"ነጋ ወይስ አልነጋም" ብለን ስልካችንን በተደጋጋሚ ቼክ ምናረድ ሰዎች ጥቂት አደለንም፣ ግን ለምን ብላችሁ እራሳችሁን ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ምክንያቱን ካወቅክን ለመፍትሄው አንቸገርም።
1. ከመጠን ያላፈ ጭንቀት: ምናልናት ነገ ጠዋት ሚጠብቀን ሚያጓጓ ወይም ሁሉ ነገራችንን ሚፈትን ስራ ይጠብቀን ይሆናል፡ ጭንቀት መነሻው ብዙ ቢሆንም፣ ፍርሃትን ያቀፈ የስሜት ስብስብም ነው። አብዛኛው የስነ-ልቦና አማካሪዎች እንደሚሉት፡ ጭንቀት የአብዛኛው ሰው እንቅልፍ አለመተኛት ምክንያትም ነው። ስለዚህ የመንቃት ከዛም በትግል የመተኛት ድግግሞሽ ውስጥ እንገባለን። ጭንቀታችን ሰው እንደሞናችን ሚጠበቅ ቢሆንም፣ ጭንቀትን ለመቀነስ ደሞ ህይወት እድል ሰታናለች። የሁላችንም ችግር ይለያያል።
2. የተፋረሰ የእቅልፍ ሰዓት: እራሳችንን ማስለመድ ያለበት ነገር፣ ምንተኛበትን እና ምንነቃበትን ሰዓት ተመሳሳይ ማድረግ ነው። ስንፈልግ ቀን፣ ስንፈልግ ማታ መተኛታችን፣ ለሊት ላይ እንቅልፍ ጨርሰን እንድድነቃ ያደርገናል።
3. የጤና ችግሮች: የስኳር መጠን መውረድ፡ ቶሎ ቶሎ መሽናት.....ድብርት ምናምን...ተያያዥ ህመሞች እንቅልፋችንን በሰላም እንዳንተኛ ያደርጋሉ።
@addisposts ነን! መልካም ሰኞ!