Kune demelash kassaye -Arba Minch⛪️

@kunedemelashkassayearba


በደቡብ ኢትዮጽያ አስተዳደራዊ ክልል ውስጥ ስላለቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው

Kune demelash kassaye -Arba Minch⛪️

11 Feb, 09:23


700ሺ ብር ውዝፍ አስራት ያለው ደግ ምዕመን ከተገኘ ይህቺን የቅዱስ ገብርኤል ማምለኪያ ስፍራ ወደ መቅደስ ይቀይራት
***

ይህኝ በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ቁጫ ወረዳ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። ስፍራው ላይ መቅደስ ይሰራበት ዘንድ 1ሄክ (10,000 ካሬ) ቡራኬ ከተደረገ ከ5 ዓመታት በላይ አልፎታል።

የአቅም የቁጥር ውስንነት ችግር ሆኖባቸው መቅደስ ማነጽ ተስናቸው ዛሬም ይህቺን ደሳሳ የሣር ክዳን ቤት በየጊዜው እያደሱ ስርዓተ አምልኮ በየሳምንቱ በእዛው ያደርጋሉ።

ሊቀ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል ከአፋቸው የማይጠፋ ልዩ ስም ነው። " ገብሬላ"። ቤተክርስቲያን ሲባል ነፍሳቸው ሁሉ በጉጉት ይመጥቃል።

ምናልባት ለቆርቆሮ፣ለመሰረት መስሪያ ሲሚንቶ፣ለአሸዋ፣ለድንጋይ ለሚስማር፣ ለቀለም ግዢ እና ለባለሞያ ክፍያ ወጪ መሸፈኛ እስከ 700ሺ ብር ውዝፍ አስራት ወይም መባ አድርጎ የሚሰጥ አንድ ለነፍሱ ያደረ ምዕመን ከተገኘ የ5 ዓመት መከራቸውን በአንድ ጀንበር ያበቃል።

ለህንፃ መቅደስ ግንባታ የሚሆኑ የጉልበት ሥራ ፣የእንጨት መቁረጥ፣ጭቃ መርገጥ እና መለሰን እዛው ያሉ ጥቂት ምዕመናንን በደስታ ይሰሩታል።

እስኪ አንተ ደግ የቸርነት ምዕመን ተገለጥልን ....እንጠብቃለን !!! ከተገኘህ በ0982341985 የቴሌግራም እና የዋስአፕ መስመር መልእክት አስቀምጥልኝ። ህጋዊ የቤተክርስቲያን አካውንት ላቀብልልህ።

#share በማድረግ ይህን ባለውዝፍ አስራት ምዕመን አፈላልጉኝ።

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

Kune demelash kassaye -Arba Minch⛪️

16 Jan, 10:13


በገጠሪቷ ለምትገኘው የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማስመረቂያ ነዋዬተ ቅዱሳት የሚለግስልን ምዕመን እንፈልጋለን።
***
#share ይደረግልን !

በኦይዳ ወረዳ በምትገኘው ዑባ ዳማ ቀበሌ የሚገኙ አርሶ አደር ኦርቶዶክሳውያን ከዓመታት ልፋት በኃላ የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተክርስትያን ሰርተው ጨርሰዋል።

ህንፃ መቅደሱን ለማስመረቅ የነዋዬተ ቅዱሳት እንድናስተባብርላቸው ተማጽነዋል። እነሆ ከታች የተዘረዘሩት ነዋዬተ ቅዱሳት ያስፈልጋሉ።
***

1.የብረት መንበር ትንሿ..ብዛት 1 *42,000 = 42,000 ብር
2. ልብሰ ተክኖ..........ብዛት 1*15,000 = 15,000
3. መጾር መስቀል .....ብዛት 1*4,700= 4,700
4. መባረኪያ የእጅ መስቀል ...ብዛት 1* 1200 = 1200 ብር
6, ጽና ....ብዛት 1* 1500 = 1,500 ብር
7. መቆርቆሪት.....ብዛት 1* 2,500 = 2,500 ብር
8. ታቦት ማክበርያ ትልቁ ጃንጥላ(ድባብ)....ብዛት 2*2,300= 4,600 ብር
9. ደወል....ብዛት 1*15,000....15,000
10. ጽናጽል..... ብዛት 10*450=4500 ብር
11. መቋሚያ.....ብዛት 10* 200= 2000 ብር
12. ቃጭል.....ብዛት 1* 2000 = 2000 ብር
13. መንጦላይት ......ብዛት 2* 3000 = 6000 ብር
14. ከበሮ.....ብዛት 2*4000= 8,000

ጠቅላላ በድምር ....109,000
***
የውስጥ መገልገያ መጽሐፍት ግዢ

11. ስንክሳር የአመቱ.....3800
12. ወንጌል................3,000
13. መጽሐፈ ክርስትና...450
14. መዝሙረ ዳዊት....550
15. ድርሳነ አማኑኤል....250
16. መልከ አማኑኤል....250
18. ታምረ ማርያም ....3500
19. ታምረ ኢየሱስ ....1400
20. ሃይማኖተ አበው.....1400
21. ጸሎተ እጣን ...100
22. መጽሐፍ ግንዘት...250
23.ግጻዊ .....250.
24. መጽሐፈ ቅዳሴ....ብዛት 1*4,000= 4000
26. መልካ ገቡኤ....900
27. ሰዓታት.....2,500

በድምሩ .....22,600 ብር

በአጠቃላይ በድምሩ 131,600 ብር ያስፈልጋል።በመሆኑም ነዋዬተ ቅዱሳቱን ገዝቶ የሚያቀብለን ከተገኘ በአደራ የተረከብነውን በአደራ እናስረክባለን። በመግዛት ብቻ።

መልሳችሁን በፔጃችን የውስጥ መስመር ፣ዋስአፕ መስመር ወይም በ0982341985 የቴሌግራም መስመር ማሳወቅ ይቻላል።

ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ!!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

Kune demelash kassaye -Arba Minch⛪️

09 Jan, 14:36


"በወር 100 ብር ለገጠሪቷ ቤተክርስቲያን" የቴሌግራም ግሩፕ አባሎቻችን ለ14ኛ ዙር ተረጅ አጥቢያ ወራዊ ግዴታ ድጋፍ ዛሬ ማታ ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ ይጀምራል።
***

በወር 100 ብር በቋሚነት ለገጠሪቷ ቅድስት ቤተክርስትያን የተሰበሰቡ ምእመናንን 14ኛ ዙር ተረጅ አጥቢያን ለመደገፍ ከዛሬ ማታ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በቴሌግራም ግሩፓችን እንገናኝ።

በቴሌግራም ግሩፕ ውስጥ አባል በመሆን ያለመዘንጋት በወር 100 ብር ለገጠር አጥቢያ የደገፍ የምትፈልጉ ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ተጭናችሁ አባሉ ሁኑ።

https://t.me/geterbetekiristian

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

Kune demelash kassaye -Arba Minch⛪️

07 Jan, 10:50


100ሺ ብር የገና ስጦታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በዘመቻ እንለግስ
***

እግዚአብሔር ቢፈቅድ 100,000 ብር ለእዚህች 121 ዕድሜ ላስቆጠረችው ደሳሳዋ የላ ማርያም ቤተክርስትያን ዛሬ ከቀኑ 11:00 እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ልንሰበስብ አስበናል።

አጠቃላይ ታቦተ ማርያምን ከእዚህች ደሳሳ መቅደስ ለማውጣት የሚፈለገው 300ሺ ብር ቢሆንም በዓለ ልደቱን አስመልክተን 100ሺ ብር በአንድ ቀን ከሰበሰብን ቀሪውን ነገ ከነገ ወዲያ እናፈላልጋለን። እግዚአብሔር ይርዳን !!!

ስለዚህ ለድንግል ማርያም ስጦታ ያላችሁ ትራዱን ዘንድ እንማጸናለን

***

...100,000 ብር የሚሰጠን 1 የማርያም ባሪያ ....
...50,000 ብር የሚያቀብልልን 2 የአዛኝቷ ወዳጅ....
...10,000 ብር የሚልክልን 10 በረከት ተካፋይ ምዕመናንን...
....1,000 ብር ብቻ የሚለግሱ 100 ሰዎች ....
.... 500 ብር የሚራዱ 200 ሰዎች....
....አለበለዚያ 100 ብር የሚሰጡልን 1000 ሰዎችን እንፈልጋለን...

***

እነሆ ስጦታ መቀበያ ህጋዊ የቤተክርስቲያኒቷ የሂሳብ ቁጥር

1000377538025

የላ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን
***

ስለቅድስት ድንግል ማርያም !!!

እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ስጦታችሁን በገጻችን የውስጥ መስመር ወይም በፓስቱ ኮመንት ሴክሽን ትልኩልን ዘንድ ተማጽነናል።

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

Kune demelash kassaye -Arba Minch⛪️

06 Jan, 14:02


121 ዓመት ላስቆጠረችው የማርያም መቅደስ የገና ስጦታ የሚሆን 300ሺ ብር የሚለግስልን ምዕምን እንፈልጋለን!!!
***
#share ታደርጉ ዘንድ ተማጽነናል።

ይህቺ በጋሞ ዞን ከምባ ወረዳ ራቅ ባለ የገጠር ስፍራ ላይ ከዛሬ 121 ዓመት በፊት ተተክላ ስፍራው ላይ ሐዋርያዊ አገልግሎት በመፈጸም ኦርቶዶክሳዊነት እንዲጸና ካደረጉት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት መሐከል አንዷ ናት።

የላ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስትያን ትባላለች። ዛሬ ላይ ግን እነሆ በእዚህ ደሳሳ እና እጅግ በጣም በደከመ መቃኞ መቅደስ ውስጥ ትገኛለች።

ጎርፍ የምትከላከልበት ወለል፣ከዝናብ የትጠለልበት ጣሪያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ያፈሳል።

ይህችን ጥንታዊ ታቦተ ህግ ከእዚህች ደሳሳ መቅደስ አውጥቶ ወደሚሰራላት አዲስ መቅደስ ለማስገባት አሁን ላይ 300ሺ እንደሚያስፈልግ የደብሩ አገልጋዮች ነግረውኛል።።

አንድ የድንግል ማርያም ወዳጅ እንደ ሰብእ ሰገል ይህን 300ሺ ብር የገና ስጦታ አድርጎ በመስጠት ለታቦተ ማርያም ውለታ ይውል ዘንድ እንማጸናለን።

300 ሰዎችም በ1,000 ብር የገና ስጦታ ትደግፉን ዘንድ ተማጽነናል

600 ምዕመንም 500 ብር ቢራዳን ዘመቻውን እንጨርሳለን።

ከ10 ብር ጀምሮ በረድኤት የሚያስበን ከተገኘ አንጠላም።

ለቁጥጥር እንዲመች መልስ እና ስጦታችሁን በገጻችን የውስጥ መስመር ወይም በኮመንት ሴክሽን ያሳውቁን

***
እነሆ ስጦታ መቀበያ ህጋዊ የቤተክርስቲያኒቷ የሂሳብ ቁጥር

1000377538025

የላ ደብረ ምጥማቅ ቤተክርስቲያን
***

ስለቅድስት ድንግል ማርያም !!! ስለአዛኝቷ። የገና ስጦታችሁን አበርክቱልን!!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minchh

Kune demelash kassaye -Arba Minch⛪️

26 Dec, 13:14


ለ11 ዓመታት የቆመውን የቅዱስ ገብርኤል መቅደስ የ7 በር እና 12 መስኮት ሥራ እናጠናቅቅ ዘንድ የሊቀ መላእኩ ወዳጆች ተጠርታችዋል
***
መልእክቱን #share ታደርጉ ዘንድ እንማጸናለን

ይህ በጋሞ ጎፋ ሀገረስብከት ጋርዳ ማርታ ወረዳ የሚገኘው እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ በወረዳው የሚገኘው ብቸኛው ቤተክርስቲያን ነው።

ከመቅደስ ውስጥ በወጡ ተሃ*ሶ መናfiqan ይህ የገናናው የቅዱስ ገብርኤል መቅደስ ለ11 ዓመታት ባለበት ግንባታ እንዲቆም ተደርጎ ምዕመናንን ተስፋ ይቆርጡ ዘንድ ተፈትነዋል።

እነሆ አሁን ላይ የበር መስኮት እና የመቅደስ አየር እና ብርሃን ማስገቢያ መስኮት(Ventilation window ) ለማሟላት እጅግኑ ተቸግረው ለተማጽኖ እጃቸውን ዘርግተዋል።

7 ብር እያንዳንዱ 10,000 ብር (ከቤቴሌሔም በር ጋር)
12 የማህሌት መስኮት እያንዳንዱ 6,000 ብር
14 የመቅደስ የአየር መስኮት እያንዳንዱ 5,000 ብር

በድምሩ የ212,000 ብር የበረከት ሥራ ተማጽኖ እናቀርባለን።

በቅዱስ ገብርኤል ቤት ያደጋችሁ፣ከሊቀ መላእኩ ጋር ልብ ለልብ ተነጋግራችሁ ሸክማችሁ ያቀለላችሁ፣ገብርኤል ሲባል ሐሴት የሚሰማችሁ የራማው ልዑል ወዳጆች ሆይ ....ኑ ይህ በረከት ለእናንተ ነው።

የቻላችሁ የሊቀ መላእኩ ወዳጅ በር እና መስኮት በማገዝ ውለታ ዋሉልን።በረከቱ ይደርስላችሁ ዘንድ ከ10 ብር ጀምሮ ለእዚህ ቤት እናበረክት ዘንድ እንማጸናለን ።

***
እነሆ ስጦታ መቀበያ ህጋዊ የቤተክርስቲያኒቷ ሂሳብ ቁጥር

ጋርዳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

1000192944768

***
ያስገባችሁበትን የባንክ ስሊፕ በውስጥ መስመር ወይም ኮመንት ሴክሽን ይላኩልን

ስለ ቅዱስ ገብርኤል !!! ስለራማው ልዑል!!! ስለ ሊቀ መላእኩ

Kune Demelash kassaye -Arba Minch