ቦናፋይድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተወካዮቻቸውን በኦን ላይን መርጠዋል። ባለፉት ቀናት ተወካይ ለመሆን ራሳቸውን ዕጩ አድርገው የቀረቡ ተማሪዎች ሀሳባቸውንና ምልክታቸውን ሲያስተዋውቁና የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ከእሮብ ጀምሮ ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ ቤታቸው ሆነው በኦንላይን ድምጽ ሰጥተዋል። ይህ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ተወካይ የምርጫ ውጤት በትላንትናው እለት ተገልጿል። ይህ አይነቱ ልምምድ ተማሪዎች ዲሞክሪያሳዊ ስርዓትን በተግባር በግዜ እንዲለማመዱ እና ቴክኖሎጂን በተለያዩ ሁነቶች ውስጥ የመጠቀም ዕድል ይሰጣል ተብሎ ይታመናል።