅነቷ በረከት አይለየን።
እንኳን አደረሳችሁ።

ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን👇
@EL_MAROS
@EL_MAROS📱