ከዚያ በኋላ ሰዎች መጥፎ ነገር ላይ ወድቀው ካየሁ ከመተቸቴ በፊት ምክንያታቸው ምን ይሆን ብዬ መጠየቅን ለመድኩ። ሁሉም ሰው መጥፎ ነገር የሚሰራው ከመፈለግ ብቻ ላይሆን ይችላል። ነፍስያ አሸንፎን ወንጀል የምንሰራውን ያህል ህይወት አስገድዳቸው መጥፎ ነገር ላይ የወደቁም ብዙ አሉ።
እነዚያን ህፃናት ቤንዚን ለምን ትስባላችሁ ብዬ ከመቆጣቴ በፊት ልብስ መስጠት ከኔ ይጠበቅ ነበር። ከእኔ የሚጠበቀውን ሳልወጣ እነሱን መውቀሴ ተገቢ አልነበረም።
እንዲሁ ሰዎችንም እኛ የምንጠብቀው ደረጃ ለምን አልደረሱም ብለን ከመንቀፋችን በፊት ያለፈ ህይወታቸውን ማጥናት አለብን። ምክንያቱም የመጣንበት መንገድ ይለያያልና ሁሉም ሰው እኩል ውጤት ሊያመጣ አይችልም። ቁርሱን ሳይበላ ትምህርት ቤት የሄደና መቅሰስ ተጠቅሶለት የተላከ እኩል ትኩረት ለምን አልሰጡም ካልን ሚዛናችን ተዛንፏል።
ይሄ ምስል ታዲያ ያንን አጋጣሚ ያስታውሰኛል። በሰዎች ላይ ከመፍረድ በፊት የራስን ሃቅ መወጣት እንደሚገባ የተመከርኩበት ነው።
ከማ ቃለ ሰልማን