ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

@memehirhenok


ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

22 Oct, 19:06


https://youtu.be/n82GGVceFJo?si=v1dYMwVBYl0pSwgX

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

17 Oct, 06:00


https://youtu.be/iTDs4opdNtY?si=Grd3oxnqu4TH-I7M

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

16 Oct, 05:41


https://youtu.be/mHQ3A21Tc80?si=2mX7xDkZpd_qw_y_

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

14 Oct, 18:03


https://youtu.be/Ae278wnscJw?si=mllWt2T1V7uVKn3a

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

13 Oct, 21:33


https://youtu.be/r36vXGjWJ70?si=A_yDTDP97FN4_bNH

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

10 Oct, 16:52


https://youtu.be/f7mZWhcCl9c?si=kCrAyBlWXpUkx6gf

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

09 Oct, 04:49


ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችን ምድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማዕቷ ለትውልድ የሚተላለፍ የዘላለም ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ መታሰብያዋን ያደረገ ስሟን የጠራ፣በስሟ ቤተ ክርስትያን የሠራ፣የተራበውን በስሟ ያበላ፣የተጠማውን በስሟ ያጠጣ፣የገድሏን መጽሐፍ የጻፈውን፣ያጻፈውን፣ያነበበውን፣የተረጎመውን፣ሰምቶም በልቡ ያኖረውን፣የልቡን መሻት እንደሚፈጽምለት እና በመንግስተ ሰማያት እንደ እርሷ የክብር አክሊል እንደሚያቀዳጀው፤ሥዕሏን አሥሎ በክብር በቤቱ አስቀምጦ ሽቶ እየረጨ ቢጸልይበት ጸሎቱ እንደሚሰማና ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ እንደሚያሸተው፣ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በስሟ የሰየመ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስም እንደሚሰጣቸው፣ዕጣን፣ስንዴና መብራትን፣ልብሰ ተክህኖ፣መጋረጃ ቢሰጥ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስ እንደሚለብስ፣ያለ ወቀሳ ያለከሳ ባህረ ሲኦልን ተሻግሮ መንግስቱን እንደሚወርስ ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡

፨ ሰማዕቷን ከሌሎች ቅዱሳን ልዩ የሚያደርጋት ታሪክ ፨

በግብጽ አገር አርባ ዓመታት የነገሠ ባለ 12 ክንፉ ብጹአዊ አቡነ ሙሴ የሚባሉ ታላቅ ጻድቅ አሉ፡፡ እኝህ ጻድቅ ከንግስና ወደ ምንኩስና የተሸጋገሩ መንፈሳዊ አርበኛ ናቸው፡፡

ታድያ እኝህ ጻድቅ የቅዱሳን፣የሰማዕታትን ዓጽም እሰበሰቡ ደግላቸውን እያጻፉ፣ቤተ ክርስትያን በመስራት፣ታቦታቸውን በማክበር፣በበዓላቸውም ቀን ይቀድሱ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ታቦት ለማሰናዳት፣ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ በወርቅ የተለበጠ እና በላዩ በሮማይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት ያገኛሉ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰቡ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመሩ፡፡ ግን የቅድስት አርሴማን ግድልና የሞቷን ዜና አላገኙም፡፡ ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች እና የሰማዕትነቷን ሥራ ያስረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አመለከቱ፡፡

ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለአቡነ ሙሴ ተገልጦ ‹‹ብጽአዊ ሙሴ ሆይ የብጽእት አርሴማን ሥራ እነግርህ ዘንድ ስማ፡፡ ይህቺ ሰማዕት ገና አልተጸነሰችም፣አልተወለደችም፤በወርቅ ዓምድ በሕይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ፡፡ ነብዩ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይጻፋል እንዳለ እርሷም በኋለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች፤በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል፡፡

ተአምሯ የሚነገረው በኢትዮጲያ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰብያ መጥራት አትተው፡፡ ጽላትዋም ከአንተ ጋር ይኑር፡፡ የመቅደስዋም ህንጻ በህንጻህ ቦታ ጎን ይኑር፡፡ ስምህ በተጠራበትም የስሟ መታሰብያ ይጠራል›› ብሎ መልአኩ ወደ ላከው እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡

አቡነ ሙሴም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ ሰማዕቷም ገና ሳትወለድ በፊት እንደ እመቤታችን በእግዚአብሔር ህሌና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ እኛም እንደ እንደ ጻድቁ አቡነ ሙሴ በሰማዕቷ ጸሎት እና ቃል ኪዳን ልንጠቀምባት ይገባል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዮንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶም ስለ ዮፍታሔ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነብያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና›› ነው ያለው፡፡ /ዕብ 11÷32/ እኔም ስለ እዚች ድንቅ ብርቅ እና ከወርቅ በላይ የከበረች ከአልማዝም በላይ የተወደደች ስለ ሰማዕቷ ለመተረክ ጊዜ ስለማይበቃን እዚህ ላይ ይብቃን፡፡

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ጸሎት፣ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

በሰማዕቷ በቅድስት አርሴማ ስም ‹‹ሼር›› አድርገው ለወዳጆ ይዘክሩ፡፡

በድጋሚ የተለጠፈ

መስከረም 29/1/17 ዓ.ም
ሎስ አንጀለስ

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

09 Oct, 04:49


#_አርሴማ_ቅድስት_ሰማዕት!

#_አጠር_በጠር_ያለ_ታረኳ_እና_አስገራሚ_ቃል_ኪዳኗ!

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ከመወለዷ በፊት ፅላት እንደተቀረጸላት ያውቃሉ?

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ- ማርያም

ሼር በማድረግ ለሰማዕቷ ወዳጆች አድርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከሚያከብሩ ብሩካን ከሆኑ፤ በጾም በጸሎት በስግደት በትጋት ከሚኖሩ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስ ከእናቷ ከቅድስት አትናስያና በጥር 6 ቀን የተወለደች ደገኛ የገድል አርበኛ ናት፡፡

በተለይ ስትወለድ ይህ ቀረሽ የማትባል እጅግ መልከኛ እና ግርማዋ የሚያስፈራ ነበር፡፡ እናት እና አባቷም በጾም በጸሎት በስዕለት ስላገኟት እስከ 3 ዓመት ካሳደግዋት በኃላ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም በተሰራች ቤተ ክርስትያን ታገለግል ዘንድ ሰጧት፡፡ እመቤታችንን 12 ዓመት አገልግላ ያለፈቃድዋ በቤተሰቦችዋ ግፊት በ15 ዓመቷ ዳሯት፡፡ ሰማዕቷ ግን ዓለማዊ ሕይወት ባለመፈለግዋ ወደ ገዳማዊ ምናኔ ህይወት ገብታለች፡፡

በዚያን ዘመን ብዙ ሰማዕታት ያስፈጀ ጨካኙ የሰው አውሬ ካሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ መላኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሴት ሊያገባ ሽቶ በየአገሩ ሁሉ ፈልገው መርጠው ያመጡለት አንድ አሽከሮቹን አዘዘ፡፡

እንግዲህ የሰማቷ አሳዘኝ የመከራ ሕይወት ከዚህ ነው የሚጀምረው፡፡

የዲዮቅልጥያኖስ ሠራዊቶች አርሴማ የምትባል ውብ ሴት በሮሜ በአንድ ገዳም እንዳለች ሰሙ፡፡ አዋቂዎችም የሰማዕቷን ውብ መልኳን ስለው ለንገሡ ለዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ስዕሏን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና በሥጋዊ ጋብቻ አብሯት ሊኖር እንዳሰበ ለመኳንንቱ ነግሮ ለሠርግ እንዲመጡ አዘዘ፡፡

ቅድስት አርሴማ ይህንን በሰማች ባወቀች ጊዜ ከደናግሉ ጋር የንጉስ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነው አርመንያ አገር ሸሸች፡፡ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ የከበረች አርሴማን አስፈልጎ ባጣት ጊዜ በአርመንያ እዳለች ሰማ፡፡

ዲዮቅልጥያኖስም ለአርመንያው ንጉሥ ለድርጣድስ ከእሱ ሸሽታ እንደሄደች እና ባስቸኳይ አስጠብቆ እንዲልክላት አዘዘው፡፡ ደናግሉ ይንን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሰወሩ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በክብር ያመጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ሰማዕቷም ወደ እርሱ መምጣትን እንቢ ባለች ጊዜ በመሬት እየጎተቱ ወደ ንጉሡ አቀረቧት፡፡

ድርጣድስ የቅድስት አርሴማን ደም ግባት እና ውበት ባየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ የመንፈስ እናቷን አጋታን አባብላ እሺ ታሰኛት ዘንድ አዘዛት፡፡ አጋታም ወደ ሰማዕቷ ሄዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት ‹‹እወቂ ይህ ርኩስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ምሽራሽን ክርስቶስን እንዳትተይ›› ብላ አጸናቻት፡፡

ንጉሥ ድርጣድስም ሰማዕቷን ይዞ ወደ እልፍኝ ሊያስገባት ከአደባባይ መካከል ተነስቶ ድንግል አርሴማ በእጁ ያዛት፡፡ በዚያን ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው፡፡ ድርጣድስም በጦትነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለነበር በታናሽ ብላቴና ስለተሸነፈ መኳንንቱ ፊት ስለተዋረደ አፈረ፡፡

ከዚህ በኃላ በሰው አንደበት ለመናገር የሚከብድ መከራና ስቃይ አጸናባት፡፡ ሰማዕቷም ከንጉሡና ከጋሻ ጃግሬዎቹ የሚደርስባትን መከራ በመታገስ በረታች፡፡ ንጉሥ ድጣድስ በሰማዕቷ ላይ የሚያደርሰውን ሥጋዊ መከራ የልቡ ስላልደረሰለት ጡቷን በማስቆረጥ ዓይኗን በወረንጦ በማስወጣት ቢያሰቃያትም ሰማዕቷ ይበልጥ በክርስቶስ ፍቅር ጸናች፡፡ በሚደርስባትም ነገር ደስ ተሰኘች፡፡

ወዳጆቼ እኛ በሚደረስብን ሥጋዊ ህመም ስቃይ መከራ ፈተና እንደሰታለን? አንደሰትም ይልቁንም እናማርራለን፡፡ ምንያቱም የክርስቶስ የመከራ ሕይወት ውስጣችን ስላልገባ ነው፡፡ ክርስቶስ ጋር ለመድረስ መንገዱ፣በአጋንንት እና በሥጋ እየተጎዱ መሆኑን ስለማንረዳ ነው፡፡ ብንረዳም የደስታ እንጂ የመከራ ትከሻ ስለሌለን ነው፡፡ የመከራ ትከሻ ቢኖረንም ትዕግስት ስለሌለን በመከራችን አንጸናም፡፡

በመጨረሻም ንጉሥ ድርጣድስ የሚያደርገውን ሲያጣ አንገቷን በሰይፍ ሊያስቆርጥ ወሰነ፡፡ ከዚህ በኃላ ንጉሥ ድርጣድስ ቡርክት ቅድስት አርሴማን ወደ መገደያ ወንዝ እንዲወስዷትና በዚያም የከበረ ራሷን ይቆርጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን ወታደሮች አንገቷን ሲቆርጧት ያይ ዘንድ ከእርሷ ጋር ወጣ፡፡ ሰማዕቷ በምትገደልበት ትይዩ ከሠራዊቱ ጋር ተቀመጠ፡፡

የእጃቸው ክንድ የበረታ ልባቸው ግን የጨከነ ሮማውያን ወታደሮች ሰይፍ ይዘው ወደ ሰማዕቷ ቀረቡ፡፡ ሰማዕቷ ሞቷ ሰማያዊ እረፍቷ ስለሆነ በደስታ ትመለከታቸው ነበር፡፡ ቅድስት አርሴማም ወታደሮቹን የጸሎት ጊዜ እንዲሰጧት ጠይቃቸው ፈጣሪዋን ካመሰገነች በኃላ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ ወገቧን ታጥቃ አንገቷን ከፍ አድርጋ ለሚቆርጧት ታመቻችላቸው ነበር፡፡

ቆራጮች ወታደሮች ከቅድስት አርሴማ ግርማ የተነሳ ደንግጠው ሰይፋቸውን እንደያዙ በምድር ላይ ወደቁ ሰይፋቸውንም ጣሉ፡፡ ሰማዕቷም እያበረታታች ‹‹የታዘዛችሁትን ፈጽሙ›› ትላቸው ነበር፡፡ ወታደሮቹም ‹‹እኛስ ወዳንቺ መቅረብ እና አንገትሽን መቁረጥ አልቻልንም በግንባርሽ ላይ ያለው ትዕምርተ መስቀል አስፈርቶና፤ግንባርሽን ካልሸፈንሽልን አንገትሽን ፈጽሞ ልንቆርጥ አንችልም›› አሏት፡፡

ሰማዕቷም ለወታደሮቹ ፊቴን የምሸፍንበት ቁራጭ ልብስ ወይም ቁራጭ ጨርቅ ስጡኝ አለቻቸው፡፡ እነሱም ቁራጭ ጨርቅ ጣሉላት እሷም ፊቷን ሸፈነች፡፡

ቅድስት አርሴማም ንጉሥ ድርጣድስ እና ሠራዊቱ ሕዝቡም እየተመለከቱ ምስከረም 29 ቀን አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ፡፡ ወዳጆቼ እኛን ጌታችን እንደ እነ ቅድስት አርሴማ፣ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ወዘተ አንገታችሁን ተቆረጡልኝ ሰማዕት ሁኑልኝ አላለንም፡፡ ኃጢአትን ከእናንተ ሰውነት ቆርጣችሁ ጣሉት ነው ያለን፡፡

የዝሙትን ፍላጎት ከሰውነታችሁ ቁረጡና ደም አላባ ሰማዕት ሁኑ ነው የተባልነው፡፡ የኃጢአቶችን ተቀጽላ ከሥጋችሁ ላይ ቁረጡና በንስሐ ጻድቅ ሁኑ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት በደማችሁ ዋጋ ገነት ግቡ ሳይሆን በደሜ ፈሳሽት መንግስቴን ውረሱ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት ጽኑ መከራን በሥጋችሁ ተቀበሉ ሳይሆን ቅዱስ ሥጋዬን ብሉና የርስቴ ተካፋይ ሁኑ ነው ያለን፡፡ ሰማዕት ሁኑ ሳይሆን በእኔ መስዋዕትነት ዳኑ ወደ መንግስቴ ጎዳና አቅኑ ነው ያለን፡፡ አወይ አለመጠቀማችን እንደ እኛ ያደለው ማን አለ?

ቅድስት አርሴማም በሰይፍ ስትሰየፍ ከአንገቷም ደም፣ውኃ፣ወተትና ማር እንደ ክረምት ነጠብጣብ እየተንጠባጠበ መነጨ፡፡

ደም ከአንገቷ የመነጨው ስለ ሃይማኖትዋ ቆራጥነት ስለ ሞት አለመፍራት እና የጌታችንን መከራ ተሸክማ ሰማዕት ስለሆነች ነው፡፡

ውኃ የፈሰሰው ስለ ብዙ ጸሎትዋ፤ስለልመናዋና የቤተ ክርስትያን መጻሕፍትንና ምስጢራትን ሁሉ ልብ ስለምታደርግ ነው፡፡

ወተት የመነጨላት ስለ ክብሯ ስለ ከፍታዋ እና ንጽሃ ድግልናዋን ስለጠበቀች ነው፡፡

ማር የወረደው ስለሚያስደንቅ የፊቷ ወዝ፣ደም ግባቷ፣ስለ ጣፋጭ የከንፈሯ ቃልና የሰማዕታት ሁሉ እህት ስለሆነች ነው፡፡

ከዚህ በኃላ ብሩህ የሆነ የደመና አምድ ወረደና በላይዋ ጋረዳት፡፡ ወደ ሰማይም እንደ መብረቅ ሳባት፡፡ የቅዱሳን መላእክትም ማህበር ነፍሷን አሳረጓት፡፡ በክብር በእልልታ በዝማሬና በማህሌት ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አስገቧት፡፡

እርሷ እንደ ሞተች ባወቁ ጊዜ ወታደሮቹ ደናግሉን ሁሉ ጫማቸውን እየበሱ እራሳቸውን ቆረጡ፡፡ ቁጥራቸውም ሰባ ሁለት ነፍሳት ነበሩ፡፡

፨ ቃል ኪዳንዋ ፨

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

08 Oct, 03:52


https://youtu.be/et0boa5cm_M?si=7xs6Pvti_DxAzrT1

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

08 Oct, 00:51


የጌቻንን የልደት በዓል በቤተልሔም ማክበር የፈለጋችሁ መጓዝ ትችላላችሁ!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

08 Oct, 00:48


ለጌታችን ልደት ወይም ለገና በዓል ኢየሩሳሌም አብራችሁን መሄድ የፈለጋችሁ ተመዝገቡ!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

06 Oct, 07:04


እያለ ይወቅሰናል፡፡ /ፊል 3÷9/

የወለላይቱ እመቤት ልጆች በተአምረ ማርያም ላይ እንደሰማነው በፍጹም ልቡና በፍጹም ሐሳቡ እመቤታችንን ይወዳት የነበረው ኤጲስ ቆጶሱ ደቅስዮስ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ባበሰራት ቀን በዓሏን እንዳከበረና የልደትን በዓል ከማክበር አስቀድሞ 8 ቀን እንደ ጾመና ታህሳስ ሃያ ሁለትን ስለ ፍቅሯ እንዳከበረ ይነግረናል፡፡ ደቅስዮስ የጾመው ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ የለም የአዋጅም አይደለም፡፡ ግን ስለ እመቤታችን ፍቅር ብሎ ጾመ ታድያ ደቅስዮስ ምን አገኘ?

የደቅስዮስን የፍቅር ጾም የወደደችለች እመቤታችን በእጅዋ የከበረ ልብስ ይዛ ተገለጸችለት፡፡ ‹‹በእውነት አገልጋዬ ወዳጄ ደቅስዮስ ሆይ እኔ አመሰግንሃለሁ በአንተም ደስ አለኝ፡፡ ሥራህንም ወደድሁ›› አለቸው፡፡ ወዳጆቼ እመቤታችን በስቶቻችን ተደስታ ይሆን? የስንቶቻችንን ሥራ ወዳልን ይሆን? ‹‹በእኔ ደስ እንዳለህ ገብርኤል የሚባል መልአክ ባበሰረበት ቀን በዓሌን አክብረሃልና ስለ እኔ ሰውን ሁሉ ደስ አሰኝተሃልና እኔም ዋጋህን ልሰጥህ እወዳለሁ፡፡ አንተም በዚህ ዓለም በሰው ፊት እንዳከበርከኝ አከብር ዘንድ እወዳለሁ፡፡ እሷን ትለብስ አንድ ይህችን ልብስ እነሆ አመጣሁልህ፡፡ በላዩም ትቀመጥባት ዘንድ ይህንን ወንበር አመጣሁልህ፡፡ ከሰው ወገን አንድስ እንኳ ይህችን ልብስ ሊለብሳት በዚህችም ወንበር ላይ ሊቀመጥባት አይችልም፡፡ ነገሬን ያፈረሰ እሱን አጠፋዋለሁ›› ብላ ሰጥታው ከእሱ ተሰወረች፡፡

ደቅስዮስ ስምንት ቀን ስለ ፍቅሯ ማንም ያልጾመውን ጾም ጾሞ ለሰው ያልተሰጠ ጸጋ ከእሷ አገኘ፡፡ እኛስ ታላቁን የስደትዋን ጾም ብንጾም ምን እናገኝ ይሆን? እንዴትስ አመስግናን ይሆን? እንዴትስ ደስ ተሰኝታብን ይሆን? በሰው ፊት ጾምዋን ‹‹የፍቃድ ነው›› እያልን ከምናቃልል ለሌሎችም እንዳይጾም የስንፍና ምክንያት ሳንሆን አክብረን ብንጾም እሷም እንደ ደቅስዮስ ባከበረችን ነበር፡፡

ደቅስዮስ በጾሙ ያገኘውን የክብር ልብስና የክብር ወንበር ከእሱ ውጪ ለሚቀመጥበት እና ለሚነካው ሰው መከራ እንደሚመጣበት ተነግሮታል፡፡ እኛም የፅጌ ጾምን ስለ ፍቅሯ በመጾማችን የስንፍና ቃል ለሚናገሩን መከራ ይገጥማቸዋል፡፡ ከዚህ በኃላ አባታችን ደቅስዮስ የዚህ ዓለም አኗኗሩን በተጋድሎ ካበቃ በኃላ እመቤታችን ነፍሱን አቅፋ ከእሷ ጋር በተድላ ገነት አኑራዋለች፡፡

ከደቅስዮስ በኃላ የተሸመው ኤጲስ ቆጶስ እሱ ሳይለፋ ሳይደክም በድፍረት የደቅስዮስን ‹‹ልብስና ወንበሩን አምጡልኝ እኔም ሰው እሱም ሰው›› ብሎ አስመጥቶ በድፍረት ቢቀመጥበት ተቀስፎ ሞቷል፡፡ ኤጶስ ቆጶሱ እንደ አሁኑቹ እንደ እኛ ጾምን የማይሻ ግን በአፍ ብቻ አውርቶ ጸጋን ማግኘት ስለወደደ ሞተ፡፡ ጸጋ ደግሞ እንዲሁ አይገኝም፡፡

ወዳጆቼ እኛም በእመቤታችን በጾምዋ ከምንከራከር ‹‹የፈቃድ ነው›› እያለን ሰንፈን ሰውን ከምናሳንፍ ብንጾም ኖሮ፣ደቅስዮስ የሆነላትን ብንሆንላት ኖሮ እመብርሃን እንደ ደቅስዮስ ስንት ክብር እና ጸጋ ባሰጠችን፣በሰጠችን ነበር፡፡ ውድ የእመቤታችን ልጆች የደቅስዮስ የስምንት ቀን የፈቃድ ጾም ምን ያህል ክብር እንዳሰጠው አያችሁ? እኛማ የስደትዋ መታሰብያ የሆነውን ፅጌ ጾምን አርባ ቀን ብንጾመውማ ምን እናገኝ ይሆን? የሚፈትነን አጋንንት በራቀን፣የተቋጠረብን በእሷ ጸሎት በተፈታልን ነበር፡፡

ግን እዚህ ላይ አንድ ነጥብ ያዙልኝ እንዲህ ስል ፅጌ ጾምን በግሌ የአዋጅ ይሁን እያልኩ ሳይሆን የወዳጅ ይሁን ነው፡፡ ብንጾመው እጅጉን ተጠቃሚና አትራፊዎች ነንና፡፡ መከራ ወደ ምድር የመጣው በጾም ሳይሆን በመብል ነው፡፡ ወፎች የሚያዛቸው ወጥመዱ ሳይሆን ሆዳቸው ነው፡፡ የቻልን በርትተን ብንጾም ብሎም ሱባኤ ገብተን ብንጠይቃት መልስ አናጣም፡፡

አንዳነድ ሰነፎች ‹‹ፅጌ ጾምን ያል ጾመ ችግር የለውም፡፡ በመጾሙም አይጸድቅም ባለ መጾሙ አይኮነንም ›› ይላሉ፡፡ በእርግጥ ልክ ነው፡፡ ግን በእመቤታችን የፍቅር ሚዛን ላይ ተመዝኖ እንደ ገለባ መቅለል እንዳለ መርሳት የለብንም፡፡ እመቤታችን እኛን አገራችንን ብትወድ አስራት አድርጋ ተቀበለችን፡፡ እኛ ግን ለእሷ እንደ ደቅስዮስ መሆን አቃተን፡፡ የፍቃድ ነው እየልን ከመሳነፍ፣ጾመን ጸጋ ብናተርፍ ይሻለናል፡፡

‹‹መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው፣እግዚአብሔር ግን ይህንንም ያንንም ያጠፋቸዋል›› /1ኛ ቆሮ 6÷12-13/

‹‹ከእመቤታችን በጸሎት መልስ የምናገኝበት ጠቃሚ መንገዶች›› ከሚለው ከቁጥር አንድ መጽሐፌ ተወስዶ ተሻሽሎ የቀረበ፡፡

ጾሙ ለሀገራችን ለቅድስት ቤተ ክርስትያናችን ሰላም የሚወርድበት እኛም አንድ የምንሆንበት ያድርግልን።

አንብበው ሲጨርሱ ልጆችዋ ጽጌ ጾምን ጾመው በረከት እንዲያገኙ ሼር ያድርጉላቸው፡፡

መልካም ጾመ ፅጌ ይሁንልን!

መስከረም 25/1/17 ዓ.ም

ሎስ አንጀለስ

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

06 Oct, 07:04


#_የፈቃድ_ጾም_እያልን_ያልተጠቀምንበት_ፅጌ_ጾም

#_ፅጌ_ጾም_ብንጾም_እመቤታችን_እጅግ_ትወደናለች

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወለላይቱ ልጆች አዳርሱ

የወለላይቱ እመቤት ልጆች በቅድሚያ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን የፅጌ ጾም አደረሰን፡፡ ፅጌ ጾም የምንለው በአጭሩ የእመቤታችን የስደት ጊዜ ማለት ነው፡፡ ይህም ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 6 ቀን ያለው ነው፡፡ ስደት ሲነሳ ሐዋርያት በወንጌል የተነሳ ተሰደዋል፣ሞተዋል፡፡ ቅዱሳን ስለ ክርስቶስ ፍቅር በየገዳሙ ተሰደዋል፡፡ እነዚህና ሌሎችም ስለ ስሙና በስሙ ምክንያት ሲሰደዱ የእመቤታችን ስደት ግን ልዩ ነው፡፡ ተወዳጅ ልጅዋን ቅዱስ አማኑኤልን ይዛ ነው የተሰደደችው፡፡ ቅዱሳን በአምላካቸው ስም ሲሰደዱ እመቤታችን ደግሞ አምላክን ይዛ ተሰዳለች፡፡

እመቤታችን የተሰደደችው ምድራዊ ንጉስ ሄሮድስን ፈርታ ሸሽታ አይደለም፡፡ እሷማ ይዛው የተሰደደችው ሰማያዊ ንጉስ የሆነውን ሄሮድስን በዓይኑ እይታ ብቻ ከምድረ ገጽ የሚደመስስ አልፋና ኦሜጋ ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛው ነው፡፡ ደግሞም እናውቃለን ልጅዋ ሐናንያና ሰጲራን ሳይመታ የጣለ ነው፡፡ /የሐዋ 5÷1-10/ ምናልባት ከእነሱ በኃላ ይሆና ሰው ሳይመታ መውደቅ የጀመረው፡፡

ስድት የማይገባት የእኛ እናት ወላዲተ አምላክ የእኛን የኃጢአተኞችን ፈንታ ተሰደደች፡፡ እመቤታችን በመሰደድዋ ከገነት እንድንሰደድ ያደረገን ሰይጣንን አሳደደችው፡፡ እመቤታችን በስደትዋ ወቅት በቀላሉ የማይነገር ከሕሊና በላይና ልብ ሰማሪ መከራ ተቀብላለች፡፡ በዚህም ስደትን ተሰዳ ባርካ ሰጥታናለች፡፡ በተለይ በውጭ አገር ያላችሁ ወንድም እህቶቼ በስደታችሁ መከራ ሲገጥማችሁ ስደትን ከእናንተ በበለጠ የእግር ጥፍራ እስኪነቀል ሀገር ለሀገር የተሰደደችውን እመቤታችንን እያስታወሳችሁ ተጽናኑ በነገሮች ሁሉ እንድትረዳችሁ ተማጸኗት፡፡

ተወዳጆች ሆይ አሁን ስለ ስደት ለማውራት ሳይሆን በስደትዋ ምክንያት ታስቦ ስለሚጾመው ስለ ፅጌ ጾም ነው፡፡ በመሠረቱ ጾም ጾም ሲባል መጾሙ ላይ እንጨቃጨቃለን መብላቱ ላይ ግን እንስማማለን፡፡ ይህ የሚሆነው ለነፍሳችን ሳይሆን ለሥጋችን ስለምናደላ ነው፡፡ ለስንት ዘመን ስንበላ የከረምነው ዓሳ ‹‹ይበላል አይበላም›› እያልን የምንጨቃጨቀው የመጾም ሳይሆን የመብላት ፍላጎታችንን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ለዚህም ነው የዓሳ ጉዳይ ሐሳብ ሆኖብን ጎራ በመለየት በመብላት የተጠመድነው፡፡

ወዳጆቼ ይህ ችግራችን ገፍቶ በገና ጾም ቅበላ ላይ ገና ጾም የሚገባው ‹‹ህዳር 14 ነው አይደለም ህዳር 15 ቀን ነው የሚገባው›› እያልን የምንወዛገበው አንዱ የመብላት ፍላጎት ማሳያችን ነው፡፡ ብቻ ጾም ሲነሳ ጻር የሚሆንብን ሥጋን ለመብላት ካለን ሥጋዊ ፍቅር እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

እውቀትና ጥበብ እንጂ ሃይማኖት የሌላቸው የሰለጠኑት ምዕራባውያን እና ሌሎች ሀገራት ሥጋ ለሥጋችሁ ስጋት ነው ያስረጃል፣ጤና ይነሳል እያሉ በሚዲያ እያስተማሩ ብሎም እያስጠነቀቁ ሕዝባቸውን አትክልት ተመጋቢ ሲያደርጉት እኛ በሃይማኖት የምንኖረው ጠንካራ ጿሚ መሆን አቃተን፡፡

አዳም እና ሔዋን በገነት ሲኖሩ ይመገቡት የነበረው ሥጋ ሳይሆን አትክልት እና ፍራፍሬ ነው፡፡ በየትኛውም መጽሐፍ በገነት ሥጋ በሉ የሚል ተጽፎ አናገኝም፡፡ ይልቁንም ከገነት ከተባረሩና ወደዚህ ምድር ከወደቁ በኃላ ነው ሥጋን የበሉት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሥጋ ከበደል በኃላ የመጣ የሰው ልጆች ምግብ ሆነ፡፡

አንዳንዶቻችን ስናስተምር ‹‹የጾም ጥቅሙ ሥጋን ለነፍስ ለማስገዛት እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ ሥጋህን ከገዛህ በጥቂቱ ጾመህ ብትበላ ችግር የለውም›› እያልን የራሳችንን የጾም ድክመት ለሰዎች እያሳየን በጾም ሕይወት እንዳይጠነክሩ እናደርጋለን፡፡ አባቶቻችንና እናቶቻችን በየገዳሙ ከሚገባቸውና ከመጠን በላይ የሚጾሙት ሥጋቸውን ለነፍሳቸው ማስገዛት አቅቷቸው ሳይሆን ጾም ወደ ብቃት ደረጃ ሚያደርሳቸው መንገድ አንዱ መሆኑን ስለሚያውቁና ስለተጠቀሙበት ነው፡፡

አባቶቻችንን ከጾም ትጋታቸው የተነሳ በመጨረሻ ከተፈጥሮ ሕግ በላይ በመሆን እስከ አለመብላት ደረጃ ይደርሳሉ፡፡ በጾም ትጋታቸው ድካማቸው ተቆጥሮላቸው ከመልአክ እጅ ሰማያዊ ህብስትና ጽዋ እየተቀበሉ እስከ መብላት ይደርሳሉ፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ የሚደርሱት እንደ እኛ ‹‹አግዚአብሔር የማያውቀው የለም›› እያሉ በመብላት በመጠጣት ሳይሆን በጾም ተወስነው ነው፡፡

ጾም አንዱና ዋኛው የጸጋ መንገድ ነው፡፡ የትኛውንም ገድለ ቅዱሳን ብንመለከት አባቶቻቸን በልተው ሳይሆን ጾመው ነው የበቁት የተሰወሩት፡፡ ለዚህም ነው ጾሞ እንጂ በልቶ የበቃ ቅዱስ እስከ ዛሬ ያልተገኘው፡፡ ምናልባት ከበቁ በኃላ እንደ ፈለጉ ሊበሉ ይችላሉ፡፡

ተወዳጆች ሆይ ብዙዎቻችን እንደለመድነው እንደተማርነውም ‹‹ፅጌ ጾም የፍቅር ጾም እንጂ የአዋጅ ጾም አይደለም›› እንላለን፡፡ ልክም ነው፡፡ ግን ፅጌ ጾም የፍቅር ጾም ከሆነ ለምን በፍቅር አንጾምም? ‹‹አይደለም›› በምትለዋ አፍራሽ አማርኛ በፅጌ ፆም ስንቱ ሳይጠቀምበት ቀረ፡፡ ከሌሎቹ አጽዋማት እያሳነስነው ስንት የእመቤታችን በረከት ቀረብን፡፡ ዛሬ እንኳን በልተን፣ጾም ትተን ቀርቶ ጾመንም ጸልየንም ሰይጣን ከእኛ አልርቅ፣ፈተናችን አልላቀቅ ብሎናል፡፡

እመቤታችን ለእኛ እንደምትሆንልንማ ቢሆኖ ኖሮ ፅጌ ጾምን ብቻ ሳይሆን የተሰደዱትን የሚያረጋጋ ልጅዋን ይዛ መሰደድዋን፣ የተራቡትን የሚመግብ ልጅዋን ይዛ መራብዋን፣የተጠሙትን የሚያጠጣ ልጇን ይዛ መጠማትዋን በአጠቃላይ የእመቤታችንን እንግልት አስበን ከዓመት እስከ ዓመት በጾምን ነበር፡፡ ፅጌ ጾምን በአግባቡ በብንጾም በጾማችንም ፍቅራችንን ብንገልጽላት ከስደትዋ በረከት ተሳታፊ እንሆናለን እሷም የበለጠ ፍቅሯን ጸጋዋን ባሳደረችብን ነበር፡፡

ወዳጆቼ እውነት እንነጋገር ከተባለ ጾመ ነነዌና ጾመ ሐዋርያት የአዋጅ ጾም ነው፡፡ ጾመ ነነዌን የምንጾመው የታላቅዋ የነነዌ ሕዝብ ጾመው የእግዚብሔር መቅሰፍት ስለራቀላቸው እኛ እንደ እነሱ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዲርቅልን እንጾማለን፡፡ እነሱ በዳኑት እኛም እንድንድን እነሱን እያሰብን አብነት አድርገን እንጾማለን፡፡ ዛሬ ነነዌ የቀድሞ ስሟና ሃይማኖትዋን ይዛ የምትገኝ አገር አይደለችም በድሮ ታሪኳ እናስባታለን እንጂ፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ የወንጌል አገልግሎታውን እንዲባርክላቸው ስለጾሙ እኛም እነሱን አብነት አድርገን ሰኔ ጾምን እጾማለን፡፡ ደስም ይላል እጅግም መልካም ነው ቀኖናም ነው፡፡ ግን ለነነዌ ሕዝብ ከተደረገላቸው ነገር ለእኛ በእመቤታችን በኩል የተደረገልን የመዳናችን ምስጢር እና ውለታ አይበልጥም? በተለይ ለእኛ ለኢትዮጲያውያን፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን ሰጡን እመቤታችን ደግሞ የወንጌሉን ባለቤት ጌታን ወልዳ ሰጠችን፡፡ ዛሬ ታሪካቸው እንጂ ውለታቸውን የማናውቀውን የነነዌ ሕዝብን ጾም እዚህ አምጥተን በአዋጅ እየጾምን የእናታን የእመቤታችንን የስደትዋ መታሰብያ የሆነውን ፅጌ ጾምን አለመጾማችን ትዝብት አይሆንም?

እባካችሁ ‹‹ፅጌ ጾም የአዋጅ ጾም አይደለም እያላችሁ›› ቀለል አድርጋችሁ ከእመቤታችን በረከት እና ጸጋ አትራቁ፡፡ ምስጢረ ሥጋዌ፣ምስጢረ ቁርባን ስንል በእነዚ ድንቅ ምስጢራት እመቤታችን በዋጋ የማይተመን ሚና አላት፡፡ ለሰው ልጆችም የድህነት ምክንያት ናት፡፡ ይህን ውለታዋን ያወቁ አበው ፅጌ ጾምን በሱባኤ ሲጠቀሙበት እኛ ደግሞ ስንት ችግር እና መከራ ተሸክመን በመብላት እናሳልፋለን፡፡ እንዲህ ላለነው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሆዳቸው አምላካቸው ነው፣ክብራቸው ነውራቸው ነው፣አሳባቸው ምድራዊ ነው››

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

05 Oct, 15:58


https://youtu.be/eA5aRcsWFSA?si=qsFrl8fK3kfWohEZ

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

04 Oct, 14:57


https://youtu.be/PbEEn-IlQr8?si=bYGJsjnoUG9Irj90

12,599

subscribers

1,287

photos

90

videos