Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት) (@diresabian2011)の最新投稿

Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት) のテレグラム投稿

Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት)
Wel Come To Our School.
3,463 人の購読者
3,524 枚の写真
126 本の動画
最終更新日 01.03.2025 04:22

Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት) によってTelegramで共有された最新のコンテンツ


https://bit.ly/3Dz0qd9 ( ለ2017.ዓ.ም ለግል አመልካች /ፕራይቬት ተመዝጋቢዎች ፎርም ለመሙላት የአጠቃቀም መመሪያ )

ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለቁሉቢ ገብርኤል ንግስ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረስን፡፡ መልካም በአል !!!

ታህሳስ 18/2017ዓም
በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የሚደረገው የጥያቄ እና መልስ ውድድር የመክፈቻ መርሃግብር በድምቀት ተጀመረ።

በሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚካሄደውን የጥያቄ እና መልስ ውድድሩን በይፋ ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ በውድድሩ መክፈቻ እንደተናገሩት የጥያቄ እና መልስ ውድድር በክፍል ውስጥ ከሚደረግ የመማር ማስተማር ሂደት ባለፈ ተማሪዎች እርስ በርስ በማቀራረብ ለትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ከማስቻሉም በተጨማሪ በውድድር መንፈስ ከተለያዩ መፅሃፍት ላይ እውቀትን በማሰስ ትምህርታዊ ድረ-ገፆችን በመጠቀም ራሳቸውን ለማብቃት የሚያስችላቸው በመሆኑ ብቁ እና ተስፋ ሚጣልበት ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከማፍራት አንፃር ጉልህ ሚና አለው ብለዋል::

የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ከአለፈው ዓመት ተሞክሮው በመነሳት ዘንድሮም ውጤቱን በማስጠበቅ በዚህ እንቅስቃሴው በአስተዳደር ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን በማፍራት እንደሚታወቅ ገልፀው ከፊታችን በሚደረገው አስተዳደር አቀፍ ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ከትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ውጤቱን አስጠብቆ ለመሄድ የሚያስችል የቤት ስራውን ከወዲሁ መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኤጀታ መኮንን በበኩላቸው ይህ "ተወዳዳሪነት ለላቀ ውጤት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የ12 ተኛ ክፍል የጥያቄ እና መልስ ውድድር ለቀጣዮቹ 6 ሳምንታት የሚካሄድ መሆኑን ገልፀው ተማሪዎችን ለትምህርታቸው ተገቢውን ትኩረት እንዲያደርጉ ለእውቀት ከማነሳሳት ባሻገር በአስተዳደር ደረጃ ለሚዘጋጀው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ብቁ እና እጩ ተማሪዎችን የሚመረጡበት መድረክ አንደሚሆን አመላክተዋል።

በመሆኑም ባጠቃላይ የጥያቄ እና መልስ ዙር 460 የሚጠጉ ጥያቄዎችን በማካተት ተማሪዎች ራሳቸውን አንዲፈትሹ እና ለ12ተኛ ክፍል የምዘና ፈተና ዝግጁ ለማድረግ እንዲሁም እንደ አስተዳደር ወካይ የሆኑ ተማሪዎች ለማፍራት ጥረት እና ሂደቱ በተጠናከር መልኩ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል። በውድድሩ መጨረሻም ከ8 ተወዳዳሪዎች 6ቱ ለቀጣይ ዙር ማለፋቸው ተገልጿል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Facebook፡- https://www.facebook.com/dire.educ?mibextid=ZbWKwL
Telegram፦ https://t.me/DireDawa_14
Tiktok፡- https://www.tiktok.com/@diredawaeducationbureau
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Weynshet Getahuru _12. M

Edlawit Habtamu 12N

EHDINA UMER 12F

KENENISA JEMAL MOHAMED

AISHA BILISA _12. N

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አክሰስ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓትን ተካሄደ
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አክሰስ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም (English Access Scholarship Program) ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮች፣ የመንግስት ትምህርት ቤት ተወካዬች፣ ተማሪዎች እና የተማሪ ቤተሰቦችን ጨምሮ ከ90 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም አክብሯል። ከህዳር 2017 እስከ መስከረም 2019 ዓ.ም. ለሁለት አመት በሚቆየው በዚህ ነፃ የትምህርት ዕድል ከስድስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 18 ሴትና 18 ወንድ፣ በድምሩ 36 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በመክፈቻ ንግግራቸው የፕሮግራሙ አላማዎች የተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ከማሳደግ በተጨማሪ፣ ለወደፊት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸ የሚያግዝና እና በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማበረታታት መሆኑን አስረድተዋል። ዶ/ር ኡባህ በተጨማሪ በፕሮግራሙ ተሳታፊ ለሆኑ ተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው በፕሮግራሙ ስኬታማ የሆነ ጊዜ እንዲያሳልፉ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው አሳስበው እና ፕሮግራሙ በድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ እንዲጀመር አስተዋፅዖ ላደረጉት ለአሜሪካ ኤምባሲ እና ለዩኒቨርሲቲው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማእከል ምስጋና አቅርበዋል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የአሜሪካ ኤምባሲ ይህንን ፕሮግራም በማስጀመርና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላደረገው አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበው፣ ዩንቨርሲቲው ለፕሮግራሙ መሳካት አመቺ የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ አስፈላጊውን ሁሉ ድግፍ እንደሚያረግ ገልፀዋል። ተማሪዎችም የወደፊት ስኬታቸውን እውን ለማድረግ ይህን ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።

በአሜሪካ ኤምባሲ የምስራቅ አፍሪካ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ኦፊሰር (Regional English Language Officer- RELO East Africa) የሆኑት ዶ/ር ጂና ሮድስ በፕሮግራሙ መጀመር መደሰታቸውን ገልፀው ተማሪዎቹ የእንግሊዘኛ ቌንቋ ችሎታቸውን በማሻሻል የወደፊት የስራ እድላቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ አብራርተዋል። ተማሪዎች የአመራርና ችግር ፈቺ ክህሎትን ለማዳበር በተዘጋጁ የመስክ ተግባራት ላይ እንደሚሳተፉ ገልፀዋል።

የአክሰስ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ነቢል መሀመድ የፕሮግራሙን ዋና ዋና መገለጫዎች፣ መርሃ ግብሮች እና ተማሪዎችን የተመረጡበትን ሂደት አስረድተው፣ ተማሪዎቹ ፕሮግራሙን በተሳካ ሁኔታ እንዲያጠናቅቁ የወላጆች ተሳትፎና እገዛ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ የተማሪ ወላጆች በፕሮግራሙ መጀመር የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

በመጨረሻም የፕሮግራሙ ተሳታፊ ሆነው የተመረጡት 36 በፕሮግራሙ ተሳታፊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከዶ/ር ኡባህ እና ከዶ/ር ጂና ተረክበው ስነ-ስርዓቱ ተጠናቋል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: https://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

COMING SOON