ጉባኤ ሐዋርያት @apostolic_council Telegramチャンネル

ጉባኤ ሐዋርያት

ጉባኤ ሐዋርያት
እንኳን ወደ ጉባኤ ሐዋርያት በደህና መጣችሁ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት "ሐዋርያት በሰበሰቧት ከሁሉ በላይ በምትሆን በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን"

ከእግዚአብሔር ቃል የተጣረሱ ሐዋርያዊ ወንጌልን የሚጻረሩ አስተምህሮዎችን ሁሉ እያነሳን በቃሉ ሥልጣን እንለያቸዋለን ከሐዋርያት የተቀበልነውን ቅዱሱን ወንጌል አጽንተን እንቀጥላለን።
1,875 人の購読者
59 枚の写真
5 本の動画
最終更新日 01.03.2025 03:48

類似チャンネル

✨ኢየሱስ ይመጣል✨
9,751 人の購読者
Amharic Spritual Books
4,587 人の購読者
Spiritual Books
3,569 人の購読者

የጉባኤ ሐዋርያት ታሪክ እና ምንነት

ጉባኤ ሐዋርያት የክርስቲናን ታሪክ ይታወቅ እና ከመጀመሪያ ከወርደ ወቅት ጀምሮ ወነት ትስስር የአሰማሪ ዘንድሮችን ይይዣው ይባላል። የጉባኤ ሐዋርያት የክርስቲና ግንባር ላይ እንዲሆን ይበል ፣ ያስተባበሩ የዘይታ ከጉዛቸው መረጃ ይጠቀማል። እነዚህ የሐዋርያዎች ታሪክ የተመለከተ የክርስቲናን ዝርዝር እና ኢንቀስተመዋ ይለያዩ፣ ይላን ደምቁ ይላን መነታቸውን ይሙያሉ።

ጉባኤ ሐዋርያት ማለት ምንድነው?

ጉባኤ ሐዋርያት የክርስቲና እምነት የሚያንሰሳቸው የስራዎች ጉባኤ ነው፡፡ እምነታቸው ከመጀመሪያዎቹ ወንጌሎች ነው የተመነዚባቸውን ዝርዝር ይሰጣሉ፡፡ እንዲህ ያለው ወይም የሐዋርያው ይባላል፡፡

እንዲሁም ሐዋርያት ከአሐዲል ቅድስ ቤተክርስቲያን ይገድድ የአለሙ የሚለው ምንነት ከነማ የዚያ ወንጌል ዝርዝር ይመለከታሉ።

ጉባኤ ሐዋርያት የክርስቲና ዳሰሳዎችን እንዴት ይይዙ?

ጉባኤ ሐዋርያት የክርስቲና አስተያየት ይሰጣሉ ይነመሩዋል የሞገድ ዝርዝር ጉባኤ ይሆንባቸው ይገባሉ፡፡ ሐዋርያዊ እምነት ከአስተያይት ያለው ውስጥ ይተወቀ ይገባል፡፡

ወይም የማህበረሰብ አዋጁ የእምነቶች እና ዛርይየት ዝርዝር ስለሚኖረው ይይዙ። እንዲሁም መረጃ የሚለውን ወማዞ ለነበሩ ያኖሩ ይይዙ፡፡

ጉባኤ ሐዋርያት ከአምላክ ቃል የተለዩ የምንድን አስተያየት አለ?

ጉባኤ ሐዋርያት ከአምላክ ቃል ይይዙ የኅሊው ወይም እንዲሁም ወሚለውን እንዲሁ ወይም ኃይል ይለያዮች መረጃ ይይዙ የማስተላለፊያ ይመለክ ይለዩ፡፡

ወይም የሐዋርው ቃል ለመጠቀም ዝርዝር ይለያዩ ይወዳድሩ ይኖርዋን ይኖሩ።

ጉባኤ ሐዋርያት テレグラムチャンネル

ጉባኤ ሐዋርያት በሃኪማት እንደሚሆን ቅዱሳን ወራሪዎች ላይ አስተማማኝ እና አስተምህሮዎችን መንፈሳዊ መልዕክቶች እንሻገናለን። በሌላም በተከለከለው ኳስ ፈጽሞ እርጋቹን መስለጥ እንደሆነ እንደዚህ ውሰድ ይችላል ሐዋርያት ከቁስለምለስ ቤተክርስቲያን፣ መልክምን አርግቼ እንቀርባለን። ሐዋርያት የተቀበለበት የእንግሊዝ ርሑስ ወንጌልን በቀን እናምናለን።

ጉባኤ ሐዋርያት の最新投稿

Post image

𝑉. 𝐿𝑒𝑡 𝑢𝑠 𝑏𝑒𝑐𝑜𝑚𝑒 𝑙𝑖𝑘𝑒 𝐶ℎ𝑟𝑖𝑠𝑡, 𝑠𝑖𝑛𝑐𝑒 𝐶ℎ𝑟𝑖𝑠𝑡 𝑏𝑒𝑐𝑎𝑚𝑒 𝑙𝑖𝑘𝑒 𝑢𝑠. 𝐿𝑒𝑡 𝑢𝑠 𝑏𝑒𝑐𝑜𝑚𝑒 𝐺𝑜𝑑'𝑠 𝑓𝑜𝑟 𝐻𝑖𝑠 𝑠𝑎𝑘𝑒, 𝑠𝑖𝑛𝑐𝑒 𝐻𝑒 𝑓𝑜𝑟 𝑜𝑢𝑟𝑠 𝑏𝑒𝑐𝑎𝑚𝑒 𝑀𝑎𝑛.

ክርስቶስ እንደ እኛ ስለ ሆነ [እኛ] እንደ ክርስቶስ እንሁን። እርሱ ስለ እኛ ሰው ሆኖአልና ለእርሱ ብለን የእግዚአብሔር እንሁን።

ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ (ነባቤ መለኮት)
𝐺𝑟𝑒𝑔𝑜𝑟𝑦 𝑜𝑓 𝑁𝑎𝑧𝑖𝑎𝑛𝑧𝑢𝑠 (𝑇ℎ𝑒𝑜𝑙𝑜𝑔𝑖𝑎𝑛)
𝐎𝐫𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 1:5

መልካም ዕለተ ሰንበት🙏

23 Feb, 07:05
476
Post image

«የማይታየው የእግዚአብሔር መልኩ ማንን ይመስላል ቢባል የሚታየውን የኢየሱስን መልክ ይመስላል «እርሱ የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው» [እርሱ] የክብሩ መንጸባረቅ እና የባሕርዩ ምሳሌ ነውና። Gregory Thamumaturgus-Wonder worker) (ጎርጎርዮስ ገባሬ ተአምራት ወመንክራት) 213-270) ስለዚህ ነገር በአመሥጥሮት ሲናገር... «ኮነ በአርአያ ሰብእ እስከ ኮኑ ሰብእ ድልዋነ ይርአይዎ ለመለኮት» ይላል። ትርጓሜውም «ሰዎች መለኮትን ያዩት ዘንድ የበቁ እስኪሆኑ ድረስ በሰው ባሕርይ ተገለጠ፤ ይላል። እንደው ግን መቼ ይሆን የሰው ልጆች አምላክን በመለኮትነቱ ለማየት የበቁ የሚሆኑት?? መልሱ መቼም ነው። ራሱ ጎርጎርዮስ ከዚህ ቃሉ ከፍ ብሎ ፦
"የሰውን ባሕርይ እስኪዋሐድ ዘመዳቸውም ሆኖ ሰውን ሁሉ ወደእርሱ እስኪያቀርብ ድረስ ሰው ፊትህን አይቶ ሕያው መሆን አይቻለውም ነበርና"

ስለዚህ ክርስቶስ የማይታየውን ባሕርይ የምናይበት ፍኖታችን ነው። «ወበእንተዝ ውእቱሂ ኮነ በአርአያ ሰብእ» ይላል ይህ አባት ጎርጎርዮስ ትርጓሜውም በእውነት በሰው ባሕርይ ተገለጠ ማለት ነው።

እስኪ ዐይናችንን ወደ ክርስቶስ አቅንተን በሙላት እግዚአብሔርን እንየው።

መልካም ቀን 🤗

19 Feb, 09:04
696
Post image

ዐዕይንተ-ባልትዛር ◈ የባልትዛር ዐይኖች

«ከፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ» 2ቆሮንቶስ 10፥7

ባልትዛር ጌታ ኢየሱስ ከተወለደ ከ33 ዓመታት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ለንግድ ያቀናል። ነገር ግን ቀድሞ ከብዙ ዓመታት በፊት ያውቃት ነበርና ዛሬ ግን ሲያያት ይህች የሰላም ከተማ ባድማ ነበረች፤ ሰው ይበዛባት የነበረች ይህች ከተማ አሁን ሰው አልባ ሆነች። ይህንን አይቶ ባልትዛር እየተደነቀ ሳለ አንዲት እናት ስትመጣ ዐይቶ «ዛሬ ኢየሩሳሌም ያለ ወትሮዋ ምነው ባድማ እና ሰው አልባ ሆነች» አላት። ይህችም ሴት፦«አንተ ለኢየሩሳሌም እንግዳ ነህን? አልሰማህምን የደሃ አባት፣የፍቅር መምህር፣ሰላምን የሚሰጥ፣ለተቸገሩት ሁሉ የሚደርሰውን አንዱን ክርስቶስን ይዘውት ሰዎች ሊሰቅሉት ወደ ቀራንዩ ሄደዋል» አለችው።

ባልትዛርም መንገዱን ወደ ጎልጎታ አቀና። ከመድረሱ በፊት ግን በመንገዱ ላይ ሰዎች ከበውት ወደ ኋላ.. ወደፊት.. በገመድ አስረው መስቀል አሸክመው የሚያጋፉትን ሰው አየ።መልኩን ጠጋ ብሎ ሊያይ ብዙ ጭፍሮች አሉና አልፈቀዱለትም ብዙም ሳይቀርብ ጥቂት ሲጠጋው ፊቱ በደም ስለ ተመላ ሊያውቀው አልቻለም፤ ጥቂትም ውሃ ሊሰጠው ወደደ ነገር ግን ጭፍሮቹ ሊያቀርቡት አልቻሉም።

ከብዙ ጊዜያት መንገላታት በኋላ ግን ቀራንዮ ደረሱ፤አሁንም ባልትዛር ዐይኑ ወደፊት ነው።ለስቅላት የተያዙ ሦስት ሰዎችን አይሁድ ሰቀሏቸው። በዚህ ሰዐት ባልትዛር ዐይኑም ልቡም በመካከል ላይ በተሰቀለው ዐረፈ

ባልትዛር ከ33 ዓመት በፊት በአካለ ሥጋ በቤተልሔም ለተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ መባዕ ካቀረቡ ሰብዐ ሰገል አንዱ ነበረ ለካ። ጌታ ኢየሱስን ወዲያኑ ለየው አወቀው፤ ተንበረከከና ❝ጌታ ሆይ ዛሬ አንዳች የምሰጥህ ነገር የለኝም፤ ያን ጊዜ ዕጣን ወርቅን  ከርቤን መባዕ ይዘው ከመጡ ሰዎች መሃል አብሬ መጥቼ መባዕ ሰጥቼህ ነበረ ዛሬ ግን የምሰጥህ የለኝም ራሴን ሰጠሁህ❞ ብሎ ተንበረከከ።
"እኛስ ምን እንሰጠው ይሆን?" የባልትዛር ታሪክ እንደሚነግረን ከሆነ ባልትዛር ከዛ በኋላ ዘመኑ ተባርኮ ሰላምን፣ እውነትን፣ፍቅርን፣የደግነት ጥግን፣በሞት የሚገለጥ ደግነትን በዐይኑ ተመልክቶ በልቡ ሸምቶ ተመለሰ።

ዐይናችን ዛሬ የት ነው ያለው? የቤተክርስቲያንስ ዐይኗ የት ነው ያለው? ቤተክርስቲያን ማለት እኛ ነንና።ኢየሩሳሌም ያለ ወትሮዋ ባድማ ነበረች፤ የባድማነቷ ምሥጢር ግርማ የሚሰጣትን አምላክ አሳልፋ መስጠቷ ነበረ። ዛሬ የሰላም ማጣት የባድማነትን እና የባዶነት ምሥጢር የሰላም አለቃ ክርስቶስ ከዐይናችን ፊት ስለ ተጣለ ነው የባልትዛር ዐይኖች መሀል ላይ በተሰቀለው በክርስቶስ ላይ ነበሩ በፊታችን ያለውን ክርስቶስን እንመልከት። 

እግዚአብሔር ይርዳን አሜን።

ፕሮፌሰር አባ ኀይለ ገብርኤል ግርማ። የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት። በአንድ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ተገኝቼ ካስተማሩት የተወሰደ። የካቲት 2/2017 ዓ.ም

11 Feb, 18:28
982
Post image

መልካም ቀን🙏

@Apostolic_Council

07 Feb, 07:20
1,096