በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ምን መደረግ አለበት?
ክፉውን ያርቅልንና ድንገት ከበድ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት እነዚህን ጠቃሚ መረጃዎች ማወቅ ይበጃል።
- መረጋጋት! ቤት ውስጥ ከሆኑ የመሬት መንቀጥቀጡ እስኪቆም ድረስ በዚያው በቤት ውስጥ ይቆዩ። ውጭ ከሆኑም ወደ ውስጥ ለመግባት አይሞክሩ እዚያው ይቆዩ።
- ቤት ውስጥ ከሆኑ በከባድ የቤት እቃዎች ( ጠንካራ ጠረጴዛ) ስር ይግቡ ያ ከሌለ በቤት ውስጥ በሚገኝ የውስጥ ግድግዳ ኮርነር ላይ ፊቶንና ጭንቅላቶን ሸፍነው ይቁሙ።
- ከመስኮቶች እና ከመሰበሩ መስታወቶች አጠገብ ይራቁ።
- ከቤት ውጭ ከሆኑ ከኤሌክትሪክ መስመሮች ወይም ሊወድቅ ከሚችል ማንኛውም ነገር ርቀው ክፍት ቦታ ላይ ይቆዩ።
- በውጪ የሚገኙ ከሆነ ከህንጻዎች አከባቢ ይራቁ
- ሻማ ወይም ማንኛውንም ተቀጣጣይ ነገር አይጠቀሙ።
- መኪና ውስጥ ከሆኑ መኪናውን ያቁሙ እና የመሬት መንቀጥቀጡ እስኪቆም ድረስ በመኪናው ውስጥ ይቆዩ።
- ሊፍት በፍጹም አይጠቀሙ ወደ ውጪ ለመውጣት ደረጃን ይጠቀሙ።
በቤታችን ለዚህ ብቻ ሳይሆን ለሌላም አደጋ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ መስጫ ኪት ቢኖር ይመረጣል። እንዲሁም ስለመጀመሪያ የህክምና አሰጣጥ መሰረታዊ እውቀት መያዙም ይመከራል።
@tikvahethmagazine