آخرین پست‌های African Leadership Excellence Academy (@afleexac) در تلگرام

پست‌های تلگرام African Leadership Excellence Academy

African Leadership Excellence Academy
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
1,875 مشترک
2,199 عکس
82 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 01.03.2025 06:10

کانال‌های مشابه

Project Management
16,395 مشترک

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط African Leadership Excellence Academy در تلگرام


“ተቋም ግንባታ እንደ ድልድይ ግንባታ ነው። ሲገነባ ጥንቃቄን ይፈልጋል። በደንብ ታስቦበትና በዕቅድ የሚገነባ ድልድይ በአገልግሎትም ይሁን በዕድሜ ለረጅም አመታት እንደሚቆየው ሁሉ ተቋምም እንዲሁ ነው። “ ይላሉ አቶ ዛዲግ ለሀሳባቸው አጽንኦት ሰጥተው ሲናገሩ።

ስኬታማ የሚሆኑ የተቋም መሪዎች ተቋማቸውን በህግ መሰረት የሚመሩ ናቸው። አንድ መሪ ተቋም ለመገንባት ዘመዱን፤ ሀይማኖቱን፤ ጾታውን፤ ዘሩን፤ ቀለሙን፤ እና ብሔሩን መርሳት ብቻ ሳይሆን መካድ እንዳለበትና እነዚህን ነገሮች በጉያው የያዘ መሪ ተቋም መገንባት እንደማይችል አቶ ዛዲግ አብራርተዋል።

ተቋማት የሚገነቡ መሪዎችን ከድንጋይ ጠራቢ ጋር በማመሳሰል የገለጹት አቶ ዛዲግ ሁለቱም ገደብ አልባ ስልት እና ትዕግስት (strategic patience) እንደሚያስፈልጋቸው ጠቅሰዋል። ድንጋይ የሚጠርብ ጠራቢ በትዕግስት ድንጋዩን እንደሚጠርበው ሁሉ መሪም ተቋም ለመገንባት ሰፊ ትዕግስት ያስፈልገዋል።

መሪዎች ተቋም ግንባታ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ቀላል ግምት የሚሰጠው ባለመሆኑ ሲያበረታቱም ሆነ የሚመሯቸውን ለስራ ሲያነሳሱ የሚጠቀሟቸውን ቃላት እና ድርጊት በማስተዋል ማድረግ እንደሚገባም በስልጠናው ላይ ተነስቷል።

ተቋም እና ስልጣኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ “ተቋማት የስልጣኔ ዘብ ናቸው። ስልጣኔን ያስቀጥላሉ። ተቋም ስትገነቡ ስልጣኔን እያዋቀራችሁ ነው። የተቋም ግንባታ ከአንድ ሰው እድሜ በላይ ነው። ተቋም የሚገነባ ሰው የብሔረ መንግስቱ አናጺ መሆኑን መርሳት የለበትም። “ ብለዋል።

አፍሌክስ ለኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የአመራር ልማት የሚሰጠው ስልጠና የአራተኛ ቀን ውሎ እንደቀጠለ ነው።

“አንድ መሪ ተቋም ለመገንባት ዘመዱን፤ ሀይማኖቱን፤ ጾታውን፤ ዘሩን፤ ቀለሙን፤ እና ብሔሩን መርሳት ብቻ ሳይሆን መካድ አለበት። እነዚህን በጉያው የያዘ መሪ ተቋም መገንባት አይችልም “ አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

ሱሉልታ- የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ) - የሀገራት የስልጣኔ መነሻ እና መድረሻ የተቋም ግንባታ እንደሆነ የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ። ፕሬዚደንቱ ይህን የገለጹት ለኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ስለ ተቋም ግንባታ የአመራር ልማት ስልጠና ሲሰጡ ነው።

ጠንካራ እና ተሻጋሪ ተቋማትን የገነቡ ሀገራት ስልጣኔያቸውን አስጠብቀው መዝለቃቸውን የሚጠቅሱት አቶ ዛዲግ፤ ተቋማት የስልጣኔ የማዕዘን ድንጋይ እንደሆኑና ይህ አዕማድ በአግባቡ ከተቀመጠ ትናንትን እንደሚዘክር፤ ዛሬን እንደሚሰራ እና ነገን እንደሚተልም ይህም ከትውልድ ትውልድ እየተሻገረ

የሀገረ-መንግስት መሰረት እንደሚሆን ተናግረዋል። አያይዘውም፤ የአንድ ሀገር የዕድገትት እና የብልጽግና መለኪያ ኒኩለር የማመንጨት እና የማስወንጨፍ፤ በማዕድን ሀብት መበልጸግ እና በነብስ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ መሆን ሳይሆን የተቋም ግንባታ ላይ የተመሰረተ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

“ሃገራት ሲበለጽጉ እኛ እንዴት ወደኋላ ቀረን? ይህ የዚህ ትውልድ ትልቁ ጥያቄ ነው!” አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

አፍሌክስ ለኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የአመራር ልማት ስልጠና መስጠቱን ቀጥሏል።

ሱሉልታ- የካቲት 21/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ) - ውስብስብ የሆነው የተቋም ግንባታ በደንብ ካልተሰራ የውድቀት ምንጭ ነው ሲሉ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በስልጠናው ላይ ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ ለኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አመራሮች የተቋም ግንባታን የተመለከተ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል።

“ስለተቋም ግንባታ ስናስብ በቅድሚያ እንደማህበረሰብ ትክክለኛውን ጥያቄ ልንጠይቅ ይገባል፣ ትክክለኛውን ጥያቄ ለመጠየቅ ደግሞ በጥልቀት ማሰላሰል አለብን።” ብለው በጥልቀት የማሰላልሰልን ዘርፈብዙ ትሩፋቶች አንስተዋል።

“ትክክለኛውን ጥያቄ መጠየቅ መጪውን ጊዜ በደንብ እንድናይ ያስችለናል ይሄም ለተቋም ግንባታ መሰረት ነው።” ያሉት አቶ ዛዲግ ትክለኛውን ጥያቄ ጠይቀው መጻዒውን ጊዜ መመልከት በመቻላቸው ስኬትን የተጎናጸፉ ታላላቅ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን፣ በአንጻሩ ደግሞ ያንን ማድረግ ባለመቻላቸው ለውድቀት የተዳረጉ ተቋማትን በምሳሌነት አንስተዋል።

“ሃገራት ሲበለጽጉ እኛ እንዴት ወደኋላ ቀረን? የሚለው ጥያቄ የዚህ ትውልድ ትልቁ ጥያቄ ነው!” ሲሉ ተናግረዋል።

ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የአመራር ልማት ስልጠናው ተቋማዊ ባህል እና የተቋም ግንባታን ጨምሮ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በውጤት መምራት የሚያስችል ብቃት ለመገንባት የሚያግዙ የተለያዩ ርዕሶችን አካቷል።

በርዕሶቹ ዙሪያ በአሰልጣኞች የተሰጡ ማብራሪያዎች እና አሳታፊ ውይይቶች የስልጠናው አካል ናቸው።

These initiatives are a result of collaboration with key governmental bodies, including the Office of the Prime Minister, the Ethiopian Civil Service Commission, and the Planning and Development Commission.

The Marquee Leadership Award is designed to recognize exemplary leadership within the public sector, while the National Leadership Development Forum will address critical issues such as governance, innovation, technology, and youth empowerment, fostering a culture of excellence and accountability in leadership.

The structure of the Marquee Leadership Award was a focal point of discussion, targeting leaders from 24 federal ministries and over 120 affiliated institutions. Participants will go through a rigorous four-tier selection process evaluated by a jury, the public, stakeholders, and the media, ensuring transparency and fairness.

Mr. Tilahun Arega presented the award criteria, emphasizing attributes such as community impact, governance commitment, crisis management skills, collaboration, and leadership legacy. The National Leadership Development Forum will include workshops, research presentations, and panel discussions, with the award ceremony scheduled during the forum to honor outstanding leaders.

Participants engaged actively in the discussions, raising questions and sharing ideas. Mrs. Meseret Desta, Vice Chief of the Academy for Leadership Development, highlighted the benefits of the award for the public sector and government, noting the forum's potential to stimulate meaningful conversations on leadership and governance.

The discussions concluded on an optimistic note, with both initiatives seen as significant steps towards inspiring transformative leadership and promoting excellence, innovation, and collaboration in public leadership.

These efforts mark a pivotal moment in fostering a new era of accountable and visionary leadership in Ethiopia.

AFLEX Unveils 2025 Marquee Leadership Award and National Leadership Development Forum to Champion Excellence in Public Sector Leadership

Addis Ababa, February 27, 2025 (AFLEX) - The African Leadership Excellence Academy (AFLEX) has unveiled its action plan for two significant initiatives aimed at enhancing public sector leadership in Ethiopia: the Marquee Leadership Award 2025 and the National Leadership Development Forum.

4️⃣ . Resilience & Determination: Against all odds, Ethiopians showed unwavering determination. Leaders should embrace challenges with courage and perseverance.

5️⃣ . Cultural Pride: The battle reinforced national pride and identity. Leaders must celebrate and leverage cultural strengths to inspire and motivate their teams.

Let us carry forward these timeless lessons into our leadership practices. Together, we can achieve greatness! 🇪🇹

#Ethiopia #AdwaVictoryDay #LeadershipLessons #HistoryInAction #UnityAndStrength

🌟 Commemorating the Ethiopian Adwa Victory: Lessons for Senior Leaders 🌟

Today, we honor the historic #AdwaVictory, a momentous triumph that resonates with lessons of unity, resilience, and strategic leadership.

On this week in 1896, Ethiopia stood as a beacon of defiance against colonial powers, showcasing values from which every senior leader can draw inspiration:

1️⃣ Unity in Diversity: The victory was achieved through the collective strength of diverse ethnic groups united under one cause. As leaders, fostering inclusivity and collaboration is key to overcoming challenges.

2️⃣ Strategic Vision: Emperor Menelik II and Empress Taytu Betul demonstrated foresight and tactical brilliance. For leaders today, having a clear vision and adapting strategies to changing circumstances is crucial.

3️⃣ . Empowerment & Trust: The success at Adwa was rooted in empowering local leaders and trusting their expertise. Modern leaders must similarly empower their teams and build trust within their organizations.

Leadership & the Courage of Independent Thought

Leadership isn't about amplifying the loudest voices or conforming to popular opinion. It's about cultivating the courage of independent thought. It's about challenging the status quo, asking uncomfortable questions, and forging your own path, even when it's unpopular.
Are you truly thinking for yourself, or simply echoing the narratives around you?
How can you create space for independent thought in your own leadership, regardless of your role?

#AFLEX #Leadership #IndependentThinking #CriticalThinking #Integrity #Authenticity #VisionaryLeadership #Innovation #LeadershipDevelopment

እንኳን ወደ አፍሌክስ ቤተ-መጽሐፍት መጡ 📚

በሱሉልታው የአካዳሚያችን የአመራር ልማትና ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ የሚገኘው ቤተ-መፃህፍታችን ለዛሬ እና ለነገ መሪዎች የእውቀት መናኸሪያ ነው! 🌟

ወደ ቤተ-መፃህፍታችን መጥተው ስለ አመራር ልማት በሰፊው ያስሱ! ምን ይፈልጋሉ

🔹ስልታዊ አስተሳሰብ?
🔹የተግባቦት ክህሎቶች?
🔹ወይስ ተቋማዊ አመራር?
ለሁሉም የሚሆኑ መጻህፍትን እኛ ጋር ያገኛሉ!📖

ምን ይሄ ብቻ❗️ ሰፊው ዲጂታል ቤተ-መጻህፍታችን በርካታ መጻህፍትን የያዘ ነው! የQR ኮዱን በስማርትፎንዎ ስካን በማድረግ ብቻ ኢ-ላይብረሪያችንን ይጠቀሙ! 📱

ወደማዕከላችን ሲመጡ በሚያርፉባቸው ምቹ መኝታ ክፍሎች ውስጥ በተገጠሙ ኮምፒዩተሮች አማካኝነት ከዲጂታል ቤተ-መጻህፍቱ መጻህፍትን በቀጥታ ማውረድ ይችላሉ!💻

ከአሜሪካ ኤምባሲ🇺🇸 እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የፈጠርናቸው አጋርነቶች የዲጂታል አቅማችንን እያሰፉ፣ ቤተ-መጻሕፍታችን በአመራር ልማት መስክ ቀዳሚ የእውቀት ምንጭ እንዲሆን በማድረግ ላይ ናቸው።

የአፍሌክስ ቤተ-መጻሕፍት ማንበቢያ ብቻ ሳይሆን፣ ሀሳቦች የሚያብቡበት፣ መሪዎች የሚገኙበት የእውቀት ቤት ነው።

ወደማዕከላችን ለስልጠና ሲመጡ ቤተ-መጻህፍታችን ሁሌም በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቆታል 🌟📚

#AFLEX #Library #LeadeshipDevelopment

የአፍሌክስን የሪፎርም ስራዎች በተመለከተ ገለጻ ያደረጉት እሸቴ አበበ (ዶ/ር) ተቋሙ ከምን ተነስቶ ወደየት እየሄደ እንዳለ፣ እየከወናቸው የሚገኙትን ትልልቅ ስራዎች እንዲሁም ስለሱሉልታ ዳቮስ ፕሮጀክት አብራርተዋል።

ስልጠናው ለ4 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ዛሬ በመጀመሪያው ቀን የኢቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ ኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ስፖርት ለሃገረ መንግስት ግንባታ በሚኖራቸው ሚና ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመጀመሪያ ዙር ከፌዴራል፤ ከክልሎችና ከሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ 250 የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራርና ባለሞያዎች ተመሳሳይ አላማ ያለው የአመራር ልማት ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል።