ኤዞፕ መጻሕፍት (@azop78)の最新投稿

ኤዞፕ መጻሕፍት のテレグラム投稿

ኤዞፕ መጻሕፍት
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
8,884 人の購読者
9,064 枚の写真
26 本の動画
最終更新日 06.03.2025 09:30

ኤዞፕ መጻሕፍት によってTelegramで共有された最新のコンテンツ

ኤዞፕ መጻሕፍት

05 Mar, 04:53

710

ውብ ኦሪጅናል የታሪክ ሰነዶች !!!
ኤዞፕ መጻሕፍት

01 Mar, 10:51

722

#ዐይነ_ልቡና
(ትምህርተ ጽድቅ ቅጽ ኹለት)

ርጡብ ነፋስን ከባሕር፣ ደረቅ ነፋስን ከምድር አስነሥቶ የመብረቅ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማናል፤
ከምድር ዳርቻ ደመናትን የሚያወጣ አምላክ ለዝናም መብረቅን ማምጣት አይሳነውምና። ለዚህም ዘመን እንደ መብረቅ የሚወረወሩ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ የማያስፈሩ ወጣት መምህራንን ባየሁ ቁጥር “ለዝናም ጊዜ መብረቅን አደረገ" የሚለው የዳዋት መዝሙር ትዝ ይለኛል። ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት የተወለዱ መሆናቸው መብረቅ ያሰኛቸዋል። እኔ በዘመኔ ትውልድ እንድኮራ ከሚያደርገኝ ወጣት አገልጋዮች
እንዲ መምህር ዮሐንስ ነው። በትምህርተ ጽድቅ መጽሐፉ ብዙ ነፍሳትን ወደ እውነተኛው ትምህርት
እጃቸውን ይዞ መርቷል ዛሬ ደግሞ ዓይነ ልቡናችንን የሚ ያበራ በኦርቶዶክሳዊ የአበው አስተምህሮ የተቃኘ ትምህርት ያለበት መጽሐፍ ይዞልን በመምጣቱ ለገበሬ ዘርን ለእንስሳ ሳርን የሚሰጥ አምላክ ለመምህራንም በየጊዜው የሚጽፉትን የሚ ያስተምሩትን አይከለክልምና ሞገስ እነዲሆኑን በዦጥረ መባርቅት አምሳል በቤተ ክርስተያን ሰማይ ላይ ለገልጣቸው ሳይ ደስ ይለኛል።

ከሰማይ በታች ያሉ ምዕመናንን የሚያስደነግጥ ሳይሆን የሚያንፅ ሆኖ ስላገኘሁት እሳት መስሎ
በታችሁ እነ ኢሳይያስ ከንፈራችሁን የሚ ያነጻ እንጅ የሚያቃጥል እሳት ስላልሆነ ከናፍረ ምዕመናንን የነጻ ዘንድ የተገለጠ መጽሐፍ መሆኑን ባነበብሁት ወቅት ተረድቻለሁና እነሆ በሃይማኖቱ ኦርቶዶክሳዊዋ፣ በትውልዱ መጽሐፍ ቅዱሳዋ፣ በነገዱ ቄርሎሳዊ፣ በግብሩ ዐቃቤ ልቡና መሆኑን ለማስረዳት ምስክር ሆኜ መጥቻለሁ
ምስክርነቴን ከተቀበላችሁኝ ከአበው ትምህርት የተወለደ ለመሆኑ እናንተም ሩቅ ሳትሄዱ የአነጋገሩን ለዛ ስታዩት ብሔረ ሙላዱ መጻሕፍት፣ አባቶቹ ሊቃውንት መሆናቸውን እንደምታረጋግጡ ያለኝን እምነት እየገለጽሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ብቻ ሳይሆኑ በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ላይ ያልጠራ አመለካከት ያለው ሁሉ ቢያነበው ምኞቴ መሆኑን እገልጻለሁ።
#ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ ለመፅሐፉ የሰጡት አስተያየት
ኤዞፕ መጻሕፍት

28 Feb, 16:10

811

መነበብ ያለባቸው
ኤዞፕ መጻሕፍት

28 Feb, 12:58

886

በፃም ሠዓት የምታነቧቸውን መንፈሳዊ መፅሐፍት ከፈለገቹህ ብቅ በሉ ደውላችሁ እዘዙን።
ኤዞፕ መጻሕፍት

25 Feb, 17:16

438

ቀድሞ ለደወለ
ኤዞፕ መጻሕፍት

15 Feb, 14:07

495

በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የመካከለኛው ዘመ7 ታሪክ በነገረ-ሃይማኖታዊ ድርሳኖቻቸው ስመ ጥር ከሆኑ ሊቃው3ት መካከል ቅዱስ ሳዊሮስ ዘእስሙናይገ (987 ዓ.ም እ.ኤ.አ ያረፈ) ግ3ባር ቀደም ነው:: ሳዊሮስ ኢብኑ እልሙቃፋ እየተባለም ይጠራል። የጻፈው በአረብኛ ቋንቋ መሆኑ ደግሞ የግብጽ ቤተ ክርስቲያ3 አስልምና 3 ተከትሎ እየገነነ በመጣው ጸረብኛ ቋ3ቋ አስተምሀሮዋ3 ለመግለጽ ካስለፈቻቸው ታላላቅ ሊቃው3ት ቀዳሚው ያይርገዋል። ሊቀ ጳጳስ ላዊሮስ በታሪክ፣ ነገረ-ሃይማኖት እና ሥርዓታት ዙሪያ በጻፋቸው ድገቅ ዕቅበተ-እምነታዊ ድርሳናቱ ቤተ ክርስቲያጓጓ አገልግሎ ያለፈ ትጉህ ሊቅ ነው። ከእነዚህ ድርሳናቱ አጓዴ በግእዝ መጽሐፈ ሳዊሮስ በሚል የምናውቀው १४८६ ९१० १६-१.९४( )حاضي إلا بات ك PC ይህ መጽሐፍ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ድርሰት ነው። PAD

Lህ መጽሐፍ ጥጓታዊው፣ ኦርቶዶከላዊ የቤተ ከርስቲያ3 አስተምህሮ ከዘመነኛው ተግዳሮት (በተለይ እስላማዊው የአስተምህሮ ትችት) አጓጻርቃኝቶ ያዘጋጀው ድርሰቱ ነው። ምሥጢረ ሥላሴ፣ በአብዛኛው በኩነታት እጓጻር ሲያብራራ እናገኘዋለጓ። ይህም ለእስላማዊው 777 የተሻለ የሚሆነው በኩነታት ላይ የተመሠረተው ሐተታ በመሆኑ ነው። ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆጓም ይህ ኩነታት7 በሰፊው የመጠቀም እዝማሚያ ወደ ኢትዮጵያ ሊቃው37 ዘጓድ የደረሰው በዚህ ሊቅ ድርሳናት በኩል ሳይሆጓ አይቀርም። የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰት በሆነው መጽሐፈ ምሥጢር ውስጥ የምናገኘው ጉዳዩ፣ በጥንቃቄ የማየት አካሄድ ለዚህ 63650 የሚሰጥ ነው።

ይህ መጽሐፍ በሳዊሮስ እና በሌሎች አረብ-ክርስቲያጓ ሊቃውጓት ድርሳናት በተለመደ መልኩ ጥልቅ እና ረቂቅ የሆኑ ተመስጦጸዊ ሐተታዎች 7 የያዘ መጽሐፍ ነው። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ነገረ ገረ-ሃይማኖታዊ ሳይሆ፣ ጥልቅ የሆኑ የመጓፈሳዊ ሕይወት መመሪያዎች3 እና ተሞክሮዎች 3 የያዘ እጅግ ጠቃሚ መጽሐ ሐፍ መሆኑ ነው።

ኤፍሬም ከጓዴ ዬ ይህጓ በቀላሉ የማይገኝ ውድ መጽሐፍ ከ ግዕዝ ወደ አማርኛ ተርጉመው ለአገባ ገባብያ፣ ማብቃታቸው በእጅጉ የሚ ያስመ ►:: ለመ/ር ኤፍሬም እግዚእብrሔር ብዙ የሚያገለግሉበትን ጸጋ ያድልል!

ዷ /3 በረከት አዝመራው
ኤዞፕ መጻሕፍት

14 Feb, 17:15

724

ሰሞኑን አፍሪካውያን ፣ አፍሪካን ላፍሪካውያን የሚሉ ይመስላሉ።

በመዲናችን አዲስ አበባ እየመከሩ ነው።

የአፍሪካውያን ህብረት እንዴት ተመሰረተ ?


የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አ.አ.ድ.)  Organisation of African Unity (OAU))፣ ግንቦት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ተመሥርቶ የድርጅቱ መመሪያ ውል (OAU Charter) በ፴፪ቱ መሥራች አገር መሪዎች ጸድቆ ተፈርሟል። የድርጅቱም ጠቅላይ መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ እንዲቆይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ግብዣ መሠረት እስካሁን ድረስ እዚያው አዲስ አበባ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በ፲፱፻፺፬ ዓ/ም ተደምስሶ የአፍሪካ ኅብረት በሚባለው ድርጅት ተተክቷል።

ለብዙ ሺ ዓመታት ኢትዮጵያ ብቻዋን በአኅጉሩ ውስጥ ከአውሮፓውያኖች የቅኝ ግዛት ቀንበር ውጪ ቆይታ የሙሶሊኒ ፋሺስት ኢጣልያ በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ወርራት በነበረ ጊዜ አርበኞች ልጆቿ ውድ አገራቸውንና ነጻነታቸውን አሳልፈው ላለመስጠት አምስት ዓመታት ሙሉ ተዋጉ። ንጉሠ ነገሥታቸውም የእዚህን የግፍ ወረራ ለማጋፈጥ በዓለም መንግሥታት ማኅበር መድረክ ላይ ሲቀርቡ፣ ከአፍሪቃ አኅጉር ብቸኛዋ አባል ኢትዮጵያ ማንም አጋዥ አገር አልነበራትም።
ለአኅጉሩ ነጻነት በቅኝ ግዛት ሥርም የነበሩት ሕዝቦች፤ በነጻነትም ላይ የነበሩት አገራት የአውሮፓውያንን መዥገራዊ ልጥፍነት ለማላቀቅ ብዙ ከታገሉ በኋላ በሰሐራዊ አፍሪቃ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፵፱ ዓ/ም ጋና ነጻ ሆነች። ከዚያ አስከትሎ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት እስከተመሠረተ ድረስ በ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ጊኒ ነጻ ስትሆን በ ፲፱፻፶፪ ዓ/ም አሥራ አምስት አገራት፤ በ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ሦሥት አገራት፤ በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም ደግሞ አራት አገራት ነጻነታቸውን ተቀዳጁ።
የአኅጉሩ መሪዎች በዓለም መድረክ ላይ ለበለጠ ተሰሚነት የትብብርን ግንባር ማሳየት እንደነበረባቸው በመገንዘብና ገና ነጻ ላልወጡትም ወንድም አገሮች ሉዐላዊነት መታገል ስለነበረባቸው ዓላማቸውን ግብ ለማድረስ በሁለት ቡድን ተከፍለው ፣ ባንድ በኩል እራሱን “የዘመናዊ ተራማጅ” ብሎ የሚጠራው፣ በጋናው ፕሬዚደንት ክዋሜ ንክሩማ የሚመራው የ “ካዛብላንካ ቡድን” በ ፲፱፻፶፬ ዓ/ም ተመሠረተ። ይሄ ቡድን የአኅጉሩን መንግሥታት በኅብረት ለማዋሃድ ዓላማ የያዘ ሲሆን አባላቱ ጋና፣ አልጄሪያ፣ ጊኒ፣ ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ማሊ እና ሊቢያ ነበሩ።
ሁለተኛው ቡድን የ”ሞንሮቪያ ቡድን” ሲሆን የተመራው በ ሴኔጋል ፕሬዚደንት ሊዮፖልድ ሴዳር ሴንግሆር ነበር። አባላቱ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያ፣ ላይቤሪያ እና ኢትዮጵያ ሲሆኑ የነሱ የኅብረት አስተያየት ደግሞ የዱኛ ኅብረት ሳይሆን ፍላጎታቸው ረጋ ባለ ሁኔታ የዱኛኪን ኅብረት አንድነትን ያስከትላል የሚል ነበር።
መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ከተማ ይፍሩ ታላቅ ጥረትና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድጋፍ ሁለቱም ወገኖች አዲስ አበባ ላይ እንዲገናኙ በተደረገው ጥሪ መሠረት ተሰባስበው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን የስምምነት ውል ፴፪ ነጻ ሀገሮች ሲፈርሙ ድርጅቱ ተመሠረተ።

ይኸው ዛሬ ካለበት  ደረጃ ደርሷል።


መጻሕፍት ቤታችን ደግሞ ልዩ ልዩ የአፍሪካውያንን ታሪክና ፍልስፍና ፣ የስልጣኔ መነሻነትን የሚተነትኑ መጽሐፍትን አዘጋጅቷል።
ሳምንቱንም አፍሪካን ለአፍሪካውያን ብለን እነሆ እንድትጎመኙን በራችን ከፍተን እንጠብቃችሗለን!!!!


ኤዞፕ መጻሕፍት !!!



ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
ኤዞፕ መጻሕፍት

08 Feb, 16:35

468

ዛሬ በጣም ቆንጆ ዶክመንቶች አግኝተናል !!!

ብቅ ብለው ይጎብኙን !!

!ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
ኤዞፕ መጻሕፍት

04 Feb, 17:42

830

ማነው ናቅፋን የያዘውና እንዳለ ያለቀው ሠራዊት ሦስተኛ ክ/ጦርና 17ኛው ክ/ጦር አይደለም እንዴ ? አይው የ3y h/me sur ኰለኔል ተሻገር ይማም ይባላል፡ የጐንደር ልጅ ነው፡፡ የ17ኛው ክ/ጦር አዛዥ ኩለኔል መኮንን ወልዴ ይባላል፡ ጠና ያለ መኰንን ነበር፡፡ የግንባሩ አዛዥ እዛው በጦሩ ፊት የተሾመ ወጣት መኰንን ጄነራል ውበቱ ፀጋዬ ይባላል፡፡ እነኚህ ናቸው የተሰጣቸውን መመሪያ በትክክል ሥራ ላይ ያዋሉት፡፡ በስልት በጣም አስቸጋሪ በሆነ የተፈጥሮ አቀማመጥ ላይ ዳገት ቧጠው ጠላት ላያውቅና ሳይነቃ ደርሰው ዱብዕዳ ተኩስ ነው የከፈቱበት፡፡ ጠላት ቁርበቱን ጠቅልሎ ናቅፋን ለቆ ለመሸሽ በመዋለል ላይ እያለ በውቃውና በመበረቅ ዕዝ ግንባር ተስልፎ ከነበረው ጦር አንስቶ በደረሰለት ተጠባባቂ ጦር ከኋላም ከፊትም መጥቶ ተረባረበባቸው።

ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም በቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት (1974 የካቲት)

ብዙ ቀይ እምቡጦች ብናጣም ድሉ የእኛ ሆኖአል፡ በዚህ ዕለት ዘጠኝ መቶ የጠላት ሬሣ ተቆጠረ፡ በቦምብ ከጋዩት ሌላ አያሌ መሣሪያዎች በወገን ጦር እጅ ገቡ፡ የቀይ እምበጥ ዘመቻ አርማ ከከፍታ ነጥብ 1702 ላይ ሲተከል የነበረው ስሜት አጅግ አድርጎ ልብ የሚነካ ነበር፡ ሁሉም የሞቱት የጀግና ሞት ነበር፡ አብዛኛዎቹ የሞቱት የእጅ ቦምብ እንደጨበጡ ጠላት ምሽግ ውስጥ ዘሎ በመግባት ነበር፡፡ ብቻውን የወደቀ አንድም የቀይ እምቡጥ ጦር አላየሁም፡ የጠላቅን አንገት አንቀው የወደቁ ብቻ ነበሩ፡፡ አስደናቂ ድል ነው፡ ግን ድሉ የቀይ እምቡጥ ብቻ አይደለም፡ ከጥሩ ቅንብርና ዕቅድ የተገኘ የጋራ ድል ነው፡፡

ከቡር አቶ በአሉ ግርማ - የማስታዎቂያ ም/ሚኒስቴርበናቅፋ ጦር ግንባር በመገኘት ስለ አጥፍቶ መጥፋት ጦር የሰጡት ምስክርነት ነበር ።


📚📚 ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
ኤዞፕ መጻሕፍት

04 Feb, 16:00

663

የአለማየው ሞገስ ሥራዎችን በብዛት ስትጠይቁን ለም በራችኹ ወዳጆቻችን ትንሽ ቅጅዎች እጃችን ላይ ይገኛሉ።


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21