Al Qalam School @alqalamschoolplc Channel on Telegram

Al Qalam School

@alqalamschoolplc


A smart person
Knows what to say
A wise person
Knows whether or not
to say it

Al Qalam School (English)

Welcome to Al Qalam School, a Telegram channel dedicated to feeding your mind with wisdom and knowledge. The name 'Al Qalam' translates to 'The Pen' in Arabic, symbolizing the power of words and knowledge. Our channel, @alqalamschoolplc, aims to provide you with thought-provoking quotes, insightful messages, and motivational content to inspire you on your journey towards personal growth and enlightenment. At Al Qalam School, we believe that being smart is not just about knowing what to say, but being wise is knowing whether or not to say it. With that philosophy in mind, we curate and share content that will stimulate your mind, challenge your perspectives, and encourage you to think deeper about life and the world around you. Whether you are looking for daily doses of inspiration, uplifting quotes to brighten your day, or profound messages to contemplate, Al Qalam School is the perfect place for you. Join our community of like-minded individuals who are committed to continuous learning and self-improvement. So, if you are ready to embark on a journey of enlightenment and wisdom, join us at Al Qalam School. Let the power of words guide you towards a brighter and more fulfilling life. Remember, a smart person knows what to say, but a wise person knows whether or not to say it.

Al Qalam School

28 Dec, 10:41


እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ለሆኑ ሴት ተማሪዎች ከታህሳስ 21 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በትምህርት ተቋማት የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ ተገለጸ።

(ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም) የክትባቱን ሂደት በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።

የማህጸን በር ካንሰር ክትባት እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ሆኖ ከዚህ በፊት ክትባቱን ላልወሰዱ ታዳጊ ሴት ልጆች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ገልጸው ዘንድሮ በከተማ አስተዳደሩ ክትባቱን እንዲወስዱ በዕቅድ ከተያዙ 177,000 በላይ ታዳጊ ሴቶች ውስጥ 90% የሚሆኑት በትምህርት ተቋማት እንደመገኘታቸው በትምህርት ቤት ለሚሰጠው ክትባት ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።

የማህጸን በር ካንሰር በሀገራችን ኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በገዳይነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በሽታ እንደሆነ በተለያዩ ጥናቶች መረጋገጡን ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ጠቁመው ክትባቱ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ መቆየቱን በመጥቀስ የዘንድሮ መርሀግብር ስኬታማ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Al Qalam School

20 Dec, 16:35


ዛሬ እለተ ጁማዓ ፣ታህሳስ 11/2017 አልቀለምን ወክለው የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ በመሳተፍ በሁለቱም የክፍል ደረጃዎች ት/ቤቱ አንደኛ አንዲወጣ ላደርጉ አምባሳደሮቻችን በሰልፍ ሥነስርዓት ላይ ወላጆቻቸው በተገኙበት የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው።

Wow! Wow! Wow!
Nice! Nice! Nice!
Bravo! Bravo! Bravo!
Mashallah! Mashallah! Mashallah!

Al Qalam School

19 Dec, 15:34


ለመላው የት/ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ!!

ተደገመ!ተደገመ!ተደገመ!
በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ፤እንኳን ደስ ያለን!

ዛሬ እለተ ሐሙስ፣ ታህሳስ 10/2017በወረዳ 05 አስተዳደር ትምህርት ጽሕፈት ቤት ቃሌ ክላስተር ማዕከል ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል በተካሄደው የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ ሀምዛ ኢድሪስ ከተጠየቃቸው ጥያቄዎች መካከል ሁሉንም በመመለስ 1ኛ የወጣ ሲሆን በትምህርት ቤት ደረጃም አልቀለም ትምህርት ቤት በድጋሚ የ1ኛነትን ማዕረግ አንዲጎናፀፍ አስችሏል።

በድርብርብ ድል ወደፊት!!!


           አልቀለም የስኬት ዓለም!!!

Al Qalam School

22 Nov, 16:54


ለተከበራችሁ ወላጆች(አሳዳጊዎች) ከላይ በተገለፀው የፈተና መርሃግብር መሠረት             ለልጆቻችሁ የጥናት ፕሮግራም በማውጣት ድጋፍና ክትትል ያደርጉላቸው ዘንድ አደራ እያልን ሰኞ ሕዳር 16/2017 ከሰዓት ለተማሪዎች የአጋማሽ ፈተና ዝግጅት እንዲያደርጉ ፣ እንዲሁም የአጠቃላይ መምህራን ስብሰባ ስለሚካሄድ   መደበኛ   የት/ት አገልግሎት የሚሰጠው ለግማሽ ቀን እስከ 6፡00 ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

መልካሞ የጥናትና የክትትል ጊዜ!!!

መልካም ውጤት!!!

         አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!

Al Qalam School

13 Nov, 16:27


ለ2017 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ፕሬዚዳንታዊ (የተማሪዎች ጀመዓ አሚር ) ምርጫ እለተ ጁመዓ ጥቅምት 29/2017 በድምቀት መካሄዱ ይታወቃል ። ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴውም ውጤቱን ሰኞ፣ በሰልፍ ሥነ ስርዓት ላይ በይፋ አሳውቋል:: በዚህም መሰረት
ከሴቶች:-
ተማሪ ሂክማ ዳውድ=ፕሬዚዳንት/አሚር
ተማሪ ሂባ ናስር =ም/ፕሬዚዳንት/ም.አሚር
ተማሪ አሊያ ሪድዋን =ፀሀፊ
ከወንዶች:-
ተማሪ ሀምዛ ሁሴን =ፕሬዚዳንት/አሚር
ተማሪ አነስ አደም =ም/ፕሬዚዳንት/ም.አሚር
ተማሪ ዑመር አብዱልበር =ፀሀፊ
ሆነው ከተመረጡ በኃላ በትናንትናው እለት ስራቸውን በይፋ የጀመሩ ሲሆን ከ4ኛ-8ኛ ክፍል ከሚገኙ የተማሪዎች ዋና አለቆች ጋር ስብሰባ በማካሄድ
👉የትምህርት ጥራትና ቁጥጥር አሚር ፣
     ም/አሚርና ፀሀፊ
👉የዳዕዋና ኢርሻድ አሚር ፣
     ም/አሚርና ፀሀፊ
👉የማህበራዊና በጎ አድራጎት
    አሚር ፣ም/አሚርና ፀሀፊ
👉 የሥነምግባርና ደንብ ማስከበር
    አሚር ፣ም/አሚርና ፀሀፊ
በድምፅ
    ብልጫ በመምረጥ ትምህርት
    ቤታቸውን በትጋት ለማገልገል
    ቁርጠኛነት አሳይተዋል ::

     አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!

Al Qalam School

08 Nov, 23:05


የ 2017 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ፓርላማ ፕሬዚዳንታዊ (የተማሪዎች ጀመዓ አሚር ) ምርጫ በዛሬው እለት ጥቅምት 29/2017 ከጁመዓ ሰላት በኃላ  በድምቀት ተካሄደ ።ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴውም ውጤቱን ሰኞ፣ በሰልፍ ሥነ ስርዓት ላይ በይፋ ያሳውቃል።

Al Qalam School

02 Nov, 04:52


ለተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ።

በሚቀጥለው ሳምንት ለተማሪዎች የአንደኛው መንፈቀዓመት  ሙከራ ሁለት  ይሰጣል።በመሆኑም ልጆቻችሁ ከመጀመሪያው ሙከራ የተሻለ ውጤት ያስመዘግቡ ዘንድ ዛሬን ጨምሮ ባሉት የእረፍት ቀናት በፕሮግራም እንዲያጠኑ ክትትልና ድጋፍ ያድርጉላቸው።

ማስገንዘቢያ
:- የሙከራ ውጤቱ ከ5 በታች የሆነ ማንኛውም ተማሪ ወላጁ (አሳዳጊው) በአካል ተገኝቶ ከሚመለከተው መምህር ጋር በመወያየት ለቀጣይ ሙከራ (ፈተና) በክትትልና ድጋፍ ማሻሻያ ለማድረግ ቃል በመግባት በመወያያ ቅፅ ላይ መፈረም ይኖርበታል::

         አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!

Al Qalam School

26 Oct, 03:15


Video from Bedru

Al Qalam School

20 Oct, 03:58


#ትኩረት🚨

ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በተለይ ትንንሽ ህጻናት በጉንፋን እና በጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት ህመም እየተያዙ ይገኛሉ።

ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመክቶ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያጋራ መግለጫ ልከዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

➡️ ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ ሙከስ መምብሬን ” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡

➡️ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

➡️ ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

➡️ የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል።

➡️ ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ ፦
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° አይን ማሳከክ እና መቅላት፣
° ማስታወክ፣
° ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣
° ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

➡️ ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

➡️ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

➡️ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል።

➡️ የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን የምንከላከልባቸው መንገዶች ምንድናቸው ?
° የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) ማድረግ
° በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት
° የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡


#ማሳሰቢያ ፦ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

#MoH #EPHI

@tikvahethiopia

Al Qalam School

18 Oct, 17:23


በዛሬው እለት ጁመዓ፣ጥቅምት 08/2017 በጠዋቱ ክፍለጊዜ ከአጠቃላይ የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ መምህራን ጋር በአራት አበይት አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር ለቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን በጠዋቱ መርሃግብር  በቪዲዮ የታገዘ ''Interactive English Language Learning & Teaching Techniques'' በሚል ርዕስ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን ፣ ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ መምህራን በከሰዓቱ መርሃግብር በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ሥልጠና ተሰጥቷል።

Al Qalam School

17 Oct, 17:25


በ2017  የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሚፈተኑ የተማሪ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።በውይይቱም ከ2012-2016 የት/ት ዘመን ድረስ የተማሪዎች የክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በንፅፅር የቀረበ ሲሆን፣በቤት ውስጥ የጥናት ቅፅ አጠቃቀም፣ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተማሪዎች ሥነምግባርና ውጤት ላይ በሚፈጥረው አሉታዊ ተፅዕኖ እና በማጠናከሪያ ትምህርት አተገባበር ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተሞክሯል።እንዲሁም በወላጆች/አሳዳጊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች እና ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን ለጥያቄዎቹም ምላሽ በመስጠት የእለቱ መርሃግብር ተጠናቅቋል።

Al Qalam School

15 Oct, 17:44


ለተከበራችሁ የክልል አቀፍ ፈተና አስፈታኝ ወላጆች(አሳዳጊዎች)

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ
እለተ ሐሙስ፣ጥቅምት 07/2017 ከ6ኛ እና ከ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪ ወላጆች(አሳዳጊዎች)ጋር በትምህርት ቤቱ ቤተመፃህፍት ከጠዋቱ 2:30-4:30 ስብሰባ ስለሚካሄድ በሰዓቱ እንዲገኙ በአክብሮት እናሳውቃለን።


አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!

Al Qalam School

11 Oct, 18:12


የ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው የኹጥባ ስነስርዓት

1,142

subscribers

988

photos

92

videos