የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

@yefkrtarik


🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹


➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1

Since 2011 E.C.

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

21 Oct, 16:14


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 32...🌹
.

"ልክ እኔ እና አንቺ የአልጋላይ ጫወታውን እንደጨረስን
ያ ጠይሙ የውዝዋዜና የዳንስ ዳኛ ብድግ ብሎ አንቺን አንቺን ብቻ እያየ
"ዋው ዋው  ዋው " እያለ ያጨበጭብና ቁጭ ይላል።
ቁጭ እንዳለ ማይኩን ብድግ አድርጎ•••የሚገርም ኬሮግራፊ፣ የተጠናና እና ውበት ያለው እንቅስቃሴ፣ የሚገርም ወገብ ፣ ዋው በአስር ደቂቃ ውስጥ  ሁሉንም የጭፈራ አይነቶች ማሳየት መቻል ድንቅ ብቃት ነው።
ለብዙዎች እስቴጁን ተጠቀሙበት ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ ነው በተግባር ያሳየሽልን።
አልጋውን ማለቴ መድረኩን አጠቃቀምሽ ልዩ ነበር፣ ያልጨፈርሽበትን የአልጋ ክፍል ማግኘት ይከብዳል።በተለይ መሀል አከባቢ እሱ ቁጭ እንዳለ አንቺ እሱ ላይ ተቀምጠሽ ያሳየሽን እንቅስቃሴ ገራሚ ነው።
እንደዛው እንደተቀመጥሽ ወደላይ ወደላይ እያልሽ  የአፋሮችን ባህላዊ ውዝዋዜ ስትስትጫወቺው ያየ ሰው አልጋውን ማለቴ መድረኩን አጠቃቀምሽ ልዩ ነበር፣ ያልጨፈርሽበትን የአልጋ ክፍል ማግኘት ይከብዳል።በተለይ መሀል አከባቢ እሱ ቁጭ እንዳለ አንቺ እሱ ላይ ተቀምጠሽ ያሳየሽን እንቅስቃሴ ገራሚ ነው።
እንደዛው እንደተቀመጥሽ ወደላይ ወደላይ እያልሽ  የአፋሮችን ባህላዊ ውዝዋዜ ስትስትጫወቺው ያየ የሰው ልጅ ቁጭ ብሎም መዝለል ይችላል እንዴ? ማለቱ የማይቀር ነው።ወድያው ከአፋርኛ ወደ ሸጎዬ ቢት ቀይረሽ ግራ ቀኝ ዘንበል ቀና ስትይ ልዩ ትእይንት ነበር ።
እሱን አይተን ሳንጠግበው እንቅጥቅጥን ታስነኪው ጀመር፣ እዛ ላይ እንደተመሰጥን ወደ ጀርባሽ ድንገት ዝንጥፍ ብለሽ ስትታጠፊ እኔ በእውነት ወገብሽ ቅንጥስ ያለ ሁላ መስሎኝ ልጮህ ነበር።
ቃልዬ ሳቋን መቆጣጠር እያቃታት እያቃረጠች ብታስቸግረኝም  ስቃ ጋብ እስክትል እያረፍኩ የዳኛውን ማብራሪያ   ቀጠልኩ•••

አንድ ሳልነግርሽ ማለፍ የማልፈልገው ድንቅ እንቅስቃሴ  መጨረሻ አከባቢ አንቺ ከስር ሆነሽ እሱን ከላይ ካደረግሽው በኋላ እግሮችሽን ወገቡ ላይ አጠላልፈሽ ያሳየሽው አለም ነው ።
እሱን አላላውስ ቢለውም ድንቅ ፍትወቶግራፊ የታየበት የዳኞቹን እና የ ተመልካቾችን ስሜት ሰቅዞ  የሚይዝ ድንቅ ፐርፎርማንስ ነበር።
በዚሁ ቀጥይ ነገ ትልቅ ቦታ እንደምትደርሺ አልጠራጠርም ።
ይልና ባንዴ ፊቱን ዘፍዝፎት ወደኔ ይዞራል ከዛ እንዲህ ይለኛል •••
" ወዳንተ ስመጣ በጥቅሉ የሷ እንቅስቃሴና ፍጥነት ከጠበቅከው ውጪ የሆነብህና ግራ የተጋባህ መሆኑን ነው ያስተዋልኩት።
ለዚህ ማሳያው ዙሩ እየከረረ  እና እየተጋጋለ ሲመጣ አንተም እንደኛው በሷ ሁኔታ የተገረምክ በሚመስል ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴያችሁን ቁጥጥር  አንቺ እንዳሻሽ እንደፈቀድሽ አድርጊኝ ብለህ ለሷ በመተው ለመሳተፍ ሳይሆን እንደኛው ለመዳኘት የመጣህ ይመስል በአድናቆት ስትመለከታት ማየቱ በቂ ነው" ይለኛል ።
ከዛ የድምፅ ዳኛው  ማይኩን ይቀበልና
ማነሽ ቃልኪዳን እኔ ላንቺ አድናቆቴን የምገልፅበት ቃል የለኝም።
በጥቅሉ ስታሰሚን የነበረው በስሜት የበለፀገ ድምፅ  እንደ እንቅስቃሴው የሚፈጥን እና የሚረግብ ሪትሙ ልክክ ያለ ፣ ቴምፖው የተመጠነ ለጆሮ የሚጥም ድምፅ ነበር።
ወደ ኤፍሬም ጋር ስመጣ  እእእ ኤፍሬም አንተ ጋር የነበረው ነገር በጣም ግራ የሚያጋባ ግራ የገባው ድምፅ ነው ።
እኔ የምታወጣው ድምፅ ማጓራት ይሁን ማቅራራት በፍፁም ሊገባኝ አልቻለም። እንቅስቃሴው ትንሽ ከበድ ብሎህ ስለነበር ድምፅህን አዛብቶታል።
ላንተ ያለኝ ምክር ሰፈራችሁ ጫካ አልያም ተራራ ካለ ባይኖርም ከከተማ ወጣ ብለህ  ሰው ወደማይኖርበት ጫካ በመሄድ ጮክ ብልህ  የድምፅ (ቮካል ) ልምምድ በመስራት ይህንን አባጣ ጎርባጣ ድምፅህን ልትሞርደው ይገባል " ይለኛል።
"ካካካካ አባጣ ጎርባጣ ድምፅ ግን ምን አይነት ነው ቃልዬ?" ስላት ቃልዬ እየሳቀች ስለነበር መልስ አልሰጠችኝም።
"ከዛ ሶስተኛው ዳኛ ደሞ•••" ብዬ ልቀጥል ስል•••
"ኧረ ኤፍዬ በቃህ መሳቅ ደከመኝ  ኪኪኪኪ በእውነት ሆዴን አመመኝ በቃህ" አለችኝ።
ከወንበሬ ላይ ተነስቼ ወደ አልጋው በመሄድ ቃልዬን አቅፊያት ተኛሁ።

እሁድ አመሻሹ ላይ ወደ ድሬ ተሳፈርን። የሚኒባሱ የመጨረሻ ወንበር ላይ ያለነው እኔና ቃልዬ ብቻ ነን።
ሚኒባሱ ገና አልሞላም ከመናሀሪያ ቢወጣም ከመንገድ ላይ ለሞሙላት
"የሞላ የሞላ አወዳይ፣ ሀሮማያ ፣ደንገጎ ፣ ድሬ ዳዋ ሁለት ሰው" እያለ ይጣራል።
ውስጤ እርብሽብሽ አለብኝ ።  ከቃልዬ ጋር ድሬ ስንደርስ መለያየታችን ግድ መሆኑን ሳስበው አ
ስጠላኝ።
"ቃልዬ ተነሽ እንውረድ !" አልኳት እጇን ያዝ አድርጌ እየተነሳሁ።
"ምነው ኤፍዬ ምን ረስተህ ወጣህ " እያለች ተከተለችኝ።
"ሀይ በቃ ሊነሳ ነውኮ ግቡ እንጂ አለ ረዳቱ"
"ዝም ብዬው የቃልዬን ክንድ ይዤ እየጎተትኩ  ትንሽ እንደተራመድን
" አንተ ልበ ቢስ ምን ረስተህ ነው ?  ለምንድን ነው የወረድነው?" አለችኝ።
"ምንም አረሳሁም ቃልዬ"
"እና ለምን ወረድን ይሄም በግድ ነው የሞላው ሌላ እናገኛለን ኤፍዬ ?"
"ወደድሬ መሄድ አስጠላኝ ቃልዬ !   ድሬ ዳዋ ገና ግብት እንዳልንባት አንቺን ከኔ ነጥቃ በመውሰድ እዛ ግቢ ውስጥ እንደምትወረውርሽ ውል ሲልብኝ መሄድ ቀፈፈኝ! "አልኳት  አይን አይኗን እያየሁ።
ቃልዬ ማውራት ብትፈልግም ማውራት አልቻለችም እንባ እየተናነቃት  ሲፈታተናት ዝም ብላ  አቀፈችኝ። አጥብቃ አቀፈችኝ።
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 33 ይለቀቃል🌹
           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

18 Oct, 16:25


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 31...🌹
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል
.
.
በተለያየ አጋጣሚ ሁለቴ ከሞሞካከር በስተቀር እኔ በዚህ ዙርያ ብዙ ልምዱ እንዳልነበረኝ ባልክድም ያ ሙከራ እንጂ ትግበራ ለመባል እንኳን የማይበቃ መተሻሸት እንደነበረ ያመንኩት አሁን ነው።
ቃልዬ እያገለበጠች ስታንገላታኝ  በተለይ አንደኛዋ ከዚህ ቀደም ያጋጠመችኝ ሴት ትዝ አለችኝ ። ምን ሆና ነው ግን እንደዛ አይኗን ጨፍና የተጋደመችው? ማደንዘዣ መርፌ ተወግታ ነው እንዴ የመጣችው?  አልኩ።
ቃልዬ ትለያለች ። ወንድ ነኝ እኔ መብለጥ ነበረብኝ እንዴት እበለጣለሁ ብዬ በአጉል ትእቢት ደስታዬን መቀነስ አልፈለኩም።
ሁልግዜ ወንድ መብለጥ አለበት የሚል ነገር በአንዳንዶቻችን ወንዶች ጭንቅላት ውስጥ ያለ ኩፈሳ እንጂ ከተግባሩ ጋር ሲነፃፀር እውነቱ ሌላ የሚሆንበት አጋጣሚ እንዳለ እንደቃልዬ አይነት ተውረግራጊ የአልጋ ንግስቶች ያጋጠሟቸው ወንዶች መች ይክዳሉ።
እኔም መበለጤን አምኜ ስታጋድመኝ ስጋደም ፣ ስታስቀምጠኝ ስቀመጥ፣ ስታስቆመኝ ስቆም ፣ ስትንጠለጠልብኝ ስሸከም፣ ስትጨፍርብኝ ሳስጨፍር ወገቤ ተንቀጠቀጠ፣ ጉልበቴም ተብረከረከብኝ።
ሁለት እጄን ወደላይ ሰቅዬ •••
" ቃልዬ ገደልሽኝኮ የዕረፍት ሰአት የለም እንዴ ?"ልል ትንሽ ነበር የቀረኝ። እየተሽከረከረችና እያሽከረከረች ልኬን ስታሳየኝ እኔም እሷም ውስጥ የነበረው የደስታ ሲቃ ልዩ ነው።
እና እኔ ነኝ ቃልዬን ለምን ልጃገረድ አልሆንሽም ብዬ ለመደንፋት ሞራል ያለኝ?።  ከድንግልናዋ ምን ጉዳይ አለኝ። ኧረ ምንም ። ብራንባር ቅብርጥሴ ኧረ የታባቱ ። ደሞ እሱ ኖረ አልኖረ ብዬ ልጨነቅ እንዴ። ጥንቅር ይበል ።
   ብር አንባር ድሮስ  ምን ያደርጋል ?እንደዉም ድንግልናኮ የወንዶች  ባላንጣ ነው፣ የምሬን ነው  ድንግልና  ምቀኛ ነገር ነው።
እንደአመፀኛ ሚዜ በር ዘግቶ አላስገባም ሰርገኛ አርፈህ ተኛ እያለ ከመከላከል በቀር ምን ስራ አለው? ምንም።
እና እባክህ አሳልፈኝ በሞቴ ልግባ አልግባ እያልኩ  ከሱ ጋር ግብግብ መግጠም  ምን ያደርግልኛል? ምንም።
ኧረ እንኳንም አልኖረ ፣ ድንግል ሆና ዝም ብላ በጀርባዋ ተንጋላ በል ከቻልክ ግባ ካልቻልክ ስራህ ያውጣህ ብትለኝና  ነገር አለሙን ሁሉ ለኔ ብትተወው ምን ይውጠኛል?እንደዛች ማደዘዣ መርፌ የተወጋች እንደምትመስለው ልጅ ሳትገላበጥ ሰትላወስ አይኗን ጨፍና በመጋደም ኧረ አሳመምከኝ ቀስ በል እንጂ ኤፊ አመመኝ እኮ እያለች የአልጋ ላይ ትራፊክ ሆና ብታሳቅቀኝ መሳቀቅ እንጂ ምን አተርፋለሁ?።
ልጃገረድ ብትሆን ለሷ ትልቅ ነገር ሊሆን ይችላል። ለኔ ግን  ከሱ ጋር ትግል ገጥሜ ላቤን ከማንቆርቆር በስተቀር ምንም እንደማይሰራልኝ  ያሳመነችኝ እራሷ ነች ።
ድንግል ከምትሆን ይልቅ እንዲህ እላዬ ላይ እንደቬንትሌተር እየተሽከረከረች አለሜን ብታሳየኝ እንደሚሻለኝ ያወቅኩት በሌላ በማንም ሳይሆን በቃልዬ ነው።
ይህንን ደስታ ድንግልና ኬት አባቱ አምጥቶ ይሰጠኛል።
ትርፉ ድካምና ሰቀቀን ብቻ ።ኧረ ወደዛ እንኳንም ቀረብኝ ።
ቃልዬ ፍቅር ሲይዝ እንዴት እንዴት እንደሚያደርግ ብቻ ሳይሆን ፍቅር እንዴት እንደሚሰራም ዛሬ አስተማረችኝ።
ቃል ለኔ የ ፍቅር አስተማሪዬ ነች ። እኔ ደሞ ተማሪዋ ።
ይህን ሁሉ  የምለው ቃልዬ መታጠቢያ ቤት ገብታ እኔ ደግሞ  ዝብርቅርቁ የወጣው አልጋ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ያንቃቃችውን  ወገቤን እያሸሁ ነው  ።
ታጥባ እንደጨረሰች አጠገቤ መጥታ ጋደም አለችና
"ምን እያሰብክ ነው ጣራ ጣራ የምታየው ?" አለችኝ አንገቴን እየሳመችኝ።
"ያሯሯጥሻት ልቤን እስክትረጋጋ እየጠበኳት ነው"
"ኪኪኪ እሺ ሌላስ?"
"ሌላስ ምን ቃልዬ?"
"ሌላስ ምን እያሰብክ ነበር?"
"ሌላ ሌላ ሌላ  ደሞ ያንቺ  ፍቅረኛ በመሆኔ ምን ያህል እድለኛ እንደሆንኩም እያሰብኩ  ነበር"
"ሌላስ?"
"ሌላማ ቃልዬ እንዲህ ስብርብር ያደረግሽውን ኤፍሬም እንዴት እንደምታድኝውና ይዘሽው ወደድሬ እንደምትመለሽ እያሰብኩ ነበር"
"ኪኪኪ•••ስንደጋግምበት ይለቅሀል እሺ ኤፍዬ" ብላኝ እርፍ።
"በለው በለው ያልቅልሃል ነው ይለቅሀል?" አልኩ የእውነት ደንግጬ።
ቃልዬ ከልቧ ሳቀችና
"እና ሌላስ ምን አሰብክ ምን ተሰማህ ደስ ብሎሀል ኤፊዬ?"
እየደጋገመች ሌላስ ሌላስ የምትለኝ ድንግል ነሽ ብዬ ጠብቄ ነበር እንድላት ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ።
ብላት ምን ሊሰማት እንደሚችልም አሰብኩ።ባይከፋትም የጠበኩትን ስላጣሁ ቅር ያለኝ ሊመስላት ስለሚችል እንደዛ ማለት አልፈለኩም።
"በጣም ደስ ብሎኛል ቃልዬ. ፣ ሌላ ነገር ግን ምን እንዳስብኩ ልንገርሽ?" አልኳት።
" እስቲ ንገረኝ ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ቀና ብላ በመቀመጥ አይን አይኔን እያየች
"የዳንስ፣ የውዝዋዜና፣ የመዝፈን ተሰጥኦ ያላቸውን በየቴሌቭዥኑ የሚዳኙት ዳኞች አሁን እኔና አንቺ እዚህ አልጋ ላይ  ከደቂቃዎች በፊት  ያደረግነውን ግብግብ
ተመልክተው የዳኝነት አስተያየት እንዲሰጡ ቢጠየቁ ምን ሊሉ  እንደሚችሉ እያሰብኩ ነበር  ስላት•••
" ኪኪኪ ምን ስትል አሰብከው በጌታ ! ፣  እስቲ ምን የሚሉ ይመስልሀል ኤፍዬ? አለችኝ እየሳቀች።
"ምን እንደሚሉ ልንገርሽ? ••• ቆይ ልክ እንደነሱ  ፊት ለፊት ወንበር ላይ ተቀምጬ ነው የምነግርሽ እንደውም" እያልኩ ገና የቀጨችውን ወገቤን ደግፌ ስነሳ ነበር ሁለት ትራስ ደራርባ እግሮቿን ወደፊት ዘርግታ  ግርግዳውን በመደገፍ መሳቅ የጀመረችው።
ክፍሉ ውስጥ ያለውን ወንበር ወደ ክፍሉ በር አከባቢ ወስጄ በቃልዬ ትይዩ ተቀመጥኩና•••
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 32 ይለቀቃል🌹
   https://vm.tiktok.com/ZMhPw4syW/        

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

15 Oct, 16:27


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 30...🌹
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል
.
.
ልክ ወደግቢው ስንቃረብ ግን የሁለታችንም አንደበት ተዘጋ። ተመካክረን በቃ ዝም እንበል የተባባልን ያህል አልጋ ወደያዝንበት ግቢ ልንደርስ ትንሽ እርምጃዋች ሲቀሩን በመካከላችን ፀጥታ ሰፈነ።
እንደተቃቀፍን በፀጥታ እራሳችንን ማዳመጥ ጀመርን። የልብ ትርታዬ ከእጥፍም በላይ  ሳይሆን አይቀርም ምናልባት የቃልዬም እንደዛው ሆኖባት እሱን እያዳመጠች ይሆናል ዝም ያለችው። ምነው ዝም አልክ ምነው ዝም አልሽ እንኳን ለመባባል አልፈለግንም። ለምን ዝም ፀጥ ረጭ እንዳልን ሁለታችንም ገብቶናል ። የግቢውን በር አንኳኳሁ በሩ ስር ያለው ጥበቃ ወድያው ከፈተ። አሁንም በፀጥታ ወደ ክፍላችን አመራን።
የክፉሉን በር ከፍተን እንደገባን በውስጥ በኩል በሩ ላይ አስደግፌ አየኋት የቃልዬ አይኖች ተስለመለሙ  ከንፈር ለከንፈር ተናነቅን።
ቃልዬ የላይኛውንም የስረኛውንም ከንፈሯን ገጥማ አፌ ውስጥ ስትሞጅረው አየር ማስወጣት የለ አየር ማስገባት መንገዱ ተዘጋ።ትንፋሽ አጠረን።
ከንፈሮቻችን ሳይላቀቁ እንደተጣበቁ እጄን ወደ ፁጉሯ ልኬ ፀጉሯ ላይ የተሻጠውን የፀጉር ማስያዣ መዘዝኩት ። ፀጉሯ እኔም እሷም ፊት ላይ ተነሰነሰ። ሳንላቀቅ ወዳልጋው እየተጠጋን የአንድ እጄ ጣቶች ፀጉሯ መሀል እየተርመሰመሱ የሌላኛው እጄ ጣቶች ወደጀርባዋ አምርተው  የቀሚሷን ዚብ ከላይ ከትከሻዋ ጀምሬ እስከ ቀጭኑ ወገቧ ድረስ ተረተርኩት። ቀሚሷ እየተንሸራተተች ወርዳ ቀጭን ወገቧን ተሻግራ  ዳሌዋ ላይ ጉዞዋ ተገታና እንደጉርድ ቀሚስ  ተንጠለጠለች።
የቀሚሷን መሄድ ተከትለው ጡቶቿ ከጡት ማሳይዣዋ አፈትልከው ለመውጣት አመፅ ላይ ያሉ ይመስል  እንደተወጣጠሩ ሳያቸው ልቤ ዝቅ አለች።
ከንፍሯ ከከንፈሬ አፍንጫዋ ከአፍንጫዬ  እንደተያያዙ የፍቅርን ረቂቅ ጣእም በትንፋሽ እና በፈሳሽ መልክ እየማጉ በቃልዬም በኔም ሰውነት ውስጥ ሲያሰራጩ የፈጠሩት ሙቀት መንደድ ጀመረ።
ምላሷ ላይ የሚንከባለለውን ምላሴን  ከምላሷ እያፋታሁ ዝቅ ብዬ አንገቷን ከፍ ብዬ ጆሮዋን ስስማት መላ አካላቷ በንዝረት ሲርገፈገፍ ይታወቀኛል።በፍቅር ሲቃ  እየቃተተች የምታወጣው ድምፅ አቅሌን አሳጣኝ ።
በስሜት ማእበል እየቀዘፉ ወደ ጀርባዋ ያመሩት እጆቼ የጡት ማስያዣዋን ፈትተው ለቀቁት። በከፊል ብቅ ያሉት ጡቶቿ ነፃነታቸውን አውጀው  ከደረቴ ጋር ለመፋለም የተቀባበሉ ይመስል ወደ ፊት ተቀሰሩ።
ወደጀርባዬ ገፋ አድርጋኝ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ከላይ የለበስኩትን ነጭ ሸሚዝ ቁልፎች ስትከፍት ፊት ለፍት እያየኋት ዋጣት ዋጣት የሚል ስሜት የፈነቀለው ልዩ ግፊት ሁለመናዬን ናጠው።
ሸሚዜን አውልቃ አሽቀንጥራ ጣለችውና ከደረቴ ጀምራ በከንፈር በምላሷ እያራሰች በአንገቴ በኩል ወደላይ ተሻግራ ከንፈሬን ስትጎርሰው የጋለው ሰውነቴ እንደኤርታሌ እስተ ጎመራ ፈንድቶ  መፍለቅለቅ ጀመረ ።
ብድግ አድርጌ አልጋው ላይ በጀርባዋ አንጋለልኳት። እግርና እጆቿን

ሸሚዜን አውልቃ አሽቀንጥራ ጣለችውና ከደረቴ ጀምራ በከንፈር በምላሷ እያራሰች በአንገቴ በኩል ወደላይ ተሻግራ ከንፈሬን ስትጎርሰው የጋለው ሰውነቴ እንደኤርታሌ እስተ ጎመራ ፈንድቶ  መፍለቅለቅ ጀመረ ።
ብድግ አድርጌ አልጋው ላይ በጀርባዋ አንጋለልኳት። እግርና እጆቿን ግራ ቀኝ ከፋፍታ፣ የተቀሰሩት ጡቶቿ በትንፋሿ ልክ እላይ ታች እያሉ ፣  አይኗን ከደን ከፈት እያደረገች ወደላይ ስትመለከተኝ አልጋው ጠርዝ ላይ ቆሜ እየተመለከትኳት   የፍቅር አውሎንፋስ ከቆምኩበት ወደላይ አንስቶ ሲያንሳፍፈኝ ተሰማኝ። እንደዛው እየተንሳፈፍኩ ዝርግትግት ያለው የቃልዬ ገላ ላይ አረፍኩ።
በአልጋው ሜዳ ላይ የፍቅር ፍልሚያው ተጀመረ። ከዚህ  በኋላ በያንዳንዷ ሰከንድ የተፈጠርው ነገር ለኔም የማልቋቋመው  ተዓምር ሆነብኝ•••
ድንግልናዋ የለም። ነገር ግን  አይደለም ድንግል አይደለሽም እንዴ ብዬ የምጠይቅበት አንደበት ለትንፋሽ የሚሆን ግዜ ስታሳጣኝ ድንግል ለምኔ የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ  መዝፈን  ጀመርኩ።
የሷን ድንግል ልወስድ ቋምጬ እኔ እራሴ እስከዛሬ ምንም የማላውቅ ድንግል እንደነበርኩ ያሳመነችኝ የፍቅር ድብድቡ በተጀመረ በአራት ደቂቃ ውስጥ ነበር።
ከአራት ደቂቃ ቡሃላ አጠቃላይ እንቅስቃሴያችንን በበላይነት የተቆጣጠረችው ቃልዬ ነች።
የሚሰበር ነገሬን ሁሉ ሰባብራ እና ከጥቅም ውጪ አድርጋ ለመዘረር ዘጠኝ ደቂቃዎች ያህል ካልጋው ጫፍ እስከጫፍ ስታሽከረክረኝ እንደዚህም አይነት ሴት አለች ለካ  እያልኩ በሷ መደመም ብቻ ሳይሆን  ከዚህ ቀደም አንቀላፍተው እንቅልፌን የሚያመጡብኝን ሁለት ሴቶች ጭምር አስረገመችኝ።
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 31 ይለቀቃል🌹
        https://vm.tiktok.com/ZMhfjFSYU/

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

13 Oct, 07:00


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 29...🌹
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል
.
.
ስለው " ውይ ኤፍዬ እልሁን ተወዋ በቃ ይልቅ ንገረው ሄዶ ያምጣልህ ሄደህ ክፈት አልከፍትም ስትጨቃጨቅ አከራዬቹም ሊደብራቸው ይችላል" አለችኝ ገነት። ነገርኩት ። 
ሊያመጣልኝ እንደሄደ " በቃ ይዞ ይምጣና እዚሁ እኛ ቤት ቀያይረህ ትሄዳለህ " አለችኝ።
ከአስር ደቂቃ በኋላ ይዞልኝ መጣ።
"ምናልህ?" አለችው ገነት።
" አይ ምንም አላለም ምን ይላል ብለሽ ነው?" አላት።
"አንተ ግን የእውነት ጓደኛው ከሆንክ ምከረው ፣ ቆይ እሱ እድሜ ልኩን እንደወህኒ ቤት እስረኛ ሌላው ካልቀመሰለት አይበላም እንዴ? ሀይ ሁሌ ጓደኞቹ የጀማመሯቸው ሴቶች እያፈላለገ መጨረስ ነው ስራው ?" ስትለው ሳቄን አመጣችው።
"ገኒ ደሞ ጥፋቱ የሱ ብቻ ነው እንዴ ሴቶቹ ባይፈልጉ በግድ አያመጣቸው" አለ የኪያ ጠበቃ ተስፋዬ።
"ስማ ተስፋዬ አንተ ለኪያ የምትከራከረውን ያህል እሱ እራሱ ለራሱ እንዲህ ሲከራከር አይቼም ሰምቼም አላውቅም ትገርማለህ አቦ" ስለው እኔን እንዳልሰማ  አልፎኝ ከገነት ጋር የጀመረውን ክርክር ቀጠለ።
እነሱ ሲከራከሩ እኔ ከሱቁ ጀርባ ወዳለው የነገነት ቤት ገባሁና ተጣጥቤ ልብሴን በመቀየር እኔና ቃልዬ ወደተቀጣጠርንበት መናሀሪያ ሄድኩ።

ቀድሚያት ነው የደረስኩት። ደወልኩላት ። እየደረስኩ ነው አለችኝ። ከአምስት ደቂቃ በኃላ ቃሌ ከመጣችበት ባጃጅ ወርዳ ወደኔ ስትመጣ አየሁዋት።
አምሮባታል። አጠገቤ እስክትደርስ አላስችል ብሎኝ ወደሷው ሄድኩና እቅፍ አድርጌ
"እንዴት እንዳማረብሽ የኔ ቆንጆ"
"አመሰግናለሁ አንተም አምሮብሃል ኤፍዬ"
ወደ ሀረር ጉዞ ተጀመረ። እኔና ቃልዬ እያወራን አምስት ደቂቃ ያህል የተጓዝን ሳይመስለን ነበር ሀረር የደረስነው።
"አሁን ወዴት ነን ኤፍዬ?" አለችኝ እንደወረድን።
"መጀመሪያ ምሳ እንብላ ከዛ ማየት የምትፈልጊውን ሄደን እናያለን።
ቃልዬ በዋናነት ማየት የምትፈልገው አምስቱን የጀጎል ግንብ በሮች እና የሀረርጌን ለማዳ ጅቦች ነው።
ምሳ በልተን እንደጨረስን ወደ ጀጎል ይዣት ሄድኩ።

መካከለኛውን በር አይተን በስተቀኝ በኩል ወዳሉት ሁለት በሮች እየሄድን
" እና ዝም ብዬ ነው እንዴ የማየው አስጎብኝዬ?" አለችኝ ፈገግ ብላ
"እየጮህሽም ማየት ትችያለች እመቤት"
"ኪኪኪኪ•••አንተን ብሎ አስጎብኚ  ፣ እንዴ አስጎብኚ እያብራራ ሲያስጎበኝ ነው እኔ የማውቀው ነው አንተም ምንም አታውቅም?"
"አቦ አያቴ እዚህ ነበር የምትኖረው ሶስት አመት እዚህ ተምሪያለሁ አላልኩሽም እንዴ ከፈለግሽ አምስቱንም በር በአምስት አይነት ቋንቋ እየነገርኩ አስጎበኝሻለሁ እሺ ቀልደኛ እድሜ ላያቴ ሀረርን በደንብ ነው የማውቃት"
"እኔ ፎክርልኝ መች አልኩህ ካውቅክ መናገር ነው እንኳን በአምስት ቃንቋ በአንንዱም ባወቅከው ኪኪኪ"
"የምሬን ነው ቃልዬ አምስቱም የሀረር በሮች በአምስት ቋንቋዎች የተለያዩ ስያሜዎች እኮ ነው ያላቸው "
"ኧረ ባክህ?"
"እና በኦሮምኛ፣ በአማርኛ ፣በሀረሪ፣በአረብኛ እና በሱማሊኛ ቋንቋዎች ስያሜ አላቸው በፈለግሽው ቋንቋ ልነግርሽ እችላለሁ በየትኛው ልንገርሽ?
" አቤት ጉራ እሺ በአምስቱም ካውቅካቸው በአምስቱም ንገረኝ እስቲ"
"አቦ ስሚ እንግዲህ አያውቅን ብለሽ ነው አደል
ያ መጀመሪያ ያየሽው  መሀለኛው በር
በኦሮምኛ -ከርረ ሀማሬሳ ፣በአማርኛ- ሸዋ በር፣ በሀረሪ- አስማእዲን በሪ፣ በአረብኛ- ባቡል ነስር፣ በሱማሊኛ-    አልባብ ሀማሬይሳ    ይባላል።
ይሄ በስተቀኝ ያለው የመጀመሪያው በር
በኦሮምኛ -ከርረ ቡዳዋ፣ በአማርኛ-  ቡዳ በር፣ በሀረሪ-  በድሮ በሪ ፣በአረብኛ- ባቡል ሓኪም፣ በሱማሊኛ- አልባብ ቢዳ  ይባላል።
እሄ በስተቀኝ ያለው ሁለተኛው በር ደግሞ
በኦሮምኛ - ከርረ ሶፊ፣ በአማርኛ-  ሰንጋ በር፣ በሀረሪ- ሱጉድ አጥ በሪ፣ በአረብኛ- ባቡል ቀላም ፣ በሱማሊኛ- አልባብ ቢስዲሞ. ይባላል
"እንዴ ኤፊ አልተቻልክም ኪኪኪኪ "
"ድሬ እና ሀረር ያደገ አብዛኛው  ወጣት  እኮ ከአፍ መፍቻው በተጨማሪ በትንሹ ሁለት እና ሶስት ቃንቋ ያውቃል ። እንደናንተ እንግሊዘኛ ለማወቅ ብቻ የምንጋጋጥ መሰለሽ እንዴ?"
"ኪኪኪ •••እኛ እነማን እኔ ብቻ አይደለሁ እንዴ አብሬህ ያለሁት " አለች ወደቀኝም ወደግራም ገልመጥ ገልመጥ እያደረገች ።
"  አዎ  አንቺን ማለቴ ነው ልክ ነሽ ስላንቺ እንጂ ስለሌላው ምን አውቃለሁ ፣ ነይ አሁን በስተግራ ወዳሉት ሁለት በሮች እንሂድ።

" እሄውልሽ እሄ ከመሀለኛው በስተግራ ያለው የመጀመሪያው በር በኦሮምኛ - ከርረ. ፈልኣና፣በአማርኛ- ፈላና በር፣ በሀረሪ- አሰሱም በሪ፣ በአረብኛ- ባቡል ፍቱሕ፣ በሱማሊኛ- አልባብ ፈልዳና  ይባላል።
ይህ በስተግራ ሆኖ  የታችኛው በር  ደግሞ
በኦሮምኛ -ከርረ ኤረር ፣በአማርኛ- ኤረር በር፣በሀረሪ- አርጎብ በሪ፣ በአረብኛ-  ባቡል ራሕማህ፣ በሱማሊኛ- አልባብ ኤረር  ይባላል።
ጨረስን እያንዳንዱ ስያሜ ለምን እንደተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ ትፈልጊያለሽ?
ስላት እያጨበጨበች "  አመሰግናለሁ ኤፍዬ ቀጣይ ምንድን ነው እምታሳየኝ?"
አለችኝ።
"ትንሽ አረፍ ብለን ቡና እንጠጣና ጅቦቹ ጋር እንሄዳለና ?"
"ወይኔ ጉዴ እኔ ግን እፈራለሁ አልጠጋቸውም "
"በቃ እኔ ሳበላቸው ታያለሻ ምን ችግር አለው "

ቃልዬ በቃ ወደድሬ እንመለስ እንዳትለኝ በውስጤ ብፈራም ጭራሽ የመሄድ ሀሳብም ሳታነሳልኝ ሲመሻሽ ከስጋት ተላቅቄ ደስታዬን ማጣጣም ጀመርኩ።
ቃልዬ ስለፈራች ጅቦቹን በሩቁ አይተን ከመመለስ በቀር አልተጠጋንም።
ፀጥ ረጭ ያለ የመኝታ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ ቤት አልጋ ያዝንና እራት ለመብላትኗ  በዛውም ትንሽ ዘና ለማለት ወጣ አልን ።እኔም ቃልዬ ፉት ላይ ያለው ደስታ ልዩ ነው።
መጠጣት ብፈልግም ቃልዬ ብዙ እንድጠጣ ስላልፈለገች በስሱ ጠጥተን ወጣን።
በሀረር ጎዳናዎች ላይ  በከተማው እኔና ቃልዬ ብቻ ያለን እስኪመስለኝ ድረስ እየተቃቀፍን ፣ ደሞ እየተላቀቅን፣  እየተላፋንና  እየተሳሳቅን አልጋ ወደያዝንበት አመራን ።
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 30 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhUh1Ynb/           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

12 Oct, 06:58


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 28...🌹
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል
.
.
"ቁልፍህን ይዘሀል አደል ኤፊ?"
"የምን ቁልፍ?"
"የባጃጇን ነዋ ረስተህ እንዳትወጣ ብዬ ነው"
"እንዴ ገና አልነቃህም ልበል ? እየቃዥህ ነው እንዴ አንተ ልጅ ረስቼ ብወጣስ በምን አስነስቼ እነዳለሁ?"
"አቦ ታድያ  ተመልሰህ ቁልፉን ለመውሰድ እንዳትደክም ብዬ ነዋ"
"እዚሁ ግቢ በር ላይ ነች እኮ ባጃጇ የት ያደረች መስሎህ ነው? እዚሁ ገኒ ሱቅ በር ላይ እኮ ነው ያሳደርኳት"
"ሀይ እዚሁ ነች እንዴ?" አለና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ
"መንጃ ፍቃድ ዋሌት ገለመሌህንስ ይዘሀል አደል ኤፊ?" አለኝ። "አዎ ይዣለሁ "አልኩት ሳቅ እያፈነኝ።
ዝም አለና ልክ ልወጣ ስል ጠብቆ
" ምንም አረሳህም አይደል ኤፍዬ መታወቂያ እና ሌሎች የሚያስፈልጉህን ነገር በሙሉ ይዘሀል ?" ሲለኝ በጤናው አልመስልህ አለኝ።ዛሬ ለሊቱን ሙሉ በህልሙ  እኔ እቃ ረስቼ ስወጣ ያየም መሰለኝ።
"ቆይ አንተ ከመች ወዲህ ነው እኔ መታወቂያ መንጃ ፍቃድ ረስቼ እንዳልወጣ ማሰብና ማስታወስ የጀመርከው"
"ዛሬ ብጀምርስ ምን ችግር አለው"
"ምንም ችግር የለውም ኪያ ፣ አንተስ ጭንቅላትህን ይዘኸዋል አይደል?"
"ማለት?"
"አይ ያው በትንሹም ቢሆን ለማሰብ ይጠቅምሀል ብዬ ነው ፣ረስተኸው እንዳትወጣ እሺ" ብዬው እየሳቅኩ ወጣሁ።

ቁርስ በልቼ ፣ ፀጉሬን ተስተካክዬ ስመለስ አራት ሰአት ሆኗል።
ቃልዬ ጋር ተገናኝተን ወደ ሀረር ለመሄድ  የቀረችኝ አንድ ሰአት ነች። ቃልዩ ጋር ደውዬ ልትወጣ እየተዘገጃጀች እንደሆነ አረጋገጥኩ።
ገላዬን ተጣጥቤ ልብስና ጫማዬን ቀያይሬ ለመውጣት ወደቤት እየሄድኩ በር ላይ እንደደረስኩ  እኔና  ኪያ ተከራይተን ከምኖርባት ግቢ ፊት ለፊት ካለችው ሱቅ
"ኤፊ ፣ ኤፍሬም " ብለው ተጣሩ ባለስቋ ገኒና ሱቁ በር ላይ የቆመ አንድ  ተስፋዬ የሚባል  የኪያ ጓደኛ ።
"አቤት ምነው ?" አልኳቸው በሩቁ።ባለሱቋ ገኒ የታላቅ እህቴ እኩያ ነች ። ከታላቅ እህቴ ጋር አብረው ነው የተማሩት። ና አንዴ አለችኝ በምልክት።
እኔ ልቤ ተሰቅሏል ምን ፈልገው ነው የሚጠሩኝ ?  እያልኩ ጠጋ ብዬ
"ምነው ፈለግሽኝ ገኒ ?" አልኳት። ከተስፋዬ ጋር ተያዩ እና ዝም አሉ። ግራ ገባኝ
"ምንድን ነው? ለምን ጠራችሁኝ " አልኳቸው ሁለቱንም በየተራ እየተመለከትኩ።
"ኤፊ ምነው ዛሬ ስራ የለም እንዴ?" አለኝ ተስፋዬ።
"እንዴ ይህንን ልትጠይቁኝ ነው የጠራችሁኝ ?"
"አይ አደለም ፣ ኣረ አይደለም " አሉኝ በየተራ አሁንም እየተያዩ።
"እህ እና ምንድን ነው ?"
"አይ ወደቤት ልትገባ ከሆነ ቤቱ ዝግ ነው"
"ምንድን ነው እየቀለድክ ነው ተስፋዬ ዝግ ቢሆንስ  የቤቱ ቁልፍኮ  እኔም ጋር አለ"
"አይ ኤፍዬ ከውስጥ ነው የተዘጋው ኪያ ውስጥ ከሰው ጋር ነው ያለው እንግዳ አለበት ኪኪኪኪ" አለች ባለስቋ ገኒ።
"ገ. ባ. ኝ " አልኳት ፈገግ ብዬ ።
ተያይተው እሷ ስትስቅ ተስፋዬ ፊት ላይ ግን ፈገግታ ሳይሆን ጭንቀት ነበር የሚነበበው።
"ኪያ ጥዋት ስወጣ  ያለወትሮው እቃ ረስቼ እንዳልወጣ አስታዋሽ የሆነበት ሚስጥር ተገለጠልኝ"
ስል ገነት "ኪኪኪኪኪ  እቃ ረስተህ እንዳትመለስ እያሳሰበህ ነበር  አይ ኪያ ይገርማል"ስትል
"አቦ ገኒ ደሞ ተያ ነገር አታጋግይ " አላት ተስፋዬ።
"ስለምን ነገር ማጋጋል ነው የምታወራው ፣ ለማንኛውም እኔ ልብስ ቀይሬ ልወጣ ነው ብዙ አልቆይም"
ብያቸው ልሄድ ስል
"አይ አትሂድ ይቅርብህ ኤፊ ብትደውልም አያነሳም ብታንኳኳም አይከፍትልህም  ልብስ ለመቀየር ከሆነ የምትገባው ይቅርብህ ፣ ትርፉ መቃቃር ነው" እያለ  እንዳልገባ ሲሞግተኝ ጤነኛ መስሎ አልታይህ አለኝ።
"ማነው ውስጥ ያለው ኪያ አይደል እንዴ? ማለቴ  ከማንም ጋር ይሁን ግን ኪያ ነው ውስጥ ያለው አይደል?"
"አዎ እሱማ ኪያ ነው ሌላ ማን ይሆናል"
"እና ታድያ ምን እያልከኝ ነው ለምንድን ነው የማይከፍትልኝ ልብስና ጫማዬን በር ላይ ሆኜ እንዲያቀብለኝ መንገር እንጂ መግባት አልፈልግ"
" በሩን ከፍቶ እንደማያቀብልህ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው" ብሎኝ እርፍ ። ብልጭ አለብኝ።
"ቆይ ውስጥ ከማን ጋር ነው ያለው?"
"ከሴ ጋር"
"እና ከሴት ጋር ቢሆንስ ታድያ ቆይ ማነች ሴቷ እኔ አውቃታለሁ?" ስለው ለኔ መልስ ሳይሰጠኝ ልንገረው አልንገረው በሚል ዳይለማ ውስጥ በገባ ስሜት  እንዴ እኔን  አንዴ ከሳቋ ጋር የምትታገለውን ገነትን  ሲመለከት ኪያ ከማን ጋር እንደሆነ ገባኝ።
"ተወው አትንገረኝ ከማን ጋር እንዳለ ገብቶኛል ፣ ከመክሊት ጋር ነው አይደል?"
"አዎ ኤፊ " አለኝ ፈራ ተባ እያለ።
"እንኳን መክሊትን ዘር ማንዘሮቿን ይዞ ቢጋደም  ለደንታው ነው እኔ ገብቼ ልብሴን ወስዳለሁ ሳንኳኳ አይክፈትና እንትያያለን እንግዲህ!" ብዬ ልሄድ ስት ክንዴን ያዝ አድርጎ
"ኤፍሬምና ኪያ በሴት ተጣሉ ሲባል አይደብርም ኤፊ  ፣ ልብስ መቀየሩ ይቅርብህ አትግባ"
" ሀ••••ይ አቦ ልቀቀኛ እንግዲህ አታበሳጨኝ ከመክሊት ጋር ስለሆነ ነው ከሱ ጋር የምጣላው ዝም ብለህ በማታውቀው ነገር ውስጥ ገብተህ አትንቦጫረቅ ልቀቀኝ አቦ"
ስለው ጭራሽ ወገቤ ላይ ተጠምጥሞ " ኤፊ ኤፊ የለበስከው እኮ አፖስቶ ነው በቃ ዛሬ ቅዴ ቢሆንም በዚሁ ልብስ ብትውል ብዙ አያሳጣም ልጅቷም ኪያም ከሚደብራቸው"
ሲለኝ ከኪያ በላይ በማያገባው ገብቶ የሚንዛዛብኝ ጓደኛው ደሜን አፈላው።
"ተስፋዬ የምሬን ነው ከኪያ ጋር ሳይሆን ካንተ ጋር ልጣላ ነው ፣ ሰአቴን አትግደልብኝ ፣ አሁን ትለቀኛለህ አትለቀኝም?"
"አለቅህም ኤፊ" ሲለኝ ..ትዕግስቴ በዚህ መሀል ባለስቋ ገነት ከሱቅ ወጥታ መሀላችን ገባች።
"ኤፊዬ በሱም አትፍረድ እንዳትጣሉ ብሎ እኮ ነው ፣ አንተ ደሞ እላዩ ላይ እንደባብ ተጠምጥመህ ነው እንዴ እንዳይገባ የምታደርገው ኧረ ትገርማለህ" እያለች አላቀቀችኝ።
"ኤፍዬ እንደድሮው በረባ ባረባው በየመዳው መጣላት እንደተውክ አውቃለሁ ፣ ብትሄድም እንደማትጣላው እርግጠኛ ነኝ ግን ኤፍዬ የግድ አሁን ገብተህ ልብስህን መቀየር አለብህ?"
"አዎ ገኒ ዛሬ ስራ አልሰራልም ሌላ ፕሮግራም አለኝ አሁኑኑ ልብሴን ቀይሬ መሄድ አለብኝ " አልኳት ሰአት እያየሁ አራት ሰአት ከሀያአምስት ሆኗል።
"ከልጅቷ ጋር ስለሆነ አልተናደድክም አይደል ኤፍዬ?
"ኧረ ገኒ ምናገባኝ እና እና ነው የምናደደው? ዛሬ ነው እንዴ ኪያ ከመክሊት ጋር የጀመረው ቆየኮ፣ የዚህ ድርቅ ማለት ነው እንጂ የገረመኝ እኔ ስወጣ ትገባለህ ኤፍሬም እንዳይመጣብን ጠብቅልን ብሎሃል እንዴ?  ወዳ ከተደፋች እንኳን አንተና ኪያ ስትፈልጉ የገራዥን ወንዶችን  በመሉ አስለፋችሁ አስገቡላት አይመለከተኝም ፣ ያንተ ግግም ማለት ግን ያስጠላል እሺ"
ስለው ዝም አለ።
"በቃ ኤፍዬ እራሱ ተስፋዬ ሄዶ ልብስና ጫማህን ያምጣልህ አንተም እርግጠኛ ነኝ ባታየቸው ነው የምትመርጠው ፣ ሂድ እራስህ ይዘኽለት ና ፣ ንገረው ኤፍዬ እንዲያመጣልህ የምትፈልገውን ልብስና ጫማ!" አለችኝ።
"አሪፍ መላ ነው ገንዬ እንዴት እንደዚህ አይነት ሀሳብ እስካሁን እንዳልመጣልኝ ይገርማል " አለ ተስፋዬ።
"ይገርማል አደል የምትገርመው እማ አንተ ነህ። አንተ እንድታመጣልኝ አልፈልግም እራሴ ሄጄ ነው የምወስደው...።

ክፍል 29 እሁድ ጠዋት 4:00 ይለቀቃል🌹
  https://vm.tiktok.com/ZMhUh1Ynb/         

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

10 Oct, 15:32


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 27...🌹
.

.
.
ብፅአት ስዩም "አቤት አቤት ሲጥም" ብላ ለምን እንደዘፈነች የገባኝ አሁን ነው።
የቃልዬን ከንፈር ጥፍጥና በምን እንደምገልፀው ቸገረኝ። ማር ማር ይላል አልል ነገር  ማር የሚጣፍጠው ምላስ ላይ ብቻ ነው። የቃልዬ ከንፈር ጥፍጥና  የሚፈጥረው ስሜት ግን ከራስ ፀጉር እስከግር ጥፍር ይሰማል።
እኳንስ የፍቅር ከንፈር የፍቅር ዱላም ይጣፍጣል ስትል የሰማኋት ተከራይ ማን ነበር ስሟ ጠፋብኝ። በቃ ሚስጥሩ እዛ ላይ ነው። ጥንዶች በነፃነት የሚዝናኑበት ከለል ያለ ቦታ ላይ ስለሆንን ሰው አየን አላየን ብለን አልተጨነቅም። 
ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ..

ትንሽ አቆይቻት ለቀቅ አደረኳትና "  ማን ጀምሪ አለሽ ቃልዬ እኔ ቅምሻ አልወድም  መላቀቅ የለም" ስላት ያንን ሳቃን ልትለቀው ስትንደረደር አፏን በአፌ ከድኜ አቋረጥኳት ።
ወደጀርባዬ ገፋ አደረገችኝ እና እየሳቀች ቁጭ አለች። ከፊት ለፉቷ ልቀመጥ ስል " ና እንጂ ከጎኔ ሁን ኤፍዬ" አለችኝ። በጠረጴዛው ዙርያ ሶፋ መሰል መቀመጫ ነው ያለው ።
አንደኛው ላይ ጎን ለጎን ተቀመጥን።
"ከትናንት ወድያ እኮ ኪሴ ውስጥ ብር ስላልነበር እንጂ ስለወደድሻት እንደምገዛልሽ እያሰብኩ ነበር የወጣሁት እኔም በጣም ወድጃታለሁ ይቺን ቀሚስማ እስክገዛ ቃልዬን አላገኛትም  ብዬ ነው ግብዣሽን ያልተቀበልኩት አልከፋሽም አደል ቃሌ?"
"ኧረ አልከፈኝም ኤፍዬ ያው ምክንያቱን ስንገናኝ አወራሻለሁ ብለኸኝ የለ? በቃ በቂ ምክንያት ቢኖረው ነው ብዬ አሰብኩ እንጂ አልከፋኝም። ግንኮ ኤፊዬ ባለፈው የገዛኽልኝን እስካሁን አለበስኳትም"
"አዎ  ለብሰሻት አላየሁም ያው ስላልወደድሻት ሊሆን እንደሚችል አስቤ ዝም አልኩ"
"ውይ ኤፍዬ ሙት ስላልወደድኳትማ አይደለም ያለበስኳት"
"እና ለምንድን ነው?"
"ምክንያቱን አሁን አልነግርህም"
"ባክሽ ስላልወደድሻት ነው ፣  እኔ ስለገዛሁልሽ አልወደድካትም ብትይኝ ቅር የሚለኝ መስሎሽ ነው፣ ይልቅ በወቅቱ ማለት ወድያው ብትነግሪኝ ሄደን እንቀይራት ነበር"
"ኤፊ ሙት ብዬ እየማልኩልህ አታምነኝም"
" ከመሀላ ምክንያቱን ብትነግሪኝ አይሻልም ቃልዬ?"
"እምብየው አልነግርህም" አለች። ዝም አልኳት። መልሳ ደግሞ "ልንገርህ?" አለችኝ።ምን ሆና ነው ቃልዬ በጣም ቀላሉን ነገር ለማውራት ይህን ያህል ልመና የፈለገችው ? ብዬ አሰብኩና

"በቃ ተይው ቃልዬ መናገር ካልፈለግሽ ያን ያህል የሚያሳስብ ነገር አይደለምኮ "እያልኳት ዘወር ስል አስተናጋጁ 
ሊታዘዘን ቆሟል ። ቃልዬ የምትወደውን ምግብ አዝዤው ካጠገባችን እንደሄደ " ለምን መሰለህ እስካሁን ያለበስኳት? የዛሬ ሁለት ወር ምን እንዳወራን ታስታውሳለህ ? እንደውም ድሬ ከመጣሁ ሁለት አመት ቢያልፈኝም እስካሁን ድረስ ሀረርን ሄጄ አላየኋትም ። አንድ ቀንማ ሄጄ ሀረርን መጎብኘት እፈልጋለሁ ስልህ ምን ነበር ያልከኝ?"
"እኔ ወስጄ በደንብ አስጎበኝሻለሁ እንደውም ለምን ሰሞኑን አንሄድም ? ስልሽ አይ አሁን አይደለም ግን መሄዳችን አይቀርም ነበር ያልሽኝ ከዛ ወዲህ ስለሀረር አውርተን አናውቅም"
"አዎ አውርተን አናውቅም ግን የሆነ ቀን እንደምንሄድ እያሰብኩ ልብሱን ገዝተህ ስጦታ ሰጠኸኝ ከዛ ። በቃ ያኔውኑ ከኤፍዬ ጋር ሀረር ስንሄድ ነው የምለብሳት ብዬ ነው ያስቀመጥኳት ?" ስትለኝ ሀረር የመሄዳችን ጉዳይ እውን ሊሆን መሆኑ ታወቀኝና የደስታ ስካር አዝሮ ሊደፋኝ ደረሰ።
መልሳ ደሞ "አሁን ግን ሀሳቤን ቀየርኩ" ስትለኝ
"ሀሳቤን ቀየርኩ ማለት?" አልኳት የመሄድ ሀሳቧን የቀየረች ስለመሰለኝ በጋለው  የደስታ ስሜቴ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የደፉበት ያህል ቅዝቅዝ ብዬ።
"፣በቃ ሀሳቤን ቀየርኳ ይቺን ነው ለብሼ መሄድ የምፈልገው፣ መች እንሂድ ኤፍዬ በዚህ ሳምንት ቅዳሜ ወይ እሁድ ብንሄድስ ይመችሀል?" ስትለኝ ውስጤ በደስታ ጎርፍ ተጥለቀለቀ።
ግማሽ ፉታን የሸፈነውን ፀጉራን ወደ ጀርቧዋ ብትን አድርጌ ግንባሯን ሳም አደኳትና " እንኳን ቀጣይ ቅዳሜ አሁን በዚህ ምሽት እንሂድ ብትይኝ ትራንስፖርት ብናጣ እንኳን ተሸክሜሽ እሄዳለሁ እንጂ አይ በቃ መሽቷል ትራንፖርትም የለም የምልሽ ይመስልሻል ቃልዬ?"  ስላት ረጅም ሳቅ ሳቀች።
"በቃ ቅዳሜ እንሄዳለን ሃሳብሽን አትቀይሪም አደል ቃል?"
"ኤፍዬ ሙት እንሄዳለን ምነው ድንገት አሁን የወሰንኩ መሰለህ እንዴ ? ሳስብበት ነበርኮ" ስትለኝ የተሰማኝ የደስታ ስሜት ቃልዬን ካገኘኃትም፣  ከዛ በፉትም፣  በቃ ከተወለድኩ ጀምሮ ተስምቶኝ የማያውቅ ልዩ ስሜት ነበረው።
በቃልዬ ትንሽ ስከፋ በዚህ ምድር ላይ አንድ የከፋው ሰው ቢፈልግ እኔ ብቻ የምገኝ የሚመስለኝን ያህል በቃልዬ ደስ ሲለኝም እንዲሁ  በአለም ላይ የኔን ያህል ደስተኛ የሆነ ያለም አይመስለኝ።
ደስ የሚል ምሽት አሳለፍን። ሸኝቻት ስመለስ ቀን ቆጠራ ጀመርኩ። እስከቅዳሜ ድረስ ስንት ቀን ነው ያለው? ዛሬ ማክሰኞ ፣ እእ ማክሰኞ እማ አይቆጠርም በቃ ነጋኮ እሮብ ሀሙስ አርብ ሶስት ቀን አለ ገና ብዙ ነው ። ሶስት ቀኑ የሶስት ወር ያህል ረዝሞ ታየኝ። ሀረር ከሄድን በትንሹ አንድ ቀን ሳንድር እንደማንመለስ እርግጠኛ ነበርኩ።አብረን ካደርን ደግሞ ••••አልኩኖ ሳልጨርሰው ኪያ ትዝ አለኝ። እሱን ብሎ አማካሪ ፣ አቦ ካሁን በሁዋላ ስለቃዬ ከኪያ ጋር በጭራሽ ማውራትም የለብኝም ። ጭራሽ ትንፍሽ አልልለትም። እዛው ገራጅ የተበላሸ መኪኖ እያስጎተቱ ከሚመጡ  ሹፌሮች ጋር ይመካከር። ድሮስ እሱ ስለመኪና እንጂ ስለፍቅር የት ያውቃል። ቢያቅም የሚያውቀው በፍቅረኛሞች ፀብ ማሀል ገብቶ የራሱን ማብሰል እንጂ ሌላ ምን ያውቃል ? ምንም አያውቅም እያልኩ ጋደኛዬን ብቻዬን እያማሁት ሰፈር ደረስኩ።
ገብቼ ከሰላምታ ዉጪ ከኪያ ጋር ምንም ሳላወራ ተጠቅልዬ ለሽ አልኩ ።

አይደርስ ነገር የለ ቅርፍፍ እያሉ እልሔን ያስጨረሱኝ ሶስት ቀኖች አልቀው ቅዳሜ ደረሰ።  ትናንት ማለትም አርብ ማታ ከቃልዬ ጋር ተደዋውለን  ከአራት ተኩል እስከ አምስት ሰአት ባለው ግዜ ውስጥ ተገናኝተን ለመሄድ ቀጠሮ አስረናል። ፀጉሬን መስተካከል ብቻ ነው በኔ በኩል የቀረኝ ስራ ። ማታ ዘወትር የሚቆርጠኝ ልጅጋ ፀጉሬን ልስተካከል ብሄድም ወረፋ ስለነበር   ጥዋት  ሁለት ሰአት  ቀጠሮኛል።
ከእንቅልፌ የነቃሁት  አስራሁት ሰአት ላይ ቢሆንም እዛው እየተገላበጥኩ  እንደምንም አንድ ሰአት ተኩል ሆነ።
ተነሳሁ።ለወትሮው ከአንድ ሰአት በፉት ስራ የሚሄደው ኪያ ተጋድሟል።
ከላይ የለበሰውን ጎተት ሳደርገው ተገላብጦ መልሶ ተኛ። ወዝወዝ አደረኩት።
"እ ምንድን ነው?" አለኝ እጅና እግሩን ወደላይ እና ወደታች እየወጣጠረ ።
  "ስራ አትሄድም እንዴ ረፍዷል እኮ ?"
"ደና አደርክ ኤፊ ስራ ገባለሁ ግን ትንሽ አርፍጄ ነው የምገባው ብዬ ነው የተኛሁት እራሴን አሞኛል ባክህ አንተ ልትሄድ ነው ?" እያለኝ ተነስቶ መለባበስ ጀመረ።
"አዎ ልሄድ ነው" አልኩት እኔ የምሄደው ፀጉሬን ልቆረጥ እንደሆነ ልቤናዬ ቢያውቀውም ለኪያ ምንም ላለማውራት ለራሴ ቃል በገባሁት መሰረት  ስለኔና ስለቃል የሀረር ጉዞ ልነግረው አልፈለኩም።
.
.
ከ 150 ላይክ ቡኋላ ክፍል 28 ይለቀቃል🌹
           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

08 Oct, 17:03


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 26...🌹
.
.

.
.
የባጃጇ ሞተር በብሶት እስኪያጓራ ወደተገኘው አቅጣጫ ሁሉ ስበር ለሊቱ ተጋመሰ። በንጋታውም በለሊት ተነስቼ ነበር ስራ የጀመርኩት። ከምሳ እረፍት ዉጪ ግዜ አላባከንኩም ስሰራ አምሽቼ ገባሁ። ከቃልዬ ጋር ከሶስቴ በላይ ተደዋውለናል ። ቃልዬ እኔ የምፈልጋትን አይነት ቃልዬን ስለሆነችልኝ አምላኬን አመሰገንኩት።
ማክሰኛ ረፋድ አምስት ሰአት አከባቢ ስራ ላይ እያለሁ ቃልዬ ደውላ•••

" ዛሬ ምሳ እምጋብዝህ እኔ ነኝ እንገናኝ " ብትለኝም ያቺን ቀሚስ ሳልይዝ ቃልዬን ማግኘት አልፈለኩም።
ለመጀመሪያ ግዜ ከቃልዬ የመጣልኝን ግብዣ ለመጀመሪያ ግዜ ውድቅ አደረኩት።
" ቃልዬ ከትልቅ ይቅርታ ጋር  አልችልም ለምን እንደሆነ ስንገናኝ እነግርሻለሁ የምሳ ግብዣው  ለነገ ምናልባት ደሞ ለማታ ይዙርልኝ ለማንኛውም እደውልልሻለሁ " አልኳት ።  አይመቸኝም ስላት ቅር እንዳይላት ውስጤ እየፈራ።
"እሺ ኤፍዬ ካልተመቸህ ችግር የለውም" አለችኝ። ይህን ሶስት ቀን ቃልዬ ላይ የነፈሰው የተባረከ ንፋስ ከየት በኩል ነው የመጣው በፈጣሪ ፣  አቦ ቃልዬ ሁሌም እንዲህ በሆነች ብዬ ከልቤ እየተመኘሁ ዘመቻዬን ቀጠልኩ።

ስጦዝ ውዬ  ቀን ዘጠኝ ሰአት የኮንትራት ደንበኛዬ የሆነው ሱማሌው አብዱራህማን ሲደውል•••
"ዋውው አቦ ይመችህ በቃ የቃልዩ ቀሚስ ተገዛ እያልኩ ስልኩን አነሳሁ"
"ወርያ የት ነው ያለው እኔ አንተን ጫት ተራ መላክ ይፈልጋል" አለኝ።
"መጣሁ መጣሁ አብዱዬ ቅርብ ነኝ" አልኩትና በረርኩ ወደሱ።
ምርጥ ከፋዬች ከሚባሉት ደንበኞቼ ተርታ የሚመደብ ነው።
እንደጠበኩት የቀሚሷን  ዋጋ ለመሙላት የሱ መልክት ብቻ በቂ ሆነ።  ተጨማሪ ትንሽ ሰራሁና ወደ ፑቲኳ በረርኩ።
እንደደረስኩ ባጃጄን ጥግ አስይዤ እያቆምኩ  ኬት ተክለፍልፎ እንደመጣ እንጃ •••"ቀሚሷ ተሽጣ ቢሆንስ?" የሚል ጥያቄ ሹክ ሲለኝ። ኧረ አይሸጥም በዛ ዋግ ማን ይገዛል ? ቢሸጥስ አንድ ብቻ ነው እንዴ የለው ከለለም የገባበት ገብቶ ያመጣል እንጂ ሌላ ቀሚስ አልገዛ " እያልኩ ዘው ብዬ ስገባ እዛው ቦታዋ ላይ ተሰቅላለች። ቃልዬ ቀሚሷ ውስጥ ሆና ፈገግ ስትል ታየችኝ።
ቀንስልኝ እንኳን እንዳላልኩት ትዝ ያለኝ ብሩን ከፍዬ በስጦታ መጠቅለያ አስጠቅልዬ ወደነ ቃልዬ ግቢ መብረር ከጀመርኩ በኋላ ነበር።
ምን ሆኜ ነው ግን ትናንት በጠራበት ዋጋ ከፍዬው የወጣሀት? አይ መጣደፍ እያልኩ ባጃጇን ከአቅሟ በላይ እያጣደፍኩ ግቢ አከባቢ እንደደረስኩ ቆምኩ።
ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ለቃልዬ ከመደወሌ በፉት ድንገት ቀና ብዬ ፉት ለፉት ወዳሉ ተማሪዎች አየት ሳሳደርግ
ከግቢ ወደከተማ የሚወጡ፣ ከከተማ ወደግቢ የሚገቡ እንዲሁም እዛው በሩ አከባቢ ለወሬ አልያም ታክሲ ጥበቃ ከቆሙ የተማሪዎች ግርግር  መሀል ቆሞ  እኔ ባጃጅ  ላይ እንዳፈጠጠ አየሁት ። አጠገቡ ያለችው•••ሲያፈጥብኝ ኪያ የቃልኪዳንን እና የዛኪን ግኑኝነት እንዲያጣራ ልላከው ሲለኝ ይቅር ያልኩትን ልጅ ቶማስ መሆኑን ለመለየት አድጎ በተንጨፈረረው ፀጉሩ ምክንያት ተቸግሬ ነበር።

ቶማስ መሆኑን እንዳወቅኩኝ  ፀጉሩን እየነካካ ትክ ብሎ ወደኔ ባጃጅ ሲመለከት የፀሀይ መከላከያውን አውርጄ ወደተቃራኒ አቅጣጫ ፊቴን በማዞር ማዶ ማዶውን ማየት ጀመርኩ።
  ከሰከንዶች ቆይታ በኃላ አየት ሳደርገው አሁንም አይኑ ወደኔ አቅጣጫ ነው ።
ካጠገቡ አንዲት ቀጭን ሴት ፊቷን ከሱ ጀርባ ወዳለች ሌላ ሴት አዙራ እያወራች ቆየችና ልጅቷ እንደሄደች ከቶማስ ጋር ማውራት ጀመሩ።
ይለየኝ አይለየኝ ባላውቅም አጠገቡ ካለችው ልጅ ጋርም እያወራ አይኑ ግን እኔ ባጃጅ ላይ ነው።
ምናልባት ወደከተማ መሄድ ፈልገው ወደጊቢ ሰው ይዞ በሚመጣ ባጃጅ ለመሄድ እየጠበቁ ሳይሆን አይቀርም።
ቶማስ እነቃልዬ ግቢ ቢማርም እስከዛሬ ድረስ ለብዙ ግዜ ወደዚህ ግቢ ስመላለስ አንድም ግዜ አይቼው አላውቅም።
ከኪያ ጋር ስለሱ ካወራን ሳምንት እንኳን ሳይሞላ ሳየው ገረመኝ።
አንዲት ደብተር ጠቅልሎ እንደያዘ የጎፈረ ፀጉሩን እየጠቀለልና ከልጅቷ ጋር እያወራ ካሁን ካሁን ተጠጋ አልተጠጋ ብሎ እየጠበቀኝ ነው መሰል ወደኔ ባጃጅ አማትሮ ማየቱን ቀጥሏል።
ከሱ ጋር ሰላም መባባልም መተያየትም ስላልፈለኩ ባጃጄን አስነስቼ ከነሱ በተቃራኒው ሽቅብ ትንሽ ጠጋ አልኩና  በኔና በነሱ መካከል ያለውን ርቀት አስፍቼ  በማለፍ  ጠጋ ብዬ ቆምኩ።

በጎን መስታወት አየት ሳደርግ ጭራሽ ልጅቷም ተጨምራ ሁለቱም አይናቸው እኔ ባጃጅ ላይ ነው። እሱ ያወራል ልጅቷ ወደኔ እያየች ትስቃለች ።
" ምን እያወራላት ነው የምትስቀው?  ኪያ ችክ ካለ አይመለስ አትንገረው ይቅር እያልኩት ስለኔና ስለቃልዬ ነግሮት ይሆን እንዴ ? ኪያ  አያደርገውም አይባልም ፣ ድሮም ተው ሲሉት ይብስበታል  ።
ብቻ ነግሮት ይሁንና እኔና ኪያ ተጋደልን" እያልኩ እነሱ እስኪሄዱ ቃልዬ ጋር ሳልደውል ቆየሁ።
ፎርስ በመባል የሚታወቀው ከፍ ያለ ባጃጅ መጥቶ ቶማስን እና ልጅቷን ጨምሮ  አጠገባቸው የቆሙትን  ጠራርጎ እንደወሰደልኝ ቃልዬ ጋር ደውዬ በር ላይ መሆኔን ነገርኳት።
ከመምጣቷ በፊት የገዛሁላትን ስጦታ ብር በማስቀምጥበት  የባጃጇ ዳሽቦርድ ውስጥ አስገብቼ ቆለፍኩበት።
ቃልዬ ከግቢ እየወጣች ከሩቅ እንዳየኋት ልቤ መዝለል ጀመረች።
የናፈቀችው  እናቱ ከገበያ ስትመጣ አሻግሮ እንዳያት ህፃን ልጅ ሮጠህ ተጠምጠምባት ተጠምጠምባት የሚለኝ ነገር መቼ እንደሚቆም እያሰብኩ ፈገግ አልኩ።
በቃልዬ ምርጫ ከድሬ ሆቴሎች ወደ አንዱ አመራን።
ሆቴሉ በር ላይ እንደደረስን
" ቃልዬ ሂጂ ግቢ መጣሁ በዛ በኩል ላቁማት እዚህ ጋር መንገድ ዘጋለሁ " ስላት።
"እንብየው ብቻዩን አልገባም እዚሁ ጋር ልጠብቅህ ሂድ አቁማትና ና " አለችኝ።
ጠጋ ብዬ አቆምኩና ስጦታዋን ከጀርባዬ ደብቄ ተያይዘን ገባን።
እሷ ቁጭ ስትል እኔ ዝም ብዬ ከፊት ለፉቷ በመቆም ስመለከታት ቀና ብላ እያየችኝ•••
"እህህህ ምን ሆነህ ነው እንደዚህ የምታየኝ ኤፊዬ  ቁጭ አትልም እንዴ ?" አለችኝ።
ስጦታውን ከጀርባዬ አውጥቼ ሰጠሁዋት ።
"ምንድን ነው ኤፊዬ?"
"ከፍተሽ እይዋ"
ከፍታ እንዳየችው "እኔ አላምንም ኤፍዬ ፣ ወይኔ ጉዴ  በጣም በጣም ነው እሺ የማመሰግነው ኤፍዬ " አለችና የቀሚሷን ትከሻ ይዛ በመቆም ገላዋ ላይ ለጥፋ "እንዴት እኮ እንደምታምር  አመሰግናለሁ እሺ የኔ ፍቅር" ብላ ጠጋ አለችና ከንፈሯን ከንፈሬ ላይ መረገችው።
.
.
ከ 150 ላይክ ቡኋላ ክፍል 27 ይለቀቃል🌹
           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

04 Oct, 16:34


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 25...🌹
.
.

.
"አይዞህ እንዲያጣርልኝ ለምልከው ሰው ስላንተ እና ስለቃልኪደን ምንም ነገር አልነግረውም አትጨነቅ ግን በቃ ለኔ ተወው"
"ኪያ የኔን ጉዳይ ለምንድን ነው ላንተ እምተወው ቢያንስ በምን መልኩ በማን በኩል ልታጣራ እንዳሰብክ እኮ ማወቅ አለብኝ "
"ቶማስኮ ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ነው የሚማረው"
"ቶማስ ቶማስ ቶማስ ደሞ የቱ ነው እኔ አውቀዋለሁ?
" እንዴ ተማስን በደንብ ነዋ የምታውቀው አብሮን ኳስ ይጫወት ነበር እኮ ከሶስት ነው ከአራት አመት በፊት ከግንፍሌ ወጥተው ግሪክ ካምፕ ሰፈር  ቤት ገዝተው የገቡት ማን ነበር ስሟ እህቱ የሚስጥረ ወንድም ቶማስ ነዋ አስታወስከው?"
"አዎ አስታወስኩት እኔኮ እሱ ልጅ ጢባሩ ብዙም አይመቸኝም"
"ተወው ስለ ጢባሩ ምናገባን ፣ ጢባሩ ምናምን ትላለህ እንዴ ሲጀመር እኔ ስላንተ ምንም አልነግረውም ዝም ብዬ ቃልኪዳን እና ያ ዛኪ ያልከው ልጅ የእውነት ዘመዳሞች መሆን አለመሆናቸውን ብቻ እንዲያጣራኝ ነው የምነግረው ልጅ ደሞ ፈጣን ነው በርግጠኝነት በዚህም በዛም ብሎ አጣርቶ ይነግረኛል ። ቃል ኪዳን በዚህ አመት መጨረሻ  ትመረቃለች አደል?"
"አዎን "
" ምን ዲፖርትመት ነበር የምትማረው?" አለኝ። ነገርኩት።
"ካንተ ጋር ፌስ ቡክ ላይ ፍሬንድ ናችሁ!"
"አዎ ምነው?"
"ፎቶዋን ከዛ ላይ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። በቃ ይሄን ጉዳይ በኔ ጣለው ሳምንት አይፈጅብኝም " አለኝ። በዚህ ተስማምተን ተኛን ። ኪያ በቶማስ በኩል ለማጣራት ያሰበውን ሀሳብ ማታ ተስማምቼ ባድርም ጥዋት ላይ ግን ቀፈፈኝ በቃ በቶማስ በኩል ቃልዬን መከታተል ቀፈፈኝ።
አብረን ኪኪያ ጋር ቁርስ እየበላን ነው።
"ኪያ የማታውን ሀሳብ ትቸዋለሁ አንተም ተወው በቃ ይቅር ባክህ "
"ምኑን?"
"በቶማስ በኩል ያልከውን  ለምን እንደሆነ አላውቅም በቃ ደበረኝ ይቅር ተወው በራሴ መንገድ እውነቱን እስካውቅ ድረስ ቃልዬ ያለችኝን ነገር ማመን ነው እምፈልገው እሷን ከጀርባ መከታተሉ ቀፎኛል ይቅር ኪያ ተወው ለሱም ምንም አትበለው እሺ ኪያ?"
"እሺ ኤፍዬ ከደበረህ ይቀራላ ምን ችግር አለው"
"አዎ ይቅር በቃ አደራ ምንም አትንገረው ለሱም "
"ጣጣ የለውም ኤፊ ቅድም ወደዚህ ለቁርስ እየመጣን  ዛሬ እፈልግሀለሁ ሲመችህ ደውልልኝ ብዬ መልክት ልኬለታለሁ ከደወለም የሆነ ነገር ልጠይቅህ ነበር በቃ ሌላ ሰው ነገረኝ ምናምን ብዬ አስቀይሰዋለሁ "
"በቃ አዎ እንደዛ በለው " አልኩት ድሮ ለቶማስ እንደዛ ብሎ መልክት መላኩ እየገረመኝ።
ኪኪያ ጋር ተለያይተን ስራ ጀምሬ ትንሽ እንደቆየሁ ከረፋዱ  አራት ሰአት አከባቢ ቃልዬ ደወለች።
እንዲሁ ሰላም ልበልህ ብዬ ነው ብላ ትንሽ አወራን። ለስራ ሳይሆን ለቁርስ የወጣሁ እንደመሰላት ባውቅም ምንም አላልኳትም።
ቀን ዘጠኝ ሰአት አከባቢ ደግማ ወወለች። እህቴ ጋር ምሳ በልቼ ለሊቱን ደህና እንቅልፍ ስላልተኛሁ ትንሽ አረፍ ለበል ብዬ ጋደም ብያለሁ።
"አንተ እንቅልፋም እስካሁን ተኝተኻል?"  ብላ በመጀመር አሁንም እንዲሁ ልታወራኝ ፈልጋ እንደሆነ ነግራኝ አምስት ደቂቃ ያህል የባጥ የቆጡን ስናወራ ቆየንና ከመሰነባበታችን በፊት•••
"ኤፍሬሜ"
"ወዬ ቃል"
"አፈቅርሀለሁ እሺ "
"እኔም ከምታስቢው በላይ አፈቅርሻለሁ ቃልዬ"
ተባብለን ነበር ስልኩ የተዘጋው።
ቃልዬ እንዲህ ለመሆን ለምን ስድስት ወር እንደፈጀባት ግራ ገባኝ።  ስድስቱንም ወር እኔን ፍቅር ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ እያላጋ ሲጫወትብኝ እሷ ግን በመሳቅ ነበር ያሳለፈችው።
ውስጧን ማየት ስሜቷን ማወቅ እስክቸገር ብዙ የማትናገር ፣ እንድታወራ ስወተውታት ፣ ጭቅጭቅ የሚመስላይ ፣ ጨቀጨከኝ ላለመባል መደወል እየፈለኩ ያልደወልኩባቸው ማውራት እየፈለኩ ዝም ያልኩባቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው።
እኔ በማውቀው  መንግስትም ሆን የግል ድርጅት አንድን ሰራተኛ በቋሚነት ለመቅጠር የሙከራ ግዜ የሚባለው የስራ ቆይታ አርባ አምስት ቀን ነው።
ቃልዬ ስድስት ወር በሞላን ማግስት ያልተመደ ለውጥ ያሳየችኝ  እኔን በቋሚነት ለመቀበል እና አሁን እንደምትደውለው ቶሎ ቶሎ ለመደወና ፍቅሯን በግልፅ ለመናገር ስድስት ወር ሙሉ የቆየችው ስድስት ወሩ የሙከራ ግዜ ነበር ማለት ነው?
በቃ ይህ የቃልዬ  ሁኔታ ለኔ አዲስ ነው ፣ ቃልዬ እና እኔ የምንገናኝበትን ቦታ ለመቀጣጠር የት ደረሽ የት ደረስክ ለመባባል ካልሆነ በስተቀር በስልክ ብዙ አናወራም ብናወራም እኔ በቃ ናፈቅሽኝ ድምፅሽን ልስማው ብዬ ካልደወልኩ ቃልዬ ብዙ አትደውልም። ያው አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር በጥናት እና በትምህርት መሀል ከተደዋወልን ሀሳቧ እንዳይበታተን ብላ እንደሆነ ስለነገረችኝ እኔም ባለመደወሏ ቅር ብሎኝ አያውቅም ባልልም መቻል ግዴታዬ ነበር።
ትናንት በዛ ሁኔታ ከተለያየን በኃላ ሶስተኛ  ግዜ መደወላ ብቻ ሳይሆን አወሯሯ እና የምትለኝ ነገር በሙሉ  ግራ ቢያጋባኝም የደስታው ስሜት ያመዝን ነበር። በቃ እኔ ቃልዬ እንዲህ እንድትሆን ነበራ የምፈልገው።ማታም ደወለች ። አወራን።
"ነገ እቃ ልገዛ ከግቢ እወጣለሁ እደውልልህና የሚመችህ ከሆነ እንገናኛለን" አለችኝ። እኔ በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ቃልዬን ለማግኘት የማይመቸኝ ምንም ሰአት የለም። ሀኔታዋ ግር ቢያሰኘኝም በስንቱ ግራ ተጋብቼ እችለዋለሁ ብዬ መልሼ ተውኩት። ተሰነብቻት ስልኩን እንደዘጋችው ዝም ብዬ ባፈቅራት ነው የሚሻለኝ አልኩ ለራሴ ።
በንጋታው ቀኑን ሙሉ የቃልዬን ስልክ ስጠብቅ ነው የዋልኩት  አስር ሰአት አከባቢ ደወለች።
"ሄሎ ቃሌ ግቢ ነሽ ልምጣ ወይስ  ወጣሽ ?"
"ወጣሁኮ ኤፊዬ ኮኔል ነው ያለሁት እሩቅ ከሆንክ ቀረብ እንድትል ነው በቃ የምፈልገውን ገዛዝቼ እንደጨረስኩ እደውልልሀለሁ እሺ"
"እኔም እኮ ኮኔል አከባቢ ማለት ታይዋንጋ ነው ያለሁት የቱጋ ነሽ አንቺ ?"አልኳት።
ያለችበትን ነገረችኝ ከሶስት ደቂቃ በኃላ አገኘኋት።
"ልትገዛ የወጣችውን እየገዛች ቆየችና ጨርሻለሁ በቃ እንውጣ" ብላኝ እየወጣን ፑቲኩ በር ላይ የተሰቀለች አንዲት የምታምር ቀሚስ ላይ የኔም የቃልዬም አይኖች እኩል አረፉ።
"ቀሚሷ አታምርም ቃል?" አልኳት።
"ማማር ታምራለች ግን አሁን ላይ ፋሽን ስለሆነች ዋጋዋ አይቀመስም ኤፍዬ  ና እንውጣ ባክህ ብላ እንደመውጣት ስትል ዘወር አልኩና •••
"  እቺ ቀሚስ ስንት ነች ባባ" አልኩት ሻጩን። የጠራው ዋጋ አይደለም ቆሌ ልብስ ይገፋል።
ስቅቅ ስል ቃልዬ  አየችኝ።
"ኪኪኪኪ አላልኩህም  ኤፍዬ ና ባክህ እንሂድ" አለችኝ ክንዴን ይዛ እየጎተተች። ዛሬ ጥዋት የተከፈለውን  ያን መከረኛ እቁብ በሆዴ ረገምኩት ።  ኪሴ ውስጥ ያለው እንኳን ለመግዛት ለቀብዲም አይበቃምና ቃል ስትጎትተኝ  አፌን ዘግቼ  እየተጎተትኩ ከመውጣት  ውጪ አማራጭ አልነበረኝም።
ቀሚሷ ግን ከአይኔ አልጠፋ አለችኝ። በዛላይ ቃልዬም ወዳታለች።
በሰአቱ መግዛት ባልችልም  በሁለት በሶስት ቀን ውስጥ  እንደምገዛላት እርግጠኛ ነበርኩ።
ይህን ሁለት ቀን ባጃጇን በድሬ ጎዳናዋች ላይ ሁሉ እየጋለብኩ ሳስነጥሳት ታየኝ።
ከቃልዬ ጋር ትንሽ አብረን ቆይተን እንደተለያየን ነበር ቀሚሷን ለመግዛት ልዩ የስራ ዘመቻ የጀመርኩት።
.
.
ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 26 ይለቀቃል
           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

01 Oct, 17:55


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 24...🌹

ሄሎ ኤፍዬ ደናነህ? ለቀቀህ?"
"ምኑ ቃልዬ?
" ትራፉኩ ካካካ ፣ ድብርቱ ነዋ"
"ምነው በዚህ ሰአት በሰላም ነው ምን ሆነች ብዬ ደነገጥኩ"
"ሰላም ነኝ ኤፍዬ ምን ሆናለሁ ብለህ ነው፣ ገባህ እንዴ ወደቤት?"
"አዋ እቤት ነኝ ቃልዬ"
"ድብርቱ አለቀቀህም ማለት ነው?"
"ሌላ ግዜ በዚህ ሰአት ስራ ላይ ነህ ብዬ ነዋ"
"አንቺስ እስካሁን እንዴት አልተኛሽም ቃልዬ?"
"እያሰብኩ"
"ስለምንድን ነው የምታስቢው "
"ስላንተ እና ስለኔ"
"ስለኔና ስላንቺ ምን?"
"እስቲ በዛሬዋ ቀን ምን ታስታውሳለህ?"
"በዛሬዋ ቀን ማለት ዛሬ?"
"አይ የዛሬ ስድስት ወር ልክ በዛሬዋ ቀን በሀያ ሰባት"
"ምን ላስታውስ ? ያንቺ ፍቅር ስሜንስ ሳያስረሳኝ ይቃራል ቃልዬ እስቲ አንቺ አስታውሽኝ"
"ልክ የዛሬ ስድስት ወር በዚች ቀን በዚች ሰአት  ምሽት ላይ ነበርኮ እዛ ሆቴል በር ላይ የተገናኘነው"
ስትለኝ ልቤ ተረጋጋ።
ስድስት ወር እንደሞላን በደፈናው ባውቅም ቀኗን ለይቼ አላሰብኳትም ነበር። ትኩስ ትንፋሽ በረጁሙ አስወጣሁና።
"ቅድም አብረን እያለን ለምን አልነገርሽኝም ቃልዬ ነው አንቺም ትዝ ያለሽ አሁን ነው?"
"እኔ ነገ ነው የምንገናኘው ስልህ ዛሬ ካልተገናኘን ሞቼ እገኛለሁ ብለህ ስትለኝ ቀኑን አስበህ ነው ብዬ አንተ እንድትነግረኝ ስጠብቅ ነበር አንተ ግን  ሌላ አለም ውስጥ ነበርክ ኤፍዬ ምን ብዬ ልንገርህ"

"ይቅርታ ቃልዬ ረበሽኩሽ አይደል?"
"አንተ መረበሽህ ነው የደበረኝ ለማንኛውም ይህን ላስታውስህ ብዬ ነው በቃ ተኛ ኤፍዬ እንደማፈቅርህ እንዳትረሳ እሺ" ቃላቶቿን  በጆሮዬ የሰማኋቸው ሳይሆን በደምስሬ በስሪንጅ የወሰድኩ እስኪመስለኝ ድረስ በሁለመናዩ ሲሰራጩ ተሰማኝ።
" እንዳትረሳ ማለት ምን ማለት ነው ቃልዬ?"
"ሆሆሆ ኪኪኪ ይሄ ደሞ ሌላ  ምን ማለት ይሆናል ? በቃ እሺ አፈቅርሀለሁ "
አለች። አዎ እንደዛ ነው የሚባለው  እንዳትረሳ ስትይ የመጨረሻ  የ መለያያ ንግግር አስመሰልሽዋ ታድያ ምን ላድርግ ቃልዬ ልላት አልኩና ካፌ መለስኩት።
"እኔም አፈቅርሻለሁ የኔ ማር"
"ቻው"
"ቻው ደና እደሪልኝ"
ኡፍፍፍፍፍ አልኩና ስልኩን ትራሴ ስር ወትፌ በጀርባዬ ስንጋለል።
አውርተን እስክንጨርስ አንዴ ፈገግ አንዴ ጭፍግግ እያለ ሲሰማን የነበረው ኪያ እኔን ተከትሎ በረጅሙ ተነፈሰና።
"ቆይ ለምንድን ነው ስልኩን ማንሳት የፈራኸው ኤፊ?"
"እኔ እንጃ!"
"አቦ ተወና ኤፊ ደሞ ሀይ በቃ እሺ ስሜትህን ሳልረዳ የማይሆን ነገር ተናግሬ ከሆነ ይቅርታ"
"ተጨማሪ ወሬ ለመስማት ብሎ ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው አንተን አየሁ"
"አቦ እኔ ለወሬው ብዬ ነው እንዴ? ወንድሜ አደለህ እንዴ ያንተ ጉዳይ አያስጨንቀኝም ኤፊ"
"ባክህ አንተ ከራስህ ዉጪ ለማንም ተጨንቀህ አታውቅም"
"እሺ ስልኩን ለማንሳት የሸከከህ ለምን እንደሆነ ብቻ ንገረኝ"
"ኧረ ኪያ ልተኛበት ተወኝ ••• በቃ አንደኛ ቃልዬ ሰላም ያልሆነች መሰለኝ ሁለተኛ ቅድም ምን አውርተን ተጦላልበን እንደተለያየን ነግሬህ የለ ስለዛኪ ሌላ ወሬ ሌላ እውነት የምትነግረኝ መስሎኝ ነበር የፈራሁት እኔ ሌላ እሷ ሌላ አለም ውስጥ እንደነበርን ያውቅኩት ግን የደወለችው ልክ የዛሬ ስድስት ወር በዚህ ቀን መገናኘታችንን ልትነግረኝ መሆኑን ስትነግረኝ ነው" አበቃ ይሄው ነው ብዬው ተጠቅልዬ ተኛሁ።

እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ ከአንድ ሰአት በላይ ስገላበጥ ቆየሁ፣ ኪያ እንቅልፍ የወሰደው መስሎኝ ስለነበር ድንገት
" ኤፊ !" በማለት ሲጣራ  እየቃዠ መስሎኝ ዝም አልኩት።
" አንተ ኤፍሬም!" በማለት በድጋሚ ተጣራ ።
"አቤት  ኪያ  ምንድን ነው አልተኛህም እንዴ?" አልኩት ቀና ብዬ የክፍሉን መብራት እያበራሁ። ተነስቶ ፍራሹ ላይ ቁጭ ብሏል።
"አንተስ መች ተኛህ "
"እኔማ መች ተኝቼ አውቃለሁ ኪያ በግድ እኮ ነው እንቅልፍ የሚወስደኝ"
"ፍቅር ከያዘህ ወዲህ ነዋ በፊትማ ገና ጋደም እንዳልክ አልነበር••••" ሲል ብስጭት ብዬ•••|
" እንቅልፍ እንቢ ሲልህ ነቆራህን ለመቀጠል ነው የተነሳኸው?"
"ኧረ ጋደኛዬ ምን ሆነሀል   የምናገረው ነገር በሙሉ  ያንተን ስተትና ድክመት እያነሳሁ አንተን ለማብሸቅ እየመሰለህ የተቸገርከው አንተ እኮነህ፣ ለማንኛውም ዝም ብዬ ከስንት ወር በኋላ ዛሬ ዘለግ ላለ ግዜ ብናወራ እንዴት መግባባት አቃተን ቆይ ለምንድን ነው ኤፊ የምለው ነገር በሙሉ ያልጣመው ዋናው እኔን ማማከር የፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው ብዬ እያሰብኩ ነበርና አሁን መጨረሻ ላይ ስልኩን ለምን ማንሳት እንዳልፈለክ የነገርከኝ ነገር አንድ ነገር አመላከተኝ"
"በህልምህ ነው በውንህ"
"ምኑ ኤፊ"
"ያመላከተህ ወይ የታየህ"
"አንተ ማሸፍ ከጀመርክ አይጣል ነው እስቲ ቁም ነገር እናውራ"
"በቁምነገር የሆዴን የውስጤን እውነት ሳካፍልህ እቃቃ ጫወታ መጫወት ያማረህ እኮ አንተ ነህ ኪያ"

"በቃ ይቅርታ ኤፊ ጋደኛዬ ታውቃለህ እኔ  ሌላው ነገር ላይ ትኩረት አድርጌ ያላስተዋልኩት ነገር ግን አንተን በጣም የረበሸህ ጉዳይ የዛ ዛኪ የተባለ ልጅ ጉዳይ መሆኑ ቆይቶ ነው የገባኝ። ልክ ነኝ አደል እራስ ምታት የሆነብህ የልጁ ጉዳይ ነው አይደል  ኤፊ?"
"እና እሺ ነው እንበል እና እሺ ምንድን ነው?"
"እንበል እና እሺ ምንድን ነው አይደለም ነው ወይ አይደለም በለኝ ኤፊ ያ ነው አደል ?
ቃልኪደን ዛኪ  ያክስቴ ልጅ ነው ብትልህም አምነህ ለመቀበል ተቸግረሀል አደል ኤፊ?"
"እኔ ነው አደለም እንድልህ ለምን ትጠብቃለህ ኪያ ቆይ እሱ ቢሆንስ ምን ልትለኝ ነው? "
አልኩት ጮክ ብዬ ። እንቅልፍ የወሰደው እስኪመስለኝ ድረስ  ከአንድ ሰአት በላይ ድምፁን አጥፍቶ ከተኛ በኋላ ምን ሊለኝ እንደተነሳ ግራ ገብቶኝ።
" ኤፊ የሱን ልጅ ጉዳይ በኔ ጣለው በቃ!"
"በኔ ጣለው ማለት?"
"አንተ ልጅቷ የድሬ ልጅ ስላልሆነች ከጎረቤትም ከሰፈሯ ልጆችም ስለልጁ እና ስለሷ የእውነት ዘመዷ ይሁን ፋሟ ማጣራት የማይቻል መስሎህ እንደተጨናነክ አሁን በደንብ ገብቶኛል ፣ ቅድምም ፍቅር ያዘኝ ስትለኝ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብቼ ንትርክ ውስጥ ገባን ሙሉውን ታሪክ ስትነግረኝ ደሞ  እስካሁን ምንም አለማድረጋችሁ •••ሌላ ሌላውን ነገር እያሰብኩ ሀሳቤ ተበታተንና እንዲሁ ያለውን ነገር ልትነግረኝ ብቻ እንጂ  የሆነ ያስጨነቀህ ጉዳይ እንዳለ አላስተዋልኩም ነበር አሁን ተኝቼ ሳስበው ያልኩህ ነገር ሁሉ ያልተዋጠልህ ለምን እንደሆነ ገባኝ። በቃ የልጁ ጉዳይ ሰላም እንደነሳህ ገባኝ። የሱን ጉዳይ እኔ በራሴ መንገድ አጣራለሁ እሱን ለኔ ተወው"
"እኮ በምን መንገድ?"
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 25 ይለቀቃል🌹
           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

27 Sep, 13:42


.♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 23...🌹
.

ደስታዬ መሉ የሚሆነው ምንም ይሁን ምንም እኔም እሷም ፈልገን ስናደርገው ነው። አለመፈለግ ማለት ጭራሽ አለመፈለግ ሳይሆን የግዜ ጉዳይ ነው።
አንሶላ ለመጋፈፍ አሁን ላይ አልፈለገችም ማለት እስከመጨረሻው አትፈልግም ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው ምን ያጠድፈኛል የት ይሄድብኛል ? እስቲ ንገረኝ የት ይሄድብኛል ኪያ? ይህ እንዲገባህኮ የግድ እንደኔ ማፍቀር አለብህ ብዬ አላስብም ነበር አሁን ግን እንደዛ እንዳስብ እያደረከኝ ነው" ስለው..

አዎ እስካሁን ባንተ እና በቃል ኪዳን መካከል የነገርከኝ በሙሉ አልገባኝም እንደዚህ አይነት ነገር ሊገባኝም አይችልም!"
"ምኑ ነው ያልገባህ ሁሉንም ነገር አንድ በአንድ በግልፅ አይደል እንዴ የነገርኩህ"
"ካካካ ታድያ እሱ አይደል እንዴ አልገባ ያለኝ"
"እንዴት?"
"ስድስት ወር ሙሉ አዲስ ነገር አለመኖሩ ነዋ፣ ሁሌ መገናኘት ፣ ማውራት፣ መሳሳቅ መለያየት ቆይ አንተና ቃልኪዳን ምንና ምን ናችሁ ? ቆንጆ ነችና አንተ ፊቷ ተቀምጠህ ያንን ቆንጆ ፊቷን በማሳቅና ስትስቅ በመመልከት ነው እንዴ አምሮትህን የምትወጣው? "
"አቦ በዚህ ቢራ አናትህን እንዳልልህ አንተ ልጅ!"
"ምታኝ ችግር የለውም ግን የምሬን ነው ኤፊ  ምንም እንኳን ሴት ልጅ የሚያስቃት የሚያጫውታት ወንድ ቢመቻትም ሁሌ በተረት ተረት ስትፋታት ግን ያቅራታል ። ህፃን ልጅ እንኳን ሁሌ ተረትተረት ብቻ እያወራህ ተኛ ብትለው አይሰማህም። ተረቱም የሚጥመው ሆዱ ሲሞላ ነው ፣ በኛ እድሜ ያሉ ሴቶች ደሞ ከሆድ ሞምላት ያለፈ ሌላ ፍላጎት ወይም አምሮት አላቸው።
ያ ደሞ ተፈጥሯዊ ነው ፣ ምናልባት ፋላጎቱ እና ውትወታው ካንተ ጫን ብሎ እንዲመጣ ትፈልግ ይሆናል እንጂ በፍቅር አብራህ ለመሆን ፍቃደኛ እስከሆነች ድረስ ተከትሎ የሚመጣውን ሁሉ ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነች ማለት ነው ።
ይህንን እውነት ለመካድ አትሞክር!"
"እሱን አልካድኩም ባክህ ያልከውን ጉዳይ አስቤም አንስቼባትም አላውቅም አላልኩህም  አንድ ሁለቴም በግልፅ ባይሆንም ሀሳቡን አንስቼባት ነበር በአፀፋው ግን አራት ቀን ነው የቀጣችኝ"
"የቀጣችኝ ማለት?" አለ ኪያ ከተጋደመበት ብድግ ብሎ እየተቀመጠ።
"አይ ኪያ በቃ ስለዚህ ነገር ሲወራ ነው አደል ሁለመናህ ጆሮ የሚሆነው ተኝተህ አታወራኝም እንዴ ለምን ተነሳህ?"
"ካካካ አቦ ተዋ ካወራህ አውራ የምር ግን ሀሳቡን አንስተህባት ነበር ? አራት ቀን የቀጣችህስ በምንድን ነው!"
"በመጥፋት"
"በመጥፋት ማለት?"
"ፍቅር ጀምረን ሁለት ሶስ ወር ገደማ እንወሆነን በተገናኘን ቁጥር ልትሄድ ስትል በቀጥታ ሳይሆን በገደምዳሜው  ለምን አብረን አናመሽም ለምን እብረን አናድርም አይነት ጥያቄ በተደጋጋሚ ሳነሳባት ፈተና ጥናት ገለመሌ እያለች ለሰከንድ እንኳን ሳላገኛት አራት ቀን ተሰውራ በናፍቆት ልትደፋኝ ደረሰች። በአምስተኛው ቀን አልቻልኩም  የእውነት ሳላያት ባድር የምሞት ነው የመሰለኝ ።
ከተገናኘን በሶስተኛው እና በአራተኛው ቀን ግቢ አከባቢ ነኝ አንዴ ወጣ በይና አምስት ሰከንድ አይቼሽ ብቻ ልሂድ ቃልዬ ስላት።
" እእእር እኔና አንተ ከተገናኘን ቶሎ አንላቀቅም ኤፍዬ አልመጣም ትለኛለች። በቃ በአምስተኛው ቀን አልመጣም ለማለት ሼም እንዲይዛት ምን ላድርግ ብዬ ቀመር ቀመርኩና አንድ የምትወደውን ምግብ ሆቴል አሰርቼ የግቢው እራት ከመድረሱ ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ግቢያቸው አከባቢ ሄጄ ደወልኩላት።
"ቃልዬ ምሳ ሰአት እዛ ቤት የምትወጂውን ምግብ አዘዝኩና ብቻዬን መብላት አቅቶኝ ነካክቼ ጥየው ወጣሁ ።
አሁን ሲርበኝ አብረን እንድንበላ አሰርቼ መጣሁ ነይና ባጃጅ ውስጥ አብረሽኝ በልተሽ ትመለሻለሽ፣ ያለበለዚያ እኔም አልበላውም ላንዱ የኔ ቢጤ ሰጥቼው ነው የምሄደው"
ስላት አልጨከነችም መጣች። አብረን በልተን ወደ ግቢ እስክትመለስ ናፍቆቴን አስታገስኩ።
አራት ቀን የቀጠችኝ በዛ ምክንያት መስሎ ስለተሰማኝ ከዛ ወዲህ እኔም ክላስ ይዘን እንዋል እንደር ብያት አላውቅም እሷም አራት ቀን ጠፍታ አታውቅም።"
ስለው ኪያ ፈገግ ብሎ ኤፊዬ አንጀቴን በላኸው የሚል በሚመስል አስተያየት እያየኝ
"ኤፍዬ አንተ እንደዛ ብለህ ስላሰብክ እንጂ ምናልባትም እንዳለችው ለጥናት ሊሆን ይችላል። አይ ኤፊ እውነትም ፍቅር እንጥልህ እስኪወርድ ነው ያጠናፈረህ ባክህ ይገርማል ካካካካ"

"አንተ በቃ የምነግርህን ነገር በሙሉ ለመሳቅና እና ለማብሸቅ ከመጠቀም በቀር ምንም እርባና ያለው ነገር አታወራም አደል ኪያ።
መቼም ስሜቴን ልትረዳኝ እንደማትችል እርግጠኛ ሆንኩ ካሁን በኋላ ካንተ ጋር ምንም ማውራት አልፈልግም" አልኩት ብስጭትጭት ብዬ።
"እኔንም ግራ አጋባኸኝ እኮ ኤፊ.... እኔ የምልህ ሁሉ አይጥምህም ምን ላድርግ? ፣ የምልህ ሁሉ የማይዋጥልህ ከሆነ ታድያ ምንድን ነው ልታማክረኝ የፈለከው•••?" አለኝ።
"እኔ እንጃ!" አልኩት።
"ቆይ የምታፈቅርህ ይመስልሀል?"
"እኔ እንጃ "
ካልወደደችህ ካላፈቀረችህ ካንተ ጋር የምትሆንበት ሌላ ምክንያት ያላት ይመስልሀል"
"እኔ እንጃ አላውቅም አልኩህ እኮ"
"ካፈቀረችህ ደሞ ሁሉ ነገሯን ላንተ ለመስጠት የምትሰስት ወይ የማትፈልግ ይመስልሀል"
"በናትህ ተወኝ ኪያ    እ.   ኔ.    እ.   ን.  ጃ  በቃ እኔ እንጃ"
"አቦ ያንጃጃህ ያባቴ አምላክ" ብሎኝ ተሸፋፍኖ ተኛ።
ትንሽ ቆይቶ •••
"ኤፊ"
"አቤት ምንድን ነው?"
"ፍቅራችሁን እኔ እንጃ ፍቅር ብየዋለሁ ካካካካካ"
የኪያን ሳቅ ላለመስማት ትራሱን ጆሮዬ ላይ ጭኜ ተኛሁ።

እኩለ ለሊት ነው። ከለሊቱ ስድስት ሰአት። ስልኬ አንቃጨለ ቃልዬ ነች የደወለችው። ደነገጥኩ።መብራቱን አብርቼ ስልኩ ላይ አፈጠጥኩ ግን አላነሳሀት።
ኪያም "ማነው በዚህ ሰአት የደወለው ኤፊ?" አለኝ ከተጋደመት ቀና ብሎ ዝም አልኩት። ስልኬ እየጠራ ነው።
ቃልዬ በዚህ ሰአት የደወለችው ምን ልትለኝ ይሆን? ቅድም ስንለያይ የሁለታችንም ስሜት ጥሩ አልነበረም።
ለምን ጠረጠረኝ ብላ ይሁን አይሁን ባላውቅም ቅር ብሏት ነበር።
እና አሁን ለምን ደወለች?
"ዛኪ ያክስቴ ልጅ አይደለም ቅድም ዋሽቻሀለሁ" ልትለኝ ይሆን የደወለችው? ማንሳት ፈራሁ። የመጀመሪያው ዙር ጠርቶ እንደዛጋ ወድያው ደግማ ደወለች። ቃልዬ በደናሽ ይሆን? አልኩ ።
ኪያ••••" አታነሳውም እንዴ ማነው?"አለኝ ።
"ቃልዬ ነች ማንሳት ፈራሁ ኪያ !" እያልኩ አነሳሁት ።

"ሄሄሄሄ.  ሄሎ ቃልዬ••••"

መልካም በዓል....🛖

... ላይክ ሼር እያረጋቹ ..👍

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

24 Sep, 16:39


♥️ተማሪዋ♥️
🌹...ክፍል 22...🌹


ሁኔታዎቿ ያወዛገቡኝም ያንን ማረጋገጥ ባለመቻሌ ነው አይገባህም እንዴ ኪያ?"
"ገብቶኛል ኤፊ አንተ ያልገባህ ግን  ያንን የምታረጋግጥበት መንገድ አንዱ እፍታውን መውሰድ መሆኑ ነው። ቆይ እንዲህ ምድር ሰማዩ እስኪዞርብህ ያፈቀርካት ጡት እንድታጠባህ ነው እንዴ ወደድክም ጠላህም የትዳርም የፍቅርም ምሶሶው የሚተከለው ካንሶላው ስር ነው ።
ይልቅ ፍጠን፣ ከወንድ ጋር አየኋት አላየኋት እኔ የምፈልጋት ለ  ዘላቂ ሂወት ነው  ቅብርጥሴ እያልክ አሁን ስርስሯ ለሚሄደው ልጅ እፍታውን ታስረክብና  ዘላቂ የለ  አብረቅራቂ  የለ ሁሉንም አጥተህ እጅና እግርህን አጣጥፈህ ትቀመጣለህ ።

እፍታውን ካስረከበችው አንተ የምታጣው እፍታውን ብቻ እንዳይመስልህ ከነአካቴው እሷንም ታጣታለህ ፣ ዘወር ብላ አታይህም!"አለኝ።

"በቃ ኪያ ከዚህ የተሻለ ምክር የለህም?" አልኩት።

"እንግዲህ ከዚህ በላይ ምክር ከፈለክ የፍቅር እና የትዳር አማካሪ ባለሞያዎች ጋር ሂድ እኔ ያቅሜን መክሬሀለሁ!" እያለኝ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ በሩ ተጠጋና በሩን ከፈት አድርጎ ቆም አለ።
"ምነው  የት ልትሄድ ነው ?"
"እንዲህ በፍቅር ተዝረክርከህ ወጥ በወጥ መሆንህን ለመክሊት አለመንገር አልችልም በቃ ካሁኑ አፌን እየበላላኝ ነው ፣ ሆድ ቁርጠትም ጀምሮኛል ኤፊዬ ሆዴንም ከሚያመኝ አፌንም ከሚበላኝ  ደውዬ ልንገራት ባክህ !"
አለኝ ።
ባዶ የቢራ ጠርሙስ ብድግ ሰደርግ እየሳቀ በሩን ከፍቶ ወጣ "የጨነቀ ለት አለ ሰውየው እኔነኝ ባለጌው  ሰው ነህ ብዬ ካንተ ጋር ማውራቴ  አንተ ስለመፍቻ እንጂ ስለፍቅር ምን ታውቃለህ ድሮስ"  አልኩት ጬክ ብዬ።
ኪያ ግቢ ውስጥ ቆሞ በዛ ሰሞን በተደጋጋሚ እየከፈትኩ ስሰማው የነበረውን የቴዲ አፍሮን ዘፈን
"ለይምሰል አይደለም ልቤ የሚወዳት
                   አይ ልቤ
እስከመቼም ቢሆን ምን ግዜም አይከዳት
              አይ ልቤ
ተኩላ ተኩላ ስትሄድ እያየሁዋት
                 አይ ልቤ
መልኳን ይዛው ወጥታ.  ታድያ እንዴት ልመናት
•••• •••• እያለ ጬክ ብሎ ሲዘፍን ሰማሁት••••

ትንሽ ቆይቶ ተመለሰ።
" እ ደውለህ ነገርካት ሆድህንስ ተሻለህ ? ለመክሊት ለመደወል ነው አደል የወጣኸው? እኔ  ለፍቅር እጅ መስጠቴን ስታውቅ ደስ አላት?  ለዚህ አቃጣሪነትህ በምላሹ ምን ልትሰጥት ተስማማች?"
"አቦ መስመር አትለፋ አንተ ደሞ ቀልድ አይገባህም እንዴ ኤፊ ሙት አልደወልኩም"
"ይሄን ግዜ ስልክ አላነሳ ብላህ ነው"
"ሀይ አልደወልኩም አልኩህ እኮ ምን አስቸኮለኝ ነገ አይደርስም እንዴ?"
"ይደርሳል ነገ ንገራት እሺ ፣ እኔ እሷ ሰማች አልሰማች የሚያስጨንቀኝ መስሎህ አትጃጃል፣ ደንታ የለኝም።
እኔ ቃልዬን ማፍቀሬን አለም ሁሉ ቢያውቅልኝ ደስታዬ ነው።እሷን በማፍቀሬ ደስተኛ ነኝ። ለማፍቀር ባትታደልም ማፍቀር መታደል ነው ሲባል ሰምተሀል መቸስ"

"ሃሃሃሃ መታደል የሚሆነው ግን ሙሉ ሲሆን ነዋ ወሬ ማሳመርማ ማን ብሎህ ኤፊ አንተና የኢትዬጲያ ብሄራዊ ቡድን ግን አንድ እንደሆናችሁ ታውቃለህ?"
"አላውቅም እንዴት ? ምን ለማለት ፈልገህ ነው?"
"በቃኣ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን በጫዋታ ከማን ያንሳል ጫወታውን ለጉድ ይጫወተው የለ እንዴ፣ ትልቁ ችግሩ ምንድን ነው? ጎል ማግባት አደል እንዴ?"
"አዎ ነው የነሱ ተጫውተው ጎል አለማግባት ከኔ ጋር ምን ያገናኘዋል?"
"ካካካካ እስካሁን አልገባህም ኤፊዬ በደንብ ነው እንጂ የሚገናኘው ፣ አንተስ ሴት ልጅ ቀርበህ ጫወታ መች ተቸግረህ ታውቃለህ?  ለጉድ ትጫወተው የለ እንዴ፣ ካንተ ጋር የተወሰነ ደቂቃ አውርታ  ሶስት አራቴ ከልቧ ሳትስቅ የቀረች ሴት አለች እንዴ? እኔ እስከማውቀው የለችም።
" አየህ ይህንን የምታውቀው እኮ እኔ ከምቀርባቸው ሴቶች ስር ስለማትጠፋ ነው ።
ሁሉም ሰው ደካማ ጎን አይጠፋውም ያንተ ደካማ ጎን  ግን ያስጠላል"

"ሃሃሃ ኤፊ ያንተ ደካማ ጎን ደሞ ከቤህራዊ ቡድኑ ጋር መመሳሰሉ ይገርማል።
እንዴልኩህ እነሱ ተጫውተው ጎል አያገቡም ያንተም  ትልቁ ችግር አስቀህ አሳስቀህ በጎል ወይም በውጤት ማሳረጉ ላይ ነው ፣  ሹፌሩ እስከሚመጣ ሞተር የሚያሟሙቅ የከባድ መኪና  ረዳት  ይመስል  ሞተር አሙቀህ ሳትነዳ መውረድ አመልህ ነው።
ሞተር አሟሙቀህ ሳትነዳ የማትወርደው ከባጃጅህ ላይ ብቻ ነው ካካካ•••"
"ክፍታፍ ነገር ነህ ባክህ ፣ የምትናገረው ነገር  የቱንም ያህል እውነትነት ቢኖረው እንኳን አንተ ለማብሸቅና ለመሳቅ እንጂ ድክመቴን እንዳስተካክል አስበህ እንዳልሆነ ስለሚገባኝ ምንም ብትል አይዋጥልኝም"
"ካካካካ መስሎህ ነው ባክህ የግድ በትዛዝ መልክ መናገር የለብኝም ድክመቱን ማስተካከል የፈለገ በቀልድም መልክ ተነገረው በቁምነገር ዋናው ድክመቱን አምኖ ለመስተካከል ያለው ፍላጎት ነው" አለኝ።
" ስማ ኪያ አንዳንድ ሀሳቦች ትክክል የሚሆኑበት ቦታ አለ ያ ማለት ትክክል የማይሆኑበት ቦታና ሁኔታ የለም ማለት አይደለም።
አንድ ሀሳ ልክ ሊሆንም ላይሆንም የሚችለው ሀሳቡ ልክ ስላልሆነ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን እንአውዱ እንደሁኔታው ስለሚወሰንም ጭምር ነው።
ስለዚህ ላንተ ትክክልየመሰለህን ነገር ሁሉ ከማውራትህ በፊት እኔ ያለሁበትን ሁኔታ በደንብ ለመረዳትና አንተ በምታስበው እና እኔ ባለሁበት እውነት መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ሞክር!"
"አቦ አንተ ልጅ አሁንስ  የማውቀው ኤፍሬም አልመስልህ አልከኝ እኮ ፣ መፈላሰፍ መጀመርህን ለምንድን ነው ያልነገርከኝ? ካካካካ•••አይ ፍቅር •••ፍቅር ምን የማያደርገው ነገር አለ ?የቀረህ የጥበብ ሰው መሆን ብቻ ነው ኤፊዬ ግጥም ምናምንስ መፃፍ አልጀመርክም? እስካሁን ካላፃፈክም ወደፊት መፃፍህ አይቀርም፣ አሁን ፈላስፋ አድርጎሀል፣ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ግጥም መጣጥፍ ምናም ያፅፍህና ከጥበቡ ጎራ ይቀላቅልሀል ሆሆሆሆ••••"
"ግልፍጥ ነገር ነህ ዝም ብለህ ገልፍጥ " አልኩት በገዛ እጄ ኪያ ምላስ ላይ ወድቄ እየተንጨረጨርኩ።
"ለማንኛውም ኤፊ ለመረዳት ሞክር የምትለኝ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። ብሞክርም አሁን ከገባኝ የተለየ አዲስ ነገር አይገባኝም ።
እኔ በምለው ነገር እና አንተ ባለህበት እውነት መካከል ያለውን ልዩነቱን ምን እንደሆነ ከገባህ አንተው ንገረኝ "
"ልዩነቱማ ኪያ አንተ ለጭን እንጂ ለፍቅር ተንበርክከህ ስለማታውቅ የሁሉም ነገር መክፈቻም መዝጊያም ቁልፉ የሚገኘው ጭን ውስጥ ነው የሚመስልህ።
እኔ ደሞ እያልኩህ ያለሁት የእውነት ካፈቀርክ ከምታፈቅራት ልጅ የምትፈልገው ፍቅርን ነው ፣ ምንም ነገር ላይ አትቸኩልም፣  ምንም እንድትሆንልህ አትጫናትም እሷን ተጭነህ የምታደርገው ነገር ደስታ አይሰጥህም።
ምክንያቱም ስታፈቅር ከራስህ ደስታ በላይ የሷ ደስታ ያረካሀል፣ ከራስህ ፍትወት ይልቅ የሷ ፍላጎት ይመራሀል ስለዚህ ለራስህ ፍላጎትና ደስታ አትሽቀዳደምም።
ሁሉ ነገርህ ፣ሁሉ መሻት እና ፍላጎትህ ከሷ ፍላጎት ጋር አብሮ እንዲሄድ እንጂ ለኔ ፍላጌት ቅድሚያ ካልተሰጠው አልያም እኔ የፈለኩትን ነገር ሁሉ ለምንድን ነው አንቺም በተመሳሳይ ሁኔታና ግዜ ላይ የማትፈልጊው ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትልም።
ስለምታፈቅራት ሁሉ ነገርህን ትሰጣታለህ እንጂ እሷ ያላደረገችልኝ እሷ ያልስጠችኝ ምን አለ እያልክ እሱን አንተ በፈለክበት ግዜ ብቻ ለማግኘት ባገኘሀት ግዜ ሁሉ አትነዘንዛትም።
.
.
ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 23 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMh2s1nsh/

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

24 Sep, 16:39


📌እስፕሪንግ ማቆንጠጫ ( spring clamp )


☎️ Contact us:- +251914855557 ☎️


JOIN OUR TIKTOK CHANNEL
https://vm.tiktok.com/ZMhYMxcmU/



#springclamp #Salodatrading

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

20 Sep, 17:44


♥️ተማሪዋ♥️
🌹...ክፍል 21...🌹

አይ ኤፏ እኔ የባረኩትን ዳቦ ያልሽው ነገር ግን የመጨረሻ ነው የተመቸኝ ግንኮ ኤፋ አንተ ትባርካለህ እንጂ አትበላም ኤፊ ሙት አንተ ጀማምረህ የተውከውን ወይ የባረከውን እንጂ የቀመስከውን ግን ነክቼ አላውቅም!" አለኝ ሳቅ እየተናነቀው።
"በናትህ ኪያ ተወኝ በቃ፣ እራስህ ነህ ነካክተህ ወደዛ የወሰድከኝ እንጂ  እኔ ስላለፈ ነገር የማውራት ፍላጎቱም የለኝም ።"
"እሺ አሁን ስለተፈጠረው ነገር በቁም ነገር እናውራ በቃ እስቲ ያለህበትን ሁኔታ በግልፅ በተን ተንተን አድርገህ ንገረኝ "
"ትቸዋለሁ!"
"ለምን ኤፊ?"
"እህም ገና ፍቅር ያዘኝ ስልህ ጥሩንባ ይዘህ መለፈፍ የቃጣህ ፣ ሙሉውን ስሰማ እማ በድሬ ትቪ አልያም በድሬ ኤፍ ኤም ለሙሉ የድሬዳዋ ሰው ካልተናገርኩ ማለትህ የማይቀር ነው። እኔ የተለወጥክ መስሎኝ እንጂ ላንተ ሚስጥር ብሎ ማውራት  እኔን ለማብሸቅ ተጠቀምበት እንደማለት እንደሆነ እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም ጓደኛችህ የሚያውቁት አመልህ ነው!"
ስለው ኪያም በተራው ተናደደደ። እስካሁን ሳቅ ሳቅ የሚለው ፊቱ ደመነ።
"አቦ እንግዲህ አታብዝዛዋ ሀይ ኤፊ ደሞ ፣ እስቲ ነገረኝ አንተ ቁም ነገር ኖሮህ ያውቃል እንዴ ? ሲጀመር ከየትኛዋ ሴት ጋር ነው ቁም ነገር ኖሮህ የሚያውቀው፣ ነካክቶ መተው አይደል እንዴ አመልህ ። ምነው ከሌላ ሰው ጋር የምታወራ መሰለህ እንዴ  ከልጅነት እስካሁን አብሮህ ከኖረ ከኔ ከኪያ ጋር እኮ ነው እያወራህ ያለኸው። እስቲ አንተ ሚስጥር ወይ ቁም ነገር ብለህ የነገርከኝን አንድ ነገር ንገረኝ ፌዘኛ እድሜ ልክህን ስታፌዝ አደል እንዴ የኖርከው !" አለኝ።
ወደኃላ ሄጄ ማሰብ ጀመርኩ። ክያ እውነት አለው። በቁም ነገር ያፈቀርኩት ቃልዬን ብቻ ነው።
"ለማንኛውም ልነግርህ ያሰብኩትን ትቸዋለሁ!"
"አቦ ተወዋ ታድያ !" ብሎኝ ወጣና አራት ቢራ ይዞ መጣ። አንዱን ለኔ አንዱን ለራሱ ከፍቶ መጠጣት ጀመረ።
ለብቻዬ በሀሳብ መወዝወዙ ቢቀልልኝ፣ ለኔ ያልታየኝን ለኪያ ቢታየው፣  እኔ ቃልዬን ማወቅ ከብዶኛል ፣ ቃልዬ ባህሪዋ እንዲህ ነው ብሎ አንድ ቦታ  መርጋት ተስኖኛልና ለኪያ ስለ ቃልዬ ስነግረው ፣ ከነገርኩት ነገር ተነስቶ ስለቃልዬ ያሚኖረው  መረዳት ምን ሊመስል እንደሚችል ፣ እንደጋደኛ እንደውንድምም እንዲነግረኝ ፈልጊያለሁና ለትንሽ ደቂቃዎች በዝምታ ከቆየን በኋላ በራሴ ፍላጎት  የኔን እና የቃልዬን የስድስት ወር የፍቅር ታሪክ ድንገት ከተዋወቅንባት ከዛች ምሽት ጀምሬ እስከዛሬዋ ቀን ያለውን ፣ የሚሰማኝን ስሜት፣ የሷን ባህሪና ሁኔታ ጭምር አንድ በአንድ በግልፅ ነገሩክት።
"እውነተም እየቀለድኩ መስሎት ነበር እንዴ ?" እስክል ድረስ በተገረመ ፊቱ ማውራት ከጀመርኩ ጀምሮ ቢራውን አንዴ እንኳን ሳይጎነጭ በተመስጦ ሲያዳምጠኝ ቆየ።

እንደጨረስኩ በመዳፉ ፊቱን ጠራረገ፣ በረጅሙ ተንፍሶ ወደጀርባው ጋለል ብሎ ግርግዳውን ተደግፎ ቢራውን በማንሳት አንዴ ተጎነጨና •••
"አቦ ይገርማል!" ብሎ ባዶው ወለል ላይ አይኑን ተክሎ ትንሽ ቆየና ፎቶዋን እንዳሳየው ጠየቀኝ ከሞባይሌ ላይ አሳየሁት።
"ዋው አስማት የሆነ ውበት ነው ያላት!" አለ።
"አስማት አስማት አስማት የሆነ ውበት ምን ማለት ነው?" አልኩት የእውነት አስማት የሆነ ውበት ምን አይነት እንደሆነ ስለማላውቅ ነው የጠየኩት ኪያ ግን
"አቦ ኤፍዬ አታልምጣ በቃ የሚገርም ነው ለማለት ነው " አለኝና አሁንም ወለሉ ላይ ተትክሎ ሲያስብ ቆየና
"ወንዶች ስንባል ግን እንገርማለን   አይ ወንዶች " አለ ። መልስ አልሰጠሁትም።
"አብዛኞቻችን ማለት ትችላለህ በቃ በፍቅር የምታጦዘን ሴት ልክ እንደቃልኪዳን አይነት ሴት ነች ። እውነቴን ነው እኔ ከታዘብኩት  አፈቀርኩህ ብላ ስሜቷን የምትገልፅ ፣ ናፈቅከኝ ብላ በየደቂቃው የምትደውል ፣ ሲብስባት ፍለጋ የምትመጣ፣ ለመገናኘት አንተ እንገናኝ እስክምትላት የማትጠብቅ ፣ ልታገኝህ ስትፈልግ የምታገኝህ፣ ልትስምህ ስትፈልግ የምትስምህ ሌላም ሌላም የሚሰማትን ሁሉ ይንቀኛል ይሰለቸኛል ሳትል  ፍቅሯንም ድርጊቷንም ስሜቷንም በግልፅ የምታሳየን ሴት ላይ መንጠባረር ያምረናል አደል? ሌሎቹን ተዋቸው መክሊትና ቤትን የተንጠባረርክባቸው ለዛ ነው አደል?"
"ኪያ ኪያ ኪያ እባክህ ከኔ ጋር በሰላም ማውራት ከፈለክ ስለቃልኪዳን ብቻ እናውራ ምነው አንተ ከነዚህ ሴቶች አናት ላይ አልወርድ አልክ እኔ እንኳን አናታቸው ላይ  ምናቸውም ላይ ተፈናጠህ መዋል ማደር ትችላለህ ግን ኪያ በቃ ስለነሱ እኔ ፊት አታውራ!"
"ኪኪኪ እሺ ቱግ አትበላ ምንድን ነው እኔ እነሱን ያነሳሁት እነሱ ያው የድሬ ሴቶች ግልፅ ናቸው። በመልክ ያው ከቃል ኪዳን አያንሱም፣   በነሱ እና በቃል ኪዳን መካከል ያለው የባህሪ ልዩነት በአዱገነትና በድሬ ሴቶች መሀል ያለውን ልዩነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል ለማለት ነው ለምሳሌ •" ብሎ ሊያብራራልኝ ሲሞክር ምን ለማለት እንደፈለገ ስለገባኝ ደሜ ፈላ። ሳይጨርስ አቋረጥኩት።
"ኪያ እኔ የሚያስጠላኝና ብዙ ሰው ላይ የማየው ስህተት ምን እንደሆነ ታውቃለህ?"
"አላውቅም!"
"በአንድ ወይም በውስን ሰዎች ሁኔታ ላይ ተነስቶ ድፍን የከተማውን ሰው ለመፈረጅ የሚንጠሯሯጥ  ሰው በጣም ያስጠላኛል።
መክሊት እና ቤቲ እዚህ መጥተው ስለተነፋረቁ ድፍን የድሬ ሴቶች ነፍራቃ ናቸው ማለት ነው?
  ቃል ኪዳን የማትያዝ የማትጨበጥ ወፍ ስለሆነች ድፍን የአዱገነት ሴቶች ወፍ ናቸው ብሎስ መደምደም ይቻላል? እንደዛ ማሰብ  ሁላችንም እንደ ጣት አሻራችን የተለያየ ባህሪ እንደለን ካለመገንዘብ  ወይ ከመጀዘብ የመጣ ድፍረት እንደሆነ  ነው የሚገባኝ።
ያንተ አክስት መንታ ሴት ልጆች አሏት አደል?  የሁለቱ ባህሪ ግን ምን ያህል እንደሚለያይ እኔም እንተም እናውቃለን ።ኪያ ንፅፅሩንም ውድድሩንም ተወውና በቃልዬ ዙርያ ብቻ የምትለኝ ነገር ካለህ በለኝ፣  ከለልህ በቃ ይህን ጉዳይ እንተወውና ሌላ ነገር እናውራ"

"እሺ ኤፊ ቆይ ከቃል ኪዳን ጋር የመጀመሪያ ቀን እዛ ሆቴል አድራችሁ ጥዋት ላይ ካወራችሁት ወሬ ምን ተረዳህ እኔ እንኳን አሁን ስትነግረኝ አንድ ነገር ተረድቻለሁ አንተስ?" አለኝ።

" ያው ከዚህ ቀደም ከሌላ ወንድ ጋር ምንም ግኑኝነት እንዳልነበራት እና ድንግል ልትሆን እንደምትችል ፍንጭ ይሰጥ ነበር የዛን ቀን አውራሯ ቢሆንም ከአንደበቷ እንዲህ ነኝ የሚል ነገር ስላልወጣ ከመጠራጠር አያልፍም ስለዚህ እርግጠኛ መሆን ይከብዳል!"
"አይ ኤፊዬ በአንደበቷ እንድትነግርህ ለምን ትፈልጋለህ? አንደበቷ ምን ያደርግልሀል ? ከንግግር በላይ ማረጋገጥ የሚቻልበት ወሳኝ መንገድ አለኮ ይልቅ እዛ ላይ ፍጠን!"
"ማለት ምኑ ላይ የምፈጥነው?"
"ኤፍሬም ደሞ  እንደህፃን ልጅ ይሄ ኡፉ ነው እሺ ያቃጥላል እንዳትነካው ተብሎ ካልተነገረኝ  የምትለው ነገር አለህ ። በቃ ማድረግ ያለብህን አድርጋ ምን ብዬ እንድነግርህ ነው የምትጠብቀው?"
"ኪያ ደሞ  ዞረህ ዞረህ  ከሱ አናት ላይ አትወርድም እኔ እኮ ቃልን አፈቅራታለሁ።
እስከመጨረሻው የኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ ፣ ዋናው ፍላጎቴም ያ ነው ።
እሷም ውስጤ ያለው ፍላጎት ገላዋን የመሻት ግዚያዊ ስሜት ሳይሆን  ዘላቂ አብሮነት  እንደሆነ እንድትረዳኝ ነው የምፈልገው።
በሷም ውስጥ ያ ፍላጎት እንዲኖር ነው ምኛቴ የተቸገርኩትም በኔ ልክ እሷም ያንን የኔን ምኞት የመኖር ፍላጎት እንዳላት ማወቅ ነው ።

ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 22 ይለቀቃል🌹
 https://vm.tiktok.com/ZMhFYcYjr/

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

17 Sep, 16:48


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 20...🌹
የሳቁ ድምፅ  ያለንበትን ቤት ጣራ ገንጥሎ እቴቴ ቤት ድረስ የሚሰማ መስሎኝ እስክደነግጥ ድረስ ሳቀብኝ። ምን ሳቀብኝ ቆሌዬ እስኪገፈፍ አንባረቀብኝ ።

"ቆይ ከሳቅክ ስንት ግዜ ሆነህ ኪያ? ረዥም ግዜ ሆኖሀል እንዴ? " አልኩት ከሳቁ ረገብ እንዳለ።
"ካካካ •••ገና መች ተሳቀና ኤፊዬ በዚህ ጉዳይማ ቢያንስ በትንሹ ሶስቴ ከልቤ እንደምስቅ እርግጠኛ ነኝ!"
" ለምን አመት ሙሉ አትስቅም ለደንታህ ነው ባክህ!"
"ኪኪኪኪ የምሬን ነው ኤፊዬ አንተ አሁን መሳቄ ነው አደል የገረመህ....? ለቤቲ ስነግራት ከዚህ በላይ ነፍራለሁ ፣ ለመክሊት እማ ይህን ዜና ስነግራት በሳቅ ጧ ብላ ስትፈነዳ አብሪያት እንዳልፈነዳ ነው የምፈራው ካካካ•••!" ሲለኝ
"ድሮም ይሄን ነበር የፈራሁት !" የሚልለው ዘፈን ትዝ ያለኝ ።
የኪያ እንደዚህ ማሰብና  ማለት አብግኖኝ እኔ እራሴ በንዴት ጧ ልል ምን ቀረኝ? ምንም።
ቤቲና መክሊት አስራ ሁለተኛ ክፋል እያለሁ በተለያየ ግዜ መልካቸውን አይቼ ፍቅር ብጤ ልጀምር ልሞክር ብዬ ብቀርባቸውም  ፍቅር እራሱ ካልያዘኝ በቀር እኔ ስለፈለኩ ብቻ አሳድጄ ልይዘው  አልችልምና ሳንግባባ ቀረን ፍቅር በግዢ አይመጣ ምን ላድርግ እነሱ ሙዝዝ ንዝንዝ ሲሉ እኔ ፍዝዝ ድንግዝ  ችላ አልኳቸውና ተለያየን።
ያው ሴቶች ደሞ ችላ ሲባሉ እልህ ይሁን ፍቅር ብቻ የሆነ ሙጫ የሚያደርጋቸው ነገር አለ አይደል ሰፈር እና እቤት ድረስ እየመጡ መግቢያ መውጫዬን ሲዘገብኝ  እኔ ደሞ ጭራሽ እነሱን ባየሁ ቁጥር እሩጥ አምልጥ ይለኝ ጀመር።
ውስጤ እሩጥ፣ ተደበቅ፣ የለም አስብል፣ እያለ ካዘዘኝ ደግሞ ገና ሳያቸው ከመሸሽ፣ከመደበቅ፣ እያለሁ የለም ከማስባል በስተቀር ምርጫ የለኝም።
እኔ ሳመልጥ ያላቸው እጣ ፋንታ ከጓደኛዬ ከኪያ ጋር መፋጠጥ  ሆነ፣ መፋጠጡን ይፋጠጡ  ነገር ግን ኪያ አጋጣሚውን ይጠቀምበታል። ኪያ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በመጠቀም በመላ ጓደኞቹ የተመሰከረለት እና ሰርተፍኬት የተበረከተለት ልጅ ነው።
እሱ ተዋውቆ ከጠበሳቸው ሴቶች ይልቅ የሚበዙት በጓደኞቹ ምክንያት የተዋወቃቸው ናቸው። የኪያ መጥበስ አንሶላ ስር እስከመደባበስ ነው ረጅሙ እድሜ። 
በኔ ምክንያት ኪያን ማግኘት ከጀመሩ በኃላ ንግግራቸው ኤፊ የት ሄዶ ነው? ለምንድን ነው ስልኬን የማያነሳው? ከሚል ጥያቄና ብሶት ወደ  መሞላፈጥ ትንሽ ቆይተው
"አማነው ኬያዬ? አንተም ዘጋኸኝ ምነው?"  ወደሚል መቆለማመጥ ይቀየራል። ኪያም የሚለውን ይላል ቀመሩን ይቀምራል። ትንሽ ቆይቶ የራሱን መረብ ይዘረጋል፣ የቻለሁን ያህል አጥምዶ እሱም ይጠመዳል። ትንሽ ቆይቶ ይጣዳል።
እኔ የተውኳት ሴት ላይ መጣድ ልማዱ ነው። ያ ግን አይመለከተኝም። አሁን ኤፍሬምን  ፍቅር ጥባጥቤ እየተጫወተበት ነው ብሎ ስቆ መክሊትን ሊያስቅብኝ ሲጣደፍ ሳየው ግን  ነደድኩ
ስማ ኪያ አንተ ሳቅ ግድ የለም ለነሱ ካወራህ  ግን ከኔ ጋር የመጨረሻችን ነው እወቀው!"
"እንዴ ኤፊ ምን ችግር አለው ። ምነው እነሱ መስማታቸው እንዲህ አሳሰበህ ፍቅር ያዘህ እንጂ ስሰርቅ አልተያዝክ ፣ መናገሬማ  አይቀርም ሁለቱም እንደዛ አፍቅረውህ እየየ ሲሉ ስታላግጥባቸው እነሱን የማፅናናት ሀላፊነት እኔ ላይ ነበር የወደቀው።

በተለይ መክሊት " ኤፍሬም በኔ ሳይሆን በፍቅር ላይ እንደቀለደ አንድ ቀን  ፍቅር ሲቀልድበት ያሳየኝ ይሆናል ፈጣሪ"  ስትል ኧረ ሀሳብ አይግባሽ ኤፍሬም ፍቅር ይዞት እንዳየሁ እኔ እራሴ  እነግርሻለሁ ያኔ አንቺ በተራሽ ትስቂበታለሽ  ብዬ ቃል ገብቻለሁ።

ቃል ደሞ ቃል ነው መክሊትማ መስማት አለባት ።
አሁን ትልቁ ነገር ያልከኝ ነገር እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ብቻ ነው። ግን የምርህን ነው አደል?  እውነት ፍቅር እያንደፋደፈህ ነው••? ግን ማን ትሆን ልጅቷ በናትህ ? የእውነት ጀግና ነች! እማዬን ነው እምልህ አቦ ባገኛት እሸልማታለሁ።ግን የምር ፍቅር ያዘህ ኤፊ•••?"

"እንጃልህ! ቆይ አንተ ግን ምን አይነት ጓደኛ ነህ •••? ባንተ ቤት መቀለድህ ነው አደል?
ስማ መቀለድ ሁሌ አያስቅም እሺ የምትቀልድበትን ቦታ እና ሁኔታ ካልመረጥቅ የሚያሸማቅቅበትም ግዜ አለ።
እኔ በማይቀለድ ነገር ስትቀልድ እጅ እጅ ነው የምትለኝ።  ስድስት ወር ሙሉ ትንፍሽ ሳልልልህ የቆየሁትም ለዚህ ነበር። ላንተ መንገሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አውቃለሁ የተለወጥክ የበሰልክ መስሎኝ ነበር !"

"አቦ ኤፊ ደሞ ምንድን ነው እንደዚህ ማካበድ ፍቅር አመልህን  ቀየረው እንዴ አባቴ ተረጋጋ እንጂ ፣ ቆይ አንተ ፍቅር ያዘኝ ማለትህ  ያዘኝ ብቻ ሳይሆን አንደፋደፈኝ ስትል እንደመስማት የአመቱ ምርጥ ቀልድ አለ እንዴ ? እና አንተ ስትቀልድ እኔ ብቀልድ ምን ክፋት አለው በዛ ላይ ቃል ገብቻለሁ"

"ዝም በል ባክህ ወደዛ ቃል ገብቻለሁ ምናም ይላል እንዴ መክሊት ከኔ ጋር ስትጣላ በአፅናኝ ሙድ ገብተህ እትት እያልክ ቆይተህ የት ይዘሀት እንደዋልክ እና ምን እንዳደረጋችሁ የማላውቅ መሰለህ እንዴ•••? እኔ ግን እኔ ያልፈለኩትን እና የተውኩትን ነገር ሌላው ሲያነሳው የምንጨረጨር ተራ ሰው ስላልሆንኩ ስለዚህ ጉዳይ መስማቴን ላንተ እንኳን አልነገርኩህም ።

ባንተ ቤት ጉድህን አላውቅም ቃል ስለገባህላት ነው አደል የምትነግራት? ሃሃሃ  በዚህ ሰበብ ጠርቻት የማደርገውን ላድርግ አትልም ወራዳ።
ቆይ ቆይ ካሁን በኋላ ያቀመስኩህን ነገር የምደግምህ ስለኤፍሬም ስታወራልኝ ነው ብላሀለች እንዴ? ለምን እራስህን ችለህ አትንቀሳቀስም ሁሌ እንደዚህ አይነት ሙድ አይደብርህም እንዴ?  እውነትም ጣሰው በቃ አንተ የማትጥሰው ህግ የለም ማለት ነው? ያልተፃፈም ቢሆን የጓደኝነት ህግ የሚባል ነገር አለ እሺ ትክክለኛ ጓደኛ ብትሆን ተዋትም አብሯት ሆነም  የጋደኛህ ከነበረች ሴት ጋር አንሶላ መጋፍፍ በዘጋህ ነበር።

ደሞ ቃልዬን ባገኛት ሸልማት ነበር ስትል አታፍርም አብጄ ነው ላንተ የማስተዋውቅህ !" ስለው ኪያ ሆዱን ይዞ ፍራሹ ላይ እየተንደባለለ ሲስቅ በንዴት ከፊቴ ያለውን ባዶ የቢራ ጠርሙስ አንስቼ ወገቡን ልለው ምንም አልቀረኝም።
ስቆ ሲወጣለት •••" መስማትሽን ግን በዚህ አጋጣሚ መተንፈስሽ ደስ ይላል ዛሬ ነገ ሰማ እአልሰማ እያልኩ ከመሳቀቅ ገላገልሽኝ ካሁን ወዲህ በነፃነት   ኪኪኪ•••!
"ተው ባክህ አንተ ነህ የምትሳቀቀው ምነው እንዲህ ስታደርግ መክሊት የመጀመሪያህ ነች ምነው የመክብብን እና የአማረን ምን እንዳደረክ ረሳኸው እንዴ?"
"ካካካካ እነሱ እኮ ጀንጅንልን ብለው ልከውኝ ነው በቃ ሴቶቹ አንዳንዴ አስጅኝጃኙን ሳይሆን ጀንጃኙን የሚመርጡበት ግዜ አለ እኔ ምን ላድርግ? ካካካካ"
ስለነሱ አያገባኝም አንተ ሲጀመር እኔ ያልባረኩትን ዳቦ በልተህ ታውቃለህ እንዴ ? ልማድህ እኮ ነው!"
ስለው
"ኧረ ኤፍ ፍቅር ስይዝ ምላስም ይረዝማል እንዴ ዛሬ አልቻልኩህም ኪኪኪኪኪ•••"
ቃልዬ ትስቃለች፣ ጋደኛዬ ይስቃል •••በቃ አለም ሁሉ እየሳቀ ነው ማለት ነው! የኔ ጋር ብቻ ነው ሳቅ ምንጩ የደረቀው፣ ቆይ ፍቅር የሳቅ ምንጭ ያደርቃል እንዴ አልኩት ለራሴ። መልስ የለም ጥያቄ ብቻ።
.
.
300 ላይክ ቡኋላ ክፍል 21 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhLrAFDo/           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

13 Sep, 16:52


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 19...🌹
.
.

.
.
ምንጭ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል
.
.
በቶሎ እዲለቀቅ ላይኩን በዛ አርጉት ቤተሰብ 🌹🌹♥️♥️
.
.
ነገ እንገናኝ ስትለኝ ዛሬ ካላገኘሁሽ ሞቼ እገኛለሁ ብዬ ወትውቼ አምጥቻት አስከፍቼ ስለመለስኳት ከፋኝ። መስራት ብፈልግም ደበረኝ፣ ጭራሽ ድውክውክ አልኩ።
ቀጥታ ወደ ቤቴ በማምራት ያን መጥፎ ስሜት እያባረረ ይገርፍልኝ ይመስል ሰፈር ውስጥ ካለች መደብር አምስት አባ ቢራ ገዛሁና ወደ ቤት ገባሁ።

ፍራሼ ላይ ቁጭ ብዬ መጠጣት ጀመርኩ። ገረዥ የሚሰራው ጋደኛዬ እስካሁን አልገባም ። ነገር ግን መምጫው ደርሷል።
ጋደኛዬ አባቱ "ጣሰው" እያሉ ሲጠሩት እናቱ ደግሞ "ኪያ" ብለው ነው የሚጠሩት። እኩያዬ ነው። እስከዚህ እድሜው እናቱ እና አባቱ በልጃቸው መጠሪያ ስም ላይ መስማማት አልቻሉም።
እናቱ የልጄ ስም ኪያ ነው ስትል አባቱ ደግሞ ጣሰው ነው ብያለሁ ጣሰው ነው እንዳሉ እሄው ሀያምናምን አመት አንዳቸው በአንደኛው ስም ሳይግባቡ ቀጥለዋል።
እሱም ኪያ እንጂ ጣሰው ሲባል ደስ አይለውም።
አባቱ ጣሰው ብለው ሲጠሩት ሶስቴ ካልተጣርሩ ባንድ ጥሪ ብቻ አቤት ባለማለት በጣሰው ሲጠራ ደስ እንደማይለው ለመግለፅ ቢሞክርም አባትየው አቤት እስከሚላቸው  አስሬ ይጠርቷል እንጂ ተሳስተው እንኳን  ክያ ብለው አይጠሩትም።

በአንድ እለት ግራ ግብት ብሎት " ኤፊ !  አባዬ ግን እዚህ ስም ላይ መጭጭ ያለበት ምክንያት እንቆቅልሹ መች እንደሚፈታልኝ ነው ግራ የገባኝ !" አለኝ። ሳቄን ስጨርስ •••
"እንቆቅልሹን እኔ ልፍታልሃ! አልኩት።
" ኤፊ ሙት እየቀለድኩ አደለም!  ። አቦ እስቲ አስበው የምጠራበት እኔ፣   ስሜን የመምረጥ መብት ያለኝ እኔ ፣ የሱን ካልፈለኩት እና እማዬ ባወጣችልኝ ስም መጠራት ከፈለኩ የሱ ሙጭጭ ማለት ሚስጥሩ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም!"
"እኔ ገብቶኛል ልንገርሀ ምን መሰለህ አባትህ ከሁለት ልጅ በላይ የመውለድ ሀሳብ አልነበራቸውም  ማዙኳሽ ደግሞ አራት ልጅ የመውለድ ፍላጎት ነበራቸው ። ስለዚህ ፋዙካሽ እሷ አራት መውለድ ስለምትፈልግ  ላለማርገዝ አትጠነቀቅም ብለው ስላሰቡ የራሰቸውን ጥንቃቄ ለማድረግ  ካንተ በላይ ያሉት ሁለቱ ከተወለዱ በኋላ ከማሚ ጋር ግኑኝነት የሚፈፅሙት  ኮንዶም እየተጠቀሙ ነበር።

አንተ ግን እንቢ እወለዳለሁ አልክና ኮንዶሙን ጥሰህ ወጣህ። እናትህ  አባትህ ሳይፈልጉ ስለተወለድክ ኪያ (የኔ) አሉህ ።
  አባትህ  ደሞ የዚህ ልጅ ስም ከታሪካዊ አመጣጡ ጋር የተቆራኘ መሆን አለበት ብለው ስላሰቡ  ኮንዶም ጥሶ የተወለደ ልጅ ስሙ ማን መባል እንዳለበት ሲያስቡ ጣሰው የሚል ስም መጣላቸው። ተመቻቸው። "
አልኩት ጋደኛዬ እንደዛን ቀን ሲናደድ አይቼው አላውቅም። ላብ በላብ እስክሆን አሯሯጠኝ። ግን አልያዘኝም። ከቆይታ በኋላ ስንገናኝ።
" አላውቅም ስልህ እውነት መሰለህ እንዴ ? ሀይ አባዬ እንደዛ ብሎ ያወጣልኝ እኔ እስክወለድ በጣም ተቸግሮ ስለነበርና እኔ ስወለድ ችግሩ ስለተቀረፈ ችግሩን ጣሰነው ለማለት ነው ጣሰው በቀለ ብሎ ከራሱ ስም ጋር አዋህዶ ሲጠራኝ ደስ ይለዋል አለቀ ። አንተ ቀልድ ችግር የለውም  ኤፊ ይሄን ነገር በቀልድም መልክ ከኔ ውጪ ለሌላ ሰው ታወራና እንጣላለን ። አንተ እየቀለድክ ነው።
ሰው ግን እውነት ነው የሚመስለው፣ እውነት መሰላቸው አልመሰላቸው ለደንታቸው ነው፣ ነገር ግን በተለይ እዛ የምሰራበት ገረዥ ውስጥ እንዲህ ብለህ ብታወራ እያበሸቁ ስራ አያሰሩኝም ፣ በተለይ ደሞ ያ ግልፍጥ ትዛዙ የሚባል ልጅ ይህን ቢሰማ ጭራሽ አይፋታኝም።
አመቱን ሙሉ ለመጣው ሰው ሁሉ እያወራ ነው የሚያበሽቀኝ " አለኝ።
ሁላችንም የሰፈር ጓደኞቹ ኪያ ብለን ነው የምንጠራው። አንዳንዴ በጣም ሲያበሽቀኝ አፉን ለማዘጋት።
"ተው እንጂ ጣሰው!" አለዋለሁ ። ያኔ ወይ ዝም ይላል ወይ ሰድቦኝ ይወጣል። እኔና ጋደኛዬ ብዙ ግዜ የማንግባባው በሴት ዙርያ ነው እሱ ለሴት  ያለው አመለካከት እና የሚያራምደው ሙድ ከኔ ጋር ተቃራኒ ነው።

እስካሁንም ስለቃል ያልነገርኩት ለዛ ነበር። ዛሬ ግን በቃል ዙርያ ባሰብኩ ቁጥር የሚሰማኝ ስሜት በራሴ ሀሰብ እና እስካሁን በመጣሁበት አካሄድ ትክክለኝነት እምነት እንዳጣ አድርጎኛልና ሲመጣ ልንገረውና የሚለኝን ልስማ ወይስ ይቅርብኝ ?  እያልኩ ስወዛገብ ቆየሁ።
በዛ ሰአት እቤት ውስጥ ሊያውም ቢራ ይዤ በፍፁም አድርጌው አላውቅም።
ኪያ  በሩን ገፋ አድርጎ ሲገባ••• ሁለት ተጠጥተው ያለቁ፣ አንድ የተጋመሰ፣ ሁለት ገና ያልተከፈቱ የቢራ ጠርሙሶች ከፊት ለፊቴ እንደተመለከተ አይኑን አሸት አሸት አደረገና••••
" እኔ አላምንም አንድ ነገር እማ አለ ኤፊ ምንድን ነው የሆንከው ••••?" አለኝ።
ምን እንደምለው  ግራ ገብቶኝ ዝም ብዬ ሳየው•••• እንባ ይሁን ብሶት ፣ ስካር ይሁን ፍቅር ብቻ የሆነ  የሚተናነቅ ነገር ተናነቀኝ ..

ምን እንደሆንኩ ለራሴ ግራ እስኪገባኝ እርብሽብሽ አልኩ። ዝም ስለው ጥያቄውን ደገመው።
"ምንም አልሆንኩም!" አልኩት።
"ኧረ ኤፊ በጤናህማ ስራ ትተህ ፣ በመሪው ፋንታ ቢራ ጨብጠህ ፣ እዚህ ቤት ውስጥ ብቻህን አትቆዝምም ነበር። እየተዝናናሁ ነው አትለኝም መቸስ መዝናናት ብትፈልግ የት እንደምትጠጣ ጠንቅቄ አውቃለሁ።
ምን እንደሆንክ ባላውቅም የሆነ ሙድ ውስጥ እንዳለህ መጠርጠር ከጀመርኩ ቆይቻለሁ !"

"ምን የተለየ ነገር አይተህ ነህ መጠርጠር ከጀመርክ የቆየኸው?

"እንዴ ምን ያላየሁት ነገር አለ ኤፍዬ መለዋወጥህ ላንተ አልታወቀህም እንዴ? ስንት ወር ሆነህ  ከኔጋ ካወራህ?
ስንት ወር ሆነህ  ዛሬ እሄን ያህል ሰራሁ ፣ ዛሬ እንዲህ አጋጠመኝ፣ ዛሬ እገሌን አገኘሁት ወይ እገኘሁዋት ብለህ ማውራት ከተውክ?
ቆየህ እኮ  እኔ እቤት ውስጥ እያለሁ ከነመፈጠሬ ረስተኸኝ ሙዚቃ ከፍተህ ወይ አብረህ ትዘፍናለህ ወይ በሆድህ ተደፍተህ ታዳምጣለህ።
እኔስ ስንት ወር ሆነኝ ኤፊን ምን አድርጌው ነው ብዬ ማሰብ ከጀመርኩ ?
አንዳንዴ ብቻህን ሁላ ታወራለህ  በፊት አይደለም ለእቁቡ የሚጣል ለሌላ የሚተርፍህ ልጅ በየሳምንቱ ለህትህ የምትሰጣት የዕቁብ ብር እስክታጣ ገንዘብ ታጠፋለህ ።
ባለፉት  አራት እና አምስት ወራት ውስጥ ከኔ ጋር የምታወራኮ ብድር መጠየቅ ስትፈልግ ብቻ ነበር ።

ቆይ መለወጥህ ደመነፍሷዊ ነው እንዴ አልታወቅህም ? ቆይ ምን አስቀይሜህ ነው ግን ወንድሜ ለምን በግልፅ አትናገርም?
ከመች ወዲህ ነው በኔና ባንተ መሀል ድብብቆሽ የተጀመረው?" አለኝ ።

በረጅሙ ተነፈስኩና•••"ተለውጬ ሊሆን ይችላል ነገርግን ካንተ ጋር የተያያዘ አይደልም ። ኪያ ሙት የምሬን ነው ካንተ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም!"

"እሺ መለወጥህን ማመንህ ነው ዋናው። ግን ለምን በምን ምክንያት ?"
"ፍቅር እያንደፋደፈኝ ነው ባክህ ኪያ ወንድሜ የምሬን ነው ። በቃ ፍቅር ቁም ስቅሌን እያሳየኝ ነው !" ስለው...
.
.
100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 20 ይለቀቃል🌹
           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

10 Sep, 17:27


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 18...🌹

ቆይ ማነው ዛኪ?" አልኳት ፈርጠም ብዬ።
"ለምን ማወቅ ፈለክ?"
"እንዴ ! ለምን ማወቅ ፈለክ ከማለት እገሌ ነው ማለት አይቀልም ቃል?"
"እሺ ዛኪ ነው!" ብላኝ እርፍ።
"ምን ማለትሽ ነው?"
"እንዴ እገሌ ነው በይኝ እላልክም ኤፊ ?ዛኪ ነዋ  ታድያ ማን ልበልህ?"
"ጥያቄዬ ስላልገባሽ ነው ወይስ እያላመጥሽ ቃል?"
"አልገባትም ብለህ ካሰብክ እስኪገባኝ አስረዳኛ ኤፊዬ!"
"እሺ ዛኪ የት ነው?"
"እህህህም ግቢ ነዋ ስናወራ ሰምተህ የለእንዴ?" አለችኝ የግርምት ፈገግታ ፈገግ ብላ በጨረፍታ አይታኝ ወደ ብርጭቆው እየተመለሰች።
"ገባኝ የግቢ ተማሪ ነው ፣ አንድ ላይ ነው የምትማሩት ማለት ነው?"
"አዎ ነው!" ብላኝ ዝም።
ሁኔታዋ ግራ  አጋባኝ። ምን እየሆነች ምን እያሰበች ፣እንዴት እንዴት ሆና  በምን አይነት ስሜት እያወራችኝ እንደሆነ ሊገባኝ  አልቻለም።
በርግጥ ቃልዬን ካወቅኳት ጀምሮ ቀስ በቀስ የሚገለጡ አዳዲስ ባህሪዋች አይባታለሁ። እስካሁን ድረስ  የቃል ባህሪ እንደዚህ ነው ብዬ ለመደምደም የተቸገርኩት አብረን በቆየን በተገናኘን ቁጥር በወሬና  በሁኔታዎች መሀል የማይባት አደዲስ ባህሪ እያምታታኝ ነው። የዛሬው ሁኔታዋ ደግሞ ተለየብኝ።
ላለመናደድ ከራሴ ጋር እየታገልኩ••••
"በቃ ወይ ስለዚህ ጉዳይ አናውራ እንዴ ቃልዬ ? ከደበረሽ ይቅር!"
"አንተኮ ነህ ኤፊ እዚህ  ከገባን ጀምሮ ልክ ያልሆንከው!"
"እሺ የኔን አልክድም፣  አንቺም ግን ስልኩ ከተደወለ በኋላ ልክ አይደለሽም ደብሮሻል!"
"አልደበረኝም ኤፊ ገርሞኝ ነው!*
" ምኑ ነው የገረመሽ?"
"ያንተ ሁኔታ!"
"የኔ ሁኔታ ምን ሆነ?"
"የሆንከውን እማ አንተው እወቀው !" ብላ አሁንም ዝም።እሷም  ይውጣላት እኔም ይውጣልኝ ብዬ በጥያቄዬ ገፋሁበት።
"ከዛኪ ጋር አብራችሁ ነው የምታጠኑት?"
"አልፎ አልፎ አዎ"
"እዚህ ግቢ ነው የተዋወቃችሁት?"ስላት " ኧረ በጭራሽ" ብላኝ እኔ ትቀጥላለች ብዬ ስጠብቅ  ዝም አለች አሁንም ።
"እና?"  ስላት "እና ምን •••?" ስትለኝማ ነደድኩ ብስጭት ያመነጨው  የሰውነቴ ሙቀት ጨመረ ።
እኔ በሷ ቦታ ብሆንና እሷ እዚህ ግቢ ነው የተዋወቃችሁት ብላ ብትጠይቀኝ እዚህ ግቢ አይደለም እኔና ዛኪ የምንተዋወቀው በዚህ ግዚ በዚህ ቤታ ገለመሌ ገለመሌ እያልኩ ሙሉ ታሪክ እንደማወራላት እርግጠኛ ነኝ። እሷም እንደዛ ነግራኝ የተጨነቀች ነፍሴን  እንደማሳረፍ አልያም እንደመገላገል. ዳር ዳሩን እየነካች  ሆን ብላ ትግስቴን  እያስጨረሰችኝ እንደሆነ ገባኝ።
ተሳክቶላታል  ትግስቴ ተንጠፍጥፋ አለቀች ። ብስጭትጭት ንድድድ አልኩ። ክፉ  አልናገራት ነገር ቃልዬ  ነች። አፈቅራታለሁ።
የነበረኝ አማራጭ  ይህን ርእስ ለግዜውም ቢሆን መዝለል እና ጥያቄዬን መተው ብቻ ነውና ።
"በቃ ተይው !" አልኳትና  ወደጀርባዬ ተደግፌ በረጅሙ ተነፈስኩ።
"ምኑን?" አለችኝ።
"በቃ ምንም አትንገሪኝ ትቸዋለሁ ካስጨነኩሽ ይቅርታ !" አልኳት።
አፏን በእጇ አፍና ከሳቋ ጋር ስትታገል። እቺ ልጅማ  እየሳቀች እኔን ልታሳብደኝ ነው። እኔ በንዴት እየተንተከተኩ እሷ ላለመሳቅ እስክትታገል ሳቋ መምጣቱ  እራሱ ይገርማል።
"በቃ ተናደድክ ኤፊ ?" አለችኝ ወደኔ ዞራ።
" ቀጥተኛ መልስ የማትመልሽልኝ ሆን ብለሽ እኔን ለማናደድ አልነበር ተሳክቶልሻል እንኳን ደስ አለሽ!"
"ቀጥተኛ ማለት እንዲህ ቀጥ ያለ?" አለችኝ የመሀል ጣቷን ሽቅብ ቀስራ በፈገግታ እየተመለከተችኝ።
መልስ አልሰጠኋትም   ሲያሻት እንድታጨረጭረኝ ፣ ሲያሻት እንድታስገርመኝ ፣ ሲያሻት እንድታስደስተኝ፣ ሲያሻት እንድትናፍቀኝ በልቤ ላይ ያነገሳትን ፍቅርን ግን  "እድሜህ ይጠር!"  አልኩት።
"ቆይምንድን ነው ማወቅ የፈለከው?" አለች በድጋሚ በተራዬ ለግዜውም ቢሆን መልስ ላለመስጠትና ዝም ለማለት ሞከርኩ።
"እ••••?" አለችኝ። በለስላሳ ጣቶቿ ፊቴን እየደባበሰች። እኔን አንዴ እሳት አንዴ በረዶ ለማድረግ ያላት ሀይል ሳይሆን የኔ እንዳሻት እንደፈለገች ስታደርገኝ ላለመደረግ ያለኝ እራስን የመቆጣጠር አቅም ዜሮ መሆን ግርም ቢለኝ ይሁና እልኩ በለሆሳስ።
"ምን ?" አለች።
"ም   ን   ም !" አልኩ እንደምንም።
"ኪኪኪኪ ••••አየ ኤፊ! ለማንኛውም ዛኪ ያክስቴ ልጅ ነው የቤተሰቦቻችን ቤትም ጎን ለጎን ነው ፣አንድ ግቢ በለው አብረን ነው ያደግነው። እንዳጋጣሚ ሆኖ ሁለታችንም ድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ ተመደብን። አባቴ ይህን እንደሰማ ሁለታችንንም አስጠርቶ   ከቤተሰብ ብዙ ኪሎሜትሮች  ርቄ መመደቤ አሳስቦት እንደነበርና ከሱ ማለት ከዛኪ ጋር አንድ ቦታ እንደተመደብን ሲያውቅ ደስ እንዳለው ከነገረን በኋላ••
" አደራ ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ እስክትመለሱ እንደታላቅ ወንድም እና እንደታናሽ እህት ሁኑ፣ ልጄን አደራ ብታጠፋ እየተቆጣህ ትምህርቷ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጋ እንድትማር እሺ የኔ ልጅ!" አለው
ከግቢ ሲያጣኝ የትነሽ ምናምን እያለ የሚደውልልኝ ለዛ ነው።ህፃን ልጅ አይደለሁም እንኳን እሱ አባዬም ተቆጣጥሮ ከምንም እንደማያድነኝ አውቃለሁ።
ነገር ግን አባዬን እንዲከፋው ስለማልፈልግ ዛኪ የትና ከማን ጋር እንደሆንኩ እንዲያውቅ አልፈልግም ። " አለችኝ።
ዝም አልኩ። ለሷ መልስ ባልሰጣትም ውስጤ ግን ብዙ ጫጫታ ተፈጠረ።
እስካሁን ባጭሩ እንደዚህ መናገር ስትችል  መነታረክ ለምን ፈለገች ታድያ? ምናልባት ምን ብላ እንደምትነግረኝ የታሪክ ፈጠራ ግዜ  ለማግኘት  እያማጠች አሁን የነሀረችኝን ያክስቴ ልጅ ነው•••የሚል እውነት ያልሆነ ዝምድና ለማዋለድ ይሆን ? የሚል ጥያቄ ያጠላበት፣ ጥርጣሬ የሸራረፈው  ከፊል ደመናማ ይሉት አይነት ደስታ ተሰማኝ።
ከነበርንበት ወጥተን ፣ግቢ በር ላይ አድርሻት፣ ተሰነባብተን እስከምንለያይ "እንሂድ በቃ ልሸኝሽ ፣ በቃ ቃልዬ ቻው ፣ቻው ኤፊ"  ከመባባል ውጪ አላወራንም።
ብቻዬን ስመለስ ግን ቃልዬን "ይጠረጥረኛል አያምነኝም !" ብላ እንድታስብ ያደረኳት እና ያስከፋኋት መሰለኝና  እርብሽብሽ አልኩ። መጠየቄ ጥፋት ባይሆንም ወቅቱ አልነበረም። ቢያንስ ለራሴ ቃል መታመን ነበረብኝ አልኩ። ቃልዬን ከማግኘቴ በፊት ምን እያልኩ ስፎክር እንደነበር አሰብኩት። ካገኘኋት በኋላ የሆንኩት፣ ያልኩት፣ ያሳየኋት ስሜት፣ የጠየኳት ጥያቄ በሙሉ ደግሜ ሳስበው በሷ ሳይሆን በራሴ ተገረምኩ።
ስሜቴን መደበቅ ፣የይምሰል መሳቅ፣ የይምሰል ማውራት መጫወት፣ የይምሰል ፊቴ ላይ የደስታ ስሜት ማንፀባረቅ የእውነት  ፍቅር ለያዘው ሰው የማይቻል መሆኑን ከማንም ሳይሆን ከራሴ አረጋገጥኩ።
እንዳገኘኋት ከልጁ ጋር ካየኋት በኃላ  ውስጤ የተፈጠረውን ምስቅልቅል ስሜት ደብቄ ምንም እንዳልተፈጠረ አድርጌ ለመተወን ድንቅ ተዋናይ መሆን  ነበረብኝ።
ሊያውም  አለማየሁ ታደሰን አልያም ሽመልስ አበራን።
ነገሩ የቱንም ያህል መተወን ቢቻል የሚቻለው በፊልም አልያም በትያትር እንጂ በእውነተኛ የፍቅር ሂወት ላይ ማን ይተውናል? ማንም።
የትኛውም ተዋናይ እኔ ቃልዬን ባፈቀርኳት ልክ በሚያፈቅራት  ሴት ፊት እኔ በተረበሽኩት ልክ ተረብሾ አይደለም ትወናው ውኔው ሁሉ ነው የሚጠፋበት።
ምክንያቱም ይህ ፍቅር ነው። ስለዚህ ምንም ያላየሁ ለመምሰል የሞከርኩት ሙከራ ፉርሽ ቢሆንብኝ በኔ ሳይሆን መፍረድ በፍቅር ነው።
ያን ሁሉ ጥያቄ ጠይቄ ወይ እውነቱን አላቅኩ ጭራሽ ተወዛግቤ ቁጭ።
200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 19 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhJcwNLg/

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

08 Sep, 18:14


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 17...🌹

"አንቺን ከማፍቀሬ ዉጪ ምንም የሆንኩት የለም አልኩሽ እኮ ቃልዬ!"
"ታድያ ፍቅር ድብርት ይለቃል እንዴ ኤፍዬ••••?"
"አንዳንዴ!" አልካት።
"አንዳንዴ ማለት ምን ማለት ነው•••?"
"እራሱን ፍቅርን ጠይቂው እኔ ምን አውቃለኩ!"
"እና በምን ምክንያት እንደደበረኽ አታውቅም•••?
እያለችኝ ከቦርሳዋ ውስጥ ስልኳ ጠራ ። እጇን ከአንገቴ ላይ  ልታነሳና ስልኳን ከቦርሳዋ ልታወጣ ስትል አንገቴ ላይ ያለውን እጇን ያዝ አደረኩት።
ግራ በተጋባ ስሜት ትክ ብላ ብላ ስታየኝ•••
"እቀፊኝ እኔ አወጣልሻለሁ !" ብያት ቦርሳዋን ብድግ ሳደርገው።"ኪኪኪኪ •••ኧረ የሴት ቦርሳ ማየት ነውር ነው ኤፍዬ!"
"ምንም አላይም እሄው እጄን ልኬ ሞባይልሽን ብቻ ማውጣት " እያልኳት አይን አይኗን እያየሁ ስልኳን ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥቼ እንደጨረስዩ የቦርሳዋን ዚፕ ዘግቼ ፊት ለፊታችን ባለው  ጠረቤዛ ላይ አስቀመጥከትና ።
ስልኳን እኩል ተመለከትነው።
የደወለው ዛኪ ነው! •••ተፋጠጥን፣  እንደተለመደው ከኔ መቶ ሜትር ርቃ እንዳታናግረው እንዳትነሳ •••አንገቴ ላይ ያለውን እጇን በግራ እጄ ያዝኩትና ••••
"ዛኪ ነው ደዋይሽ እንቺ አናግሪው!" አልኳት በቀኝ እጄ የያዝኩትን ስልክ እንድትቀበለኝ ወደሷ ጠጋ እያደረኩ። አልተቀበለችኝም ። ስልኳ እየጠራ ነው ።
ጥያቄ ባዘሉ አይኖቿ አንገቷን ወደ ቀኝ ዘመም አድርጋ በዝምታ አየችኝ።  እንደትቀበለኝ በአይኔ ወደ ስልኩ እያመለከትኳት እኔም ዝም ብዬ አየኋት•••ምንም ቃል ካፏ ሳይወጣ ስሜቱ ከአስተያየቷ የተቀዳ የሚመስል የግርምት ፈገግታ ወደ ጎን ፈገግ አለችና  ስልኩን ተቀበለችኝ። ዘገም ብላ ወደ ጆሮዋ አስጠጋችው።
እሷም እያየችኝ እኔም አይን አይኗን እያየኋት ነው።
"ሄ. ሄሎ ዛክ"
"ወዬ አዎ ይሰማኛል"
"አይ አይደለሁም። ኖኖ ቤተመፅሀፍትም አይደለሁም። እቃ ለመግዛት  ወደ ከተማ ወጣ ብያለሁ። 'አረዲ ' እየመሸ ነው•••'ኤኒዌይስ' እደውልልሀለሁ"
"እሺ ቻው!"
ተዘጋ። በቃ ይህንን ብቻ ብላ ወሬኣቸው አብቅቶ ስልኩ ተዘጋ።  እኔን ያቀፈችበትን እጇን በቀስታ አውርዳ ቦርሳዋን አነሳችና ስልኩን ቦርሳዋ ውስጥ ከተተችው።  ከልጁ ጋር ያወራችው ነገር ምንም ፍንጭ የማይሰጥ ድፍንፍን ያለ ነገር ሆነብኝ። ምን እንደምል ስለቸገረኝ እሷው የሆነ ነገር እስክትለኝ መጠባበቅ ጀመርኩ።
ያደረኩት ነገር ትክክል ይሁን ስተት ለማወቅ ቃልዬ  ቀጣይ የምትለኝን መስማት እንጂ በራሴ ትክክል ነው አልያም ስተት ነው ብዬ ለመደምደም ተሳነኝ ፣ ምክንያቱም ቃልዬ እንዲህ ሳደርግ ምን ይሰማት ይሆን? በሚል የተብሰለሰለ ስሌት ሳይሆን  ዛኪዋ በደወለባት በዛች ቅፅበት አጠገቤ ሆና እንድታናግረው ማድረግ እንዳለብኝ ባዘዘኝ ስሜት ተመርቼ ነበር አጠገቤ ሆና እንድታናግረው የተጫንኳት።
ያንን ያደረኩት ስለማፈቅራት ነው። ይሄ ሰው በደወለ ቁጥር ለምን እና ምን ለማውራት ካኔ አጠረብ ዘወር እንደምትል ውስጥ ውስጤን ሲከነክነኝ ውሎ ማደሩን ባልክድም   ያለ ፍላጎቷ እኔው አጠገብ ተቀምጣ እንድታወራ አስገድዳታለሁ ብዬ ጭራሽ አላስብኩም ነበርና ከማድረጌ በፊት ሳይሆን ካደረኩት በኋላ ምን ይሰማት ይሆን በሚል ጭንቀት ውስጤ መናጥ የጀመረው ወድያው ነበር።
ምክንያቱም በዚህ ምክንያት በኔና በቃልዬ መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ያንን ለማስተናገና እንደአመጣጡ ለመቀበል  ዝግጁ አልነበርኩም።

ስልኳን ቦርሳዋ ውስጥ ካስገባች በኋላ ወደኔ ዞራ አልተመለከተችም። ከጠረጴዛው ላይ አጋምሳ ያስቀመጠችውን ውሃ አንስታ ጠጣችና ባዶውን ብርጭቆ ጠረጴዛው ላይ አንዴ ወደ ግራ አንዴ ወደቀኝ በቀስታ እያሽከረከረች ዝም አለች።

በቃ ለሶስት ለአራት ደቂቃዎች ዝም አለች። ጨነቀኝ። አራቱ ደቂቃ የአርባ ደቂቃ ያህል ረዘመብኝ።
በዝምታዬ ለመዝለቅ ወኔ አጣሁ። አስባ አስባ ድንገት  ካጠገቤ ብድግ ብላ የምትሄድ መስለኝ።
እንዴ ወዴት ነው ? ምናምን  እያልኩ ክንዷን ይዤ ላስቆማት  ስሞክር•••  አትንካኝ ብላ የምትጮኽብኝ፣ ምን ሆንሽ  ቃልዬ ስላት •••አትጥራኝ ! እንዳትከተለኝ ብላኝ ስትሄድ በአይነ ህሊናዬ ታየኝና ከእንቅልፉ ውሃ ተረጭቶበት እንደነቃ ሰው ብትት አደረገኝ።
"ቃቃቃ •••ቃልዬ!" አልኳት በደነገጠ ድምፅ።"ወዬ ኤፊ !" አለችኝ አይኗን ከብርጭቆው ላይ ሳትነቅል። በረጅሙ ተነፈስኩና••••
"ምነው ዝም አልሽ?" አልኳት።
"አንተስ ምነው ዝም አልክ?"
"አንቺ ዝም ስትይ"
"እኔም እንደዛው"
"እንደዛው ማለት?•••ደበረሽ እንዴ?"
"ምኑ?"
"እኔ እንጃ!
" አንተስ ደበረህ እንዴ?"
"ምኑ ነው የሚደብረኝ ቃልዬ?"
"እኔ እንጃ"
በመካከለችኝ እንደድቅድቅ ጨለማ የሚያስፈራው ድቅድቅ ፀጥታ መልሶ ሰፈነ።
እኛ ጋር ብቻ ሳይሆን አለም ሁሉ ዝም፣ ጭጭ፣ ረጭ ያለ መሰለኝ። እንዴት ይጨንቃል!"
"ኧረ ቃልዬ!" አልኳት ክንዷን ያዝ አድርጌ።ዝም አለች።
"እእእ •••እኔኮ አቅፈሽኝ ስለነበር  በቃ ለማናገር እንዳትነሺና  እንደዛው አቅፈሽኝ እንድንቆይ ስለፈለኩ ነው።  ከዛ ቦርሳውን ከፍተሽ  ስልክሽን ለማውጣት ስለናይመችሽ  ብዬ ነው ያቀበልኩሽ፣   ምን መስሎሽ ነው ቃልዬ?"
"አዎ ገብቶኛል ኤፊ !
" እና እንደዛ ማድረጌ ደበረሽ ቃል?
"አልደበረኝም ! ለምን ይደብረኛል ፣ ቢደብረኝ ለምን አናገርኩት?"
አለችኝ።  በአነጋገሯ ብስጭት አልኩ በውስጤ። አንዴ ተነካክቻለሁ እንግዲህ  ቃልዬ መናደዷ ካልቀረ ልግፋበት አልኩና•••
"ቆይ ማነው ዛኪ?" አልኳት ፈርጠም ብዬ።ቆይ ማነው ዛኪ?" አልኳት ፈርጠም ብዬ።
"ለምን ማወቅ ፈለክ?"
"እንዴ ! ለምን ማወቅ ፈለክ ከማለት እገሌ ነው ማለት አይቀልም ቃል?"
"እሺ ዛኪ ነው!" ብላኝ እርፍ።
"ምን ማለትሽ ነው?"
"እንዴ እገሌ ነው በይኝ እላልክም ኤፊ ?ዛኪ ነዋ  ታድያ ማን ልበልህ?"
"ጥያቄዬ ስላልገባሽ ነው ወይስ እያላመጥሽ ቃል?"
"አልገባትም ብለህ ካሰብክ እስኪገባኝ አስረዳኛ ኤፊዬ!"
"እሺ ዛኪ የት ነው?"
"እህህህም ግቢ ነዋ ስናወራ ሰምተህ የለእንዴ?" አለችኝ የግርምት ፈገግታ ፈገግ ብላ በጨረፍታ አይታኝ ወደ ብርጭቆው እየተመለሰች።
"ገባኝ የግቢ ተማሪ ነው ፣ አንድ ላይ ነው የምትማሩት ማለት ነው?"
"አዎ ነው!" ብላኝ ዝም
200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 18 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMh1bt6S8/           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

08 Sep, 18:13


📌የማጠፊያ የሚበራ ብርሃን ( hinge led light )


☎️ Contact us:- +251914855557 ☎️

JOIN OUR INSTAGRAM
https://www.instagram.com/p/C-soCvXogOj/?igsh=NTc4MTIwNjQ2YQ==

JOIN OUR FACEBOOK CHANNEL

https://www.facebook.com/share/r/wsEdZHGTqfJQLUQg/?mibextid=oFDknk


JOIN OUR TIKTOK CHANNEL
https://vm.tiktok.com/ZMh1bn3dg/

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

07 Sep, 16:59


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 16
የቷ ቃል ኪዳን••••?!"
"አንቺ ነሽ ሌላ ቃልኪዳን የት አውቃለሁ እኔ !"
"ሂድ ወደዛ አቦ ••••ምንድን ነው ግራ የምታጋባኝ!"
"ግራ ገብቶኝ ነዋ ቃልዬ!"
"እብድ ነገር ነህ!"
"ስላሳበድሽኝ አመሰግናለሁ እሺ•••••? በፍቅር ማበድ ግን  እንዴት ደስ ይላል ቃልዬ ••••? !"
"ኧረ ባክህ •••••በል እራስህን ችለህ  ብቻህን እበድ ኪኪ•••! እሺ እንዲሁ ሳስበው በወሬኣችን መሀል  ስለትራፊክ ህግ የምታወራው ተያይዘን እንድናብድ ስለፈለክ ሳይሆን አይቀርም. ኪኪኪኪኪ " አለች ።
እንደምንም ስትደውል ባለማንሳቴ ምክንያት የደበራትን ቃሌን ፈገግ አሰኘኋት።ለቃልዬ እንደዛ ብላትም እኔ ግን እንደዛ  የሳቅኩበት ሌላም ምክንያት ነበረኝ።
ያ ገራዥ የሚሰራው አብሮኝ የሚኖረው ጓደኛዬ ገና ስራውን በጀመረ ሰሞን የጠበሳት ልጅ ወሬው ሀሉ ስለመፍቻና እና ስለመኪና መለዋወጫ ሆኖባት።
ገራዥ የምትሰራ ሴት ፈልገህ ጥበስ እኔ በቃኝ!" እንዳለችው ትዝ ብሎኝ ነው። ያንን ሁኔታ እያነሳሁ ለወራት ጓደኛዬን ለማብሸቅ ተጠቅሜበታለሁ። ዛሬ ቃልዬ እንዲህ ስትለኝ ትዝ ያለኝ እሱ ነበር ። ለካ ወዶ አይደለም ጓደኛዬ አልኩ በልቤ።
"እሺ ስልኩስ ምን ሆኖ ነው ከእጅህ ላይ የወደቀው•••?" አለች ቃል።
"እያወራሁሽ ምህረት የለሹ ትራፊክ ከፊቴ መጥቶ ነዋ!•••ትንሽ ስተት ካየ ከሩቅ ነው የቅጣት ደረሰኙን እንደባንዲራ  እያውለበለበ የሚመጣው! ልመና አይገባው ምህረት፣  በቃ እሱ ደረሰኙን እያውለበለበ ሲመጣ አንቺ ብርሽን እያውለበለብሽ መጠበቅ ብቻ ነው ያለሽ አመራጭ! ፣ በቃ እንዳየሁት ስልኩን ለቀኩት ያው ባጃጅ ውስጥ ስለሆንኩ ስልኬ ምንም አልሆነም ወንበሩ ላይ ነው የወደቀው!"ስላት
" ኤፊዬ በቃ ወሬህ ከትራፊክ እና ከትራፉክ ህግ ሲወጣ ደውልልኝ እሺ ቻው !" አለችኝ ። ቻው ማለት አልቻልኩም ስልኩን ላለመዝጋት ብቻ  ስቄ እስክጨርስ ጠበቀችኝና••••
"ቻው በቃ!"  ብላ ዘጋችው።

እህህህህ አይ ቃልዬ። ስልቹ ነገር ነች ግን ። አሁን እንደዚህ ስትማረር በተገናኘን ቁጥር ስለትራፊክ ህግ እያወራሁ ያሰለቸኋት አትምመስልም። ያንን ጓደኛዬን ይዘዝብሽ አቦ በመፍቻ እና በመኪና መለዋወጫ እቃ ወሬ እያደነቆረሽ በህልምሽ ሁላ ገረዥ ብቻ እንዲታይሽ ያደርግሽ ነበር። ወጣም ወረደ አምልጦኝ ስቀባጥር ከገባሁበት ወጥመድ አምልጫለሁ። ካሁን ወዲህ እውነቱን ማጥመድ ብቻ ነው የኔ ስራ!።  እያልኩ ትንሽ ዘወር ዘወር ብዬ ሰራሁና በግዜ ወደ ቤት ገባሁ።
ቃልዬ ቅዳሜ ነው የምንገናኘው ብትለኝም በኔ ውትወታ አርብ አመሻሹ ላይ ለመገናኘት ተስማምታለች። ሰአቱ እየደረሰ ነው ። ያው ትናት ስላየሁት ነገር ምንም ነገር ትንፍሽ ላልል ለራሴ ቃል ገብቼ ላገኛት እየሄድኩ ነው።
ተገናኝተን ትንሽ እንደቆየን ግን ••••
"ቃልዬ!"
"ወዬ ኤፊ"
"ስንት የቅርብ ጓደኞች አሉሽ•••?"
"የቅርብ ጋደኛ •••? እዚህ ነው ነው አዲስ አበባ ኤፍዬ•••?"
"አይ እዚህ"
"እዚህ የለኝም ! አሉኝ ግን ያው ያን ያህል ነው ፣ ያን ያህል ማለት ወሰን ወይም ድንበር ያለው ቅርርብ አለ አደል በጋራ ጉዳዬች እና በትምህርት ዙርያ እንጂ ከዛ ያለፈ የግል ሚስጥሬን የማካፍላት በተለየ ሀኔታ የምቀርባት ጋደኛ የለችኝም"
"የወንድስ•••?" ልላት ብዬ ፈርቼ ተውኩትና በረጅሙ ተንፍሼ ዝም አልኩ።
"ኪኪኪኪኪ እንዴ ምነው በሀይል ተነፈስክ•••? ቆይ ለምን ጠየቅከኝ•••?
" ለምንም እንዲሁ ለማወቅ!"
"ዛሬ ግን ፉትህ ላይ የሚታየው ስሜትም መድህም ልክ አይደለም ሌላ ሰው ሆንክብኝ በሰላም ነው ኤፊዬ•••?   እቤት ሰላም ናቸው አይደል••••?"
"ደና ናቸው ቃልዬ!"
ከፊት ለፊቴ ተነስታ አጠገቤ ከጎኔ ተቀመጠችና እቅፍ አድርጋኝ•••
"ምን ሆንክብኝ ኤፊዬ•••? ምንድን ነው የሆንከው•••? እስቲ ንገረኝ•••!"
"ምን ሆንኩ ቃል •••? ምንም አልሆንኩም እኮ!"
" ስሜትህ  እኮ ልክ አይደለም ታድያ•••!"
ዝም አልኳት። እንዳቀፈችኝ በፀጥታ  ቆየን።
ሌላ ነገር ማውራት ሌላ ነገር ማሰብ ተሳነኝ፣ ስሜቴን መደበቅ ለይስመላ መሳቅ መጫወት አቃተኝ።
ፊቴ ላይ ቶሎ ቶሎ የምትመጣብኝ አሁን ከኔ ጎን የተቀመጠችው ቃል ኪዳን ሳትሆን ከዚራ መንገድ ላይ በሌላ ወንድ እቅፍ እና ጉያ ውስጥ ሆና ስትሄድ ያየህኋት ቃል ኪዳን ነች።
እኔ ሳልሆን ፍቅር የማስበውን ፣  የምናገረውን ፣ የማሳየውን ስሜት እስከመወሰን ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠረኝ  አምኖ ካለመቀበል የመጣ ስህተት መሆነን አሰብኩ።
ብዙ ነገሬች መራራም ጣፋጭም ጎን አላቸው፣ ፍቅርም እንደዛው።
ለኔ ግን ጣፋጭ ጎኑን ደብቆ   መረር ካለው ጎኑ እንድጀምር  ተሰማኝ። ፍቅርን ታዘብኩት።
የንን ምስል መርሳት ያንን መጥፎ ስሜት መደበቅ አልችል አልኩ። እንደፎከርኩት የውስጤን በውስጤ ይዤ እንደበፊቱ ኤፍሬም መሆን የማይሞከር እውነት የማይወጣ አቀበት ሆኖብኝ ።
ከሷ ጋር ቁጭ ብዬ ከራሴ ስሜት ጋር ትግል ገጠምኩ፣ ትግሉን ግን በአሸናፊነት መወጣት አልቻልኩም ወሬዬ ሁሉ ከጥያቄ ውጪ ሊሆን አልቻለም •••
"ቃልዬ !"
"ወዬ ኤፊ!"
"ከግቢ ውጪ •••ማለት እዚህ ተመድበሽ መማር ከጀመርሽ በኋላ የተዋወቅሽው እና የምትቀርቢው የድሬ ሰው አለ እንዴ••••?
" የድሬ ሰው ማለት•••?"
"፣የድሬ ልጆች ማለቴ ነዋ!
" ብዙ የድሬ ልጆች ግቢ ይማራሉ እኔ በመጠኑ የምቀራረበው ግን ከአንዲት ልጅ ጋር ብቻ ነው!"
እኔ መጠየቅ የምፈልገው ሌላ የምጠይቅበት መንገድ ሌላ። እሷም እንድትነግረኝ የምፈልገው ስለወንድ ጓደኞቿ  የምትነግረኝ ግን ስለሴት ጓደኞቿ ብቻ ። በግልፅ አለመጠየቄ ያመጣው ውጤት መደናቆር ብቻ ሆነ።
አሁንም••••"እሺ !!" ብቻ ብያት ዝም አልኩ። ቃልዬ ግራ ገባት።ዝም ስል ይጨንቃታል። ተጫወት ብላ ትወተውተኛለች። ወሬ የምጀምረውም የምጨርሰውም  በጥያቄ ብቻ ሆነ። በአንደበቷ ባትናገረውም በሆዷ ግን••••
"ይሄ ልጅ ባጃጅ ሹፌር ከመሆኑ በፊት ወይ መርማሪ ፖሊያስ ወይም ደሞ ጋዜጠኛ ነበር መሰለኝ!" ብላ ሳትደመድም አትቀርም።
ፍቅር ግን  ይገርማል!።  በዛ ሁኔታ ውስጥም ሆኜ ቃልዬ የደበረኝ ስለመሰላት ከሌላ ግዜው በተለየ ሁኔታ ስትጨነቅልኝ ፣ በተለየ ሀኔታ ስታየኝ እና ስታቅፈኝ ሰውነቴ በደስታ ስሜት ይግል ነበር።
• አንዴ አንገቴን አንዴ ጣጦቼን በጣቶቿ መሀል እያስገባች ስትደባብሰኝ   ነፍሴ ሀሴት ታደርግ ነበር ። በህመምም ውስጥ ደስታ ማለት ይህ ስሜት ይሆን እንዴ እላለሁ ለራሴ።ምን እንደሆንኩ ለማወቅ ደጋግማ ስትጠይቀኝ ምንም አልሆንኩም ስላት ቆየሁ። የሆነ የሆንኩት ነገር ኖሮ እየደበኳት እንደሆነ ታውቋት ይሁን•••• ስራዋን ስለምታውቅ ብቻ መጠየቋን መተው አልቻለችም።
"ቆይ ምን እንደሆንክ ለምን አትነግረኝም••••!?"
100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 17 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMh1YaEcQ/
           

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

04 Sep, 16:01


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 15.
" ወጣ ብዬ ነበር ፣ አሁን ግቢ ገባሁ አንተ ግን ቅድም ባልተለመደ ሰአት የደወልከው በሰላም ነው•••?"
"ቤት በኩል  ገባሽ••••? •••••ደሞስ ያልተለመደ ማለት ምን ማለት ነው  ••••? " አልኳት። በዛች ቅፅበት  በመደወሏም  በጥያቄዋም ድንብርብሬ ወጥቶ ።
"ምን••••? ቤት በኩል ስትል ••••? አልገባኝም ኤፍዬ ምን ለማለት ፈልገህ ነው•••?"
"ቤት በኩል••••? የምን ቤት በኩል ••••? ቤት በኩል አልኩ  እንዴ ቃልዬ•••? ኧረ አላልኩም! "ስላት•••
"ኪኪኪኪኪኪኪኪ•••••!" ያንን ሳቋን ጆሮዬ ላይ ስትለቀው ይብስ ተደነባብሬ ስልኩ ከእጄ ላይ ወደቀ።
••••ቆይ ግን ሳቅ ሳቅ ያለው በምን ይስቃል••••• የሚል ተረት አልተረቱም እንዴ ሰዎቹ •••? ለበጎ ነው ። ስልኬ በወደቀበት ቅፅበር - ድንገት አዳልጦኝ ይሁን አምልጦኝ በጥየቋት ጥያቄ •••በምላሹ የተሰነዘረብኝን  አደናግር ጥያቄ  በምን መልኩ ማለፍ እንዳለብኝ ትንሽ ለማሰብ ግዜ አገኛለሁ••••እያልኩ ገናስልኬን ከወደቀበት ሳነሳው ደግማ ደወለች።
ለመጀመሪያ ግዜ የቃልዬን ስልክ ላለማንሳት መጨከን ቻልኩ። ጠርቶ ጠርቶ እንደዘጋ አፍታም ሳትቆይ አሁንም ደወለች፣
ምን እንደምላት እርግጠኛ ሳልሆን ማንሳት አልፈለኩም። አፍ ሲከዳ መጥፎ ነው። "ቤት በኩል አለፍሽ•••? የሚል ጥያቄ እንዴት ከአንደበቴ እንደወጣ ፈጣሪ ይወቀው። ይህን ግራ የገባው ጥያቄ አንስቼ " ቤት በኩል ገባሽ ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው••••?" ስትለኝ
ምን ልበላት••••? እየተከታተልኳችሁ ስለነበር ቤት በኩል ሸውዳችሁኝ ወደ ግቢ እንዴሄዳችሁ ግራ ገብቶኝ ነው ።ወደ ግቢ የምትሄዱ ከሆነ ፣ ከነበራችሁበት ከከዚራ ወደላይ መኮረብ ለምን አስፈለጋችሁ•••?  ከዛው ቆማችሁበት ከነበረው ቦታላይ •••• ፊታችሁን ወደ ባቡር ጣብያው መልሳችሁ በለገሀር ወደ ነምበር ዋን ፣ ከነበርዋን በአዲሱ መንገድ ቀጥታ ወደ ግቢ መሄድ ትችሉ ነበር፣ በዛ መሄድ ካልፈለጋችሁ ደግሞ•••  ቀጥታ ወደ ዲፖ መጥታችሁ ሽቅብ ወደሳብያን በመውጣት ወደ ዩንቨርስቲው መሄድ ትችሉ ነበርኮለምንድን ነው ቀጥታ ወደላይ ወደ ኮኔል አልያም ወደ ሼል ወደሚወስደው መንገድ ወጥታችሁ እናንተም ዙርያጥምጥም ሄዳችሁ  እኔንም የሸወዳችሁኝ •••?  አልላት ነገር ተቸግሬ በማይታመን ሁኔታ ቤት በኩል ገባሽ የሚል ነገር አልተናገርኩም ብዬ ካድኳት።
በዛች ቅፅበት ቀላሉ እና ማሰብ ማሰላሰል የማያስፈልገው  መንገድ መካድ ብቻ ነበር። ምክንያቱም መካድ ምክንያትም ማስረዳትም አይጠይቅም። ብለህም ቢሆን በቃ አላልኩም ካልክ አላልኩም ነው ። አይተህም ቢሆን እአላየሁም ካልክ  አላየሁም ነው።  ነገር ግን መካድ ወይ በቀጣይ እንዳትታመን ያደርግሀል ፣ ወይ ጤንነትህ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ይሆናል።
በተናገርኩ በሰከንዶች ውስጥ አላልኩም ብዬ ስክዳት ምን ነካው ኤፊ ጤነኛ ነው ግን••?  ነው ፍቅር የሚናገረውንም አሳጥቶ ያስቀባጥረው ጀመር ብላ በማሰብ ይሆናል እንደዛ የሳቀችብኝ እንጂ መካዴ  ሳቅ የሚጭር  ሳይሆን ምናልባትም የሚያናድድ ነው።
ቆይ ፍቅር ግን ፍትሃዊ ነው•••? እሷን ከወንድ ጋር አየኋት እንጂ እኔን ከሴት ጋር አላየችኝ ታድያ መደናበር ፣መርበትበት የነበረባት እሷ እንጂ እኔ ነኝ እንዴ! እሷ እየሳቀች እኔ ማጣፊያው አጥሮኝ ግራ መጋባቴ ምን ይሉታል?
እርግጥ ነው እኔ የተደናበርኩት ከልጁ ጋር ተቃቅፋ ስትወዛወዝ እንዳየኋት እንድታውቅ ስላልፈለኩ ነው።
ስለዚህ ጉዳይ በተለይ አሁን ላይ እንድናወራ አልፈልግም። ከወንድ ጋር አየሁሽ! ልጁ  ማነው•••? ምንሽ ነው•••? ብዬ መጠየቅም የለብኝም።
እኔ በራሴ መንገድ እውነቱን ሳላጣራ እና ሳላውቅ አየሁሽ ገለመሌ ብሎ መጠየቅ •••በቀጣይ እንድትጠነቀቅ የማንቂያ ደውል ከመደወል ያለፈ ለኔ የሚፈይድልኝ ነገር አይኖርም።
ቃልዬን መጣላት እና ማጣት አልፈልግም።  ነገር ግን እንዳጣት የማልፈልገው እኔም የሷ ፣ እሷም የኔ ብቻ ከሆነች ብቻ ነው። ከዛ ዉጪ ያለው መንገድ ከደስታው ስቃዩ ያመዝናል።
ቃልዬ አታደርገውም እንጂ ምናልባት ከልጁ ጋር ሌላ ግኑኝነት ካላት አሁን ላይ ምንሽ ነው•••? ብዬ ብጠይቃት •••
"ምንም •••••! በቃ ምኔም አደለም! እንቀራረባለን አለቀ !". ትለኝና የኔን ጥያቄ ባጭሩ ቀጭታው እሷ በድብቅ አለሟን እንድትቀጭ ከማድረግ ያለፈ ሌላ ነገር ትለኛለች ብሎ ማሰብ መጃጃል ነው።
በሁለቱ መሀል ያለው ነገር ለኔ ጥሩም ይሁን መጥፎ ዜና ፣ እውነቱ ላይ መድረስ ያለብኝ በራሴ መንገድ እንጂ እሷን በማወጣጣት አይደለም።
ስለዚህ ምንም ፍንጭ ማሳየት የለብኝም። ቢሆንም ግን አልኩና ••••• " አፈቅራታለሁና በቃልዬ እና በኔ መካከል ችግር እንዲፈጠር አልፈልግም!" አልኩት ፈጣሪዬን ወደ ባጃጄ ጣራ ቀና ብዬ ።
ትንሽ ሄደት  እንዳልኩ ለቃልዬ ልደውልላት ስልኬን በእጄ እንደያዝኩ ከፊት ለፊቴ ምህርት የለሹን ትራፊክ ስላየሁር እሱን አለፍ ብዬ ባጃጄን ጥግ አስይዤ  አቆምኩና  ደወልኩላት።
ትራፊኩን ማየቴ ጥሩ ምክንያት ለጭንቅላቴ ስላቀበለው ምን እንደምላት እርግጠኛ ሆኜ ነበር የደወልኩት።
አንስታው ዝም አለችኝ።
"ሄሎ•••ቃልዬ •••ሄሎ ••••ቃል!"
"ለምን ደወልክ•••••?  መዝጋትህ ሲገርመኝ ጭራሽ ስደውል አለማንሳትህ •••አኩርፌሀለሁ እሺ ቆይ ምን ሆነህ ነው•••?
" አታኩርፊኝ ቃልዬ! ••• ዘግቼብሽ ሳይሆን ስልኩ ከእጄ ላይ ወድቆ ነው፣ ስትደውይ አለማንሳቴ ግን ግድ ነበር!"
"ግድ ነበር ማለት••••?"
"ሁለተኛውን የትራፊክ ህግ ለማክበር!"
"እየቀለድክ ነው ኤፊ••••?"
"ኧረ በጭራሽ ቃልዬ እየቀለድኩ አይደለም ከዚህ በፊት አንዱን አክብረናል ዛሬ ደሞ ሁለተኛውን ማክበር ስላለብን ነው ያላነሳሁት!"
"እህም ምን እያልክ ነው ከዚህ ቀደም እኔና አንተ ብቻ ያከበርነው የትራፊክ ህግ አለ እንዴ?"
"በደንብ እንጂ ቃልዬ ሁሉ ነገር ቢረሳ ያቺ ቀን ትረሳለች እንዴ•••? እኔና አንቺ በተዋወቅን ምሽት አብረን እንድናድር ያስገደደችን እኮ ከጠጡ አይንዱ የምትለው የትራፊክ ህግ ነች።  አሁን ደግሞ እየነዱ ስልክ አያናግሩ በተለይ ከፍቅር ጓደኛዎ ጋር እያወሩ መንዳት ያጋልጣል ለጉዳት ምክንያቱም ልቦ በፍቅረኛዎ ቃል ስለሚወሰድ ልብ ብሎ መንዳት አይቻልም ። ልብ ብለው ካልነዱ አይለይም ገደል እና መንገዱ !" ስላት ብሽቅ ብላ ቆይ አንተ ግን በቅርብ ነው እንዴ መንጃ ፍቃድ ያወጣኸው•••?"
"ማለት•••?" አልኳት።
"እኔ ምን አውቃለሁ የፍቅር እና የትራፊክ ህግ ተደበላልቆብሀልኮ ! ••አብረን ያደርነው የትራፊክ ህግ ለማክበር እእእእእ ስልኬን የማታነሳው የትራፉክ ህግ ለማክበር ••ቆይ የኔና ያንተ ፍቅር የሚመራው በትራፊክ ህግ ነው እንዴ!"
ስትለኝ የንግግሯ ቃና እና በንዴት እየተንተባተበች ቶሎ ቶሎ ቶሎመናገሯ ፣ ከተናገርችው ነገር ጋር ተደምሮ  ከነበርኩበት የመከፋት ስሜት ፈንቅሎ ከልቤ አሳቀኝ። በእርግጠኝነት ወላጆቼን ሞት ከነጠቀኝ በኋላ ለመጀመሩያ ግዜ ነበር እንደዚህ ከልቤ የሳቅኩት።"
https://vm.tiktok.com/ZMrE9sbQM/