ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

@yoftahiebooks


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
የፈለጉትን መጻሕፍት በፈለጉት ጊዜና ሰዓት በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ስልክ👉 0902093535 ወይም 0918004191 ይደውሉ
ለማንኛውም ጥያቄ ሆነ አስተያየት👉 @yoftahiebot
Facebook ፔጃችን #Like ያድርጉ👇
https://www.facebook.com/yoftahiebookstore/

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

19 Oct, 13:44


#አዲስ መጽሐፍ በሽያጭ ላይ ነን።
ላምባ በአስኳትራ
በአማኑኤል ደርበው
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

14 Oct, 09:06


የከበደ ሚካኤል ሥራዎች ውስጥ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                          
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

12 Oct, 08:21


➤ ሜሎሪና ስውር ጥበብ
➤ ሜሎሪና ቴሎስ
➤ ሜሎሪና ሕይወቴ
የናሁሰናይ ፀዳሉን መጻሕፍት #እየሸጥን ነው።
"ሕይወት ድራማ ነች፤ ነዋሪዎቿም የሚተውኑትን ገጸባህሪ ይመርጣሉ። በዚህ ተውኔት ውስጥ አንዳንድ ሰዎች በሌላ ሰው ሕይወት ውስጥ ዋና ገጸባህሪ መኾን ይፈልጋሉ። የሚበጅህን እኔ አውቅልሃለው፣ እኔ እወስንልሃለው በማለት የራሳቸውን ገፀባህሪ ትተው የሌሎች ገፀባህሪን ለመተወን ይባዝናሉ።... "
ሜሎሪና -ሕይወቴ ገጽ 73
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

12 Oct, 04:41


እነዚህ የሕይወት ተፈራ መጻሕፍት ይሸጣሉ።
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Oct, 07:12


ድጋሜ እትም
ከመዝ ነአም
እንዲህ እናምናለን
መምህር ገብረ መድኀን እንየው

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Oct, 05:23


#የመጽሐፍ_ትዝታ
የመጽሐፉ ርእስ፦ ሀኖስ
ደራሲ፦ ንጉሴ አየለ ተካ
የታተመበት ዓ.ም፦ 1990
ዘውግ፦ ልብወለድ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
#በሽያጭ ላይ ነን
አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

10 Oct, 15:24


ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን -እንዴት ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ፈለጉ?

-ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮነን የተወለዱት 1942 ዓ.ም. ደብረ መዊእ ማርያም ነበር፡፡ የድጓ ሊቅ ናቸው፡፡ ድጓ በጉንጩ ማለት ትችላላችሁ፡፡ ጎንደር ቤተልሔም አስመስክረዋል፡፡ ደቡብ ጎንደር ጽርሐ አርያም ዙር አባ አረጋዊ ዘልቀው ዝማሬ መዋሥዕት ተመረቁ፡፡ ወንበር ዘርግተው ማስተማር ጀመሩ፡፡ እናም በመርዓዊ ማርያም ቤተክርስቲያን በድጓ መምህርነት ሲያገለግሉ በነበረበት ዘመን በአንድ አጋጣሚ ምክንያት ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ተነሳሱ፡፡ ለድጓ መምህሩ ደመወዝ የሚከፈለው ከአርሶ አደሩ እህል፣ ከሴቱ እና አባወራው ብርና ሳንቲም በመሰብሰብ ነበር፡፡ በዘመነ ደርግ 1968 ዓ.ም. አንድ ቀን ክፍያ ከሚያስፈጽሙት ጋር ሳንቲም ለመጠየቅ ሻይ ከምትሸጥ ሴት አዳሪ ቤት ዘለቁ፡፡ ክፍያ አስፈጻሚዎቹ “ለድጓ መምህሩ 50 ሳንቲም ክፈይ” አሉ፡፡ ያች ምስኪን ሴት “ምንም ነገር የለኝም አልክፍልም” አለች፡፡ ወዲህ ቢሉ ወዲያ እጅግ ቢለምኗት አልከፍልም በማለት በአቋሟ ጸናች፡፡ አስፈጻሚዎቹ ለእግድ በማለት ከቤቷ የሻይ በራድ ይዘውባት ወጡ፡፡ “እባካችሁ በራዴን መልሱልኝ” እያለች ለመነች፡፡ ፈጽሞ ሊመልሱላት አልፈለጉም፡፡ ከዛም ክፍያ አስፈጻሚዎቹ ከቤት ውጭ ሁነው “ክፍያ ክፈይ የድጓው መምህር እሳቸው ናቸው” አሏት፡፡ ያች ሴት የድጓ መምህሩን በላይ መኮንን ትኩር ብላ ዐየችና "ይህማ ወጣት አይደል ለምን ሠርቶ አይበላም?" አለች፡፡ ያኔ ሊቁ በላይ እድሜያቸው 27 ዓመት ነበር፡፡ ክፍያ አስፈጻሚዎቹ በንግግሯ በጣም ሳቁ፡፡ ነገር ግን ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮነን አልሳቁም፡፡ ንግግሯ ልባቸውን ነክቶት ነበርና፡፡ "እውነቷን ነው:: ስማር ለምኜ መምህር ሁኜ ለምኜ" በማለት ለምን ሠርቸ አልበላም? አሉና ሠርቶ ለመብላት ዘመናዊ ትምህርት መግባት አለብኝ በማለት ቆርጠው ተነሱ፡፡ ሁል ጊዜ ሲያስታውሱ ያች ሴት ያን ንግግር ባትናገርና ልቦናየ ባይነካ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ገብቸ አልማርም ነበር ይላሉ፡፡ ለሊቅ አንድ ቃል ትበቃዋለች የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ በብዙ ውጣ ውረድ እንዳይማሩ ግፊት በሚያደርግ የማኅበረሰብ ሽሙጥና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ተቋቁመው ዘመናዊ ትምህርቱን በ27 ዓመታቸው ከሕጻናት ጋር በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየዋሉ በመማር ጀምረው በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ዘልቀው ተምረዋል፡፡ ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን ከዘጠኝ(9) በላይ መጻሕፍት ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡ በተለይ “ዕሴተ ትሩፋት ዘቅዱስ ያሬድ” በተሰኘ መጽሐፍ ይታወቃሉ፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" በሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥናት መጽሔት ላይ በቅዱስ ያሬድ ታሪክ ጉዳይ ጥናት አሳትመዋል፡፡ “ሕያው ልሳን ግዕዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት” የተሰኘ መጽሐፍን ለማሳተም አዲስ አበባ የነበራቸውን ቤት ለመሥራት መሠረት የጣሉበትን መሬት ሽጠው አሳትመዋል፡፡ ሊቁ እጅግ በብዙ ውጣ ውረድ ተምረው ያገኙትን እውቀት ለትውልድ ለማስተላለፍ በቃልና የጽሑፍ ሥራ የደከሙ ትልቅ ሰው ናቸው፡፡ ስለ ሊቁ ዝርዝር ታሪክ ማንበብ ለሚፈልግ በ2011 ዓ.ም. በታተመ “ማኅደረ ደራሲያን” በተሰኘ መጽሐፍ ከገጽ 43-57 እንድታነቡ ይመከራል፡፡

-አይደክሜው ሊቅ አዲስ መጽሐፍ "ሐመር ዘዮናስ" የተሰኘ በቅርቡ አሳትመዋል። ስለ መጽሐፋ የሚከተለውን ብለዋል "ሐመር ዘዮናስ" በሚል ርእስ ያዘጋጀሁት ይህ የታሪክ መጽሐፍ ከይዘት አንጻር ጠቅለል ብሎ ሲታይ ቤተ ክርስቲያኒቱ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን እምነቶችን ከተቀበለችባቸው ዘመናት ጀምሮ ለ3000 ዓመታት ያህል ‹‹የአብነት ትምህርት ቤት››ን ማእከል አድርጋ ለሥነ ጥበብ፣ ኪነ ጥበብና ለሀገር-በቀል ዕውቀቶች፥ እንዲሁም ለሀገር መንግሥት ግንባታ፣ ለሀገሪቱ አንድነትና ለሕዝቦችዋ አብሮነት ያበረከተችው ኹለንተናዊ አስተዋጽዖ የተቃኘ ሲኾን፤ አሁን የገባችበት ፈተናም እንዳለ ኾኖ ያሉዋትን መልካም ዕድሎችና ተስፋዎችን ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡"

-የሊቃውንትን መጽሐፍ በመግዛት እያነበብን እናበረታታ እንደግፍ፡፡
Yosef Fiseha Sewunet

3,112

subscribers

3,952

photos

40

videos