ከለታት በአንዱ ቀን አንድ ሰውዬ ወንድ ልጃቸውን አስከትለው ወፈር ያለ ገንዘብ ይዘው ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ይጀምራሉ። ታዲያ እኚ አዛውንት ሰውዬ ለጋሽ ነበሩና ለአላፊ አግዳሚ ሲጋብዙ ሲያበሉ ሲያጠጡ በእጃቸው ይዘውት የወጡት ገንዘብ መንምኖ ወደ መንደራቸው መመለሻ ገንዘብ ያጣሉ። ከአዲስ አበባ ወደ መንደራቸው ለመድርስ ከልጃቸው ጋር 160 ብር ያስፈልጋቸዋል ሰውየው ግን እጃቸው ላይ 100 ብር ብቻ ነበር።
ሲጨነቁ ሲጠበቡ አንድ ሀሳብ መጣለቸው ልጃቸውንም ጠጋ ብለው ልጄ ያለን ብር በቂ ስላልሆነ በያዝነው መዳበሪ ውስጥ ግባና እንደ እቃ ልጫንህ ቢያንስ 20 ብር ቢያስከፍሉኝ ነው 80 ብሩ ደሞ ለኔ ይሆናል ይሉታል። ልጃቸውም በሀሳቡ ተስማምቶ መዳበሪያ ውስጥ ይገባል።
ሰውየውም ወደ ረደቱ ጠጋ ብለው የኔ ልጅ የአንድ ሰው ቦታ ይህን እቃ ደሞ ጫንልኝ ይሉታል መዳበሪያ ውስጥ መደተደበቀው ልጃቸው በጣታቸው እየጠቆሙ።ረዳቱም ወደ መዳበሪያው ሮጦ ሊያነሳው ሲል ይከብደዋል ወደ ሰውየው መለስ ብሎ ፋዘር ለእቃው 100 ብር ይከፍላሉ ሲላቸው ሰውየው በድንጋጤ የለም አልከፍልም ብለው ከመኪናው ይወርዳሉ መኪናውም ትቷቸው ይሄዳል።
ሰውየውም መዳበሪያ ውስጥ ወዳለው ልጃቸው ጎንበስ ብሎ " የኔ ልጅ ና ውጣ እቃ መሆንህ አያዋጣም ሰው መሆንህ ይሻላል " አሉት ይባላል።እውነታቸውን ነው ሰውየው ሰው መሆን ይሻላል፣ሰው መሆን ይቀድማል።
👉 መታሰቢያነቱ ሰው መሆናቸውን ዘንግተው ቅራቅንቦ መሆንን ለወደዱ ከጥፍራቸው ይልቅ የጥፍር ቀለምን ለሚወዱ፣ ከፀጉራቸው ይልቅ በፀጉር ቀለም ለተመኩ፣ ከአይናቸው በላይ ለመነፅራቸው ለሚጨነቁ፣ ከእግራቸው በላይ ጫማቸውን ለሚያደንቁ፣ ለጭንቅላታቸው ሳይሆን ለኮፊያቸው ለሚሳሱ በጠቃላይ ከሰውነታቸው በላይ ተራ የተራ ተራ የተራ ተራ ተራ ተራ ለሆኑ ሰው ከመሆን ጋር ፍፁም የማይወዳደሩ ነገሮችን ለሚያስቀድሙ ለመጨረሻው ዘመን የዕውቀት ምኩኖች ይሁንልኝ።
በኔው ዋክሳም ተፃፈ
@BBN_info