የዓለም የሕዋ ሣምንት ክብረ በዓልን በማስመልከት "ሕዋ እና የአየር ንብረት ለውጥ" በሚል መሪ ቃል " ፡ ዕለተ ሐሙስ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር ሳይንሳዊ መረሃግብር አዘጋጅቶ ነበር። መረሃግብሩ ብሪቲሽ ካውንስል እና የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይስን ሶሳይቲ አመራሮች የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን ፤ "ዩናይትድ ኪንግደም እና የሕዋ ሳይንስ የትምህርት ዕድሎች" በሚል ርዕስ ሰፋ ያለ ገለፃ ተካሂዷል። መረሃግብሩ ቀጥሎ ሲካሄድ ፤ ስለ "ስፔስ ዌዘር" ሰፋ ያለ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። በመጨረሻም የከዋክብት ምልከታ መረሃግብር የተካሄደ ሲሆን ፤ ታዳሚዎች ሳተርን እና ጨረቃን መመልከት ችለዋል።
On Thursday, as part of the World Space Week celebration themed 'Space and Climate Change', we partnered with the British Council for an exciting event. The day kicked off with opening speeches from both the British Council and the ESSS, followed by insightful discussions on UK scholarship opportunities in space science. A detailed presentation on Space Weather captivated the audience, and the event concluded with a memorable stargazing session, where participants had the chance to observe Saturn and the Moon!
#ESSS #BritishCouncil #WSW