ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንናና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስርና ወከባ በፅኑ አውግዟል።
ዛሬ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ ሕገ ወጥ ድርጊት መፈፀሙን የገለፀው ቅዱስ ሲኖዶስ፤የተፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ቤተክርስቲያን ፍጹም ታወግዛለች ብሏል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26/2015 ዓ/ም ካስተላለፈው ውሳኔና ከሰጠው መግለጫ ጋር ተያይዞ ዛሬ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል(ከላይ ተያይዟል)።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪዎቹ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።
በየካቲት 5/2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር/የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤በማጀብ በዝማሬና በምህላ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ወስኗል፡፡
@tikvahethiopia