أحدث المنشورات من ባህረ ጥበባት (@bahretibebat) على Telegram

منشورات ባህረ ጥበባት على Telegram

ባህረ ጥበባት
"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል" ት. ሆሴዕ 4:6

አለማወቅ እያጠፋን ነውና እንወቅ።

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ @Filoppader
1,352 مشترك
262 صورة
10 فيديو
آخر تحديث 16.03.2025 21:47

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة ባህረ ጥበባት على Telegram

ባህረ ጥበባት

13 Mar, 15:05

126

https://youtu.be/w0cL6tRPZDk?si=-JTulYF95cVsr5UF
ባህረ ጥበባት

11 Mar, 12:05

192

https://youtu.be/aLUxw9ymmls?si=CPN3jdfzzPbsBWp0
ባህረ ጥበባት

07 Mar, 12:21

306

https://youtu.be/LAzY4Vm_rms?si=d6dc0vkb4dY2uR3s
ባህረ ጥበባት

03 Mar, 04:10

408

https://youtu.be/_9_UWYmovuM
ባህረ ጥበባት

24 Feb, 02:36

692

እንኳን ለዐብይ ፆም በሰላም አደረሰን
👉 ፆም ማለት ምን ማለት ነው
👉 የአብይ ጾም ስያሜዎች ስንት ናቸው
👉 የአብይ ጾም ለምን ታላቁ ጾም ተባለ
👉 የአብይ ጾም ስንት ክፍሎች አሉት
👉 የአብይ ጾም ለስንት ሳምንታት ይጾማል
👉 ስለመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ምን ያውቃሉ

፩ ጾም ማለት ምን ማለት ነው
ጾም፥ ተወ" ታቀበ "ታረመ"ካለው የግዕዝ የቃል የተገኘ ነው።
ፍቹም ምግብ መተው መከልከል መጠበቅ ማለት ነው።
ፆም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል መወሰን ማለት ነው። ወይም ሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት ነው
ጾም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ።
ፆም በብሉይ እና ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው።
ነብያት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም ነበር (ዘፀ 30÷34*28)
በሐፂያት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። (ዮሐ2÷7-10//2*7-20//
በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሲ መድሐኒታችን በመዋዕለ ሰጋዌው የሰራ መጀመሪያ አድረጎ የተሰራ ህግ ነው። // 4÷2//
ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን በጾም እሚወገድ መሆኑን መድሐኒታችን ተናግራል።//ማቴ 17÷21
ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙት ሐዋሪያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው ትዕዛዝ እሚቀበሉበት በጾም እና በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር// ሐዋ 13÷2//
ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነበር።።የሐዋ// 13÷3//
ጾምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው።
ፆም ማለት ጥለላት ማባልዕት ፈፅሞ መተው ሰውነትንም ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ፣ መገዛት፣ መቆጣጠር፣ በንሰሐ ታጥቦ
በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበረከክ ምህረት በአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው።
ፆም ነፍስን ቁስልን የምትፈውስ፣ ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምትሰጥ የወንጌል ስራ መጀመሪያ ፣ የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል እና የንፅህና ጌጣቸው የንፅህና መገለጫ ፣ የጸሎት ምክንያት እናት የእንባ መገናኛ መፍለቂያ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድሐኒት ነፍስ ናት።
ከህግ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገሥታት፣ ካህናት በፆም ናበጸሎት ፅመድ ሁነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልም እንዲጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን ፈፅሞላቸዋል።

በሀዲስ ኪዳን ጾም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው።// ማቴ 5÷6//
ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ሰጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው።
ፆም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው። መፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው።
ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች ~~~ ስለዚህም የሚፆም ሰው በፈቃደ ስጋው ላይ ድልን ይቀናጃል።
በእምነት ሆኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ
የሆነውን ምስጢር ለማየት ከዓለማዊነት ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል።
በዓለም እየኖረ ከዓለሙ ይለያል። ከዓለም አይደለምና //ዮሐ 15÷19//

አብይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው።
አብይ ጾም የተለያዩ ስሞች አሉት። አንደኛው ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስተስ ከተጠመቀ በኅላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐብይ እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ
ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ //መዝ 47÷1 መዝ 146÷5//
ሁለተኛ ሁዳዴ ጾም ይባላል። ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው።፣ /አሞ 7÷1 // ሶስት በዓተ ጾም ይባላል።
ፆም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓል ማለት ነው አራተኛው ጾመ አርቦ ይባላል። ጌታችነ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመዉ 40// አርባ ቀን ስለሆነ ነው //ማቴ 4÷1 አምስተኛ ጾመ ኢየሱስ ይባላል፡፡ ጾሞ ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፣ ስድስተኛው ጾመ ሙሴ ይባላል ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ ዕዝል ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት እያለ በጾመ ድጓ ስለ ዘመረ ነው
አቢይ ጾም ጌታ ከተጠመቀ በኀላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው። //ማቴ 4÷1
ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል። አቢይ ጾም
ስምንት ሳምንታት //55 ቀኖች // አሉት። 7//ሰባት ቅዳሜ 8//ስምንት እሁድ ይገኛሉ። አስራ አምስት ቀን 55//ማለት ነው። ከጥሉላት እንጂ ከእህል ወኃ ስለማይጦሙ የጦሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል።
፫ የአብይ ጾም ሶስት ክፍሎች
  1 ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል) ፣ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ያረሰ ያለው 7 ቀን ነው።
   2 የጌታ ጾም ፣ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው አርባ ቀን ነው።
   3 ሕመማት፤ ይህ ጌታችን በአላዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጡበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው
ይህም 7+40+8=55 ቀን ማለት ነው

፬ የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው
         1 ዘወረደ
         2 ቅድስት
         3 ምኲራብ
         4 መጻጉዕ
         5 ደብረ ዘይት
         6 ገብርሔር
         7 ኒቆዲሞስ
         8 ሆሣዕና
፭ ለምን አብይ // ታላቅ ተባለ
አቢይ ጾም መባሉ ትልቅና ታላቅ ጾም መሆን ለማሳወቅ ነው። ይህ ጾም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መጾሙና ከሌሎች አፅዋማት ጋር ሲነጻጸር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የጾመው ጾምም በመሆኑ ነው።

የመጀመሪያ የአብይ መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም
ጾመ ሕርቃል ይባላል። ስያሜውም በ614 ዓ,ም ኪርዮስ የተባለ የፋረስ ንጉሥ ኢየሩሳሌም በመውረር ጥቃት አደረሰ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመዳኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱም አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅዱሳን ዘረፌ 60 ሺ የሚደረሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማውንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል።
በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተስብሰበው ከ14 ዓመት በኃላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንሥስ ሕርቃል ይናገሩታል። እርሱም ሐዋሪያት ሰው የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማን ብለን አንድ አንድ ሳምንት ደረሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል።

@Filoppader

መልካም የፅሞና ጊዜ
ባህረ ጥበባት

09 Feb, 09:59

654

https://youtu.be/pvkoKQUca98?si=D0Cuq1pOhy5LsMsE
ባህረ ጥበባት

08 Feb, 12:34

609

https://youtu.be/loxfBsez2b0?si=GfO7HChyivEU-8Dj
ባህረ ጥበባት

01 Feb, 07:41

742

https://youtu.be/GHBQesm5IOU?si=-w15UhH5e2VkhBPW
ባህረ ጥበባት

31 Jan, 15:28

710

https://youtu.be/vmHVRJ_QCCk?si=RImQ3DckxkiD--B4
ባህረ ጥበባት

24 Jan, 07:10

788

https://youtu.be/ya-xtrRSReY?si=4eC86NlxHb5NolKI