✞ገድለ ቅዱሳን✞, [8/7/19, 6:48 PM]
[ Forwarded from ✞ገድለ ቅዱሳን✞ ]
#ነሀሴ_1_ቀን_የምንጀምረው_የፍልሰታ ፆምም የበረከት ማግኛ እንዲሆን በትጋት
ልንፆመው ያስፈልጋል ።
@kegdlat
#የፍልሰታ ፆም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከተደነገጉት
ሰባት አፅዋማት መካከል አንዱ ሲሆን
#ፆመ_ፍልሰታ 👉 የዚህ ፆም ቀን የተወሰነ ሲሆን ከነሀሴ 1 ቀን እስከ ነሀሴ 15 ቀን ያለው ነው ። 👉 ይህ ፆም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መታሰቢያ ነው ። * እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ለ64 አመት ያህል በምድር ላይ የኖረች ሲሆን... *... ስጋን የለበሰ ሁሉ ሞትን
መቅመስ አለበትና በእስዋና በልጅዋ ፈቃድ አርፋለች። 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 👉 የፆመ ፍልሰታ ታሪክም በትንሳኤዋና
በእርገቷ ላይ ያተኩራል። * ይህም ቅዱሳን ሀዋርያት የእመቤታችንን አስከሬን ለመቅበር
እየሄዱ እያሉ ተንኮለኛ የሆኑ አይሁድ አይተው * ..ካሁን በፊት ልጅዋን ተነሳ እያሉ
አገራችንን እየበጠበጡ ይገኛሉ፣ ነገ ደግሞ እሷም ተነሳች ብለው ይረብሹናል *...በማለት በሰይፍ
አባረሯቸው ሲሸሹም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስከሬኗን ወስዶ በአፀ ህይወት ስር አኖረው። 👉ሀዋርያትም ሰዎች ስለ ድንግል ማርያም ቢጠይቁን ምን እንመልሳለን ብለው ተጨነቁ። በኋላም እግዚአብሔር ይህንን ሚስጥር እንዲገልፅላቸው ፆምና ፀሎትን ያዙ። 👉ሀዋርያት ፆምና ፀሎትን ሲጨርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል ማርያምን አስከሬን ሰጣቸው ። በዚህ ጊዜ ወስደው በጌቴሴማኒ በመቃብር አኖሩት። ++++++++
* በሶስተኛው ቀን በልጅዋ ስልጣን አርጋለች። እመቤታችን ስታርግ ቶማስ ለተልእኮ እንደሄደ ስላልተመለሰ
አልነበረም። * ሆኖም እመቤታችን ከሞት ተነስታ በክብር ስታርግ እሱ ደግሞ በተአምር
ደመና ጠቅሶ ከተልእኮው ሲመለስ ተገናኝተው ሰበን ለበረከት ሰጥታዋለች። * ይህንን የምስራች ለሐዋርያት ነግሯቸው ለማስረጃም ያህል ለበረከት የሰጠችውን ሰበን አሳይቷቸዋል ። * በዚህ ጊዜ የቶማስ እመቤታችንን የማየት እድል እንዲደርሳቸው
በድጋሚ ፆምና ፀሎት በመያዝ ለምነውታል። " * ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።" (የማቴዎስ ወንጌል 7:7) በሚለው አምላካዊ ቃል አምነው ጠየቁ። * የጠየቁትን የማይነሳ እግዚአብሔርም ለጥያቄያቸው መልስ ሰጥቷቸዋል። እመቤታችንንም ለማየት በቅተዋል። ++++++++++++
(ምንጭ ፣ ተአምረ ማርያም) + በመሆኑም ይህንን ድንቅ ነገር ለማሰብና የተሰወረውን ሚስጥር ሁሉ በቸርነቱ ለቤተክርስቲያን የተገለጠ እንዲሆን በማለት ምእመናን በየአመቱ
ፆመ ፍልሰታን ይፆማሉ። + እኛም ይህንን የፍልሰታ ፆም ስንፆም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት እንዲያድርብን፣ እግዚአብሔር የሚስጥሩን በር እንዲከፍትልን፣ ለምነን እንድናገኝ ፣ + በፆም በፀሎት የሚገኘውን በረከት እንድንቀበል፣ እግዚአብሄር እንዲረዳን፣ መልካምና አስተዋይ ልቡና እንዲኖረን፣ የስጋ ፈቃዳችን እንዲከስም፣ እንዲሁም ****--***** @kegdlat @kegdlat @kegdlat
ስለሀገራችን፣ ስለሰዎች ስለመበለቶች፣ ስለ ድሀ አደጎች፣ ስለታመሙ፣ ስለተጨነቁ፣ + እንዲሁም አገልጋዮች በመልካም እንዲያገለግሉ በትጋት መፆምና መፀለይ ይገባናል። + ስለፅድቃችን አይደለም ስለ እግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት ብሎ ይረዳናልና፣ ከኛ የሚጠበቀው
በተሰበረ ልብ ሆኖ መቅረብን ነው ። " +የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።" (መዝሙረ ዳዊት 51:17)
እግዚአብሔር በሰላምና በበረከት ይህንን ፆመ ማርያምን እንድንጠቀምበት ይርዳን። @kegdlat @kegdlat @kegdlat
የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት, [8/9/19, 6:16 AM]
✞ ድንግል ትንሳኤሽን
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት /2/
ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /2/
አዝ_______
ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተስወረን የትንሳኤሽ ምስጢር
በራችንን ዘግተን በፀሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/
አዝ________
መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ስው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሽንፏል መቃብር አይኖርም
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /2/
አዝ_________
ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለ ሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት
ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምህረት
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/
መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ
@senbetmezmurat