Neueste Beiträge von BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE) (@bps098) auf Telegram

BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE) Telegram-Beiträge

BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)
ቦሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
1,801 Abonnenten
976 Fotos
8 Videos
Zuletzt aktualisiert 06.03.2025 04:35

Ähnliche Kanäle

Dr.Haddis
2,179 Abonnenten

Der neueste Inhalt, der von BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE) auf Telegram geteilt wurde.

BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

27 Feb, 13:50

691

ቀን 20/06/17
ለተማሪ ወላጆች በሙሉ
በጠቅላላ ጉባኤዉ ስብሰባ ላይ በማይገኙት የተማሪ ወላጆች ላይ የተወሰነዉን ቅጣት በተማሪወች የክፍል ሃላፊ/ስም ጠሪ በኩል እተሰበሰበ ሲሆን የልማት ክፍያ ያልከፈላችሁ ደግሞ እንድታጠናቅቁ እያሳሰብን ከዚህ ዉጭ ምንም ኣይነት ክፍያ የማይከፈል መሆኑን እናሳዉቃለን፡፤
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

23 Feb, 16:41

1,424

ከ9 _12 ክፍል ለምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ ትምህርት ቤቱ የሰጣችሁን መጽሐፍ ከነገ 17/06/2017 ዓ ም ጀምሮ ይዛችሁ መገኘት እንዳለባችሁ እና ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግ እናሳውቃለን።
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

21 Feb, 16:49

1,688

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያካታቸዉ ይዘቶች

(የካቲት 14/2017 ዓ.ም) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያካታቸዉ ይዘቶችን አስመልክቶ የሚከተሉትን ነጥቦች አስቀምጣል፤

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት ፣ ከ11ኛ-12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡ በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ አሉ፡፡

በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-

1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት
2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች
3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች
4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል
5) የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

18 Feb, 17:37

1,820

በቀን 06/06/17 የተካሄደውን የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድርን ከላይ በተገለጸው ቀን በፋና ቲቪ ይከታተሉ
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

18 Feb, 17:34

3,597

በአዲስ አበባ የሚከበረውን 19ኛውን የናይል ቀን በማስመልከት የተዘጋጀ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር፤ ሐሙስ ምሽት ይጠብቁን
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

13 Feb, 19:15

2,625

ቀን 06/06/17
ለት/ቤታችን የተማሪ ወላጆች በሙሉ
እሁድ ( በ09/06/17ዓ.ም ) የት/ቤቱን የ2017ዓ.ም የስድስት ወር/ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለወላጆች በማቅረብ መወያየት አስፈላጊ ስለሆነ ሁላችሁም ከጠዋቱ 2:30 በት/ቤቱ ቤተመፅሃፍት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ
ት/ቤቱ በነገው ዕለት ማለትም በቀን 07/06/17ዓ.ም የወላጅ መጥሪያ ደብዳቤ ለተማሪወቹ ይሰጣል ስለሆነም ወላጆች በምትመጡበት ጊዜ ከተማሪወቻችሁ የመጥሪያ ደብዳቤውን ተቀብላችሁ ይዛችሁ እንድትገኙ እያልን በድጋሜ አጥብቀን እናሳስባለን።
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

13 Feb, 18:39

1,406

በቦሌ ክላስተር ማዕከል በተካሔደ የሒሳብና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ጥያቄና መልስ ውድድር ትምህርት ቤታችን አሸናፊ ሆኗል። ተሳታፊዎችን ከልብ እናመሰግናለን።
በተያያዘ ዜና የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዙሪያ በተካሔደ የጥያቄና መልስ ውድድር ተሳትፎ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ለት/ቤቱ የግድግዳ ሰዓት ለተማሪዋ ሳምሰንግ ስልክ ማሸነፍ ተችሏል።
በታህሳስ ወር በተካሔደ የ Book review ውድድር በከተማ ደረጃ 4ኛ መውጣታችን የሚታወስ ነው። ለውጤቱ የተጋችሁ ተማሪዎች እና መምህራን ከልብ እናመሰግናለን!!
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

11 Feb, 18:04

2,069

ቀን 04/06/17
ለት/ቤታችን ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በሙሉ
የ2ኛ ሴሚስተር ት/ት ሰኞ ማለትም 03/06/17 የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ተማሪወች በት/ት ገበታቸው ያልተገኙ ስለሆነ ወላጆች ልጆቻችሁን ወደ ት/ቤት በሰዓቱ እንዲሄዱ በማድረግ የበኩላችሁን ሃላፊነት እንድትወጡ በማለት በጥብቅ እያሳሰብን ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ቢገኝ ማለትም በት/ት ገበታ ላይ /በሚቀሩ ተማሪዎች ላይ የት/ቤቱ ርዕሳነ መምህራን በየክፍሉ አቴንዳንስ በመያዝ የዲሲፒሊን መመሪያው በሚያዘው እንዲሁም በ4ዮሽ ውል በተፈራረምነው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

10 Feb, 15:03

2,252

ለሁሉም የት/ቤታችን ተማሪዎች
የሁለተኛው ወሰነ ትምህርት አጀማመር መልካም የነበረ ቢሆንም አንዳንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የቀራችሁ ስለሆነ ተከታታይ አቴንዳንስ ወስደን በህጉ መሠረት ከፈተና የምናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
ት/ቤቱ
BOLE GENERAL SECONDARY SCHOOL(OFFICIAL PAGE)

09 Feb, 13:58

2,292

ቀን 02/06/17
ማስታወቂያ
ለተማሪዎች በሙሉ
እንደሚታወቀው የካቲት 03/06/17ዓ.ም የ2ኛ መንፈቅ ዓመት ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ስለሆነ ሁላችሁም
# ተገቢውን የዩኒፎርም አለባበስ
# የፀጉር ትክክለኛ አሰራርና አቆራረጥ እንዲሁም
# የትምህርት ግብዓት ቁሳቁስን በአግባቡ በማሟላት በትክክለኛው የመግቢያ ሰዓት እንድትገኝ ስንል እናሳስባለን።