ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism

@tourismethiopia


Official Corporate Telegram of Ministry of Tourism , Ethiopia ~ For realization of Tourism’s Full Potential for Ethiopia’s Economic Growth

ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism

18 Oct, 11:23


መልካም የስራ ዘመን!
ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ሆነው በመሾምዎ የቱሪዝም ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች የተሰማንን ደስታ እየገለፅን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎ እንመኛለን፡፡

ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism

03 Oct, 18:23


"ከረሀብ ነጻ የሆነች ዓለምን እውን ማድረግ ይቻላል !" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ ከጥቅምት 26-28 በአድዎ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ይካሄዳል ።
ለመሳተፍ፡- https://www.unido.org/world-without-hunger-conference...

#LandOfOrigins #VisitEthiopia #Aworld #withouthungerispossible#UNIDO
"ከረሀብ ነጻ የሆነች ዓለምን እውን ማድረግ ይቻላል !" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ ከጥቅምት 26-28 በአድዎ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ይካሄዳል ።
ለመሳተፍ፡- https://www.unido.org/world-without-hunger-conference...

#LandOfOrigins #VisitEthiopia #Aworld #withouthungerispossible#UNIDO

ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism

16 Sep, 10:39


የኢጋድ አባል ሀገራት በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ትስስር ያጠናክራሉ ተብለው የሚጠበቁ ኹነቶች በአዲስ አበባ ሊካሄዱ ነው፡፡
መስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ከመስከረም 7-9 በአዲስ አበባ የሚካሄደውን መርሃ-ግብር በማስመልት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ስለሺ ግርማ ለመብዙሃን መገናኛዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ክቡር ሚንስትር ዴኤታው በመግለጫቸው የቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች እና ሃብቶች ከመጠበቅ፣ ከማልማትና ማስተዋወቅ ባሻገር ቱሪዝም ለሃገራችን ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በቅጡ ተገንዝቦ ለመተንተን እና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ቀረጻ እና ስልታዊ የእቅድ ዝግጅትን እውን ለማድረግ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ለሃገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት (TSA) መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን የቱሪዝም ሳተላይት አካውንትን አጠናቀው ተግባራዊ ካደረጉ ጥቂት የአፍሪካ ሃገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት የገለፁት ክቡር ሚንስትር ዴአታው መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በሚካሄድ መርሃ ግብር ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡
በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ በሚካሄደው መርሃ ግብር ላይ ይፋ የሚደረገው ሌላው ወሰኝ ኹነት ኢጋድ እና አባል ሃገራቱ በቅንጅት ያዘጋጁት የኢጋድ አባል ሀገራት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን እንደሆነ የገለፁት ክቡር አቶ ስለሺ ማስተር ፕላኑ በቀጠናው ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን እውን ያርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡ መርሃ-ግብሩ መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት እና ዩኤን ኢሲኤ በተገኙበት እንደሚካሄድ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism

21 Aug, 11:17


የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ነሀሴ 15/2016 ዓ.ም

ቱሪዝም ሚኒስትር ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሚኒስትሩና ለተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች በፌዴራል አስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሚኒስቴሩ አዳራሽ ተሰጠ።
#Ethiopia
ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/MinistryofTourismETH
#ልወቅሽኢትዮጵያ #ኢትዮጵያምድረቀደምት

ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism

26 Jul, 12:08


እንኳን ደስአለን!

የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአረኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ ተመዘገበ፡፡

በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዓመታዊ ጉባዔ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአረኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሶስት መስፈርቶችን በማሟላት የዓለም ቅርስ ሆነ ተመዝግቧል

ሥፍራውን በዓለም ቅርስነት ያበቁት መስፈርቶች
መስፈርት 3 (criterion III) ከ2.5 ሚሊየን ዓመት እስከ መጨረሻው የድንጋይ ዘመን የሰው ልጅ ይጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መገልገያዎች ይዞ የሚገኝ በመሆኑ፡፡

መስፈርት 4 (criterion Iv) እስከ 2.5 ሚሊየን ዓመት እድሜ ያላቸው የተለያዩ የሰውና የእንስሳት ቅሪተ አካሎች በብዛት የሚገኙበት በመሆኑ::

መስፈርት 5 (criterion v) የሰው ልጅ ከድንጋይ የተለያዩ መገልገያዎችን/መሳሪያዎችን ይሰራ እንደ ነበር የሚያሳዩ ስምንት የባልጩትና ሌሎች የድንጋይ መሳሪያ ማምረቻ ሥፍራዎችን ይዞ የሚገኝ በመሆኑ ነው፡፡

የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ለጉባኤው በላኩት መልእክት ይህ ቅርስ የተመዘገበው ሉሲ የተገኘችበትን 50ኛ አመት በምናከብርበት ወቅት መሆኑ ለሀገራችን ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልፀዋል::

በእርግጥም ሀገራችን ምድረቀደምት መሆኗን ለአለም ተጨማሪ ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑንም አንስተዋል::

ይህ ቅርፅ ተጠብቆ እንዲቆይም የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል::

መልካ ቁንጡሬ ባልጪት ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጂራ በሚወስደው ጎዳና 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዋሽ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ቋሚ የሚዳሰሱ ቅርሶች 12ኛው ነው፡፡

ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism

26 Jul, 07:11


የቱሪዝም ሚኒስቴር ከሀገር አቀፍ ጥናትና ማማከር ኢንስቲትዪት National Research and Consultancy Institute/ ጋር በመቀናጀት እንዲሁም በFirst Consult/Master Card Foundation አጋርነት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ ለሚሰሩ በምግብ ዝግጅትና መስተንግዶ እንዲሁም በቤት አያያዝና የላውንደሪ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ  ለ362 ሴት የሆቴል ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

3,929

subscribers

3,462

photos

75

videos