የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

@hinokhailes_spiritual_teachings

"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን"
2ኛ ቆሮ. 2:14

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

22 Oct, 18:00

ሲያስተምር እንባ ከአይኖቹ ይቀድሙታል

ተስፋ የቆረጠውን ወጣት ተስፋ ይሰጠዋል

በእግዚአብሔር ቃል ተስፋውን ያለመልማል
መምህር እዮብ ይመኑ
የአገልግሎት ዘመን የተባረከ ይሁን።

Telegram channel ይቀላቀሉ👉CLICK HERE

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

22 Oct, 17:22

የመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በደረሰው የእሳት ቃጠሎና ቃጠሎውን ተከትሎ በንብረቶቻችው ላይ ጉዳት ላጋጠማቸው ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።

የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ቻናላችንን follow ያድርጉ 👉
OPEN

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

22 Oct, 16:28

"የእነርሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጕድለት እንዲሞላ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጕድለት ይሙላ"2ተኛ ቆሮ 8፥14
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
share

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

22 Oct, 13:01

⚡️⚡️⚡️ መዝሙረ ዳዊት ⚡️⚡️⚡️
➪open የሚለውን በመንካት  ይከፈቱ

መዝሙር 1 open

መዝሙር 2 open

መዝሙር 3 open

መዝሙር 4  open

መዝሙር 5 open

መዝሙር 6 open

መዝሙር 7 open

ይቀጥላል ...........

              21 መዝሙር
ተጨማሪ  ለማግኘት
ይቀላቀሉ  ➟ @m_ezmur21
ለሌሎች ያጋሩ  ➟@m_ezmur21

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

22 Oct, 12:23

"ድርሳነ ሚካኤል"

"የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኛንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልን። ቤተክርስቲያንን ጠብቅልን፣ ህዝቦቿንም።ከክፉ ነገሮች ሰውርልን።

የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ምልጃው ጥበቃና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን ..

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

22 Oct, 07:32

+  መልአኩ ነው +

       ሰዓቱ ሌሊት ነው ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚያ ሌሊት መላው የቤተሰባችን አባል አምሽቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ከዚህ የቤተሰብ ስብስብ መካከል ሳይገኝ የቀረው አንድ በወኅኒ ቤት የታሰረ ወንድማችን ብቻ ነበር፡፡ ድንገት ግን የጊቢው በር በተደጋጋሚ ተንኳኳና ሁላችንም ጨዋታችንን አቋረጥን፡፡ በሌሊት የሚያንኳኳው ማን ነው ?
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ሠራተኛችን ሮጣ ሔደች:: ወዲያው ግን በሩን ሳትከፍተው ተመልሳ እየሮጠች መጣች፡፡ በደስታ ሰክራ ‹‹የታሰረው ልጃችን በር ላይ ቆሟል!›› ብላ ተናገረች፡፡ "በድምፁ አወቅኩት!› እያለች ዘለለች፡፡ ከሁኔታዋ የተነሣ ‹አብደሻል እንዴ!?› አላት ቤተሰቡ ሁሉ፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
እስዋ ግን በእርግጠኝነት ተናገረች! በቀን የታሰረው ልጅ በሌሊት ተፈቶ መምጣቱ ፈጽሞ ሊታመንን የማይችል ነገር ነው፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ የታሰረው ልጅ መጣ ብሎ አላመነም፡፡ ባይሆን የመንግሥት ወታደሮች የቀረነውን ሊወስዱን ይሆን? ማን ሊሆን ይችላል? ብሎ ተብሰለሰለ:: በመጨረሻም የሁሉም ግምት አንድ ነገር ላይ አረፈ:: ሁሉም ሰው በአንድ ድምፅ አንድ ቃል ተናገረ "መልአኩ ነው!"
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
  መልአኩ የሰው ስም አይደለም:: ቤተሰቡ የተስማማው "ደጅ የቆመው የታሰረው ልጃችን ሳይሆን እሱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተሠጠው ጠባቂ መልአኩ ይሆናል›› ብሎ ነበር፡፡ የበሩ መንኳኳት አሁንም ስላልቆመ ቤተሰቡ ግር ብሎ ወጣና ተቻኩሎ በሩን ከፈተ፡፡ በደጅ የቆመው ግን እንደተባለው የታሰረው ልጅ ራሱ ነበር፡፡ ሁሉም ተደሰተ!!!
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
      ይህ ገጠመኝ በአሁን ዘመን የተፈጸመ ነው ብዬ ብናገር ማን ያምነኛል? እውነት በሌሊት የቤታችን በር ሲንኳኳ  መልአክ ነው ብለን እንገምታለን? ይህ ቤተሰብ ምን ዓይነት ቤተሰብ ነው?
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
በብዙዎቻችን አእምሮ ውስጥ መጀመሪያ የሚመጣው ጥርጣሬ ‹ሌባ ሊገባ ይሆን?› የሚል ስለሚሆን ዱላ ፍለጋ እናማትራለን፡፡ ወይ ደግሞ ሌሊቱ ወደ መንጋቱ እየተቃረበ ከሆነ ‹‹የምን መርዶ ሊያረዱኝ ይሆን? የቱ ዘመዴ ሞቶ ይሆን?› የሚል ጭንቀት ይፈጠራል፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
‹የሚያንኳኳው የእግዚአብሔርመልአክ ይሆናል› ብሎ የሚጠረጥር ሰው ግን በዚህ ዘመን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንዲህ ብሎ ግምቱን የሚናገር ሰው ከቤተሰባችንመካከል ቢገኝ እንኳን እንደ ዕብድ ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ታዲያ ይህን ገጠመኝ ከየት አመጣኸው ትሉኝ ከሆነ መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚል ነው፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
      በሐዋርያት ዘመን ሔሮድስ የተባለው ንጉሥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ወኅኒ ቤት ውስጥ ወርውሮት ነበር፡፡ የቀሩት ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖች በዚያ ሰሞን ሲጸልዩ ከርመዋል፡፡ በአንድ ሌሊት በማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው አምሽተው ነበር፡፡ ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳ ሮዴ የምትባል የቤት ሠራተኛ ደጁን ልትከፍት ወጣች፡፡ ማነው ብላ ስትሰማ የቆመው እስረኛው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑን በድምፁ አወቀች፡፡ ደስታ ግራ ሲያጋባት በሩን መክፈትን ረስታ ወደ ውስጥ ሮጠችና ጴጥሮስ መምጣቱን ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን አላመኑአትም፡፡ ጤንነቷን ተጠራጥረው ‹አብደሻል› አሏት፡፡ እርግጠኛ ሆና ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን መልሰው ‹‹የቆመው ጴጥሮስ ሳይሆን መልአኩ ነው፡፡›› አሉ፡፡ ይደንቃል የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንዲህ በር ሲንኳኳ ‹መልአክ ነው› ብለው የሚገምቱ መንፈሳዊያን ነበሩ፡፡ (ሐዋ. 12፡12-15)
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
      ቅዱሳንመላእክት እኛ የሰው ልጆች ከመፈጠራችን ቀድመው የተፈጠሩ ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም ምድርና የሰው ልጅ ሲፈጠር ደስ እያላቸው ‹‹እልል›› ይሉ ነበር፡፡ (ኢዮ. 38፡6) ቅዱሳን መላእክትን እግዚአብሔር ለእንዳንዳችን ጠባቂዎች አድርጎ ሠጥቶናል፡፡ ከክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብለው የተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መላእክት ጠባቂነት ጋር ይህን ያህል እምነት ከነበራቸው እኛም የመላእክቱን ጠባቂነት ማመን ለዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ያህል ይገባን ይሆን? ቅዱሳን መላእክት በክርስትና ሕይወት ለሚኖርሰው ሁሉ የመላእክት ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሁሉ ብርታት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሥጋው ወራት በተያዘባት ምሽት ሲጸልይ ‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ሉቃ. 22፡43) ይህም ቀርበው አገለገሉት‹ለከ ኃይል› እያሉ አመሰገኑት ማለት ሲሆን ለእኛም የመላእክት ርዳታ አያስፈልገኝም እንዳንል የሚያስተምረን ነው፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ቅዱሳን መላእክት በምድር የሚሆነውን ያውቃሉ:: (2 ሳሙ 14:20) በበደላችን ስንጸጸት "ኃጢአትህ ተሠረየችልህ" ይላሉ (ኢሳ 6:7) በክፋታችን ጸንተን ከቀጠልን ደግሞ "ይቅር አይሉም" (ዘጸ 23:20)
ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ቆመው "የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?" ብለው ያማልዳሉ:: (ዘካ 1:12)

ባለንበት ዘመን በዓለም ሁሉ በበሽታ የሚሠቃየው ብዙ ነው::  በሕመም ለሚሠቃየው ሁሉ

"መልአክ ቢገኝለት እየራራለት [ለእግዚአብሔር] ፡— ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው፡ ቢለው፥ ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፤ ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል" ኢዮ 33:23-25

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Deacon Henok Haile
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

22 Oct, 04:30

"ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው ወደ ዓለም ምንም እንኳን አላመጣንምና አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም ምግብና ልብስ ከኖረን ግን ርሱ ይበቃናል።

ዳሩ፡ግን፡ባለጠጋዎች ሊኾኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጐዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።

ገንዘብን መውደድ የክፋት ዅሉ ሥር ነውና አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት፡ተሳስተው
በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።"
1ኛ ጢሞ 6፥6-10

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
share

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 18:00

"እንዲህ ዓይነት ምርቃትም አለ :

ሁለት ካህናት ከአንድ ምእመን ጋር ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በእግራቸው ሲሄዱ ይመሽባቸውና ከሰው ቤት ለምነው ይገባሉ፡፡

ባለቤትየውም መንገደኞቹ ከጠበቁት በላይ ተንከባክቦ ያሳድራቸዋል። ጠዋት መንገዳቸውን ሊቀጥሉ ሲሉም ለቁርስ የሚሆን ቁራሽ ይቋጥርላቸዋል። በዚህም ሁሉ የተደነቁት አረጋዊ ካህን.

" በሰማይ ቤት ሰይጣን ከሳሽ እርስዎ ተከሳሽ እኛን ምስክር አድርጎ ያቁመን።" ብለው ያሳድራቸውን ሰው መረቀው ተሰናበቱት።

➧ ቸር እደሩልኝ ...

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 17:32

ቃና ዘገላሊ" ቀድመው የተጀመሩትን "ሕማማት" እና "የብርሃን እናትን" በመቅደም ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሟል።

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 15:56

🙏መታደል🙏

መታደል ማለት ባለ ሀብት ወይም ዝነኛ መሆን አይደለም።

መታደል ደምቆ በሰዎች ፊት ትኩረት ስቦ መገኘትም አደለም።

መታደል ማለት በሰላማዊ የእግዚአብሔር መንፈስ መቃኘት ነው።

በእግዚአብሔር መንፍስ መታጠር ነው።

ህጉን ፈፅሞ ስርዓቱን ጠብቆ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ታላብሶ መቆም ነው።

መታደል በእግዚአብሔር እጆች ውስጥ በሰላም በደስታ....ሐሴት እያደረጉ ወደ ዘላለማዊ ህይወት መጓዝ ነው።

መታደል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ሆኖ መፈጠር ነው።

መታደል ይሃ ነው።

ጃንደረባው
ጥቅምት 2017ዓ/ም
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 13:00

የቱን መዝሙር ትፈልጋላችሁ ?

➪በምን ደስ ላሰኝህ  open

➪ ምስጥረኛዬ ነሽ  open

➪ ያሬድ ካህኑ    open

➪ አልፈርድም እኔ  open

➪ ያ ደሀ ተጣራ   open

➪ ናና አማኑኤል open

➪ ገሊላ እትዊ open

➪ በብርሃን ፀዳል  open

➪ አክሊለ ፅጌ open

           21 መዝሙር
ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ
➪@m_ezmur21
➪@m_ezmur21

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 11:56

አንብባችሁት የሕይዎታችሁን መንገድ ለወጥ ያደረገውን የእናንተ ድንቁ መጽሐፍ እስኪ ለእኛም comment መፃፊያው ላይ ጋብዙን አንብበን እንማርበት።

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 11:12

ሰላም የችግሮች አለመኖር ሳይሆን በፈተናዎች ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ውጤት ነው።

እግዚአብሔር የሚሰጠውን ሰላም የትኛውም ኃይል ሊወስደው አይችልም!

@hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 06:29

+ አልፋና ኦሜጋ ክርስቶስ +

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ‘አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ’ አለ:: A እና Ω የግሪክ የመጀመሪያና የመጨረሻ ፊደላት ናቸው፡፡ ጌታችን መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ ሲል ከዓለም መፈጠር በፊት የነበርሁ ዓለምንም አሳልፌ ለዘላለም የምኖር እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ወደ ጥልቁ መለኮታዊ ዘላለማዊነት ሳንገባ ያለንባትን የምድርን ታሪክ ይዘን ብቻ እንዲሁ ካየነው ክርስቶስ መጀመሪያም መጨረሻም ነው፡፡ ‘እግዚአብሔር ‘በመጀመሪያ’ ሰማይና ምድርን ፈጠረ’  ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር አብ ‘መጀመሪያ’ በተባለው በልጁ በክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ፈጥሮአል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ የሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ይህችን ምድር በግርማው መጥቶ የሚያሳልፋትም እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ ለምድርም መጀመሪያዋና መጨረሻዋ ክርስቶስ ነው፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
መቼም እኛም ከምድር ተፈጥረናልና ይህ ነገር እኛንም ሳይመለከተን አይቀርም፡፡ ነቢዩ ከእናቴ ሆድ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ እንዳለ በእናታችን ማሕፀን የሳለንና በኋላም ለእኛ ምጽዓት በሆነችው የሞታችን ዕለት ነፍሳችንን ወደ እርሱ የሚወስዳት መጀመሪያችንና መጨረሻችን እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡
ይህ ግን ለሁሉ የማይቀር ነው፡፡ ወዳጄ ክርስቶስን አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያና መጨረሻ መሆኑን ታምናለህ፡፡ በአንተ ሕይወት ውስጥ ግን ክርስቶስ እውነት መጀመሪያና መጨረሻ ነው?
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ለአንዳንዶች ክርስቶስ መጀመሪያቸው ነበር፡፡ ዴማስ ለክርስቶስ አልፋ ብሎ ዘምሮለት ነበር፡፡ ከጳውሎስ ጋር ሆኖ ለፊልሞና ሰላምታ ሲልክም ነበረ፡፡ በኋላ ግን ዓይኑ በተሰሎንቄ ውበት ተማረከ፡፡ የአሁኑን ዓለም ወደደና ከሐዋርያት ጋር ማገልገሉን ተወ፡፡ ክርስቶስ ለእርሱ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልሆነም፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
‘ሰውን ፍጻሜውን ሳታይ አታመስግነው’ የሚለውን ቃል ዘንግተን ያመሰገንናቸው እንደ ሰማልያል አብርተው ጀምረው እንደ ሰይጣን ጨልመው የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ‘የዛሬን አያድርገውና እንዲህ እንዲህ ነበርሁ’ ብለው የሚተርኩ መነሻዬ ቤተ ክርስቲያን ነበረ የሚሉ መዳረሻቸው ሌላ የሆኑ በመንፈስ ጀምረው በሥጋ የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ክርስቶስ ግን መነሻም መድረሻም እኔ ነኝ ይላል፡፡ ክርስቶስ የማጣት ጊዜ አምላክህ የማግኘት ጊዜ ትዝታህ አይደለም፡፡ በማግኘትህ ውስጥም እግሩን አትልቀቀው፡፡ በደጅ ጥናትህ ጊዜ ጌታዬ ካልከው ስትሾምም አትርሳው፡፡ 
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ቀንህን ስትጀምር ስሙን ጠርተህ ከጀመርህ ወደ ሥራህ ቦታም ስትሔድ ቤትህ አስቀምጠኸው አትውጣ፡፡ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነውና በእርሱ የጀመርከውን ቀንህን ከእርሱ ጋር ጨርሰው፡፡ ሰው በሥራ ቦታው በንግዱ ብዙ ወንጀል የሚሠራው ፈጣሪውን ሥራ ማስጀመሪያ ብቻ ሲያደርገው ነው፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
እግዚአብሔር መፍጠር የጀመረባትን የሳምንቱን መጀመሪያ እሑድ ዕለትን አሐዱ ብለን በቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር እንጀምራለን፡፡ በማግሥቱ ወደ ሥራና ማኅበራዊ ሕይወታችን ስንገባ ግን ክርስትናችን ይጠፋል፡፡ ሳምንቱን አልፋ ብለን የጀመርንበት አምላክ ኦሜጋ ሆኖ አብሮን እንዳይሰነብት እናደርገዋለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ማደሪያው እንጂ መቃብሩ አይደለችም፡፡ እርሱ በቤተ ክርስቲያን በረድኤት ቢገለጥም በሁሉ ቦታም የሞላ አምላክ ነው፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ክርስቶስን የምናስበው እሑድ ብቻ ከሆነና በሌሎቹ ቀናት በምንውልበት ሥፍራ የማናስበው ከሆነ ፤ ‘’ሥራ ሌላ ክርስትና ሌላ’’ ብለን የምንገድበው ከሆነ ትንሣኤውን ሳይሰሙ እሑድ ዕለት በመቃብሩ ሽቱ ሊቀቡ እንደሔዱት ቅዱሳት ሴቶች በእኛ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ገና አልተነሣም ማለት ነው፡፡ ‘ከቤተ ክርስቲያን ስትወጣ ክርስቶስን ከረሳኸው ክርስቶስ ለአንተ አልተነሣም ማለት ነው’ ይላል ቅዱስ አምብሮስ፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ሐዋርያት ጌታ በምድር ሲመላለስ በነበረ ጊዜ ሁሉን ትተው የተከተሉት መጀመሪያቸው እርሱ ነበር፡፡ ዐርብ ዕለት ግን ከመካከላቸው ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ ኮበለለ፡፡ እነርሱም መከራ ፈርተው ተበተኑ፡፡ ዮሐንስ ብቻ የወደደውን እስከ መጨረሻው ወድዶ ተከተለው፡፡ እርግጥ ነው የቀሩት ወንድሞቹም ከትንሣኤው ወዲያ በንስሓ ተመልሰው መጀመሪያቸውን ክርስቶስ መጨረሻቸው አደረጉት፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ክርስቶስን ከማንም በላይ መጀመሪያዋም መጨረሻዋም ያደረገችው አልፋና ኦሜጋ የተጻፈባት ድንግል ማርያም ነበረች፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለዓለም ሊሠጥ ሲፈቅድ ዓለምን ወክላ የተቀበለችው ድንግል አልፋ ክርስቶስ በማሕፀንዋ ተጽፎባት በቤተልሔም ግርግም በእቅፍዋ ነበረ፡፡ ከመስቀሉ ሥርም ቆማ ቃሉን ትሰማ ነበር፡፡ ያለ ምጥ የወለደችው ድንግል አርብ ዕለት በልጅዋ ሥቃይ ተሰቃይታ ስታምጥ ምጥ ካለ ልጅ መኖሩ አይቀርምና ‘እነሆ ልጅሽ’ ብሎ ዮሐንስን ሠጣት፡፡ በእርስዋ ሕይወት ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ ነበረ፡፡
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
ወዳጆች ሆይ ዛሬ የእግዚአብሔር ልጆች ነን ፤ ነገ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ አልክድህም ብለን እንዳንዝት ሦስቴ እንዳንክደው እንፈራለን፡፡ መጀመሪያችን የሆነው አምላክ መጨረሻችን እንዲሆን ግን ‘እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን’ እያልን ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጸልያለን፡፡         
  
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

21 Oct, 05:00

“ መስቀል ከባረከው ወንጌል ከሰበከው አንተን ከሚያመልክ
ሰው ጨምረኝ : አየሁኝ በቃሁኝ ከማለት ከከንቱ ውዳሴ አድነኝ።

አይኔ ተከድና አፌ ተገጥሞ ጉድጓድ እስከምገባ ነፍሴ ወደ አንተ እስከምትመጣ ድረስ በራሴ እንዳለቅስ እንድጸጸት አድርገኝ። ”

የብፁዓን አባቶቻችንን ፀሎትና በረከታቸው አይለየን።

"If the cross blessed you, if you preached the gospel, from the one who worships you."
Add me a person: Save me from vain praise from saying that I am enough.

Make me repent that I weep by myself until my eyes are covered and my mouth is closed and I go into a hole and my soul comes to you. "

May the prayers and blessings of our blessed fathers not separate

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education

20 Oct, 20:22

"የአባ ገብረ ኪዳን ቀደምት ሰራዎች የሆኑት ጸያሔ ፍኖት፣መጽሐፈ ወግሪስ እና መጽሐፈ ምዕዳን በድጋሚ ታትመዋል።

ሰርዲኖስ መጻሕፍት መደብር ያገኙታል።

አድራሻ- ቅድስተ ማርያም በሸዋ ዳቦቤት በትንሽ ወረድ ሲሉ ከምስራች ማዕከል ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የገቢያ ማዕከል ይገኛሉ።
ወይንም ደሞ በአቅራቢያ በሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ስቁ አልያም በማህበረ ቅዱሳን ሱቆች መፅሀፎቹን ማግኘት ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ 0910934578

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

9,890

subscribers

450

photos

6

videos