በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

@matter_of_facts


የ በውቀቱ ስዩምና አሌክስ አብርሃም አንድሁም ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ጽሁፎች ለማገኘት ከፈለጉ join አደርጉን

🙏እባካችሁ ለሌሎችም አጋሩልን🙏

@matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

21 Oct, 14:48


😂🤣🤣🤣😭😭A handsome man went into a hotel and asked to see the boss. When the boss came, the story began.

-The client: is room 39 empty?
-The boss: yes, sir.
-The client: can I book it?
-The boss: of course you can.
-The client: thank you.

Before going to the room, the client asked the boss to provide him with a black knife, a white thread 39 cm and an orange 73g.

The boss agreed though he was surprized at the weird things the client asked to have.

The client went into his room, he didn't ask for food or anything else.

Unfortunately for the boss, his room was next to room 39.

After midnight, the boss heard strange voices and noise in that client's room. Voices of wild animals and of utensils and dishes being thrown on the floor.

The boss didn't sleep that night. He kept thinking and wondering what might be the source of the noise.

In the morning, when the client handed the keys to the boss, the latter asked to see the room first.

He went to the room and found everything alright. Nothing unusual. He even found the thread, the black knife and the orange on the table.

The client paid the bill and gave the bellboys a very good tip and left the hotel smiling.

The boss was in a shock but he didn't reveal what he heard to the bellboys. In fact, he started to doubt himself.

After one year, the client showed up again. He asked to see the boss again. The boss was in a puzzle.

The client asked the same things: room 39, black knife, white thread 39cm and an orange 79g.

This time, the boss wanted to know the truth by all means possible. He spent a sleepless night, waiting for something to happen. After midnight, the same voices and noises started, this time louder and more indecipherable than the year before.

Again, before leaving, the client paid his bill and left a large tip on the table for the bellboys. The smile didn't leave his face.

The boss started searching for the meaning of everything the client asked to have. Why did he ask room 39? why the white thread? why the black knife??? In fact, the boss didn't arrive to any convincing answer to all these questions.

The boss now was eagerly waiting for the month of March, the month in which the client showed up.

To his surprise, on the first day of March, the same client showed up. He asked the same questions. Wanted to book the same room, wanted to have the same things as before.

The boss again heard the same noises, this time more louder than before.

In the morning, when the client was leaving the hotel, the boss apologized politely to the client and asked to know the secret behind the noises in the room.

-''If I tell you the secret, do you promise to never reveal it to anyone else?''
-''I promise I will never let anyone know''.
-''Swear''
-''I swear I won't reveal your secret''
So finally, the client revealed his secret to the boss.

Unfortunately, the boss was a sincere person. Until now he hasn't revealed his secret to anyone.

When he does, I will let you know... thank you for reading.

Do you want to come and bëãt me?

Me too, I'm looking for the guy who sent me this! 😆😆😳😳🕺🕺

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

20 Oct, 06:57


በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር። "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ሰው ፣ አህያ ወይም የተናኘ ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው" አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ ፍቅረኛው ናት ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች። መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣ የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

19 Oct, 19:39


መዘበራረቅ
(አሌክስ አብርሃም)

ዝብረቃ 1.

ተኝታችሁ ከተስማማችሁ በኋላ ተንበርክካችሁ "ታገቢኛለሽ?" ማለታችሁ ትንሽ የቅደም ተከተል ችግር አለበት ልበል? ለፆለት የሚንበረከከው ወንድ ከዚህኛው መንበርከክ በቁጥር እያነሰ መምጣቱ እንዳያስቀስፈን ጓዶች።

ዝብረቃ 2.

ፊልሙን ለመስራት 1.5 ሚሊየን ብር አወጣን ካላችሁን በኋላ የዋናዋ ገፀ ባህሪ ሰራተኛ እህት ልጅ ሁና የተወነችው እንስት የሽልማት መድረኮች ላይ 2.666 ሚሊየን ብር የፈጀ ቀሚስ(አውትፊት ይሉታል) ለብሳ የምትታይበት ሳይንስ ትንሽ ግራ ያጋባል። አንዳንዴ በውበትም በዋጋም ከፊልሙ የሚበልጥ ቀሚስ ስናይ የልብስ ሰፊወች አዋርድ እየመሰለን ተቸግረናል። ለነገሩ የትም አለም የተለመደ ነው።

የውጭ ዝብረቃ 3.

ኤለን መስክ የሚባል በቴክኖሎጅ ፍቅር ልብሱን ጥሎ ያበደ ሰውየ፣ የሆነ መሪ የሌለው መኪና እያስተዋወቀ ነው። በዓለም የመጀመሪያው ካለመሪ የሚንቀሳቀስ መኪና ነው አለ። እንኳን መኪና እእእእእ 😀 እሽ ይሁን። የሆነ ሆኖ መኪናው እናንተ ቤታችሁ ተቀምጣችሁ ብቻውን ሄዶ ኡበር /ታክሲ/ ይሰራል ይሸቅላል ሲል ነበር። እና ሮቦቶች የሰወችን ስራ አይነጥቁም? ሲባል ምናለ? ይንጠቋ! ሮቦቶች ይሰራሉ ሰወች ዘና ብላችሁ የኪስ ገንዘብ እየተሰጣችሁ ትኖራላችሁ። ከመጠግረር ምን አላችሁ? የምርጫ ቅስቀሳ የመሰለ ነገር።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

17 Oct, 10:19


እንደምን ሰነበታችሁ ወገኖቸ?
(አሌክስ አብርሃም)

ቆይ ቆይ በየተራ ተናገሩ ምንድነው ለመርዶ እንዲህ መጣደፍ?! ስለኑሮው ሰምቻለሁ። ሶስት ሽ ዘመን የተኛ ኑሮ ምን እንዲህ አስፈንጥሮ እንዳስነሳው አልገባህ ብሎኛል። መነሳቱን ይነሳ ትንሽ እንኳን ሳይረጋጋ አይኑን እንደገለጠ ልብሱን እንኳን ሳይለብስ ሩጫው።

ሰው ልሸኝ ብየ በነጠላ ጫማና በቱታ እዚች ጋ ወጣ ብየ ስመለስኮነው ሶስት የመሬት መንቀጥቀጥ፣ አንድ የመሬት መንሸራተት፣ ሁለት ከተማ የሚያካክሉ ታሪካዊ ሰፈሮች መፈራረስ፣ አንድ ታሪካዊ የፖለቲካ ፓርቲ መንፈሽፈሽ ፣ አራት " እንደጦር የሚዋጋ የዋጋ ማስተካከያ" ሁለት ፌክ እና ሶስት የእውነት ታዋቂ ሰዎች ሞት፣ቁጥር ስፍር የሌለው ጦርነት፣ ሁለት "እንኳን ደስ አላችሁ" ፣ ወደሁለት አገር አየር መንገዳችን እንዳትመጣብን ጭቅጭቅ፣ የግብፅ ጦር ተግተልትሎ እዚህ አፍንጫችን ስር መምጣት...ጨምሩበት! የዛሬን አያርገውና ይሄኮ በአራት ትውልድ እንኳ ሊከሰት የማይችል ነገር ነበር። የሆነ ሆኖ ምናባቴ ልሰራ ነው ወደ ሶሻል ሚዲያ የተመለስኩት እስከምል ደህና ተዘባርቃችሁ ጠብቃችሁኛል። እስኪ አብሬ ልዘባረቅ😀

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

16 Oct, 14:58


እንደ ሰርከስ
(በእውቀቱ ስዩም)

መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
ስልጠናው ሳይኖርህ ::

በሚያድጥ ዳገት ላይ ፥በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች፥ ሳይፎርሹ መቅለብ
-ደርዘን ሙሉ አሎሎ፥
አሎሎ ቢጠፋ ፥እሾህ ተደብልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ፥ማለፍ ሹልክ ብሎ፤

እንደ ህልም እሪታ፥ በሰለለ ገመድ
ባንድ እግር መራመድ፤

ይሄን ሁሉ አድርገህ፤ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሀል፥ አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እንደ በላኤ ሰብ፥ እጅህ ወንፊት ሆኖ፤

ምንም ባትታደል፥ አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ፥ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ-
ያልተራገፈ ጥርስ ፥ያልተሰበረ ቅስም
የድል ሳቅህን ሳቅ፥ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ፥ አጨብጭብ ለራስህ::

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

15 Oct, 17:34


በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡

ግን እኔ ብቻ ነኝ መንግስት ምንም እያመጡም የሚል እልክ ውስጥ የገባ የሚመስለኝ🤔

@matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

11 Oct, 17:55


ሰሞኑን የማነባቸው ዜናዎች .....

ኢትዮ ቴሌኮም ባንዳንድ አገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማስተካከያ አደረገ።

የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተደረገ።

መንግስት ዋጋ ሲጨምር ማስተካከል ነው የሚባለው ማለት ነው🤔

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

09 Oct, 13:35


እንውጣ
(በእውቀቱ ስዩም)

ወንድ ልጅ አይጣ! ምን አይጣ? ሚስት አይጣ! መልስ አይጣ! መውጫ አይጣ! ይልቁንም ገንዘብ አይጣ!

በቀደም እሁድ ለታ፥ ኤቲኤም ማሸኑ ላይ ሄጄ ተገተርኩ ፤ ዞር ብየ ታዛቢ መኖር አለመኖሩን ካረጋገጥኩ በሁዋላ” ሁለት መቶ ብር” የሚለውን አማራጭ ጨቆንኩት ፤ ማሽኑ ካርዴን መለሰልኝና “ ውድ ደንበኛችን፤ ለሁለት መቶ ብር ብለንማ በሰንበት መጋዘናችንን አንከፍትም! እባክዎ ባቅርቢያዎ ከሚገኝ የባንክ ዘበኛ ይበደሩ “ የሚል ጽህፈት ሰደደልኝ ፤

ከላይ ያለው ቀደዳ ሲሆን፥ ከታች ያለውን ግን የገሀዱ አለሜ ነጸብራቅ ነው!

ማርያምን ወንድ ልጅ አይጣ! ወንድ ልጅ በጣምም አያግኝ ! ሲያገኝ እንደኔ ጽጋበኛ ያለ አይመስለኝም! ከበቀደም ሁለት ቀን አስቀድሞ ልዝብ ሀብታም የሚያሰኘኝ ገንዘብ ሸቅየ ነበር፤ ሼክ አላሙዲን መክሰስ በሚበላበት ባርና ሬስቶራንት ገብቼ የምግብ ናዳ አዘዝሁ፤

ለማሳረጊያ ያዘዝኩት፥ ብርቱካን አናናስ እና ፓፓየ ጠረጴዛየ ላይ ተከማችቶ ያየ ሰው የሆነ የፍራፍሬ እርሻ የሚያስመርቅ የዞን ባለስልጣን ነው ምመስለው፤

ፈንጠር ብሎ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሰውየ ተቀምጦ ያየኛል( ስሙን በሌላ ቦታ የገለጽሁት ሲሆን እዚህ ላይ አጅሬ እያልሁ እቀጥላለሁ)

አጅሬ ፈገግ ብሎ ሲያየኝ ከቆየ በሁዋላ “ ይሄን ያህል በምግብ ተጎድተሀል እንዴ ?” ብሎ ለከፈኝ ፤

እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ፤ አዝመራው የተባለ ዘመዴ ትዝ ይለኛል፤ ድሮ ከትምርት ቤት ስንመለስ የሰፈር ጎረምሶች አስቁመው ነገር ሲፈልጉን እኔ ከድብድብ ለማምለጥ ያሉ የሌሉ ዘዴዎችን ሁሉ አሟጥጬ እጠቀማለሁ፤ ጎረምሶቹ በለስላሳ ምላሴ ተማርከው በሰላም ሊያሰናብቱን ከጨረሱ በሁዋላ አዝመራው እመር ይልና ክምር እንዳየ ዝንጀሮ አንዱ ላይ ይወጣበታል ፤ ከቴስታ አቅም እንኳ ሶሰት አይነት ቴስታ ያውቅ ነበር፤ ሸራፊ ቴስታ- ማይግሪን የሚያስይዝ ቴስታ እና ለኮማ እሚዳርግ መርዘኛ ቴስታ-

ጎረምሶችን አሸንፎ ሲያበቃ የሚሸልላት አትረሳኝም፤

“ዘራፍ አዝመራ ! ( ከስሙ መጨረሻ ያለችውን “ው” ለቤት ምታት እንቅፋት ስለምትሆን ያስወግዳታል)
ቁመቱ አጣራ
ልቡ ተራራ”

ለወትሮው ሰላማዊ የነበርኩት ሰውየ ድንገት የአዝመራው መንፈስ ተጋባብኝ ፤ ብልጭ አለብኝ! በዚያ ላይ ለሁለት ወር የkick boxing ስልጠና መውሰዴ ተራራም ባይሆን የሰፈር ዳገት የምታክል ልብ አጎናጽፎኛል፤

ከለካፊየ ጋር ትንሽ የስድብ ልውውጥ ካደረግን በሁዋላ “ልብ ካለህ እንውጣ ! “ አልሁት፤ እሱ ግን ቸል ብሎኝ ድራፍቱን መቀንደሉን ቀጠለ፤ እኔ በዛቻየ ቀጠልኩ፤ አጅሬው ሰማኝ ሰማኝና በመጨረሻ በረጅሙ ተንፍሶ እንዲህ አለ፥

“ እንዲያው አሁን፥ አስሬ እንውጣ የምትለኝ ፤ ልትመታኝ ነው ብርድ ልታስመታኝ?”


https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

06 Oct, 19:46


የዛሬው ነገር

የምወደው ጉዋደኛየና ጎረቤቴ ደወለልኝ ፤

“በውቄ የት ነህ?"

“የት ነህ?”

“ ቤት”

“እንዳለ የኮንደሚኒየሙ ነዋሪ ውጭ ወጥቶ ሲተራመስ አንተ ቤት ምን ታረጋለህ?”

“ ውጭ ምን አለ?”ስል ጠየቅሁት፤

“ የመሬት መንቀጥቀጡ አንተ ጋ አልደረሰም እንዴ?”

ከስልኩ አሰር ደቂቃዎች በፊት ሶፋ ላይ ቁጭ ብየ የቆየ መጽሀፍ እየገረብኩ ነበር፤ የተቀመጥኩበት ሶፋው ከስሬ ሲዋዥቅ ትዝ ይለኛል፤ ከሶፋው አጠገብ ጠርዝ ላይ ያስቀመጥኩት የውሀ የላስቲክ ጠርሙስ እንደ ሲወዛወዝ አይቻለሁ፤ ግን የመሬት መንቀጥቀጥ የሚለውን ሀሳብ እንዴት ላምጣው? ሰሞኑን አላግባብ ስለወፈርኩ ሶፋውን እየተፈታተንኩት የሚል ሀሳብ ውልብ አለብኝ ፤

የሰው ልጅ አእምሮ ሞትን የሚያስታወሱ ነገሮች በሙሉ መጨቆን ልማዱ ነው፤

ከሀያ ቀን በፊት ቻናሌ ላይ በጫንኩት “የሹፌሩ ማስታወሻ “ በተባለ ትረካ ላይ “ አሙዋረትህ አትበለኝና ሰሞኑን የምንሰማው የመሬት መንሸራተት ሊመጣ ላለው የመሬት መንቀጥቀጥ ቀብድ ነው “ የሚል ቃል አስፍሬ ነበር፤

በሰላም እንደርና ይሄንን የነብይነት ተሰጥኦየን እንዴት እንደምንጠቀምበት የምንወያይ ይሆናል፤

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

06 Oct, 18:40


#Update

" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።

በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

06 Oct, 18:22


ከ4.5 እስከ 4.9 ይሆናል በተባለ መጠን የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቷል

በበርካታ የከተማው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በስጋት ላይ እንደሚገኙ ተረድተናል።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

02 Oct, 03:28


የህልሜ በር ቁልፍ
(በእውቀቱ ስዩም)

ከመንገዷ ሸሸሁ
በማትውልበት ዋልሁ
በማታመሽበት፤ ሰፈር ውስጥ አመሸሁ
ፎቶዋን አክስየ
ፊት የሌለው ምስል በላዩ ላይ ስየ፥

“ይደምሰስ ስራዋ
ይወድም አሻራዋ ፥
የሰደድ ነበልባል እንደበላው ሰፈር
የመታሰቢያዋ አመዱ ይሰፈር
ወግ ታሪኳ ያክትም
ከንግዲህ በሁዋላ
እንኳን ወደ ቤቴ፤ ወደ ትዝታየ፥ ድርሽ አትላትም”

ብየ ፎከርኩና አልጋየን አነጠፍኩ
የሰራ አከላቴን፥ እንደ ጃንጥላ አጠፍኩ
አበባ ይመስል ፥ጉልበቶቼን አቀፍኩ፤

ታድያ ብዙም ሳይቆይ፥ በእንቅልፌ ስረታ
ኮቴዋን አጥፍታ
እንደ መንፈስ ገባች
ከትራሴ ግድም ከተማ ገነባች፤

ነግቶ ብንን ስል ፥ ያ ሁሉ ሙከራ
ከንቱ እንደ ሆን ገባኝ ፤ ሳይገድሉ ፉከራ
ሳይጥሉ ቀረርቶ
የህልሜ በር ቁልፍ ፥ መዳፏ ላይ ቀርቶ::
https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

29 Sep, 12:39


ለነገ መኖርህ ዋስትናህ……ገንዘብህ ! ጉልበትህ ! ቤተሰብህ ! ዝናህ ! እውቀትህ ! ብልሀትህም አይደለም ! እነዚህ ሁሉ አያድኑንም !!!

አዳኙ እሱ ያለ ምሶሶ ፤ ያለ ድጋፍ ያቆመህ ፈጣሪህ ነው ! ሁሌም ምን ይገርመኛል... ዘላለም ኗሪዎች የሆንን ፍጡራን ይመስል የክፋታችን ጥግ ፣ የተንኮላችን ጥግ ፣ የምቀኝነታችን ጥግ 🙆‍♂🙆‍♀

አንዱ መቃብር ሀውልቱ ላይ ምን አፃፈ አሉ..

የምቆይ ..! የምቆይ ..ይመስለኝ ነበር

@matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

24 Sep, 12:07


https://www.youtube.com/watch?v=7l1ZtRqaf8k

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

22 Sep, 16:21


የሰንበት ወግ
(በእውቀቱ ስዩም)

አካል ጉዳተኛን እንደ ደካማ ፍጡር መመልከት፥ ከባህላች አሉታዊ ገጽታዎች አንዱ ነው ፤ ግን እስቲ አስቡት ! ሙሉ አካል ያለው ሰው፥ ሙሉ አካሉን ምን ያህል ይጠቀማል? “ተጠቅመህ መልስ “ ይላል እቃ የሚያውስ ሰው! ከተፈጥሮም በለው ከፈጣሪ፥ የተዋስነውን አካል ሳንጠቀም የምንመልስ ጥቂት አይደለንም፤ ከህዋሳት አንዱን በአደጋ ወይም በተፈጥሮ ያጣ ሰው ፥ አንጎሉን እና ቀሪ ህዋሳቱን ሙሉ አካል አለኝ ብሎ ከሚመካው ሰው በላይ እንደሚጠቀም እናውቃለን፤ ለዚያ ነው፤ ዓለማችን ሆመርን የሚያክል ባለቅኔ ፥ ቬትሆቨንን የሚያክል ሙዚቀኛ ማፍራት ያልቻለችው፤

ቁምነገሩን ለማለዘብ የሚከተለውን የሰንበት ወግ ልጨምርበት፤

አምሳ አለቃ ገብረሀና(ማእረጋቸው ለዚህ ጨዋታ ሲባል ተቀይሯል🙂) ካንድ ቦታ ተነስተው ለጉዳያቸው ሲገሰግሱ ፥ መሽቶባቸው ፤ “የእግዜር እንገዳ ነኝ “ ብለው አንድ ቤት ተጠጉ፤

ባለቤትዋ መሸታ ቤት ያላት ወይዘሮ ናት፤ ውብ ደርባባ ሆና አንድ እግር ብቻ ነው ያላት ፤ ሌላውን እግሯን በአድዋ ጦርነት ወቅት ያጣችው ይመስለኛል::

መሸተኛው ሁሉ ተሰናብቶ ገብረሀና እና ሴትዮዋ ብቻቸውን ቀሩ፤ ሴትዮዋ ላምሳለቃ እራት አብልታ እግራቸውን አጥባ አነጠፈችላቸውና አልጋዋ ላይ ወጥታ ጋደም አለች፤ ገብረሀና ለመተኛት ቢሞክሩም እንቅልፍ አልጠጋቸው አለ፤ ድንገት የሆነ ከይሲ ሀሳብ መጣላቸው ::

ብድግ ብለው ወደ ሴትዮዋ አልጋ ተሳቡ፤ አልጋው ላይ ወጡና እንደ ሽቦ ተጠመጠሙባት፤ ሴትዮዋ “ አንቱ ቅሌታም ” ብላ አክብሮት ያልተለየው ስድብ ከወረወረችላቸው በሁዋላ ፥ ገፍተር አድርጋ ፥ ለሪጎሪ እንደ ሚመታ ኳስ አልጋው ጠርዝ ላይ አመቻቸቻቸው፤ ሴትዮዋ በደህነኛ እግሯ በሙሉ አቅሟ እርግጫ ስትሰነዝር የተዘጋ ስቴድየም የመበርገድ አቅም አላት፤ ይሁን እንጂ ገብረሀና ሽማግሌ እና የእግዜር እንገዳ መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት በስሱ ብትሰንብቃቸው እንደ ላስቲክ ኩዋስ ነጥረው ፥እንደ ናዳ ድንጋይ ተንከባልለው ግድግዳው ላይ እንደ ጥቅስ ተለጠፉ፤

ገብረሀና ፥ትንፋሻቸውን ሰብስበው ፥ አለመሞታቸውን ካረጋገጡ በሁዋላ ወደ ረገጣቸው እግር እየተመለከቱ እንዲህ ብለው ተራገሙ፤

“ የወንድምህን ቀን ይስጥህ ፤”

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

21 Sep, 12:20


#moonbix

|| ይህ የባይናንስ ፕሮጀክት ነው።

|| እንደ ሌሎች ኤርድሮፖች ብዙ ኮይኖች በአንዴ ለመሰብሰብ በጣም አስቸጋሪ ነው።

|| የተሻለ ዋጋ እንደሚኖረው ምንም ጥርጥር የለውም።

|| ብዙ ነጥብ ለመሰብሰብ ታስኮችን ስሩ እንዲሁም ጌም ተጫወቱ በየሰዓቱ 6 እድል ይሰጣል።

|| ቀድሞ የጀመረ 100% ተጠቃሚ ይሆናል። አሁኑኑ ብትጀምሩት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ።


ለመጀመር

https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startapp=ref_340268780&startApp=ref_340268780
Join the Moonbix Journey! Get 1000 Coins as a new player and stay tuned for exciting airdrops and special rewards from Binance!

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

17 Sep, 06:02


የአነቃቂ ንግግር ዲስኩር አቅራቢ እንዲህ ሲል ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር አደረገ፣

"የህይወቴ ምርጥ ጊዜያት ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ያሳለፍኳቸው ጊዜዎች ናቸው"

ይህንን ሲናገር ህዝቡ በድንጋጤ ክው አለ። ተናጋሪው የህዝቡን ስሜት ከተረዳ በኋላ እንዲህ ሲል ጨመረበት ፣

"ያቺ ሴት እናቴ ናት! " ብሎ ሲናገር ህዝቡ በፉጨትና በጭብጨባ አቀለጠው።

ይህንን ንግግር ያዳመጠው ሌላው ሰው ቤቱ ሄዶ ሊሞክረው ፈለገና ራት ላይ ለሚስቱ "የህይወቴ ምርጥ ጊዜያት ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ያሳለፍኳቸው ጊዜዎች ናቸው...." ብሎ ቀጣዩን ሃሳብ ከመናገሩ በፊት ሚስቱ በያዘችው የጋለ መጥበሻ አናቱን ብላው አሁን ሆስፒታል ይገኛል።

ባሻዬ!

1.የአንዳንድ አነቃቂዎችን ንግግር እንደ አደገኛ ጨዋታ በቤት ውስጥ አትሞክረው፣

2. copy ያደረግኸውን ንግግር በአግባቡ paste ካላደረከው አደጋው የከፋ ነው።

በአጭሩ Don't copy if you cannot paste.

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

16 Sep, 05:44


10 days left for hamsters listing

start if you didn't
https://t.me/hamSter_kombat_bot/start?startapp=kentId340268780

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

14 Sep, 03:47


ገላጣ
(በእውቀቱ ስዩም)

ዛሬ የተከበረውን የዓለም አቀፍ ራሰ በራዎች ቀን ሳልዘክር ወደ ምኝታየ ብሄድ የሶቅራጥስ አጽም ይወጋኛል፤

ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “በራሕ”የሚለውን ቃል ሲተረጉሙት-“ በራ፥ መላጣ፥ ራሰ ገላጣ፥ ከቦታው የታጣ፥ የራሱ ቁርበት፥ ሳንባና ጉበት የሚመስል “ ይላሉ (መጽሀፈ ስዋሰው ወግስ ፥ ገጽ 287፤ በትርጉሙ ውስጥ ያሉትን አሉታዊ ቃላት ብዛት ለተመለከተ አለቃ ባለ ሙሉ ጠጉር እንደሆኑ መገመት አያቅተውም፤

አለቃ “ራሰ ገላጣ “ ቢሆኑ ኖሮ “ራሰ በራ ” የሚለውን ሲተረጉሙ “ራሱ የበራለት፤ ታጥቦ የተወለወለ የንጉስ ብርሌ የመሰለ፥ መላጣ፥ ከፎረፎርና ከቅማል ስጋት ነጻ የወጣ “ብለው ሊተረጉሙት ይችሉ ነበር፤

በታሪካችን ትልልቅ ራሰ በራ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ነበሩ፤ ከጌቶች መካከል ብንጠቅስ፥ ራስ ስኡል ሚካኤል፥ አጤ ምኒልክ፥ ራስ ዳርጌ፥ መለስ ዜናዊ፥ ከደራሲ ፥ሀዲስ አለማየሁ፥ ጃርሶ ኪሩቤል ሞትባይኖር፥ መንግስቱ ለማ፥ ሊጠቀሱ ይችላሉ፤ ( ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ራሰ በራ ነው ወይስ የተሸጋሸገ ጎፈሬ ነው የሚለው በታሪክ ሲያከራክር ይኖራል )

“ለኔ እየሰጠችኝ ደረቁን እንጀራ
እስዋ በነካካው በራሰው ልትበላ"

የሚለውን ጥንታዊ ውስጠ ወይራ ዘፈን መናሻ አድርገን ብንናገር ፥ ሴቶች ከሚያበጥር ይልቅ የሚወለውል ወንድ የበለጠ እንደሚማርካቸው መረዳት አያቅትም፤

ስለ ጸጉር ጨዋታ በተነሳ ቁጥር ፈገግ የምታሰኝኝ ድምጻዊ አብነት አጎናፍር የተናገራት ናት፤ አብነት እንዲህ አለ፤

“ ከጥቂት ጊዜ በፊት ጸጉር ላስተክል ቱርክ ሄጄ ፤ ጸጉር የሚተከለው ሰውየ መላጣ መሆኑን ሳይ ትቸው ተመለስኩ"🙂

በዚህ አጀንዳ ላይ ሌሎች የከተማው ነዋሪዎች ያላቸውን አስተያየት ለመስማት ከፈለጉ ከታች የጫንኩትን ትረካ ያድምጡ ::

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

12 Sep, 06:57


ማን ያውቃል
(በእውቀቱ ስዩም)

የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ
ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ
ማን ያውቃል?

(ገጣሚ መንግስቱ ለማ)

ከሁሉ አስቀድሜ፥ እጅግ የሚያምር የበአል ስርአትን ለፈጠሩልን ካህናት አባቶች እና እናቶች ምስጋና አደርሳለሁ፤ ላይን ውብ የሆነውን አበባ፥ ለጆሮ የሚጥመውን ማህሌት፤ ለአፍንጫ ጣፋጭ የሆነውን እጣን እና የሚያውድ ሳር ሁሉ አግኝተን የምናጣጥመው በበአል ነው፤

ይገርማል!

“የማይታረድበት አመትባል እና ጋቢ የማይለብስ ባል ግርማ ሞገስ የላቸውም “ ይል ነበር ጋሽ አሽኔ፥ የሰፈራችን ሸማኔ -፥የጋቢው ምርት የጠበቀውን ያክል አልሄድለት ሲል፤

ለዚያ ነው ትናንት እንዃን አደረሳችሁ ከማለት የተቆጠብኩት፤ በውነት ትናንትና ' እንኳን ተቃረባችሁ እንጂ እንኳን አደረሳችሁ” ለማለት የማይቻልበት ሁኔታ ላይ ነበርን፤

በዚህ አገር ታሪክ ውስጥ፥ ከተመዘገቡት ማሰቃያ ስልቶች አስከፊው “ወፌ ይላ” መገረፍ ይመስለኝ ነበር፤ ከፊትለፊትህ ባለው ቴሌቪዥን የአውዳመት የሙዚቃ ቪድዮ ውስጥ ፥ አጋም የመሰለ ያዶሮ ወጥ በትልቅ ሰታቴ ውስጥ ሰንተከተክ እያየህ በጦም ፍርፍር ማሳለፍን የመሰለ ስቃይ የለም፤ ለማንኛውም፥ በቀጣይም እንዲህ ያለ ሁኔታ ሊደገም ስለሚችል እነ ደመረ ለገሰ፥ የአመት በአል የሙዚቃ ቪድዮ ስትሰሩ ፥ የሱፍ ፍትፍተና ስንግ ቃርያን ማካተትን አትርሱ፤

ዘልዛይመር ያልያዛችሁ የኔ ዘመነኞች እንደምታስታውሱት፥ ልጆች እያለን በእንቁጣጣሽ መባቻ፥ የአበባ ስእል ቤት ከቤት እያዞርን ፍራንካ እንሰበስብ ነበር፤ እኔ ከፍተኛ የስእል ፍላጎት ቢኖረኝም፥ አበባ መሳል ብዙ አይሳካልኝም፤ የሰፈራችን አባዎራዎች የዘረጋሁላቸውን ወረቀት ይቀበሉና ፥የመርዶ ደብዳቤ የሚያነቡ ይመስል ፊታቸውን ዝፍዝፍ አድርገው ይገረምሙኛል፤ ሽልንግ ይሰጠኛል ብየ ስጠብቅ “ አሁን ይሄ አበባ ነው አሜባ ?” የሚል ዘግናኝ ሂስ የሚሰጠኝም አይጠፋም ፤ አጋነንከው በሉኝና፥የኛ ሰፈር ወላጆች ልጆቻቸውን "አበባ" ብለው መሰየም ያቆሙት የኔን ስእል ካዩ በሁዋላ ይመስለኛል፤

በተቃራኒው ደስታ የሚባል ጉዋደኛ ነበረኝ፤ ደስታ የንቁጣጣሽ ስእል ሰሎ ቤት ለቤት ሲያዞር እናቶች ተቀብለው ፥ስእሉን አይተው ያንን የጥይት ማስቀመጫ ሳንዱቅ የሚያክል ግንባሩን ስመው ፤ ብር ይሰጡትና ስአሉን በፍሬም አድርገው ከዋናው በር ፊትለፊት ባለው ግድግዳ ላይ ይሰቅሉታል፤ “ስታድግ አፈወርቅ ተክሌን የምትተካ ሰአሊ ይወጣኻል” የማይለው ሰው አልነበረም፤
በቅርብ የሆነ ጊዜ ሳገኘው የዲሽ ጥገና ባለሙያ ሆኖ አገኘሁት፤

የልጅነታችንን አስንተን ሰናወጋ በትካዜ እንዲህ አለ፤

“ የስእል ችሎታየ የሆነ ጊዜ ላይ ጥሎኝ ቢጠፋም፥ ከቤት ወደ ቤት የሚያዞረኝ አባዜ ግን አብሮኝ ቀጥሏል"

“የመስቀል ወፍና ትልቅ ዲፎ ዳቦ
የበአል ቀንና ማንአልሞሽ ዲቦ
ቀጠሮ እንዳላቸው ማን ያውቃል?

( ገጣሚ፥ መንግስቱ ሀይለማርያም)

መልካም አውዳመት ፤ በጎ ዘመን ይሁንላችሁ!

https://t.me/matter_of_facts