ARDI YOUTH ACADEMY @ardiyouthacademy Channel on Telegram

ARDI YOUTH ACADEMY

@ardiyouthacademy


The Center of Safety, Discipline, and Innovation !

ARDI YOUTH ACADEMY (English)

Welcome to ARDI YOUTH ACADEMY, the Center of Safety, Discipline, and Innovation! This Telegram channel is dedicated to empowering young individuals through various programs and initiatives aimed at fostering personal growth and development. Whether you are a student looking to enhance your academic skills, an aspiring entrepreneur seeking guidance on starting your own business, or simply someone who is passionate about making a positive impact in the world, ARDI YOUTH ACADEMY has something to offer you. Who is it? ARDI YOUTH ACADEMY is a community-driven platform that brings together young minds from diverse backgrounds to learn, collaborate, and inspire each other. With a focus on safety, discipline, and innovation, the channel provides a supportive environment for individuals to explore their potential and turn their dreams into reality. What is it? ARDI YOUTH ACADEMY offers a wide range of resources, including workshops, webinars, mentoring programs, and networking opportunities, to help young people navigate the challenges of today's world and achieve their goals. Whether you are interested in personal development, career advancement, or social impact, you will find valuable content and support on this channel. Join ARDI YOUTH ACADEMY today and become part of a vibrant community dedicated to empowering the next generation of leaders, innovators, and changemakers. Together, we can create a brighter future for ourselves and our communities. Let's embark on this exciting journey of growth and transformation, one step at a time! #ARDIYOUTHACADEMY #Safety #Discipline #Innovation

ARDI YOUTH ACADEMY

17 Feb, 17:17


ቀን 11 /06/2017 ዓ.ም
ለአርዲ ዩዝ አካዳሚ ተማሪ  ወላጀጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ፡፡
ጉዳዩ :-የወላጅ -መምህር ምክክር  እና  የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ማሳወቅን ይመለከታል ፡፡
1.  ሁለተኛው የወላጅ-መምህር የምክክር ቀን  አርብ  የካቲት 14  ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30  እስከ 10፡00 ድረስ የሚካሄድ መሆኑን በመገንዘብ እርሶም በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት  ት/ቤት በመገኘት የልጅዎን የቀለም ትምህርት አፈጻጸም እና ሁለንተናዊ እድገት በተመለከተ ከክፍል ኃላፊ መ/ራን ጋር እንዲወያዩ፣ በመማር -ማስተማርና በስነምግባር ግንባታ ዙሪያ ያለዎትን አስተያየት እንዲሰጡን እያሳሰብን፣  የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር በመምጣት የ4ዮሽ ስምምነት በመፈጸም እንዲሁም በቀጣይ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ እንድትወያዩ ስንል በአጽንኦት እናሳስባለን፡፡
2.  በወር ክፍያ ስርዓት የምትጠቀሙ ወላጆች  የየካቲት ወር  ፣ የ3ኛው ሩብ አመት የትምህርት ክፍያ  እና የሰርቪስ አገልግሎት ክፍያን ያልከፈላችሁ ወላጆች የተማሪው/ዋ ውጤት መግለጫ  እንደሚያዝባቸው ከወዲሁ ተገንዝባችሁ  ክፍያውን  እንድትከፍሉ እንጠይቃለን፡

ARDI YOUTH ACADEMY

29 Jan, 13:23


https://youtu.be/LteDVj4W6gs

ARDI YOUTH ACADEMY

28 Jan, 09:10


https://www.tiktok.com/@ardi.youth.academ1/video/7464889004932992262?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7451470155655251461

ARDI YOUTH ACADEMY

22 Jan, 14:41


https://youtu.be/GWrhKFL3xC0

ARDI YOUTH ACADEMY

21 Jan, 14:38


https://youtu.be/GU40uh3YvPo?si=iGnjcYwdYFNGG5Ih

ARDI YOUTH ACADEMY

09 Jan, 17:32


https://youtu.be/GgvIKBwgPG0?feature=shared

ARDI YOUTH ACADEMY

09 Jan, 14:35


https://vm.tiktok.com/ZMkPRuaJm/

ARDI YOUTH ACADEMY

04 Jan, 17:28


ቀን 25/04/2017 ዓ.ም
ለአርዲ ዩዝ አካዳሚ ወላጆች
እነሆ ሰብአዊነት የተንፀባረቀበት ወርን ወደ ማጠናቀቁ ተቃርበናል ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
1.  የአርዲ የልግስና ወር የመዝጊያ ፕሮግራም ሰኞ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም በሶስቱም ጊቢ ይካሄዳል በእለቱም አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ፡፡
2.  ከት/ቤቱ አጠቃላይ ማህበረሰብ የተሰበሰቡ አልባሳት እና ቁሳቁስ ለጥላሁን ወላጅ የሌላቸው ህፃናት መርጃ ማህበር ለተባለ ግብረሰናይ ድርጅቶች የማስረከብ ስነ- ስርዓት ይካሄዳል፡፡ የተሰበሰበው አጠቃላይ ገንዘብ ደግሞ የክብር ዶ/ር ቢንያም በለጠ በተገኙበት ለሜቄዶንያ የአረጋዊያን መርጃ  ማዕከል ይሰጣል፡፡ ሁሉም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ግራንድ አርዲ ከ2፡30 በፊት መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ በዕለቱ የአፀደ ህፃናት ተማሪዎች በየጊቢያቸው ፕሮግራም የሚያቀርቡ ሲሆን የሚቆዩት እስከ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ከ 5፡00 ጀምሮ ፈቃደኛ የሆኑ ወላጆች በግራንድ አርዲ ግቢ የሚካሄደውን ፕሮግራም እንዲከታተሉ እንጋብዛለን፡፡ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ 7፡00 ድረስ ፕሮግራም እስከሚጠናቀቅ ይቆያሉ፡፡
3.  በዕለቱ ልጅዎን የእራሳቸውን ልብስ  አልብሰው እንዲልኩልን እንጠይቃለን፡፡
4. የጥር ወር ክፍያ ስለተጀመረ እንዲከፍሉ ከወዲሁ እናስታውሳለን፡፡
                                               ት/ቤቱ

ARDI YOUTH ACADEMY

04 Jan, 11:19


በቀን 25/04/2017 ዓ.ም የአርዲ ወ.ተ.መ.ህ  ምክር ቤት  እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች የሁሉንም ጊቢዎች  የአገልግሎት ክፍሎች እና የመማሪያ ክፍሎችን አደረጃጀት  ምልከታ በማድረግ ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር በጥንካሬ የተመለከቷቸውን  እንዲቀጥሉ እንዲሁም መሻሻል ያለባቸውን የሰራ ሂደቶች በተመለከተ ግብረመልስ ስለሰጡን በመላው የአርዲ ቤተሰብ እያመሰገነን ት/ቤቱም እንዲሻሻሉ በሰጡን አስተያየቶች ላይ ማስተካከያ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።

ARDI YOUTH ACADEMY

03 Jan, 08:32


ትምህርት ቤቱ እያንዳንዱ ተማሪ ሊኖራቸው ይገባል ብሎ ካስቀመጣቸው ውስጥ 6 እና ከዛ በላይ ላሟሉ የግራንድ  አርዲ ተማሪዎች  የእውቅና መርሃ ግብር ተከናወነ። ዝርዝሩን በጊቢው ቴሌግራም ገፅ https://t.me/grandardiInfochannel ይመልከቱ

ARDI YOUTH ACADEMY

01 Jan, 13:36


Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=61552532278464
YouTube :- www.youtube.com/@ARDIYOUTHACADEMY-yo5rx
Tiktolk : https://www.tiktok.com/@ardi.youth.academ1
Telegram: - https://t.me/Ardiyouthacademy
Website: ardiyouthacademy.com

ARDI YOUTH ACADEMY

28 Dec, 09:01


አካዳሚያችን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ፣ የተማሪዎች ውጤት እና ባህሪ መሻሻል እንደሚተጋ ይታወቃል፡፡
ይህን ግብ ማሳካት የሚያስችሉ በ18/04/2017 ዓ.ም
1ኛ . ለቅድመ አንደኛ (ኬጂ) መምህራን የተማሪዎች ባህሪን መረዳት እና ማስተማር የማይንድ ሞርኒግ የስለጠና ተቋም አሰልጣኝ በሆኑት በወ/ሮ ፀምረ መዘመር ፤
2ኛ . ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ለሚያስተምሩ መምህራን ምዘና በማስተማር እና መማር ሂደት ውስጥ እንዴት ይከወናል በሚል የብሪቲሽ ካውንስል አሰልጣን በሆኑት በአቶ ኪዳኔ ገደፋው እንዲሁም
3ኛ . ለሞግዚት ፣የጥበቃ እና የጠቅላላ አገልግሎት ሰራተኞችን የአርዲን ፍልስፍና እና ተልዕኮ የተቀመጡ ግቦችን በጋራ ስለማሳካት በትምህርት ቤታችን አማካሪ በሆኑት በአቶ ዮሴፍ በቀለ አማካኝነት በ3 የተለያዩ ስልጠና ክፍሎች ተሰጥቶ ነበር ። ስልጠናዎቹን በከፊል በፎቶ

ARDI YOUTH ACADEMY

24 Dec, 21:03


https://youtu.be/p4ER1Xs9TKg

ARDI YOUTH ACADEMY

24 Dec, 18:27


https://youtu.be/zbOko99J1OA

ARDI YOUTH ACADEMY

04 Dec, 16:07


ለአርዲ ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ጉዳዩ :-የወላጅ _መምህር ምክክር ፣የብሄር ብሄረሰብ በዓል አከባበር እና ቦንድ ግዢ  ይመለከታል
1.  ሁላችንም እንደምናውቀው ሀገራችን በአባይ ወንዝ ላይ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እየገነባች ትገኛለች፡፡ ፕሮጀክቱ ዕውን ሆኖ ማየት ደግሞ የሁላችንም ህልም ነው፡፡ ለዚህም ርብርብ እና ትብብር እንደሚያስፈልግ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ከወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት በተላከልን አቅጣጫ መሰረት ተማሪዎች እያንዳንዳቸው ለዚህ ፕሮጀክት ድጋፍ 50 ብር እና ከዚያ በላይ  እንዲያዋጡ ይጠበቃል፡፡
በመሆኑም መዋጮዉን ወላጆች ለምክክር ስትመጡ  እንድትከፍሉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
2.አርብ ህዳር 27 /2017 ዓ.ም የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን በማክበር  ብዛህነትን የምናስተምርበት ቀን ስለሆነ  ተማሪው/ዋ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትን አስለብሰው እንዲልኩልን እንጠይቃለን። ትምህርት ለግማሽ ቀን እስከ 6 ሰዓት ነው።
3. የመጀመሪያው ሩብ አመት የወላጅ -መምህራን ምክክር በጣም ደማቅ በሆነ ሁኔታ እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም ይካሄዳል ። ስለሆነም በሚላክልዎ ሰዓት በመምጣት ስለ ልጅዎ የቀለም ትምህርት እና ሁለንተናዊ እድገት እንዲወያዩ ቀጠሮዎን እንዲያስተካክሉ  እንጠይቃለን።

ARDI YOUTH ACADEMY

03 Dec, 07:34


ለተከበራችሁ ውድ የአርዲ ዩዝ አካዳሚ ተማሪ ወላጆች
የልጆቻችን እድገት በመርህ እንዲመራ የነበራችሁን እውቀት እና ልምድ በድጋሚ እንድታስሱት እንዲሁም ትምህርትቤታችን ለልጆቻችን ሁለንተናዊ እድገት አብረን መስራት እንድንችል አንድ ገፅ ላይ እንድንመጣ ያዘጋጀውን ስልጠና በአርዲ የስብሰባ እና ስልጠና ታሪክ ተሳትፎን የሚቀይር ምላሽ የሚሰጥ ተሳትፏችሁን በልጆቻችን ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡
በቀጣይ ልጆቻችን እንድንረዳቸው እና እንድናግዛቸው የሚያስችሉ ስልጠኛዎችን ቀጣይነት ባለቸው ሁኔታ ለመስጠት የትምርት ቤቱ ባለቤት የሆኑት አቶ ጌትነት አለሙ ቃል ገብተዋል ፡፡ መርሃ ግብሮቹን በቅርብ የምናሳውቃችሁ ይሆናል ፡፡
በእለቱም ነባር የወላጅ ኮሚቴዎች ያከናወኗቸውን ስራዎች ሪፖርት እና በቀጣይ ሊሰሯቸው ያቀዱትን ስራዎች ለወላጆች አቅርበዋል። በመጨረሻም የየክፍሉ የወላጅ ተወካይ ተመርጠዋል ፡፡

ስልጠናው በፎቶ በከፊል

ARDI YOUTH ACADEMY

16 Nov, 05:27


ለአርዲ ዩዝ አካዳሚ ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት መጥተናል፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ !! እንኳን ደስ አለን!!

ትምህርት ቤታችን በ2016 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም መሰረት ህዳር 05/2017 .ም በወረዳ 13 ት/ፅ/ቤት በተካሄደው የትምህርት ጉባኤ ላይ በወረዳው ስር ካሉ ትምህርት ቤቶች
✔️በስድስተኛ ክፍል በከተማ ደረጃ በተመዘገበ ውጤት
1. ሶስና ታሪኩ 1ኛ
2. በእምንት አዲስ 2ኛ
3. ዮርዳኒስ ቲዎድሮስ 3ኛ በመውጣት የተሸለሙ ሲሆን
✔️በስምንተኛ ክፍል
1. ናሆም አማረ 2ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
✔️ በአንደኛ ደረጃ ምድብ መምህር አብዱልሽኩር ጀማል የተማሪዎችን ውጤት እና ስነ ምግባር በማሻሻል 1ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆናል ፡፡
✔️ በአፀደ - ህፃናት ምድብ ር/መምህርት ሚስ ብርሃን አባተ 3ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆናለች፡፡
✔️በ1ኛ ደረጃ ምድብ ር/መምህር የተማሪዎች ውጤት እና ስነ ምግባር ላይ በመስራት እንዳለ መኮነን 1ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል ፡፡
አርዲ ዩዝ አካዳሚ በ6ኛ ክፍል እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 1ኛ ዋንጫ ያነሳ መሆኑን እና በተጨማሪም በ6ኛ ክፍል እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ወረዳው በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲጠራ በማችቻሉ የእውቅና ሰርቲፊኬት በክብር ተቀብሏል፡፡ እነዚህን ስኬቶች እንዲጨብጥ አብራችሁን መሰራታችሁ ከልባችን እናመሰግናችኋለን፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

ARDI YOUTH ACADEMY

12 Nov, 09:53


ውድ የአርዲ ተማሪ ቤተሰቦች
እንደሚታወቀው ት/ቤታችን ከመማር ማስተማር ባሻገር በልጆች ሁለንተናዊ እድገት (holistic development) ላይ ስትራቴጂ ነድፎ አበክሮ እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይሄውም በተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ እድገት፣ በባህሪያቸው፣ በፈጠራ ክህሎታቸው፣ በደህንነታቸው፣ በኪነ ጥበብ ክህሎታቸው ወ.ዘተ. ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ስራዎች ወላጆች እንዲያውቁትና ልጆች እንዲማሩበት ቪዲዮዎቸን፣ ፎቶዎችና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች የሚቀመጠጥበት ልዩ የቴልግራም ቻናል በሁሉም ቅርንጫፍ ስም ስለተከፈተ ቻናሎችን በመቀላቀል እንድትከታተሉ እዲሁም ጠቃሚ ነገሮች ስለቀቁ ለልጆች እንድታሳዩ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
To All ARDI Students’ Parents/Guardians
As you know, our school is committed not only to teaching and learning but also to the holistic development of children. This approach includes a strong focus on enhancing students' English language skills, character development, creativity, safety, artistic talents, and more.
To keep parents informed and support student learning, we’ve created dedicated Telegram channels for each branch where we share helpful videos, photos, and other resources. We kindly ask parents to join these channels, follow our updates, and show their children any valuable information posted there.
https://t.me/sonardiInfochannel (for Son ARDI Nursery )
https://t.me/grandkginfochannel (for Grand KG Nursery -UKG)
https://t.me/grandardiInfochannel (for Grand ARDI Grade 1-3)
https://t.me/motherardiInfochannel (for Mother ARDI Grade 4-8)
በተጨማሪም ለሚኖራቸው ማንኛውንም አስተያየት በሚከተለው ሊንክ አስተያየታችሁን መላክ እንዲሁም ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር እንዲደርስ የሚፈልጉት በፎቶ፣ በድምፅ እንዲሁም በፁህፍ መላክ ይችላሉ፡፡
https://t.me/ardiyouthacademyinfo ፡፡

ARDI YOUTH ACADEMY

05 Nov, 12:43


ለአርዲ ዩዝ አካዳሚ የ2016 የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች
ጉዳዩ ፡- ሪፖርት ካርድ እንድትወስዱ ስለማሳወቅ
ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው የ2016 የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሪፖርት ካርድ ስለመጣ ማዘር አርዲ ቢሮ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ በመምጣት ከረቡዕ ጥቅምት 27- 29/2017 ድረስ በስራ ሰዓት መጥታችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን ፡፡

ARDI YOUTH ACADEMY

04 Nov, 07:40


ለአርዲ ዩዝ አካዳሚ ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችን እያቀረብን ልጆቻችሁ ትምህርት ቤት በሚኖራቸው ቆይታ የሚሰሯቸው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል በየጊቢዎች የተከፈቱ የቴሌግራም ቻናሎችን እንድትቀላቀሉ እንጠይቃለን ፡፡
https://t.me/sonardiInfochannel (for Son ARDI Nursery )
https://t.me/grandkginfochannel (for Grand KG Nursery -UKG)
https://t.me/grandardiInfochannel (for Grand ARDI Grade 1-3)
https://t.me/motherardiInfochannel (for Mother ARDI Grade 4-8)
በተጨማሪም ለሚኖራቸው ማንኛውንም አስተያየት በሚከተለው ሊንክ አስተያየታችሁን መላክ እንዲሁም ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር እንዲደርስ የሚፈልጉት በፎቶ፣ በድምፅ እንዲሁም በፁህፍ መላክ ይችላሉ፡፡
https://t.me/ardiyouthacademyinfo ፡፡

ARDI YOUTH ACADEMY

19 Oct, 15:22


የአርዲ ዩዝ አካዳሚ ወ.ተ.መ.ህ ኮሚቴዎች ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም  የጥቅምት ወር ወርሃዊ  ስብሰባ አድርገዋል።
1. በዕለቱ ስብሰባ የትምህርት ዘመኑ የትምህርት ቤቱ የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ማድመጥ ።
2.  ከወላጆች የተነሱ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን ትምህርት ቤቱ እንዲሰራበት ወይይይት ተደርጓል።
3.  የወ.ተ.መ ህ  ኮሚቴዎች በቀጣይ  ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ለማድረግ አቅጣጫ አስቀምጧል።

3,689

subscribers

3,329

photos

174

videos