“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

@memehir_girma


<< ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል >> ወደ ቲቶ 2 ፤ 12-13

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

22 Oct, 17:59


https://vm.tiktok.com/ZMhmrphq6

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

22 Oct, 16:52


https://youtu.be/qWfvFJ04oQo?si=WnpHo6y44HQc8nBn

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

21 Oct, 10:47


https://vm.tiktok.com/ZMhauyta7

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

21 Oct, 07:50


በኢየሱስ የሸንጎ አደባባይ የታየው በአንድነት ወንበዴን የመደገፍ ጩኸት፤ ከውስጥ በኩል ያለ የክፉ መናፍስቶች ደጉን የማፍረስ መናበብ ምሳሌ ነው፡፡ አስታውሱ! ጌታ
ለሚጮኹበት ካህናትና አይሁዳውያን አስቀድሞ እንዲህ ብሏቸው ነበረ፤ "እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ" (የዮሐንስ ወንጌል 8፥44)
በነዚህ ሰዎች አድፍጦ ያለው የዲያቢሎስ መንፈስ፤ ዘር ሆኖ እየተወራረሰ አብሮ በመወለድ፤ እንደ አባት እየመራ ለክፋት አሳድጎ ለክፋት በማኖር፤ ምቹ ጊዜና ቦታን ባገኘበት ዕድል ላይ፤ መልካም ክርስቶስን ለማስወገድ በከሳሾቹ ሕሊና እጅ ለእጅ በመያያዝ፤ በአንድ ጫና የተገፋ የአንደበት ድምፅን በሁከት አሰማ፡፡

መናፍስት አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ባልተለየ ጽኑ ሃይማኖታዊ አኗኗር ሲመላለስ፤ ጥብቅ የቅድስና ሰንሰለት ከመለኮት ኃይል ጋር እንደሚኖረው ያውቃሉ፡፡ ስለሆነ ግለሰቡን በግል ፈተና በማሰናከል የጽደቅ ትስስሩን ለመቁረጥ ካልቻሉ፤ በሥጋ ዓለም ባለ የእርስ በእርስ መናበብ አንድ ሆኖ በመምጣት፤ የሰዎችን ብዙ ቁጥርነት ምሽግ ያደረገ መልካሙን አፍራሽ የተንኮል ተኩስ ይተኩሳሉ፡፡ ዲያቢሎስ ላይ ንቃተ ሕሊና አግኝታችሁ በተግባራዊ መረጃ በመታገዝ የእምነት ኃይል ላይ በመቆም፤ ብርቱ የዕለት አምልኮተ እግዚአብሔርን የጀመራችሁ ሰዎች በብዙ የምትቸገሩበት አንደኛው ጉዳይ፤ አስቀድሞ በጌታችን ላይ የደረሰው የክፉ መናፍስት መልካሙን ለመቃወም መናበብ የሚባለው ጉዳይ ነው፡፡

✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከ መልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
11/02/2017 ዓ.ም
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

21 Oct, 07:50


✞ መሲሕ( יֵשׁוּעַ )ላይ ሁሉም ተባበሩ፡፡ ✞

ከፊቱ የሚቆሙት ሁሉ በራሳቸው ላይ እየፈረዱ እውነትን ብቻ የሚናገሩበት አስፈሪ ጉባኤ ያለው ታማኝ ዳኛ፤ በካህናትና በመኳንንት የሐሰት ክስ ሕዝብ አደባባይ ቆሞ ከጲላጦስ ደጅ ብያኔን ሊቀበል ተሰየመ፡፡
አስተዳዳሪው ጲላጦስም በክርስቶስ የታሪክ መዝገብ ላይ ምንም አይነት ስሕተት ስላላገኘ፤ "ይህ ሰው ንጹሕ ነው፥ እነሆስ ለሞት የሚዳርገውን አላጠፋምና [እንዳይከፋችሁ ሲባል]

ቀጥቼ እፈታዋለሁ" ሲል ፍርዱን ሰጠ፡፡ ነገር ግን ሁሉም በአንድነት የተላለፈው ውሳኔ ፍላጎታቸውን የሚጋፋ እንደሆነ በማሳወቅ፤ ይልቅስ ይህን ሰው[ሎቱ ስብሐት] አሰወግዶ፥ በርባንን እንዲፈታላቸው ወደ ገዢው ጮኹ፡፡

ከተወለደባት ቅጽበተ ቤተልሔም አንስቶ እስከ ተሰቀለባት ጎለጎታ አንዳችም የበደል ሽራፊ ያልፈጸመ ቅዱስ ክርስቶስ ላይ ሁሉም አደሙ፡፡ ኃጢአት ከዋጣቸው፣ ሰው ከረሳቸው፣ ሐብት ከከዳቸው፣ ደዌ ከያዛቸው፣ ግራ ከገባቸው፣ መሄጃ ከሌላቸው፣ ዘመን ከጣላቸው፣ ሞት ከገደላቸው ሚስኪኖች ጋር ከመዋል ውጪ አንዳች ሲሠራ ያልተገኘው መሲሕ ላይ ሁሉም ተባበሩ፡፡ "ሁሉም ደግመው። በርባንን እንጂ ይህን አይደለም እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ።" (የዮሐንስ ወንጌል 18፥40)

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

20 Oct, 14:11


https://vm.tiktok.com/ZMha1wCWR

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

20 Oct, 13:58


ጌታ ሆይ እየተስማ፣ እየታየ፣ እየተፈራና እየተጠበቀ ካለው ክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀን፣ ሕዝቦችህን ጐብኘን! ለዘላለሙ አሜን፡፡

ቀጣይ አገልግሎት
የፊታችን እሁድ ጥቅምት / 17 / 2017 ዓ.ም በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከቅዳሴ በኃላ አገልግሎቱ ይቀጥላል!

የቤተክርስቲያኑ አድራሻ ፤ ሳሚት ኮንዶሚኒየም 2ተኛ በር ወረድ ብሎ ከኢትዮ ቻይና ት/ቤት እንደ ሁለተኛ መንገድ አማራጭ ሰሚት ጤና ጣቢያ መግቢያ መሆኑን እየገለጽን ሼር በማድረግ ላልሰሙት አሰሙ

✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከ መልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
10/02/2017 ዓ.ም
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

20 Oct, 13:58


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ የወንጌል ትምህርትና የፀበል አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል ።

********************************************
(ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፥ኢትዮጵያ)

ጌታ ባከበራት በእለተ ሰንበት ህያው በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ብዙዎች ነፍሳት ታድሰዋል በኃያሉ አምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ብዙዎች ከጠላት እስራት ተፈተዋል። የእስልምና እምነት ተከታዮችም በጉባኤል በክርስቶስ ኃይል ተጠምቀዋል!

*በመቀጠልም የበረከት ስራ ፦ በመልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ አማካኝነት ከአንድ መቶ ሺህ ብር በላይ ለ ሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ገቢ ሆንዋል ።

*በዘመናችን እግዚአብሔር ድንቅ ስራውን እየገለጠ መሆኑን ምስክር እንድንሆን ስለፈቀደልን ስሙ ቡሩክ ይሁን ። በአገልግሎታችን ብዙዎች ከጭንቀታቸው አረፈው ስር ሰዶ በስውር ከያዛቸው እና ካሰቃያቸው ጠላት ተላቀው እንደ ማየት በጎ ህሊና ላለው የሚያስደስት ነገር የለም

ቸር አምላክ ሆይ የደከሙት ይዳኑ፣ ኃጥዓን ይጽደቁ፣ ንስሃ የገቡትም ይንፁ፣ ፃድቃንም ይጠበቁ፣ የተቸገሩት ይፈቱ፣ የተጨነቁት ይረፉ፣ ተክዘው የነበሩ ሁሉ መጽናናትን ያግኙ፡፡ ያዘኑትም በአንተ ደስ ይበላቸው፣ ተስፋ የቆረጡት ተስፋቸው ይመለስ፡፡ በአስከፊ ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በምህረት ዓይንህ ይጐብኙ፡፡ ለሥጋ ፍርሃት እጄን የማልሰጥ እንድሆን ይልቁንም በእምነት የማስከብርህ ልጅህ ___ እንድሆን እመኛለሁ፡፡ እሹ ታገኛላችሁ ያልህ ጌታ መስጠት ልማድህ _ነውና እናመሰግንሃለን

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

18 Oct, 16:52


https://vm.tiktok.com/ZMhPKHBXx

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

18 Oct, 15:57


https://youtu.be/EuEmn28jULA?si=qAv3Ov2l0ZGawNMC

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

15 Oct, 19:00


https://vm.tiktok.com/ZMhfr18EK

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

15 Oct, 16:27


https://youtu.be/n50QIb6ZpkE?si=ZaS2srwVgLdMGnOT

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

14 Oct, 20:14


https://vm.tiktok.com/ZMhybpnyN

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

14 Oct, 18:30


https://www.youtube.com/live/6BTqD19XIWs?si=CKi8xF5PvKIpGCqf live ተለቀቀ

9,411

subscribers

830

photos

54

videos