በሄሊኮፍተር ጭምር ተደጋጋሚ የውሃ ርጭት መደረጉ ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው (6:00) አካባቢ በሰጡት አጭር ማብራሪያ " አሁን ላይ እሳቱን በቁጥጥራችን ስር አድርገናል ፤ የማጥፋትና የመልቀም ስራ ነው የሚቀረን እጅግ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ እዚህ ላይ ባይገታ በጣም ብዙ ቦታ ፣ ሰፊ አካባቢዎች ላይ እሳቱ ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ከዚህ የበለጠ ሃብትም ይወድም ነበር " ብለዋል።
በመርካቶ ሸማ ተራ ከምሽቱ 1:00 የጀመረው የእሳት ቃጠሎ አሁን ላይ (9:00)ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል።በሄሊኮፍተር ጭምር በተደጋጋሚ በተካሄደ የውሃ ርጭት መቆሙ ተነግሯል።
@SEBER_ZENA_ET
@SEBER_ZENA_ET