Mattu University (MaU)

@mettuniversity


We are dedicated to serve the community! ♦️Website: https://meu.edu.et. ♦️FB: https://facebook.com/mattuniversity ♦️Youtube:https://www.youtube.com/channel/UCjDcyL1HV5A3VgkVdue0tpw?sub_confirmation=1

Mattu University (MaU)

17 Oct, 15:21


Barattoota Barnoota Remedial Barachuu Barbaaddan Hundaaf

የRemedial "ትምህርት ለመማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ

Mattu University (MaU)

11 Oct, 15:02


የሽልማትና የሽኝት መርሃ-ግብር ተካሄደ

ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም (ህ.ዓ.አ.ግ.)
===========+===========

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመጀመርያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን ለ2ኛ ደረጃ ት/ት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና አስቀምጦ 100% ከማሳለፋም በላይ አመርቂ ውጤቶችም መመዝገባቸዉን ተከትሎ ለተማሪዎቹ የሽልማትና የሽኝት መርሃ-ግብር ተዘጋጅቷል። በዚህም ለሁሉም ተማሪዎችና የት/ቤቱ መምህራን የእውቅና ሰርተፊኬት የተሰጠ ሲሆን ከ500 በላይ ላስመዘገቡ 4 ተማሪዎች ታብሌት ተበርክቷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝደንት ዶ/ር አለሙ ድሳሳ፣ የመቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተሻለ ኤጀርሶ፣ የመቱ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ሀይሉ፣ አባ ገዳ፣ የተማሪ ወላጆችና ከ9-12 ክፍል ያሉ የልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቱ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። በመድረኩም እንደ ሀገር ከገባንበት የት/ት ጥራት ስብራት ለመዉጣት እየተደረገ ላለዉ ጥረት የመቱ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሞዴል መሆን እንደሚችልና ባከባቢዉ ላሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችም መልካም ተሞክሮዉን ማስተላለፍና መደገፍ እንዳለበት ተነስቷል። ይህ ዉጤት ቀጣይነት እንዲኖረዉ ከኋላ ባሉት ተማሪዎች ላይም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል።

We're dedicated to serve the community!