أحدث المنشورات من አርምሞ🧘🏽‍♂ (@armemo_offical) على Telegram

منشورات አርምሞ🧘🏽‍♂ على Telegram

አርምሞ🧘🏽‍♂
ጥቂት ምናኔ 🧘🏽‍♂️


©³ @thoughts_painting
9,263 مشترك
1,054 صورة
25 فيديو
آخر تحديث 11.03.2025 17:01

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة አርምሞ🧘🏽‍♂ على Telegram

አርምሞ🧘🏽‍♂

09 Mar, 16:51

1,608

አለማየሁ ገላጋይ
አርምሞ🧘🏽‍♂

09 Mar, 10:19

1,702

Repost 🎯


    ፦Life A song A Dance 📖
                  -By osho


አንዳንድ ነገሮች ቁሳዊ እና ዓለማዊ፤ ሌሎች ነገሮች ደግሞ ቅዱስ እና መንፈሳዊ ናቸው..ብላችሁ አታስቡ።

በሁሉም ነገር እንዴት ደስተኛ መሆን እንዳለበት ለሚያውቅ ሁሉም ነገር የተቀደሰ ነው።
በአለም እና በእግዚአብሔር መካከል ድንበር የለም ሁሉም ነገር መለኮታዊ ነው።

አበባው ግልጽ የሆነ የዘሩ ቅርጽ ሲሆን ዘሩ ደግሞ የማይገለጥ አበባ ነው። ይህ ዓለምና ያ ዓለም በተፈጥሮአቸው ውስጥ ልዩነት የለም፤ ይህ የባህር ዳርቻ እና ያ የባህር ዳርቻ ወይም በቁስ እና በመንፈስ መካከል መለየት አያስፈልግም እነሱ አንድ ናቸው። ስለንደዚህ አይነት ነገር የሰው ልጅ እንጂ የሚጨነቀው ፈጽሞ ተፈጥሮ ስለልዩነቷ አስባ አታውቅም። ይልቅ ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች በመተው በትንንሽ ነገሮች ደስተኛ ሁኑ።

ሻወር በመውሰድ ወይም ሻይ በመጠጣት መሐከል ምንም አይነት ድንበር አታስቀምጡ  ምንም ልዩነት አትፍጠሩ
..ደስተኛ መሆንን ለሚያውቅ ሰው ሻይ መጠጣት እንደማንኛውም አምልኮ እና እንቅልፍ እንደማንኛውም ሃይማኖታዊ ተግባር ቅዱስ እና መለኮታዊ ነው። ደስተኛ መሆን ብሎም ፈገግታና አዲስ እይታን ይፈጥራል። ዙርያ ሞላው ገባው ይቀየራል ለውጡ የምድር ሁናቴ ሳይሆን የራሳችን አስተሳሰብ ነው። ከዚያም ልክ አለምን እንደረሷት መነኮሳት ማገዶን መልቀምና ከጉድጓዱ ውስጥ ውሃ መቅዳት እንደ ትልቅ ተግባራት ያማረ ይሆናል። ስለዚህ አትዘኑ ሳቁ፣ ደንሱ፣ ዘምሩ ህይወታችሁን ቀለል ባለ መንገድ በትህትና ባህሪ ኑሯት። ማደግን አንድን ነገር ለማሳካት ወይም ወደ ላይ ለመብረር ፍላጎት እና ምኞት በአዕምሮአችሁ ውስጥ ካለ ይህን መርዝ አስወግዱ!። ተራ ህይወት በጣም ቆንጆ ነው ምንአልባትም እንደፈካ ሎተስ አበባ ወይም ደግሞ እንዳጎጠጎጠች ልጃገረድ ለመኖር ለማወቅ ጉጉነትን ያጨቀ ነው። ለመርካት በተፈጥሮ ደስተኛ መሆን እንጂ ነገሮችን መጨመርና በስኬት ለማደግ መሯሯጥ ትርፉ የስግብግብነት ኪሳራ ነው። ስለሆነም ይህን መረዳት አስፈላጊ ነው.. ማንኛውም ነገር እያደገ በሄደ ቁጥር ውበቱ እየደበዘዘ ይመጣል።    
አርምሞ🧘🏽‍♂

04 Mar, 20:00

3,108

በመንገድ አህያ ከልጇ ጋር ከመጠን በላይ ሸክም ተጭኖባቸው ሲሰቃዩ አየውና ለበቅሎ እንዲህ አልኳት፦“ለዚህ ግፍ ነው ሌላ ትውልድ? እንኳንም አልወለድሽ መሃን በመሆንሽ ፈጣሪን አመስግኚ!”

ንግግሬን የሰማችው አህያ  በምፀት እያየችኝ እንዲህ አለች፦“በቅሎዋን እኔ ነኝ የወለድኳት” 🙂
አርምሞ🧘🏽‍♂

04 Mar, 19:22

3,095



ከመጣው አይቀር የሆነ የተሰማችን ነገር ልጻፍ ብዬ አሰብኩ። እንደለመድኩት የፈጠነ ስለጻፍኩትና መልሼም ስላላነበብኩት የቃል ግድፈቱን ማስተካከል እንዳይረሳችሁ። የዚህን ያህል ጥልቅ ነገር ለመጻፍ ባልመጣም፤ ስሜት ነውና የተሰማኝን ሰቅዬ ሳላወርድ ሳላሰማምርም ጭምር ጽፌዋለሁ።

“የመለስ አሳብ ዛሬም ይነፍሳል
ሞት በቤት ቁጥር ፈጥኖ ይደርሳል
ሰው ዳቦ ትቶ መሬት ይቆርሳል
አብይ አህመድ ዛሬም ይነግሳል”
🎶


እኔ ብቻ ነኝ “አድዋ አድዋ” የሚለው ነገር መስማትም ማየትም የደበረኝ?። ብቻ ባላውቅም ያላከበርነው ያከበሩት በዓል ከዓመት ወደ አመት እየደበዘዘ በዓሉ የጀግና መታሰቢያ ሳይሆን የሙት አመት ማስታወሻ መስሏል።
Etv፣ fana፣ NBC የመንግስት ቻናል በጠቅላላ የውሸት ፕሮፓጋንዳቸውን እየቀባቡ እንዲህ ያለህ፦“ምንሊክ ጥይት ጨርሰው ከግሪያዝያኒ ወታደር ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጡ፤ እና የፈጠነ አንድ ሁለቴ በቡጢ ካጣደፉት በኋላ ወደቀ፤ ይሄኔ ንጉሱ ግንባራቸው ላይ ያሰሩትን ነጭ ሻሽ በማውለቅ የወደቀው ወታደር አንገት ላይ ጠምጥመው እስከመጨረሻው ገላገሉት” “ባልቻ አባ ነፍሶ ከሁለት ወታደሮች ጋር እየተታኮሱ ሳለ፤ አንድ ታንክ እሳቸው ወዳሉበት አቅጣጫ እየበረረ መጣ፤ ይሄኔ ባልቻ አንድ ድቡልቡል ድንጋይ አንስተው የታንኩን የፊት መስታወት እምሽክ በማድረግ በተሰበረው መስታወት ዘለው ገቡ፤ አልቆዩም የገቡበትን ታንክ በመጠቀም አንድ ባታሎን ጦር ደመሰሱ”

ይቅርታ አድርጉልኝ ምዕመናን ግን እንዲህ ያለ ሳክስ ስሰማ ነበር የከረምኩት። በተለይ ፋና ላይ ሳምንቱን ሙሉ የአድዋ የጦር አሰላለፍ ብሎ አርበኞችሁ የቆሙበትን ቦታ በቅርጻ ቅርጽ ሰርቶ ሲያስረዳ ሳቄን
I can't control። እንደበረበረኩት በሐበሻ ጀብዱ መፅሃፍ፣ ኃይለ ስላሴ በእጅ ጽፈው ካደረሱን መፅሃፍ፣ በሌሎች የታሪክ መዛግብት አንብቤውም ሰምቼውም የማላውቀውን ታሪክ በመንግስት የሚድያ ድርጅቶች እንደ አዲስ እየኮመኮምኩ ነው የሰነበትኩት። በቃ ተበልተናል “We learn from history that we do not learn from history” ታሪክ እንደሚለው ምንሊክን ከሸዋ ባልቻን ደግሞ ከኦሮሞ በአንድነት ድል የተነሳ ጦርነት ነው አድዋ!። ይህን የተረዳች ጣልያን ትንፋሻዋን ሰብስባ፤ ሽንፈቷን እንደ ሬት ውጣ ቀን ጠበቀችና ሶሻሊዝምን ጥላ ፌደራሊዝም የሚባል እርስ በእርስ የሚያባላ ስርዓት ከጀርባ ሆኗ ፊት አነገሰች። ታድያ እንዴት ሆኖ ነው በዘር ማንነቱ የተጠላላ፣ በአስተሳሰብ እና በታሪክ ንግርት የተለያየ ማኀበረሰብ ስለ አንዲት አድዋ አንድ ሆኖ የሚያከብረው? አላውቅም!። እዚህ ጋር ሱፍ ለብሶ ተቀያሪ ቁንጣ እንኳን የሌለውን ሰው የሚጨፈጭፍ ፕራይ ሚንስትርን መጥላት አያስፈልግም። አዎ የተሰቀለውን የጭንቅላት ራስ አትርገሙ ሆዱ ነው የሚያዘው!። ሁላችንም ብንሆን በሆዳችን ውስጥ የተራባውን ትላትል ካላጠፋን አዕምሮአችን ትክክል አያስብም። የምናወጣው ቃል እንደማስታወክ ያለህ አስጸያፊ ነው፤ በውስጣችን የምንይዘው ደግሞ የሆድ ቁርጠት ከመሆን ውጭ ትርፉ ትርፍ አንጀት ነው።
                
አባቶቻችን አርበኞች በጊዜው ትክክል የሆነውን ነገር አድረገዋል። ያ ደግሞ የጀግንነት ምሳሌ ነው። ምክንያቱም ሰው ዘመኑን ሲመስል በማኀበረሰቡ ዘንድ ትክክል ነው። ነገር ግን አሁንም ድረስ እንደአገር ጥይትና ጦር ይዞ የሚጨፋጨፈውን እንደጀግና መቁጠር የእውርን አይን ማጥፋት፣ የደንቆሮን ጆሮ እንደ መቁረጥ ያለህ ነው። ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ አለመማራችንን ብቻ ነው። አሁን ኢትይጵያ ኢንዱስትሪያሊዝም ነች። የተሻለ የግብርና አቅርቦትን ላቀረበ ወይም ደግሞ ፋብሪካዎችን ከፍቶ ስራ አጥ የሆኑ ወጣቶችን በስሩ ቀጥሮ የሚያሰራ ሰው ለእኔ በዘመኔ አርበኛ ነው። ከዛሬ መቶ ምናምን አመት የካቲት 23 ላይ የተፈጠውን ድል ለማክበር እንዳታስብ። ጣልያን ሳይሆን አንተ እራስህ “ተበላ አበሻ” ማለት ፍቱን መገለጫ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አዎ ቁማር ተበልተናል ብቸኛው ነፃነታችን በሽንት ቤት ውስጥ ማራት ብቻ ነው።

እናም በመጨረሻ ማለት የምፈልገው መዳኒት ጣፍጦ አያውቅም። ቢመርህም ዋጠውና በሆድህ ያለውን ትላትል ግደለው። ድፍን መቶ ምናምን አመት የቆየውን የታሪክ መፋለስ ዛሬም ድረስ ካባላን ካለፈው የተማርነው የአያታችንን ጎራዴ ያፈሰሰውን ደም እንጂ ምክንያቱ ስለምን እንደነበር አይደለም!። እነሱ በዘመናቸው ታሪክ ሰርተው አልፈዋል። አፍረሰዋል ገንብተዋል። ስለምን ታድያ አባት ባጠፋው ልጅ እንደሚባለው ምንም የማያውቅን የሰው አንገት ለመቁረጥ የማንፈራው። ይልቅ አንድ ቀን አንድ ሆነን የልዩነትን አጥር እናፈርስና ከጎጃም የመጣው ወጣት የጅማውን ጎልማሳ አቅፎ በአደባባይ ይታያል። ያኔ እኮ የዛንግዜ ትክክለኛው የምናከብረው አድዋ ይኖረናል። አያቶቻችን የሞቱበት ሳይሆን እኛ የኖርንበት። ንጹህ ነው የንጹሃን አድዋ ንጽህናን የሚሰብክ!።
አርምሞ🧘🏽‍♂

04 Mar, 14:35

2,383

I'm back in another dimension. React and comment are a inspiration drug for me 💊
አርምሞ🧘🏽‍♂

04 Mar, 14:18

2,430

(It took a lot of effort to write this 🤝🏼)

It’s important to approach discussions about political leaders and complex conflicts with care, relying on verified information and balanced perspectives. Ethiopia has faced significant challenges in recent years, including the Tigray conflict (2020–2022), regional tensions, and humanitarian crises. These issues involve deeply rooted historical, ethnic, and political dynamics that are not easily reduced to simple narratives.

1. Tigray War: The conflict between the Ethiopian government and the Tigray People's Liberation Front (TPLF) began in November 2020. Reports from international organizations (e.g., UN, Amnesty International) have documented atrocities by *all sides*, including mass killings, sexual violence, and displacement of millions. The U.S. State Department and EU have accused parties to the conflict of potential war crimes.

2. Abiy Ahmed’s Role
-Abiy Ahmed became prime minister in 2018 and initially won global praise for reforms and peace with Eritrea (Nobel Peace Prize, 2019). 
-His government’s military campaign in Tigray, however, drew criticism for its humanitarian toll, including blockades and allegations of ethnic targeting. 
-Abiy has consistently framed the conflict as a "law enforcement operation" against the TPLF, which he accuses of destabilizing Ethiopia.

3. Humanitarian Impact
-1 million 6 hundred thousand of civilians have died, and over 2.4 million were displaced during the Tigray conflict. 
-Famine-like conditions were reported in Tigray due to aid restrictions, though the government denied intentional obstruction.

4. Accountability Efforts
   - Independent investigations (e.g., joint UN-Ethiopian Human Rights Commission report in 2021) found evidence of abuses by all parties. 

-The Ethiopian government has pledged accountability, but progress remains disputed.


Why Nuance Matters:
- Complexity of Conflict: Ethiopia’s conflicts involve multiple actors (federal forces, regional militias, ethnic groups, foreign troops) with competing grievances. 
- Information Challenges: Access to conflict zones has been restricted, making verification of claims difficult. Both the government and TPLF have spread disinformation. 
- Political Context: Abiy’s government faces pressure to maintain national unity in a country with over 80 ethnic groups and a history of centralized rule.

-Reliable Sources for Further Research:
- UN Human Rights Reports: Document atrocities in Tigray and other regions. 
- Human Rights Watch/Amnesty International: Investigate abuses by all parties. 
- Ethiopian Human Rights Commission: Government-affiliated but has criticized federal and regional forces! Adiós 💔
አርምሞ🧘🏽‍♂

25 Feb, 21:07


አርምሞ🧘🏽‍♂ pinned «ላልተወሰነ ግዜ አገልግሎት መስጠት አቁመናል🤗»
አርምሞ🧘🏽‍♂

25 Feb, 19:57

3,993

ለጊዜው አገልግሎት መስጠት አቁመና ብዬ ስናገር። በሰላም ተመለስ ከማለት ይልቅ የሚዘቀዝቀኝ ሰው መብዛቱ የግርምት ድንበራ አጭሮብኛል!። መዳን የሚገኘው ቁስልን ከመነካካት የተቆጠብን እለት ነው። መተውና መራቅ የአዋቂ መሳርያ ነው፤ በዛ ውስጥ መርሳት የምትባል ጥበብ ጠባለች።

ከእኔ የተሻለ ነገር የሚገኘው የተሻልኩ ከሆንኩ ብቻ ነው። “መሻል” ከነበርንበት መብለጥ ሲሆን፤ ሌላኛው “መሻል” ደግሞ ካለብን ህመም መዳን ነው።

አርምሞ ላይ ከሁለት ሺህ በላይ አርቲክሎች ተጠራቅመው ይገኛሉ። ስለዚህ  መጻፍ ማቆሜ የሚያሳጣ ነገር አይደለም። ይልቅ ከዚህ በፊት የተጻፉትን እያነበቡ ወደ መገንዘብ መድረስ ሌላኛው የዕድል በር ነው።

ሴት ሆይ ትንሿ ማህፀንሽ ልጅን ያህል ተፈጥሮ ከሰራ ከዚህ ያነሰውን ተግባር ለማድረግ ምንድነው ያቃተሽ። መከራ ዝምታን እስከሚያስተምርሽ አትጠብቂ፤ ይልቅ በዝምታ መከራን ተማሪ!። ጾምና ጸሎትሽ መንፈሳዊ መሳርያ እንደሆነ እያወቅሽ የነፍስ ወቀሳ ውስጥ መግባት አግባብ አይደለም። ቂጥሽን ከመቀመጫና ከመተንፈሻነት በዘለለ ወደ ንግድ ከቀየርሽው ጊዜያዊ ትርፍ ላይ እንዳለሽ እወቂ። ደግሞም በመቀመጫሽ መቀመጥን አታብዢ፤ አካልሽን አንቀሳቅሺ የላብሽን በረከት ተመገቢ።

ወንድ ሆይ ጠቢቡ ሰሎሞን እንዳለህ፦
“ኋላ እንዳትጸጸት ገንዘብህን፣ ልብህንና ጉልበትህን ለሴቶች አትስጥ፤ ከምክር ጋር ሁሉን አድርግ”

አዎን ጉልበትህን ለሴቶች አትስጥ ብልህነትህ በብልትህ በኩል አይመጣምና አስተውል። ለወሲብ በተጋበዝክ ቁጥር የአልጋ ትግልህ አካላዊ አቅምህን ይበላዋል። አዎን ለሴጋም ሆነ ለሴት ጉልበትህንና ስፐርምህን አትስጥ። ስጋን በስራ አድክም፤ ትርፍህን በኪሳራ መመዘን አቁመህ ነገን አሻግረህ ተመልከት። ለዓይንህ መከለያ አድርገለት እንደሚባለው፤ ከክፉህ ተግባርህ ጋር ጦርነት ግጠም፣ አሳቡን አጥላላው፣ ከስር ጀምረ እስከ ራሱ ድረስ ቀጥቅጠው። አዎን አረመኔነት ከተባለ በክፉ አሳብህ ላይ ጨካኝ አረመኔ ሁን። ሳይቀድምህ ቅደመው ሳይገድልህ ግደለው!። አዲዮስ..🙌🏼
አርምሞ🧘🏽‍♂

25 Feb, 18:15

3,693

Final Article ✍🏼

“እምነት” ልክ በምድጃ ላይ እንዳለ ትኩስ ወጥ ነው። ታድያ  ዛሬ፣ ነገና ከነጎድያን ጨምሮ ከዚህ ወጥ እየጨለፍን ከተመገብን “ሃይማኖት” ይሆናል። ነገር ግን አማኝ የነበሩት ሃይማኖተኞች ይህን ወጥ እንደቀዘቀዘ ሳያሞቁ እንደመጣላቸው ይበሉታል። ለዛም ነው ብዙሃኑ የሚታመሙት!።
አርምሞ🧘🏽‍♂

25 Feb, 16:40

4,483

“በ2023 ደስተኛ ያልሆኑ ዜጎች ከሚኖሩባት ሀገር ኢትዮጵያ በ20ኛነት ተቀምጣ ነበር። በ2024 ደረጃችንን በማሻሻል 9ኛ ሆነናል” 🤗
      
             ―World gallery