Al Qalam School (@alqalamschoolplc) के नवीनतम पोस्ट टेलीग्राम पर

Al Qalam School टेलीग्राम पोस्ट

Al Qalam School
A smart person
Knows what to say
A wise person
Knows whether or not
to say it
1,142 सदस्य
1,162 तस्वीरें
95 वीडियो
अंतिम अपडेट 09.03.2025 02:45

समान चैनल

MUSIC MIX WITH AASH
2,555 सदस्य
Abdurazak Isihak
2,002 सदस्य
Nujum Youths Excellence Center
1,120 सदस्य

Al Qalam School द्वारा टेलीग्राम पर साझा की गई नवीनतम सामग्री

Al Qalam School

28 Feb, 17:01

853

ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ!!!

እንኳን ለ1446ኛው ዓ.ሒ. የረመዷን ወር አደረሰን፤አደረሳችሁ።

ዛሬ እለተ ጁመዓ፣የካቲት 21/2017 ዓመታዊው የልግስና ሳምንት መቋጫውን አገኘ። በእለቱ ለተማሪዎች በመዝናናት ላይ የተመሠረተ ልዩ የልግስና መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይ የተማሪዎች ጀመዓ ኃላፊ መምህራንና የበጎ አድራጎት ክበብ ተጠሪ፣ እንዲሁም የቀድሞ ተማሪዎች በቅንጅት ባካሄዱት የነቃ ተሳትፎ መርሃ ግብሩ በደመቀና በተሳካ መልኩ ተጠናቅቋል።

በተለይ የዛሬውን ቀን ጨምሮ ለተከታታይ ቀናት በተማሪዎች ጀመዓ አመራር መምህራን በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ዘመቻ በተካሄደ የልግስና ንቅናቄ በአጠቃላይ በገንዘብና በአይነት 323,000 (ሦስት መቶ ሃያ ሦስት ሺ)ብር ሊሰበሰብችሏል። በእቅድ ተይዞ ከነበረው የገንዘብ መጠንም የ73ሺ ብር ጭማሪ አሳይቷል።

ለእቅዱ መሳካት ላቅ ያለውን ሚና ለተጫወታችሁ ወላጆች (አሳዳጊዎች) ልባዊ ምስጋናችንን እያቀረብን ለሰደቃ ያዋላችሁት ገንዘብ በዱንያም በአኼራም ድርብርብ አጅር የምትመነዱበት ያደርግላችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው።

አልቀለም የልግስና ዓለም!!!
Al Qalam School

27 Feb, 17:40

213

ለተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ።

በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጀምሮ እስከ ጁመዓ ድረስ ለተማሪዎች የሁለተኛው መንፈቀ ዓመት የመጀመሪያው ሙከራ ይሰጣል።በመሆኑም በአራትዮሽ አማካይ እቅዳችሁ መሠረት ልጆቻችሁ አመርቂ ውጤት ያስመዘግቡ ዘንድ በየእለቱ በፕሮግራም እንዲያጠኑ ክትትልና ድጋፍ ያድርጉላቸው።

ማስገንዘቢያ
:- የሙከራ ውጤቱ በአማካይ ከ5 በታች የሆነ ማንኛውም ተማሪ ወላጁ (አሳዳጊው) በአካል ተገኝቶ ከሚመለከተው መምህር ጋር በመወያየት ለቀጣይ ሙከራ  በክትትልና ድጋፍ ማሻሻያ ለማድረግ ቃል በመግባት በመወያያ ቅፅ ላይ መፈረም ይኖርበታል::

       አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!
Al Qalam School

21 Feb, 18:04

659

በአንደኛው መንፈቀ ዓመት አመርቂ ውጤት አስመዝግበው ከአጠቃላይ ሴክሽኖች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ 28 የደረጃ ተማሪዎች በሠልፍ ሥነስርዓት ላይ ተማሪዎች፣መምህራንና አመራሮች በተገኙበት የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው።

አስገራሚ ቅንጭብጭብ እውነታዎች

👉4 ተማሪዎች ማለትም ተማሪ ማሪያ ነጅሙ ፣ ኢንቲሳር አብዱረሂም እና ዑመር ሙሀመድመኪን ከ3ኛ ክፍል እንዲሁም ተማሪ ራዚቃ ዑመር ከ1ኛ ክፍል ሽራፊ ማርክ ሳያጓድሉ ድፍን 100 አማካይ ውጤት አስመዝግበው ከአጠቃላይ ተማሪዎች 1ኛ ወጥተዋል።

👉3ቱም የአቶ ኢድሪስ ልጆች ማለትም ሀምዛ ኢድሪስ ከ8ኛ ክፍል ተማሪዎች 2ኛሂዳያ ኢድሪስ ከ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 1ኛ፣ እንዲሁም ተማሪ ዙለይካ ኢድሪስ ከ4ኛ ክፍል ተማሪዎች 1ኛ በመውጣት ቤተሰባዊ ድል የተቀዳጁ ሲሆን  በአልቀለም ታሪክም ከፍተኛው የቤተሰብ ሪኮርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

👉የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሂባ ናስር ከምስጉን ሥነምግባር ጋር ለተከታታይ ረዘም ያለ ዓመታት ከ1ኛ ደረጃ ውጪ 2ኛ እንኳ ወጥታ ባለማወቅ አይረሴ የታሪክ አሻራዋን አሳርፋለች።


              አልቀለም የስኬት ዓለም!!!
Al Qalam School

10 Feb, 17:44

281

ለተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአልቀለም ት/ቤት በፃፈው የግብዣ ደብዳቤ መሠረት እለተ ቅዳሜ፣የካቲት 08/2017 ከጠዋቱ 2:30-6:30 ድረስ ለሙስሊም ወላጆች (አሳዳጊዎች) ልዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት እቅድ ይዟል።

ስለሆነም ምክር ቤቱ በሰጠን ኮታ መሠረት ከትምህርት ቤታችን መሳተፍ የምትፈልጉ ሃያ አምስት (25) ወላጆች (አሳዳጊዎች) ብቻ በዚህ መልካም እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ እየገለፅን እስከ ረቡዕ፣ የካቲት 05/2017 በአካል በመገኘት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል
እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

የቀደመ ተጠቀመ!!



                             ከሰላምታ ጋር


          አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!
Al Qalam School

09 Feb, 07:25

430

ለተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ።

አስቀድመን በደብዳቤ ባሳወቅናችሁ መሠረት ነገ እለተ ሰኞ፣የካቲት 03/2017 የሁለተኛው መንፈቀ ዓመት መደበኛ የትምህርት አገልግሎት ይጀመራል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ነጥቦች ትኩረት እንድታደርጉባቸው አደራ እንላለን።

👉ነገ እለተ ሰኞ የአጠቃላይ መምህራን
ስብሰባ ስለሚካሄድ የትምህርት
አገልግሎት የሚሰጠው ለግማሽ ቀን
እስከ 6:30 ብቻ ነው።

👉ከማክሰኞ ጀምሮ ከማጠናከሪያ
ትምህርት ጋር እስከ 10:00 ሰዓት
የሚሰጥ ይሆናል።

👉የውጤት ማስተካከያ ጥያቄ ያለው
ማንኛውም ተማሪ እስከ ነገ ሰኞ ብቻ
ቅሬታውን ለሚመለከታቸው መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች ማቅረብ ይችላል።

👉ወርሃዊ ክፍያ አጠናቅቆ ያልከፈለ
ወላጅ(አሳዳጊ) የልጁን ሰርተፊኬት
መቀበል አይችልም።


                             ከሰላምታ ጋር


          አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!
Al Qalam School

07 Feb, 15:27

610

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ።

ከረቡዕ፣ጥር 28/2017 እስከ ዛሬ ዓርብ፣ጥር 30/2017 ድረስ በትምህርት ቤቱ አመራር አስተባባሪነትና በዲፓርትመንት ኃላፊዎች አመቻችነት በዋና መምህራን መካከል በትምህርት እቅድ ዝግጅት (Lesson Planning) ፣በአሳታፊ መማር ማስተማር ስልቶች (Interactive Learning Techniques ) እና በፈተና ቢጋር አዘገጃጀትና በተከታታይ ምዘና (Table of Specification & Continious Assssment) ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ እርስ በርስ መገነባባት ላይ ያተኮረ የአቻ ለአቻ የስልጠና መርሃግብር ለየት ባለና ተግባር ተኮር በሆነ መልኩ ተካሄዷል።

እንዲሁም ለረዳት መምህራት በባለሞያ የታገዘ ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በሚደረግ እገዛ (Treatment Techniques for Special needs ) እና በመማር ዘይቤዎች (Learning styles) ዙሪያ ሥልጠና የተካሄደ ሲሆን በሥራ አጋጣሚ የነበሩ ጉዳዮችን በማካተት ላይ የተመሠረተ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ሥልጠናው በአራት የመማሪያ ክፍሎች ላይ ተሰባጥሮ የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም በትምህርት ቤቱ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ በድሩ ኑሩ ጋባዥነት የምሳ መርሃግብር ተከናውኖ ተጠናቅቋል።

        አልቀለም የልህቀት ዓለም!!!
Al Qalam School

24 Jan, 15:02

1,351

የተሻለ ውጤት የሚያመጡ  ተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል

📢 12 ወሳኝ ነጥቦች

📖 1. ጥናት ከመጀመራቸው በፊት
ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው
ዓላማ ያስቀምጣሉ።ይህ ማለት ምን
ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው
ያቅዳሉ።

📖 2. መፅኃፍ ገልጠው ጥናት
ከመጀመራቸው በፊት
ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ
የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ።
መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ
በኃላ የነበራቸውን ግምት
እያጠናከሩ...የተሳሳተውን
እያስተካከሉ ይጓዛሉ።
📖 3. ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ
አጠር አድርገው ማስታወሻቸው
ላይ ያሰፍራሉ።

📖 4. አንብበው ለመረዳት
ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/
ደጋግመው ያነባሉ።

📖 5. ጥናት ከመጀመራቸው በፊት
ማጥናት ስለፈለጉት ርእሰ ጉዳይ
ጥያቄዎች ይፈጥራሉ። መፅኃፍ
ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በሃላ
ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ
እንጂ ሁሉንም ነገር በማንበብ
ጊዜያቸውን አያጠፉም።

📖 6. ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ
ወይም መረጃ ከአሁን በፊት
ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ
የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን
ይመረምራሉ::

📖 7. በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለማጥናት
አይሞክሩም፡፡ በአንድ ጊዜ ብዙ
ነገር ለማጥናት መሞከር ትርፉ
ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡

📖 8. ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት
ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ
ጊዜ አላቸው፡፡

📖 9. ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ
ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፤
አያቅማሙም፡፡

📖 10. ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል
ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡

📖 11. ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፤
ያግዛሉ፤ይጠይቃሉ፡፡

📖 12. ራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ
ጎናቸውን በፍጥነት ያስተካክላሉ፡፡
Al Qalam School

21 Jan, 15:08

789

በአንደኛው መንፈቀ ዓመት ለመጨረሻ ዙር የአስራ አምስቱ ቀን ከዋክብቶች(Star Students) የፈተና ቁሳቁስ (እርሳስ፣ እስክሪቢቶ፣መቅረጫ፣ላጲስ፣መታወቂያ ወዘተ )መያዣ የሚሆን ቦርሳ በሽልማት ተበረከተላቸው።
Al Qalam School

17 Jan, 20:17

1,179

ለአንድ ሳምንት በተከታታይ ቀናት በተማሪዎች መካከል በተካሄደው የሒሳብ እና የእንግሊዝኛ ትምህርት የጥያቄና መልስ ውድድር ከየክፍሉ አንደኛ አንደኛ ለወጡ አሸናፊዎች ሽልማት ተበረከተላቸው።
Al Qalam School

12 Jan, 14:58

1,142

በዛሬው እለት ጥር 04/2017 "ልጅዎችዎን እናስተዋውቅዎ" በሚል ርዕስ ለወላጆች ልዩ የሥልጠና መርሃግብር የተካሄደ ሲሆን የእናቶች ተሳትፎ ከአባቶች አንፃር ተሽሎ መገኘቱን ለመታዘብ ተችሏል።የቀረም ቀርቶበታል።


አልቀለም የልህቀት ዓለም!!!