ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

@sundayschool1958


ይህ በፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ (አዲስ አበባ) የሚገኘው የገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።

እንኳን በደኅና መጡ!

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

22 Oct, 17:54


የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በትናንትናው የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች አጋርነቱን ገለጸ።

ጥቅምት ፲፪/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በትናንትናው የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች አጋርነቱን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ በትናንትናው ዕለት ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ገበያ ሸማ ተራ በተባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ለደሰባቸው ወገኖች ባስተላለፉት መልእክት በደረሰው የሃብትና ንብረት ውድመት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች እንዲፅናኑ እና የሕይወት ውጣ ውረድ አካል መሆኑን በመረዳት ከጉዳታቸው ለማገገም በተስፋ እንዲነሳሱ አደራ ብለዋል።

የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ሆነው የቃጠሎውን አደጋ በመስማታቸው ለሁሉም ተጎጂዎች የማጽናኛ መልእክት ማስተላለፋቸውን ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ ገልፀዋል።

በአደጋው ተጎጂ የሆኑ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በተለይም ክርስቲያኖች በመተባበር ክርስቲያናዊ ምግባር እንዲያሳዩ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል።

መንግሥትና ኅብረተሰቡ በመልሶ ማቋቋም ሥራ ለሚያደርጉት ጥረት ሀገረ ስብከቱ የበኩሉን እንደሚወጣ እናስታውቃለን ብለዋል።
መረጃውን ያደረሰን የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ነው።

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

22 Oct, 17:06


🌸🌸🌸🌸🌸🌸
🌸 ካነበብነው 🌸
🌸🌸🌸🌸🌸🌸

" ሐር አንተ ስትለብስ ድኻ ጨርቅ እያጣ
ዕወቅ ሐሩ ልብስህ በእሳት እንዲያስቀጣ "

ጣፋጭ ጥበብ ገጽ ፻፸፬ ቁጥር  ፩ሽ ፪፻፹፭

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹 ዑል ራስ ካሣ ኃይሉ 🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 16:06


ሰላም እንደምን አደራችሁ ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በእግዚአብሔር ቸርነት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተመረቁ አባሎቻችን እና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ጋብቻቸውን የፈጸሙ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት እንኳን ደስ አላችሁ መርኃግብር እና የእናት ሰንበት ትምህርት ቤታችን የ፷(60) ዓመት ምስረታ በዓል የመክፈቻ መርኃ ግብር አምስት ቀን ቀረው ።

በዕለቱ :-
✟  ትምህርተ ወንጌል
✟ የጋራ ዝማሬ
✟ መወድስ
✟ የእንኳን ደስአላችሁ መርኃግብር እና የተለያዩ መርኃግብሮች አሰናድተን እንጠብቆታለን ።

ያስታውሱ :- የመርኃ ግብሩ ቀን 17/02/2017 ዓ.ም
ቦታ:- በመሰረተ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
ሰዓት :- ከቀኑ 10:00 - 12:30 ደቂቃ

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 13:47


አጣሪ ኮሚቴው ሪፖርቱን ለቋሚ ሲኖዶስ አቀረበ።
**********
ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ዓ.ም
===================
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""""""
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ በዝርዝር በማጣራት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደያቀርብ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ባለፉት አሥራ አምስት ቀናት ሲያከናውናቸው የሰነበተውን የማጣራት ሥራዎች በማስመልከት ያዘጋጀውን ሪፖርት ዛሬ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቧል።

አጣሪ ኮሚቴው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአካል ተገኝቶ ማጣራት እንዳይችል።የተከለከለ መሆኑን በመጥቀስ መረጃውን ለሣሰባሰብ ይቻል ዘንድ ተበዳዮች በስልክ፣በቴሌጌራምና በዋትስ አፕ መልዕክቶች፣በአካል በመቅረብ፣በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ፣በድምጽና 3:30 ርዝማኔ ባለው በቪዲዮ በተቀረጸ ማስረጃ ጭምር መረጃዎችን ማሰባሰቡን፣መተንተኑን፣ማደራጀቱንና ጥቅም ላይ ማዋሉን ገልጿል።

በሪፖርቱም ከመልካም አስተዳደርና ከብልሹ አሰራር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በማስረጃ ተደግፈው የቀረቡ ሲሆን በማጣራት ስራው የተረጋገጡ ጉድለቶችንና ጥፋቶችን መሰረት በማድረግም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ችግሮቹን ለመፍታትና የካህናትና የአገልጋዮችን ቅሬታ ዘላቂነት ሊፈቱ ይችላሉ ተብለው የቀረቡ በሰባት ነጥቦች የተተነተኑ የመፍትሔ ሐሳቦችና በዘጠኝ ነጥቦች የተተነተኑ ችግሮቹን በዘላቂነት ሊፈቱ ይችላሉ ተብሎ የታመነባቸው የመፍትሔ ሐሳቦችን አቅርቧል።ይኸው የጥናት ሰነድ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል።

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 13:43


ካነበብነው
🌸🌸🌸

ጥላው አትውደደው ቃል ማስጌጥ ያጠፋል
አነጋገር ቢያምር አሟሟት ይከፋል ። "

ጣፋጭ ጥበብ ገጽ ፻፶፯ ቁጥር  ፩ሽ፻፴፪

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

🌹 ልዑል ራስ ካሣ 🌹

🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

20 Oct, 21:48


🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇

" የገነት ወፍ ሆይ ከሽቱ ተራሮች ተነሥተሽ ነይ ፤
በየአቅጣጫው  ያሉ ምዕመናንንም ጎብኚ ፤
ተአምርሽ የሚወደድ የትንቢት ርግብ ማርያም ሆይ ፤
ክንፍሽ በነጭ ብር የተጌጠ ነው ፤
ጎንሽም በአረንጓዴ ወርቅ የተሸለመ ነው "


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

ማኅሌተ ጽጌ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

20 Oct, 18:28


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

" ማርያም ሆይ !
የሚያምር የአበባ ምልክት ያላት ሥዕልሽ ፤
ከጥዑም የንግግር ቃል ጋር የምትገኝበት ጊዜ አለ ፤
ሥጋ ለብሳ የምትገለጽበት ጊዜም አለ ፤
ርጉም አይሁዳዊ ሰው በሰይፍ በቆረጣት ጊዜም ፤
ከእሷ ደም ተንጠፈጠፈ ።

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

🌸 ማኅሌተ ጽጌ 🌺

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

19 Oct, 19:30


ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተደናግል ጠባባት ገዳም

የቀረበ የእርዳታ ጥያቄ

በጸሎት ፤ በሃሳብ ፤ በገንዘብ ታግዟቸው ዘንድ ይኹን

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

19 Oct, 18:50


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

" እንደ ተወዳጁ ልጅሽ ቅዱስ ወንጌል
የጽጌ መጽሐፍ ተአምርሽ  በእኔ ዘንድ ክቡር ነው
ዐሥሩ ትእዛዝ የተጻፉብሽ የኪዳን ጽላት ማርያም ሆይ ፤
ከቃልሽ አንድ ነገር ከሚወድቅ ፤
የሰማይና የምድር ማለፍ ይሻላል ።  "

🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

🌷                    ማኅሌተ ጽጌ               🌷

🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

19 Oct, 08:27


ካነበብነው
🌸🌸🌸🌸


" ሰው አንድ ነውና ሲደመር በአዳም
በዘር ክብር አትኵራ አልቋል በኢዮአቄም "

ጣፋጭ ጥበብ ገጽ ፻፲፯ ቁጥር ፯፻፷፩

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

18 Oct, 10:23


" ጥበበኛው ሲራክ እንደተናገረ ፤
ልዑል እግዚአብሔርን ማን በመቃብር ያመሰግነዋል ፤
በፍቅርሽ የተሳለ ጦር ተወግቻለሁና ፤
ተአምርሽን በማኅሌተ ጽጌ አመሰግን ዘንድ ፤
ድንግል ሆይ ረጅም እድሜ አድይኝ ። "

ማኅሌተ ጽጌ

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

17 Oct, 19:24


ሰላም እንደምን አደራችሁ ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በእግዚአብሔር ቸርነት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተመረቁ አባሎቻችን እና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ጋብቻቸውን የፈጸሙ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት እንኳን ደስ አላችሁ መርኃግብር እና የእናት ሰንበት ትምህርት ቤታችን የ፷(60) ዓመት ምስረታ በዓል የመክፈቻ መርኃ ግብር ላይ እንዲገኙልን ስንል ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችንን አባላት በታላቅ ትሕትና እንጋብዛለን ።

በዕለቱ :-
✟  ትምህርተ ወንጌል
✟ የጋራ ዝማሬ
✟ መወድስ
የተለያዩ መርኃግብሮች አሰናድተን እንጠብቆታለን ።

ያስታውሱ :- የመርኃ ግብሩ ቀን 17/02/2017 ዓ.ም
ቦታ:- በመሰረተ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
ሰዓት :- ከቀኑ 10:00 - 12:30 ደቂቃ

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

16 Oct, 21:11


ካነበብነው
🌸🌸🌸


" ክንድሺም ደረትሽም አይገለጥም ባት
ወንድን ማስጐምጀት ነው የሴቶች ኃጢያት "

ጣፋጭ ጥበብ ገጽ ፫፻፩ ቁጥር ፪ሽ ፫፻፶፱


🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇

🍇 ልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ 🍇

🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

16 Oct, 08:10


" ክፋት : የሌለበት : ቸር ፣
በቀል : የሌለበት : የዋህ ፣
ቁጣ : የሌለበት : ትዕግሥተኛ ፣
ኃጢአት : የሌለበት : ጻድቅ ፣
እድፍ : የሌለበት : ንጹሕ ፣
ጠማማነት : የሌለበት : ቅን : ነው ፣
ያለመከልከል : ሰጪ ፣
ያለ : መንፈግ : ለጋስ ፣
ያለ : ቂምና : ያለቅናት : ኃጢያትን
የሚያስተሠርይ ነው ፣
ለሚጠሩት : ሰዎች : የቀረበ : ነው ፣
ለሚፈሩትም : በጎውን : ነገር : የሚያደርግ : ነው ፣
ለሚያንኳኩ : ሰዎች : የተከፈተ : በር : ነው ፣
ያለ : መሰናክል : ጥርጊያ : ጎዳና ፣
እሾህ : የሌለበት : ንጹሕ : ፍለጋ : ነው ፣
የአማልክት : አምላክ ፣ የአጋዕዝት : ጌታ :
እግዚአብሔር : እርሱ : ብቻ : ነው ፣

ቅዳሴ : ኤጲፋንዮስ

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርኃ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በዓል ይኹንላችሁ ።

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

16 Oct, 05:53


" የማኅጸንሽ ፍሬ ልጅሽ በመስቀል ላይ ያለበደል በተቀበለው መከራ ፤
ያዘንሽው የቀድሞ ኀዘን ይበቃልና ማርያም ሆይ ! አትዘኝብኝ የልጅሽ ደም በደሜ ተጨምሯልና ፤
በየቀኑ እየበደልኩኝ እኔ ባሳዝንሽም እንኳን ፤
በምሕረትና በይቅርታ ተአምር አድርጊልኝ እንጂ አትዘኝብኝ ። "

ማኅሌተ ጽጌ

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

14 Oct, 10:32


ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ
መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት፤

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳርና
የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
የተከበራችሁየመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች፤
የአዲስ አበበ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች፤
ከሀገር ውስጥና ከውጭ የመጣችሁ የየሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች፤
በአጠቃላይ በ43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዐቀፍ የጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመሳተፍ በዚህ የተገኛችሁ በሙሉ፤
“አሠንዩ ፍኖተ ዘተሰመይክሙ ኖሎተ ከመ ትርዓዩ መርዔተ ከመ ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሐዋርያቲሁ እለ መሀሩ በስሙ፡- ኖሎት የተባላችሁ ሆይ በስሙ እንዳስተማሩ እንደ ዐሥራ ሁለት ሐዋርያት መንጋውን ትጠብቁ ዘንድ መንገድን አሳምሩ” (ቅዱስ ያሬድ)
በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው ሹመት ወይም ኃላፊነት ካለ ተጠያቂነት የማይቀር ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም ሹመት የሚሰጠው ስራ እንዲሰራበት እንጂ እንዲሁ ለከንቱ ስላልሆነ ማለት ነው፡፡

ሹመት የመፈጸምና የማስፈጸም ሕጋዊ መሳሪያ ነው፤ መሳሪያውን በአግባቡ ከተጠቀምንበት የምንመሰገንበት፣ ያ ካልሆነ ግን የምንወቀስበት፣ ምናልባትም የምንቀጣበት አጋጣሚ ሊያስከትል ይችላል፤ ይህም በየጊዜው በሥዩማን ላይ ሲደርስና ሲፈጸም የምናየው እውነታ ነው፡፡ እኛ ካህናትና ምእመናን የእግዚአብሔርን መንግሥት ተልእኮ ልናስፈጽም በሕዝበ እግዚአብሔር ላይ የተሾምን ሥዩማን ነን፤ የመንግሥተ እግዚአብሔር ተልእኮ ከሰው ወገን አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ መጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የልጅነት ሥልጣን የተሰጠን እኛ ወደ መንግሥቱ በረት ያልገቡትን የማስገባት፣ ገብተው የወጡትን መልሶ የማስገባት፣ በበረቱ ያሉትን በጥሩ ውሀና በለመለመ መስክ በማሰማራት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን፡፡

ይህንን ኃላፊነታችን በትክክል ለመወጣት ከሁሉ በፊት እኛ ሥዩማን ተልእኮአችንን በውል መገንዘብ አለብን፤ ለተመደብንበት ተልእኮም በጽናት መቆም አለብን፣ በትጋትም መስራት ይጠበቅብናል፤ ከዚህም ጋር በእምነት በሥነ ምግባር በሥራ አፈጻጸም ከምንጠብቃቸው መንጋዎች በእጅጉ የላቅን ሆነን መገኘት በጣም አስፈላጊያችን ነው፡፡ በመንግሥተ እግዚአብሔር ተሹሞ ወደሥራ የተሠማራ ሰው ሥራው ፍጹም የተቃና ይሆንለት ዘንድ “ራሱን ክዶ” መስቀሉን መሸከም ግድ ይለዋል፤ ያለዚያ ውጤታማ መሆን አይቻልም፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
አሁን ያለነው ሥዩማን በዚህ ዘመን ላለችው ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ሆነን የተሾምን ነን፤ ወደ በረቱ ያልገባ፣ ገብቶም የወጣ ካለ ማስገባትና መመለስ ያለውም በተመቻቸ መልካም አስተዳደር፣ በለመለመ ትምህርተ ወንጌል፣ በጥሩ ሥነ ምግባር አርአያ ሆኖ መጠበቅ ከኛ ይጠበቃል፡፡ ታድያ ይህንን በተግባር መተርጐም ችለናል ወይ? በጎቻችን አልቦዘኑም ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡
ይህ ዓቢይ ጉባኤ የተሰበሰበበት ምክንያትም ይህንን ተልእኮ ለማስፈጸም በሚደረገው ጥረት ያጋጠሙ ነገሮች ካሉ ለመስማትና ለመገምገም እንደዚሁም የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ በተቀመጠው መሪ ዕቅድ አማካኝነት ተልእኮውን ለመወጣት ነው፤ ‹‹የሚደርስበትን የማያውቅ የሚሄድበትን አያውቅም›› የሚለው ብሂል በአሠራራችን ቦታ እንዳይኖረው መጠንቀቅ አለብን፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችን መዳረሻ የማይታወቅ አይደለም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በቀጣዮቹ ዐሥር ዓመታት የት ልትደርስ እንደምትችል ቅዱስ ሲኖዶስ ባጸደቀው መሪ ዕቅድ በግልጽ ተቀምጦአል፤ ይህ መሪ ዕቅድ ሁላችንም ትኵረት ሰጥተን ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይኖርብናል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
እንደ እውነቱ ከሆነ አሁን ባለን ክህነታዊ አገልግሎትና አስተደደር ክፍተቶች እንዳሉን የማይካድ ነው፤ ዘመኑ የፈጠረብን ጫና ሳያንስ በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጐደላቸው አሰራሮችም ለተልእኮአችን ከባድ ዕንቅፋት እየሆኑብን ነው፡፡ ሰበካ ጉበኤ የተቋቋመው በተዘረጋው መዋቅር አማካኝነት ቤተ ክርስቲያንን በማኅበረ ካህናት ወምእመናን የጋራ ጥበቃ ለአዲሱ ትውልድ ለማሸጋገር እንደሆነ ሁላችን አንስተውም፡፡ ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን ይህን ያህል የመልካም አስተዳደር ክፍተት እየታየ የሰበካ ጉባኤ ዓላማ ግቡን መትቶአል ለማለት ስለማያስደፍር በዚህ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በሙሉ ሊቀርፍ የሚችል አሰራር ቀይሶ ችግሩን ለመቀልበስ በጥናት ላይ የተመሠረተ ዘላቂና ፈጣን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
ያለፈው ዓመት በዝቋላ ገዳምና በሌሎች አካባቢዎች አበው መነኮሳት፣ ቀሳውስት እንደዚሁም በርከት ያሉ ምእመናን በግፍ የተገደሉበት ሆኖ አልፎአል፤ አሁንም ችግሩ እየቀጠለ ነው፤ በቅርቡም በምሥራቅ ሸዋ ከነቤተሰባቸው የተገደሉ አዛውንት ካህን ሁናቴ የችግሩን ቀጣይነት ይጠቁማል፡፡
በመጨረሻም፤
በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ካህናትና ምእመናን ልጆቻችን፣ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ሃይማኖት፣ ቀኖና እና ሥርዓት ተጠብቆ እንዲቀጥል ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ሁላችንም ተባባሪ እንድንሆን፣ በሀገራችን ያለው አለመግባባት በሰላምና በውይይት ተፈትቶ ፍጹም ሰላም ይሰፍን ዘንድ በጸሎትና በአንድነት እንድትተጉ አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን 43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዓቀፍ ጠቅላላ መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡
መልካም ጉባኤ ያድርግልን፤

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

1,377

subscribers

2,361

photos

8

videos