来自 ነጭ ነጯን ወቅታዊ (@adugna_123) 的最新 Telegram 贴文

ነጭ ነጯን ወቅታዊ Telegram 帖子

ነጭ ነጯን ወቅታዊ
31,036 订阅者
95 张照片
13 个视频
最后更新于 01.03.2025 09:22

ነጭ ነጯን ወቅታዊ 在 Telegram 上分享的最新内容


እንኳን አደረሰን!

ግሽን ማርያም

የግማደ መስቀሉ መገኛ!

በሀገራችን ኢትዮጵያ በወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ የሚገኘው ታላቁ የግሸን ማርያም ደብር የግማደ መስቀሉ መገኛ በመሆኑ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ትልቅ ተስፋና መመኪያ ነው፡፡ መስቀል የክርስትናችን መገለጫ፣ የብርሃናችን ዐምድ እንዲሁም የሰላማችን መገኛ ነውና፡፡

የከበረ ግማደ መስቀሉ በቅድስት ዕሌኒ ተገኝቶ በታላቅ ቤተ መቅደስ በጎልጎታ በክብር ከተቀመጠበት ዘመን ጀምሮ እንደ ፀሐይ እያበራ፣ ድውይ እየፈወሰ፣ አጋንንት እያስወጣ፣ ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገ፣ ሙት እያነሳና ዕውር እያበራ በነበረበት ጊዜ ከኃያላን ነገሥታት መካከል የፋርስ ንጉሥ መስቀሉን ማርኮ ፋርስ ወስዶ አስቀመጦት ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ምእመናን የሮማውን ንጉሥ ሕርቃልን ዕርዳታ በመጠየቅ እንዲመለስ አድርገው በኢየሩሳሌም ብዙ ዘመን ሲኖር እንደገና ኃያላን ነገሥታት ይህን መስቀል ለመውሰድ ጠብ በመፍጠራቸው የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአንድ ቦታ ሊቀመጥ አልቻለም፡፡

በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም፣ የቁስጥንጥንያ፣ የአንጾኪያ፣ የኤፌሶን፣ የአርማንያ፣ የግሪክ፣ የእስክንድርያና የመሳሰሉት የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን ለማብረድ ችለው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በኢየሩሳሌም የሚገኘውንም የጌታችን የክርስቶስን መስቀል ከ፬ በመክፈል በዕጣ አድርገው በስምምነት ለመካፈል ተገደዋል፡፡ ከሌሎቹ ታሪካዊ ንዋያት ጋር በየሀገራቸው በመውሰድ በክብር አስቀመጠውታል፡፡ የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በግብጽ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጦት ነበር፡፡

ግማደ መስቀሉም ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖር በግብጽ ያሉ እስላሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ በሔዳቸው ምክንያት በእስክንድርያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ሥቃይ አጸኑባቸው፡፡ በዚያን ጊዜም ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊ ዓፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መልዕክት ልከው ነበር፤ ‹‹ንጉሥ ሆይ! በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናልና ኃይልህን አንሥተህ አስታግሥልን›› ዳግማዊ ዓፄ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ኃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶአቸው ፳ ሽህ ሠራዊት አስከትለው ወደ ግብፅ ዘመቻ አደረጉ፡፡ በግብጽ ያሉ ኃያላን ፈርተውና ተሸብረው ነበር፡፡ በዚያን ጊዜም ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልእክት ለእስላሞች ላከው ነበር፤ ‹‹በተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ጋር ካልታረቃችሁ ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋዋለሁ፡፡›› የንጉሡ መልእክት ለእስላሞች እንደደረሳቸው ፈርተው እንደጥንቱ በየሃይማኖታቸው ጸንተው በሰላም እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታርቀዋል፡፡

ይህንንም ዳግማዊ ዳዊት በሰሙ ጊዜ በጉዳዩ ንጉሡ በጣም ደስ ብሏቸው ነበር፤ እግዚአብሔርንም አመስግነዋል፡፡ በወቅቱም በግብጽ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ደስታቸውን ለመግለጽ ከ፲፪ ሽህ ወቄት ወርቅ ጋር ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው እንደላኩላቸው ታሪካቸው ላይ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን ንጉሡ ደብዳቤውን ተመልከተው ደስ ቢላቸውም ወርቁን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ልከዋል፤ ‹‹በግብጽ የምትኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ! የላካችሁልኝን ፲፪ ሽህ ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ፤ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም፤ የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ ችግራችሁን ሁሉ አስወገድኩላችሁ፡፡ አሁንም የምለምናችሁ በሀገሬ በኢትዮጵያ ረኃብ፣ ቸነፈርና ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎበት የነበረውን መስቀልና የቅዱሳንን አጽም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር እንድትልኩልኝ ነው፡፡››

በእስክንድርያም ያሉ ምእመናን ይህ መልዕክት እንደደረሳቸው ከሊቃነ ጳጳሳቱና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውይይት በማድረግ ‹‹ይህ ንጉሥ ታላቅ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ ልቡን ደስ እንዲለው የፈለገውን የጌታችንን ግማደ መስቀል ከቅዱሳን አጽምና ንዋየ ቅድሳት ጋር አሁን በመለሰው ፲፪ ወቄት ወርቅ የብር፣ የንሐስ፣ የመዳብና የወርቅ ሣጥን አዘጋጅተን እንላክለት›› ብለው ተስማሙ፡፡ በክብር በሥነ ሥርዓት በሠረገላና በግመል አስጭነውም ስናር ድረስ አምጥተው ባስረከቡአቸው ጊዜ በእጃቸው እያጨበጨቡና በግንባራቸው እየሰገዱ በክብር በደስታ ተቀብለዋቸዋል፡፡ ይህም የሆነው መስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡ በኢትዮጵያም ታላቅ ብርሃን ሌት ተቀን ፫ ቀን ሙሉ ሲበራ ሰነበተ፡፡

ግማደ መስቀሉ ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ሳይደርስ በድንገት ዓፄ ዳዊት ስናር ላይ በማረፉቸው ግማደ መስቀሉም የግድ በዚያው በስናር መቆየት ነበረበት፡፡ ከዚህ በኋላ የሟቹ የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ እንደነገሡ ወደ ስናር ሔደው ግማደ መስቀሉን ከሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት ጋር አምጥተው በመናገሻ ከተማቸው በደብረ ብርሃን ላይ ቤተ መቅደስ ሠርተው ለማስቀመጥ ሲደክሙ አንድ ራእይ እንዳዩ ተገልጿል፡፡ በዚያም ጊዜ ‹‹ወዳጄ ዘርዐ ያዕቆብ ሆይ፥ መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ›› የሚል ትእዛዝም ተቀብለው በኢትዮጵያ አውራጃዎች ሁሉ መስቀለኛ ቦታ በመፈለግ ከብዙ ቦታ ላይ አስቀምጠውት ነበር፡፡ ለምሳሌ በሸዋ በደርሄ ማርያም፣ በመናገሻ ማርያም እንዲሁም በወጨጫ መስቀሉን አሳርፈውት ነበር፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ቦታ ያላገኙ በመሆኑ በራእይ እየደጋገገመ ‹‹መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ›› እያለ ይነግራቸው ነበር፡፡

ዓፄ ዘርዐ ያዕቆብም ለሰባት ቀናት ያህል ሱባዔ በመግባታቸው ‹‹መስቀለኛውን ቦታ የሚመራህ ዓምድ ብርሃን ይመጣል›› የሚል መልእክት ሊደርሳቸው ችሏል፡፡ እርሳቸውም ከዚያ እንደወጡ መስቀለኛውን ቦታ የሚመራ ዓምደ ብርሃን ከፊታቸው መጥቶ ቆሞ በዚያ መሪነት ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ ውስጥ ግሸን ከምትባል ስፍራ መርቶ አደርሷቸዋል፡፡ በርግጥም ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ሁና ስለአገኟት የልባቸው ደርሶ ደስ ብሏቸው ነበር፡፡ በዚያችም አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀምጠዋቸዋል፤ ዘመኑም በ፲፬ኛው ክፍለ ዘመን ነበር፡፡

በሀገራችን ከመጡት ንዋያተ ቅዱሳት ውስጥም ከእስክንድርያ ሀገር ከመስቀሉ ጋር በልዩ ልዩ ሣጥን ተቆልፈው የመጡትም ዝርዝር፣ ጌታ በዕለተ ዓርብ ለብሶት የነበረው ቀይ ልብስ፣ ከሮም የመጣ ከለሜዳው፣ ከአፍርጌ ሀገር የመጣው ሐሞት የጠጣበት ሰፍነጉ፣ ዮሐንስ የሳለው የኲርዓተ ርእሱ ሥዕል፣ ቅዱስ ሉቃስ የሣላቸው የእመቤታችን ሥዕሎች፣ የበርካታ ቅዱሳን አጽምና በኢየሩሳሌም ውስጥ ከልዩ ልዩ ቅዱሳት መካናት የተቆነጠረ የመሬት አፈር፣ የዮርዳኖስ ውኃ እንዲሁም በግብጽ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅ ገዳማት የተቆነጠረ አፈር ናቸው፡፡

በወቅቱም የእነዚህንም ዝርዝር ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለግሸን ካህናት መስከረም ፳፩ ቀን ፩ ሽህ ፬፻፵ ዓ.ም. ላይ ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያም ይህ ግማደ መስቀል ከእስክንድርያ ስናር የገባው መስከረም ፲ ቀን ነው፡፡ ኢትዮጵያም የገባው ደግሞ በመስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡ አሁንም በመጨረሻ ግሸን አምባ የገባው መስከረም ፳፩ ቀን ሲሆን ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረውና አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለመላው ኢትዮጵያ በጽሑፍ በመዘርዘር የገለጹበትም መስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡

እንኳን አደረሳችሁ?

♦️ልብ የሚሰብር እጅግ ከባድ ኀዘን
አረጋዊ ካህን ዐራት ቤተሰባቸውን ጨምሮ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ( ሞጆ ) ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ 41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትሕትና ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ካህኑ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የገለጸ ሲሆን ልጃቸው ዲ/ን መልአክ ወልደ ኢየሱስም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ጸሎተ ፍትሐት ሥርዓቱም የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ አበው ካህናት ሊቃውንት ፣ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕነታቸው መሪነት እየተከናወነ ይገኛል።
ዘገባው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው

https://www.facebook.com/share/r/19N7B9GVrd/?mibextid=qi2Omg

" እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን "

🔴መስቀል ደመራ ትክክለኛው ስርዓት እንዴት ነው?#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ#መስቀል
https://youtube.com/watch?v=b1UH0gKo0Nk&si=THALd3odEf0V2L2i

ትክክለኛው የበዓላት አከባበር እንዴት ነው? በድሮ ጊዜ አባቶቻችን እንዴት ነው ሲያከብሩት የነበረው? አሁንስ የመስቀል እና የጥምቀት በዓላት በምን እየተለያዩ ነው? በዚህ ቪዲዮ አብረን እናያለን።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።
#ቅዱስ #መስቀል #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
ሙሉውን በዚህ ተመልከቱ👇👇👇
https://youtu.be/b1UH0gKo0Nk?si=H_KL_Kmg_JO_ad-y

ወንድሜ ዲያቆን ተመስገን አብሮ አደጌን በርታ በሉልኝ👇
https://youtu.be/XZ2mBdEKTU0?si=9bb9OZuUBQE7BSWz

ከአዲስ አበባ ወደ ግሸን የእግር ተጓዦች በደሴ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገ !

ምእመናን በእግራቸው ከአዲስ አበባ ወደ ግሸን ከ13 ቀናት በላይ የፈጀ የእግር ጉዞ በማድረግ ወደ ደሴ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል።

ወደ ከተማው የገቡትን የግሸን ተጓዥ መንገደኞችን የደሴ ከተማ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች በደማቅ ሁኔታ በመቀበል እግር አጥበው እና ምሳ አብልተው እያስተናገዱ ይገኛሉ።

መንገዱ ፍጹም ሰላም በመሆኑ ሌሎችም በዚህ ታላቅ በዓል ላይ እንዲገኙ ተጓዥቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ :- ዲ/ን አዶንያስ