آخرین پست‌های 𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂⏰ (@bbn_info) در تلگرام

پست‌های تلگرام 𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂⏰
#Info Makes Chanege

#አንድ_ላይ_ኾነን_ለውጥ_እንፈጥራለን!

ማንኛውንም ቡልቡላ ነክ ወሬ፥ መረጃ እና ሃሳብ @Bulbula_bot ላይ ልታደርሱን አልያም #ልትጠይቁን ትችላላችሁ።

ለደላላ👉 @BDilela_bot
1,750 مشترک
4,438 عکس
156 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 09.03.2025 04:58

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط 𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂 در تلگرام

𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

08 Mar, 11:37

593

እንዲህ ሆነ አሉ…

ከለታት በአንዱ ቀን አንድ ሰውዬ ወንድ ልጃቸውን አስከትለው ወፈር ያለ ገንዘብ ይዘው ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ይጀምራሉ። ታዲያ እኚ አዛውንት ሰውዬ ለጋሽ ነበሩና ለአላፊ አግዳሚ ሲጋብዙ ሲያበሉ ሲያጠጡ በእጃቸው ይዘውት የወጡት ገንዘብ መንምኖ ወደ መንደራቸው መመለሻ ገንዘብ ያጣሉ። ከአዲስ አበባ ወደ መንደራቸው ለመድርስ ከልጃቸው ጋር 160 ብር ያስፈልጋቸዋል ሰውየው ግን እጃቸው ላይ 100 ብር ብቻ ነበር።

ሲጨነቁ ሲጠበቡ አንድ ሀሳብ መጣለቸው ልጃቸውንም ጠጋ ብለው ልጄ ያለን ብር በቂ ስላልሆነ በያዝነው መዳበሪ ውስጥ ግባና እንደ እቃ ልጫንህ ቢያንስ 20 ብር ቢያስከፍሉኝ ነው 80 ብሩ ደሞ ለኔ ይሆናል ይሉታል። ልጃቸውም በሀሳቡ ተስማምቶ መዳበሪያ ውስጥ ይገባል።

ሰውየውም ወደ ረደቱ ጠጋ ብለው የኔ ልጅ የአንድ ሰው ቦታ ይህን እቃ ደሞ ጫንልኝ ይሉታል መዳበሪያ ውስጥ መደተደበቀው ልጃቸው በጣታቸው እየጠቆሙ።ረዳቱም ወደ መዳበሪያው ሮጦ ሊያነሳው ሲል ይከብደዋል ወደ ሰውየው መለስ ብሎ ፋዘር ለእቃው 100 ብር ይከፍላሉ ሲላቸው ሰውየው በድንጋጤ የለም አልከፍልም ብለው ከመኪናው ይወርዳሉ መኪናውም ትቷቸው ይሄዳል።

ሰውየውም መዳበሪያ ውስጥ ወዳለው ልጃቸው ጎንበስ ብሎ " የኔ ልጅ ና ውጣ እቃ መሆንህ አያዋጣም ሰው መሆንህ ይሻላል " አሉት ይባላል።እውነታቸውን ነው ሰውየው ሰው መሆን ይሻላል፣ሰው መሆን ይቀድማል።

👉 መታሰቢያነቱ ሰው መሆናቸውን ዘንግተው ቅራቅንቦ መሆንን ለወደዱ ከጥፍራቸው ይልቅ የጥፍር ቀለምን ለሚወዱ፣ ከፀጉራቸው ይልቅ በፀጉር ቀለም ለተመኩ፣ ከአይናቸው በላይ ለመነፅራቸው ለሚጨነቁ፣ ከእግራቸው በላይ ጫማቸውን ለሚያደንቁ፣ ለጭንቅላታቸው ሳይሆን ለኮፊያቸው ለሚሳሱ በጠቃላይ ከሰውነታቸው በላይ ተራ የተራ ተራ የተራ ተራ ተራ ተራ ለሆኑ ሰው ከመሆን ጋር ፍፁም የማይወዳደሩ ነገሮችን ለሚያስቀድሙ ለመጨረሻው ዘመን የዕውቀት ምኩኖች ይሁንልኝ።

በኔው ዋክሳም ተፃፈ

@BBN_info
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

08 Mar, 10:26

591

Ad🔰

PROJECTer X Cinema  March 9 /2025 Schedule

👉 Join our Telegram channel for weekly schedules, fun contests, and more:
        👇👇
@Projecterx
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

08 Mar, 09:36

605

አንጻራዊ ዕይታ😊

አንዷ ሴት ከመሥሪያ ቤት ጓደኛዋ ጋር ስታወራ እንዲህ አለቻት "ይገርምሻል! ትናንት ምርጥ ምሽት አሳለፍኩ። ባሌ ቤት እንደመጣ ራት ሊጋብዘኝ ይዞኝ ወጣ። ሮማንቲክ የሆነ ራት በላን። ከራት በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል እያወጋን በእግራችን ተንሸራሸርንና ቤት ስንደርስ ሻማ አብርተን ምርጥ የፍቅር ሌሊት አሳለፍን" ብላ ነገረቻት።




የዚች ሴት ባል ደግሞ ለጓደኛው ስለ ትናንትናው ምሽት እንዲህ ብሎ ነገረው "ትናንት ማታ ጥሩ ጊዜ አላሳለፍኩም። ማታ ቤት ስገባ ራት አልነበረም። ሚስቴን የመብራት ሂሳብ ክፈይ ብያት ረስታው ስለመጣች መብራት አልነበረንም። ያለን አማራጭ ሆቴል መብላት ስለሆነ አንዱ ሆቴል ወሰድኳት። የገባንበት ሆቴል ዋጋው ውድ ስለነበረ ለታክሲ የያዝኩትን ሁሉ ከፍዬ በእግራችን ወደ ቤት ተመለስን። ቤት ስንደርስ መብራት እንደሌለ ትዝ አለኝና ሻማ ገዝተን ሌሊቱን በሻማ ለማሳለፍ ተገደድን"

ባሻዬ! መንግሥትና ሴት የሚነግሩህን ነገር በተጨማሪ ማጣራት ወይም የተገላቢጦሽ መተርጎም አለብህ ለማለት ፈልጌ ነው። ከዚህ በላይ ሌላ ነገር አታናግረኝ። ለራሴ ጤንነት እየተሰማኝ አይደለም😉😎

Happy March 8
©ተስፋዬ ኃ/ማርያም


@BBN_info
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

07 Mar, 18:03

888

በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

በቀጣዮቹ በቀጣዮቹ ቅዳሜ እና እሑድ በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የካቲት 29 እና 30 ቀን 2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መርሐ ግብር ያካሂዳል፡፡

መርሐ ግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ የተወሰኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት በሁለቱም ቀናት ከቀኑ 5:00 ሠዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦

• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

• ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ላይ)

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት)

• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ)

• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ )

• ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)

• ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ) ላይ የሚዘጋ ሲሆን÷ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ
የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@BBN_info
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

07 Mar, 18:00

801

🤰🤰🤰🤰 ስለ እርግዝና ያልተሰሙ አስደናቂ እውነታዎች 🤰🤰🤰🤰

1. የጠዋት ሕመም (morning sickness) የሚባለው ሁሌ ጠዋት የሚከሰት አይደለም፡፡ ብዙ ሴቶች ቀኑን ሙሉ አንዳንዶች ድግሞ ጠዋት፣ግማሽ ቀን ወይም ማታ ስሜቱ ሊታያቸው ይችላል፡፡

2. እረጃጅምና ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች መንታ ልጅ የመውለድ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ከቤተሰብ ውስጥ መንታ የወለደ ሰው ካለና ዕድሜዎት ከ35 በላይና ረጅም ከሆኑ መንታ ልጅ የመውለድ ዕድል አልዎት፡፡

3. የደም መጠኖ ይጨምራል፡፡ በልብዎ የሚሰራጨው የደም መጠን ከ40 እስከ 50 በመቶ ይጨምራል፡፡

4. የልብዎ መጠን በእርዝመትም በወርድም ይጨምራል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ተጨማሪ ደም ለመርጨስ ሲል ይለጣጣል፡፡

5. እርግዝና ከተከሰተበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ጡት ወተት ለማምረት ይዘጋጃል::

6. ልጅዎ ይሰማዎታል፡፡ ጆሮ ቀደም ተብለው ከሚሰሩት የህፃኑ አካለት አንዱ ሲሆን ልጅዎም የእለት ተዕለት ንግግሮን ይሰማል፡፡ በተለይ ከ6 ወራት ጀምሮ ብቻዎን ስላልሆኑ ልጅዎን ያናግሩ፡፡

7. ልጆ ከእርስዎ ቀድሞ ይበላል፡፡ ማንኛውም የሚመገቡት ቫይታሚንና ማእድናት ልጆ ከተጠቀመ በኃላ ነው የቀረው ወደ እርሶ የሚደርሰው፡፡ ለዚህም ነው በእርግዝና ጊዜ ጥሩ ጥሩ ነገር መመገብ ለልጆ ጤንነት ወሳኝ ነው የሚባለው፡፡

8. በእርግዝና ጊዜ ምግብ ቀስ ብሎ ወደ ትንሹ አንጀት ስለሚሄድ ሆድ በጋዝ ሊሞላ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአይነምድር ድርቀት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ስለሆነም ለብ ያለ ውሃ በብዛት መጠጣት ሊያስታግሰው ይችላል፡፡

9. የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ይቻላል፡፡ይህ ማለት ዕርግዝናው ጤናማ እስከሆነ ብቻ ነው፡፡፡ ውስብስብ የሆነ እርግዝና ከሆነ ግን ሐኪም ማማክር ግድ ይላል

@BBN_info
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

07 Mar, 15:10

777

Ad🔰

ካስማር (ዶ/ር ካሳሁን)መካከለኛ ክሊኒክ

ለ አምስት አመታት የቡልቡላ እና አካባቢውን ህዝብ በማገልገል መልካም ስም ያተረፈ ከመደበኛ ህክምናው በተጨማሪ የማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ በማህጸን እስፔሻሊስት
የግርዛት እና ሌሎች አነስተኛ ቀዶ ጥገና በስፔሻሊስቶች ለእርሶ እና ለቤተሰብዎ የሚመርጡት ቅድሚያ ለጤናዎ

📍አድራሻ፡ ቦሌ ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም ብሎክ 18

📞 09 74 07 00 01

@BBN_info
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

07 Mar, 13:36

771

የቡልቡላ ዘመናዊው ጎሚስታ ተከፈተ‼️


በአዲስ አበባ ውስጥ በጥቂት ቦታዎች ላይ ብቻ የሚገኝ በዓይነቱ ልዩ የኾነ High Standard የጎሚስታ አገልግሎት ተጀምሯል።

ከተለመደው የጎሚስታ አገልግሎት በተለየ መልኩ ዘመናዊ ማሽኖችን ለተግባሩ የሚጠቀም ሲኾን በከተማው ጥቂት ቦታዎች ላይ ብቻ የሚሠጠውን የBalance እና Allignment አገልግሎቶች በጥራት ይሠጣል።

አድራሻ፡ ቀይ አፈር  ገባ ብሎ ( Münschen fü Münschen የእርዳታ ድርጅት ፊትለፊት

RIFENTI GOMISTA

📍Location
📞 0911272813
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

07 Mar, 13:32

739

ናኒ ወተት እና የእንስሳት ተዋጽዖ

🍗ዶሮ
  [ የፈረንጅ ዶሮ፣የሀበሻ ዶሮ፣ ብረስት፣ ሌግ]

🐟 ዓሳ
[ አምባዛ፣ ፍሌቶ፣ ቴላፒያ፣ ቆሮሶ፣ ናይል ፐርች]

🍯ማር ፣ ቡና እኛ ጋር የሚጋገር ለምለም እንጀራ እና ሌሎችም…

በሱቃችን ከፋርማችን ከምናቀርባቸው ምርቶች ላይ የዋጋ ማሻሻያ ስላለ መጥተው ይጎብኙን።

📍አድራሻ፡ 40/60 ኮንዶሚንየም ብሎክ 25 - 1ኛ ፎቅ
📞 0944464332
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

07 Mar, 04:12

314

GOOD MORNING BULBULA🌞

ተኝተን በሰላም የምንነሳው አልጋው ስለተመቸን ሳይሆን ፈጣሪ ስለጠበቀን ነው።🙏

መልካም ቀን☀️

@BBN_info
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂

06 Mar, 17:34

671

🌜የምሽቱ ምርጥ አባባል🌛

<<የሴት እምነት የሚፈተሸው
ባሏ/ፍቅረኛዋ ምንም የሌለው ሰዓት ነው

የወንድ እምነት የሚፈተሸው
ሁሉንም ያገኘ ዕለት ነው።
>>

መልካም አዳር🙏

@BBN_info