ማስታወቂያ
ለአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ወላጆች በሙሉ
የተከበራችሁ ወላጆች የአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ22 እና 23/06/2017ዓ.ም ከወላጆች ጋር አጠቃላይ በሚከተሉት አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ አቅዷል፡-
1.የ2017ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እና የቀሪ ወራት ተግባራት
2.የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ማሻሻል በተመለከተ
3.የአራትዮሽ ውል አፈፃፀም መገምገም በተመለከተ
4.የእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ትምህርት የተማሪዎች ውጤት ማሻሻል በተመለከተ
5.የወላጆች የልማት ተሳትፎ በተመለከተ
ከላይ ከ1-5 ባሉት አጀንዳዎች ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ስለሚኖር 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የተማሪዎች ወላጆች ቅዳሜ 2፡30 የምትገኙ ሲሆን 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆች እሁድ በተመሳሳይ ስዓት የምትገኙ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-ሁላችሁም ወላጆች የልጆቻችሁ ት/ቤት በመገኘት የልጆቻችሁን ውጤት በማየት በቀጣይ ለማሻሻል የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ት/ቤቱ